
23/07/2025
የCOC ፈተና ምዝገባ ማስታወቂያ
_________
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy, Optometry እና Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የመውጫ ፈተና ያለፋችሁ እንዲሁም በድጋሜ የብቃት ምዘና ፈተናን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ጤና ባለሙያዎች፣ ምዝገባው ከሀምሌ 15 - 24/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን
http://hple.moh.gov.et/hple/ ላይ በመግባት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ እንድትይዙ እናሳስባለን፡፡
በተጨማሪም ተመዛኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚረዱና ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ Information Booklets እንዲሁም የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ የ Practice Test Booklets በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
- እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።
- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
- ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና እያሳሰብን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115186275/0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ምዝገባ ሂደቱ 👇
youtube.com/