Minladrgilih Dele

Minladrgilih Dele ታማኝ የሆነ የህክምና መረጃ :ምክር እና አገልገሎት ብቁ በሆኑ

What are the dangers of abnormal sugar levels?Both hypo- and hyperglycemia affect how you feel. First of all, the brain ...
15/03/2022

What are the dangers of abnormal sugar levels?

Both hypo- and hyperglycemia affect how you feel. First of all, the brain suffers, because its cells consume about half of all energy supplied by glucose.

Dizziness, loss of concentration, weakness, darkening of the eyes, and trembling hands are common symptoms for both low and high blood sugar levels.

With constant hyperglycemia, glucose accumulates in organs and tissues and becomes toxic - begins to destroy the liver, kidneys, retina, blood vessels, heart, nervous system.

31/12/2021

#ሳል
• ሳል ብዙ ጊዜ አጣደፊ የሆነ የአጭር ጊዜ (ከሶስት ሳምንት ያነሰ) ወይም የረጅም ጊዜ (ከአራት ሳምንት) የዘለለ ሊሆን ይችላል።
#የሳል ምክናየቶች
• ጉንፋን
• ኢንፊሎወንዛ
• አለርጅ
• የብናኝና ኬሚካል መግባት
• የሳንባ ምች
• ትክትክ በሽታ
• ቲቢ
• አስም
• የብሮንከስ ኢንፌክሽን
• የጉሮሮ በሽታ
• የሳይነስ ኢንፌክሽን
• የፈሳሽና አየር ሳንባ ውስጥ መጠራቀም
• አንዳንድ መድሀኒቶች
• የሳንባ ካንሰር
• ከባድ የልብ ችግር
• ሌሎችም
#ቤት #ውስጥ #ሳል #ማስታገሻ #መንገዶች
1. ሻይ
2. የማር ሻይ
3. የሎሚ ሻይ
4. ዝንጅብል ሻይ
5. በቂ ፈሳሽ መውሰድ
6. ስቲም ወይም እንፋሎት መጠቀም
7. ጨው ባለው ውሀ ጉሮሮን መጉመጥመጥ ወይም ማኩረፍረፍ
8. ፍራፍሬ እንደ ብርቱካን አይነት መጠቀም
9. የአናናስ ጁስ መጠጣት እና ሌሎችም

13/01/2021

አስተሳሰብን መቆጣጠር

አስተሳሰብን መቆጣጠር ማለት ወደ እኔ የሚመጣውን ወይም በውስጤ የሚፈጠረውን ሃሳብ በማጣራት ማስተናገድ ማለት ነው፡፡ አስተሳሰባችንን ሳንለውጥ ሕይወታችንንም ሆነ ሁኔታችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የሁሉ ነገር መጀመሪያ አስተሳሰብ ስለሆነና አስተሳሰባችን የማንነታችን “ወፍጮ” በመሆኑ ነው፡፡ በመጀመሪያ አንድ ሃሳብ ወደ አእምሮአችን ይገባል፡፡ በመቀጠልም ይህ ሃሳብ በውስጣችን ይብላላና በንግግርና በተግባር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ይህ ተግባር ወደ ልማድ ከተለወጠ በኋላ ፍጻሜአችንን የመለወጥና የመቅረጽ ጉልበት ይኖረዋል፡፡ ይህ ሃሳብ ጤናማም ሆነ ጤና ቢስ ሂደቱ ያው አንድ ነው፡፡

ጤና ቢስ አመለካከቶችን ለማስወጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. በሕይወትህ የምታሰላስላቸውን ሃሳቦች ለይተህ እወቅ፡፡
ለማንነትህና ለሕይወትህ አላማ የሚመጥኑ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ ለይተህ ማወቅ አለብህ፡፡ ይህንን ለይተህ ስታውቅ በሃሳቦች መካከል መለየትንና የትኛውን ማስተናገድ እንዳለብህ ጥርት ባለ መልኩ እንድታውቅ ይረዳሃል፡፡

2. ጤና ቢስ አስተሳሰቦችን አታስተናግዳቸው፡፡
የመጣ ሃሳብ ሁሉ በአእምሮህ ስፍራ ማግኘት የለበትም፡፡ ለእምነትህና ላስቀመጥከው የሕይወት ከፍታ የማይመጥነውን ተራ ሃሳብ በመጣበት ፍጥነት እንዲወጣ ተቃወመው፡፡ ይህንንም ልምምድ የዘወትር አድረገው፡፡

3. ጤና ቢሱን አስተሳሰብ በጤናማ አስተሳሰብ ቀይር፡፡
ከዚህ በፊት በውስጥህ ያስተናገድካቸውን ጤና ቢስ ሃሳቦች መልካምና ስኬታማ በሆኑ ጤናማ ሃሳቦች መለወጥ መጀመር አለብህ፡፡ ከአእምሮህ ክፉውን ሃሳብ አስወጥተህ በጤናማው ካልተካኸው ሌላ ሃሳብ መሙላቱ አይቀርም፡፡

31/12/2020
24/12/2020

?👍👍👇👇👇👇

1. ከእንቅልፍዎ ሲነሱ በደንብ ይንጠራሩ።
መንጠራራት የደም ዝውውርን እና የምግብ መፈጨትን ያቀላጥፋል፤ በተጨማሪም የጀርባ ሕመምን ይቀንሳል። ድመቶች ይህን በሚገባ ያውቃሉ።
2. ቁርስ አይዝለሉ።
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ክብደት ለመቀነስ ከሚረዱ አስተማማኝ ዘዴዎች አንዱ ቁርስ በትክክል መብላት ነው። ቁርስ ሳይበሉ የሚውሉ ሰዎች ክብደት ይጨምራሉ። ፍራፍሬ ወይም የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ከጥራጥሬ የተሰራ ምግብ፣ እርጎ እና የተቀቀለ እንቁላል ጋር ለቁርስ መብላት በጣም ጥሩ ነው።
3. ጥርስዎን ይፋቁ።
ብዙ ሰዎች ጥርሳቸውን እንዴት በአግባቡ መፋቅ እንዳለባቸው አያውቁም። ይህም ጥርስ እና ድድ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ጭራሽ ካለመፋቅ ያልተናነሰ ነው። ጥርስዎች ለሁለት ደቂቃ ያህል በብሩሽ ይፋቁ። ጥርስዎን በሚፍቁበት ሰዓት ጥርስና ድድ የሚጋጠሙበትን መስመር እንዲሁም ምላስዎን ማጽዳት አይርሱ። በየወሩ ብሩሽ ይቀይሩ።
4. ውሃ ይጠጡ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ሰዓት ለስላሳ ወይም ሌላ ዓይነት ሃይል ሰጭ የታሸጉ መጠጦችን አይጠጡ። በቂ ውሃ ይጠጡ
5. በየቀኑ በቂ እረፍት ይውሰዱ።
እረፍት በሥራ ብዛት የተጎዳ አካልን መልሶ ከመገንባት በተጨማሪ ለልብ ሕመምና ስነልቦናዊ ችግሮች ተጋላጭነትን ይቀንሳል።
mini@del

17/12/2020

የሆኑ ልምዶች

ቁርስ የማይመገቡ ከሆነ በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኘውን የደም ስኳር መጠን ስለሚቀንስ ለአንጎል የሚደርሰውን
የምግብ መጠን በማስተጓጎል ለጉዳት ይዳርገናል።
አለማድረግ
ሰውነታችን በህመም ሲጠቃ በቂ እረፍት ማድረግ እና ከህመሙ ማገገም በአንጎል ላይ ተጨማሪ ጫና እንዳይኖር
ይረዳል።

ሲጋራ ማጤስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የልብ ህመም፣ የሳምባ ካንሰር እና
ስትሮክን ከማስከተል ባለፈ በአንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
ምግቦች ማዘውተር
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጣፋጭነት ያላቸው ምግቦችና መጠጦች ማዘውተር ለአንጎል ጉዳት መንስኤ ናቸው።

አንጎል ከየትኛውም የሰውነት ክፍሎቻችን በበለጠ ኦክስጂን ያስፈልገዋል። የምንተነፍሰው አየር የተበከለ ከሆነና
ለአንጎል የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ከቀነሰ ጉዳት ያስከትላል።
#6._የእንቅልፍ_እጦት
እንቅልፍ አንጎልን እረፍት እንዲያገኝ የምናደርግበት ሂደት ስለሆነ በቂ እንቅልፍ አለመውሰድ ለጉዳት ይዳርጋል።
ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ማጣት የአንጎል ህዋሳት ሞትን ያፋጥናል፡፡

በቀን የምንወስደው የአልኮል መጠጥ ከፍተኛ ከሆነ የአንጎል ህዋሶቻችንን ቀስ በቀስ ሊገድል ስለሚችል ከፍተኛ
ጉዳት ያስከትላል።

ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መመገብ ለአንጎል ጤናማነት ወሳኝ ነው።

12/12/2020

በጨጓራችን ውስጥ ያለው የአሲድ መጠን ሲጨምርና ሄሊኮባክተር (ኤች) ፓይሎሪ በተባለው ባክቴርያ ምከንያት ጨጓራችን
ሊታመም ይችላል።የጨጓራ ህመም በሆድ እቃ ክፍል አካባቢ ደጋግሞ የሚከሰት የማያቋርጥ ቁርጠት ሲሆን ህመሙ ወደ ጎን አጥንት አካባቢም ጨምሮ ሊሰማ ይችላል፡፡ ብዙን ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ከአንድ እና ሁለት በላይ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡-
- የሆድ ቁርጠት(በላይኛው የሆድ ክፍል ላይ)
-ማቅለሽለሽና ማስመለስ
-ማስጋሳት
- እምብርት አካባቢ የሚሰማ ህመም
- ሆድ መንፋት
- ምግብ በሚወሰድበት ጊዜ ቶሎ መጥገብ
የጨጔራን ህመም ሊያመጡ ሚቺሉ ብዙ መንስኤዎችም እንደ ምክኒያትነት ሊጠቀሱ ይችላሉ ከነዚህም መሀል ፡-
- ምግብ በጨጓራ ውስጥ ብዙ ጊዜ ሲቆይና የHCL አሲድ መጠን እየጨመረ ሲመጣ
-ጨጓራ ከመጠን በላይ ሲለጠጥ
- በ H.Pylori ባክቴሪያ አማካኝነት
- እንዲሁም NSAID መድሀኒቶች ለምሳሌ ibuprofen ,diclofenac ….ወዘተ ያለ ኣግባብ መጠቀም ህመሙን ሊያመጡ ይችላሉ
- በተያያዥ የውስጥ ደዌ ምክንያቶች
- በPsychological ጭንቀት፣ ድብርትና ውጥረት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
ወደ ህክምናው ስንመጣ፡-
1. አንድ ሰው የጨጓራ ህመም ብቻ እንደሆነ ህመሙ ማወቅ በራሱ ትልቅ እረፍት ይሰጣል፤ ነገርግን ደጋግሞ የሚከሰተውን ህመም
ለማስቀረት የሚቀሰቅሰውን ምክንያት ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ደጋግሞ የሚሰማ ጭንቅት፣ድብርት እና የአእምሮ ውጥረት ካለ የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ማማከር ተገቢ ይሆናል፡፡
2. ሌላው ደግሞ የምግብ ማስተካከያ ማድረግ ነው ይህም ሲባል፡- ምግብን በንጽና እና በ ኣግባቡ ማብሰል :ቅባትነት ያልብዛበት ምግብ መመገብ፣ በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ከመውሰድ ይልቅ በመጠን አነስ ያለ ምግብ ቶሎ ቶሎ መውሰድ እና ብዙ ጊዜ ጨጓራ ህመም የሚከሰቅሱ ምግቦችን ማስወገድ ያካትታል፡፡
3. ተገቢውን የጨጓራ መድሃኒት ከሃኪም ዘንድ መውሰድ
4. የጨጓራ ህመም የሚያመጣው H.Pylori ካለ መድሃኒቱን ለታዘዘው ቀን ያህል መውሰድ
5. እንዳስፈላጊነቱ ሌሎች ተጨማሪ መድሃኒቶች ከሃኪም ዘንድ ሊታዘዝ ይችላል፡፡
6 የግል ና የቤተሰቢን ንጽና መጠበቅ
ከዚ በተጨማሪ ለዚህ ህመም የተለያዩ ህክምናዎች ሲኖሩ በተፈጥሮአዊ መንገድ የጨጓራ ህመምን ሊያሽሉ የሚችሉ እነዚህን የምግብ አይነቶች እንመልከት፦
1- ማር፦ ማር በውስጡ ከ200 በላይ ንጥረ- ነገሮችን ሲይዝ እንደ ኤች.ፓይሎሪ ያሉትን ባክቴሪያዎች የመዋጋት አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ የስኳር ህመም ከሌለብን ማርን በመመገብ የጨጓራ ህመማችንን ማከም እንችላለን።
2- ነጭ ሽንኩርት፦ ለብዙ በሽታዎች መድሃኒት እንደሆነ የሚታወቀው ነጭ ሽንኩርት የኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያ እንዳያድግ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ነው። የነጭ ሽንኩርት ጣዕምን የማንወድ ሰዎች በመድሃኒት መልክ የተቀመመውን መጠቀም እንችላለን። ነጭ ሽንኩርት በተፈጥሮው ደምን የማቅጠን ባህርይ ስላለው የታዘዙልን መድሃኒቶች ካሉ ሀኪምን ማማከር አስፋላጊ ነው።
3- ክራንቤሪ፦ ይህ በተለይ ለሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፍቱን መድሃኒት የሆነ ፍራፍሬ በመሆኑ ኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያን የመዋጋትም አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። ክራንቤሪን በጁስ፣ በፍራፍሬ እና በመድሃኒት መልክ ልንወስድ እንችላለን ሆኖም መጠኑን ካበዛን የሆድ ህመም ስለሚያስከትል በትነሹ ጀምረን መጠኑን መጨመር ይቻላል።

8 foods that may harm our kidneysThe function of the kidneys is to remove toxic waste materials from the body. The kidne...
06/12/2020

8 foods that may harm our kidneys
The function of the kidneys is to remove toxic waste materials from the body. The kidneys filter up to 200 liters of blood per day and remove 2 liters of waste materials. Here are 8 types of foods that may harm the kidneys.

1.Red meat: raw and improperly cooked meat is high with proteins that put extra pressure on the kidneys. Therefore, it is recommended to cook meat properly before consumption.
2.Salt: salt gets rid of useful nutrients from the body and may harm the kidneys. 1 teaspoon of salt per day is the recommended amount for intake.
3.Caffeine: as important as coffee and tea are to our body, we must only consume two glasses of them per day as more than that amount would put a strain on the kidneys.

4.Dairy products: dairy products such as yoghurt, cheese, milk and butter are rich in proteins that are difficult to digest and cause a strain on the kidneys.
5.Processed foods: processed and packaged foods are laced with preservative chemicals that damage the kidneys.
6.Soft drinks: soft drinks contain high calorie, too much sugar and artificial sweeteners. It is best to not consume any soft drinks as they have no nutritional value.
7.Alcohol
8.GMO: genetically modified products cause damage to the kidneys and it is recommended to purchase groceries wisely.

04/12/2020

✍ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የመናገር ወይም ተሳትፎ የማድረግ ፍርሃት/ social phobia ምንድነዉ ❓❓

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

👉 ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ፥ ለምሳሌ ያህል ስብሰባ ላይ፥ ግብዣ ላይ ወይም ትምህርት ክፍል ውስጥ ንግግር እንዲያደርጉ ወይም እንዲሳተፉ ቢጠየቁ ምን ይሰማዎታል?

👉 አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ የተሰበሰበው ሰው እነሱ ላይ ከፍትኛ ትኩረት አድርጎ የሚከታተላቸው እና የሚተቻቸው መስሎ ይሰማቸዋል

👉 ከሚከተሉት ስሜቶች መካከልም አብዛኛዎቹ ይታዩባቸዋል: •

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

✅ ከፍተኛ በሆነ ፍርሃት መዋጥ

✅ የሰ?ሰውነት መራድ/መንቀጥቀጥ

✅ በላብ መጠመቅ

✅ የልብ ቶሎ ቶሎ መምታት

✅ ከላይ ከላይ መተንፈስ

✅ የጉሮሮ መድረቅ እና የንግግር መሰባበር

✅ የሆድ መረባበሽ

✅ መብረክረክ

✅ ከቁጥጥር ውጪ የመሆን ስሜት....

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👀 ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች መካከል አብዛኛዎቹ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ እና ግለስቡን ጭንቀት ውስጥ የሚከቱ ወይም የለተለት እንቅስቃሴውን የሚያዛቡ ከሆነ እንደችግር መታየት እና መታከም ይኖርባቸዋል ።

📖 ይህ ችግር social phobia በሚል ስያሜ የሚታዎቅ ሲሆን በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ከራሳቸው የሚጠብቁትን ያህል ስኬታማ እንዳይሆኑ ፤ ለምሳሌ ያህል የሃላፊነት ቦታ ላይ እንዳይቀመጡ፥ እንዳያስተምሩ፥ ማህበራዊ ህይወታቸውን እንዳያጎለብቱ ሊያደርጋቸው ይችላል ።

👉👉 Social phobia በመድሃኒት💊💉 ወይም/እና በንግግር ህክምና ሊቀንስ ወይም ሊጠፋ የሚችልበት ሰፊ ዕድል አለ ።
👇👇

04/12/2020

የ ማህጸን በር ካንሰር
የ ማህጸን በር ካንሰር አንዱ እና ዋነኛ ሴቶች ላይ የሚከሰት የ ካንሰር አይነት ሲሆን በ አዳጊ ሀገሮች ላይ በ ሁለተኛ ደረጃ ካንሰር ተያያዥ በሽታ ሚያስከትል እና ገዳይ በሽታ ነው ።ይህ ካንሰር ከ ማህጸን በር ህዋስ/cell ሚነሳው ሲሆን በአብዛኛው ወይም ሙሉ በ ሙሉ /99.7% ከ HPV(በተለየ HPV 16 & 18) ቫይረስ ጋር ተያይዞ ሚመጣ በሽታ ነው። የ ማህጸን በር ማለት እታችኛው የ ማህጸን ክፍል ሲሆን ማህጸንን ከ ብልት ጋር የሚያገናኘው አካል ነው።ይህ ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው ከ 35 አመት በላይ በሆኑ ሰቶች ላይ ሲሆን በ አማካይ እድሜያቸው 51 የሆኑ ላይ ይከሰታል ።ነገርግን ከ 25 አመት በታች ባሉ እንስቶች ላይ የመከሰት እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው።ሁሉም ሴት ከ 20 -70 አመት እድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ የ HPV ቫይረስ ስክሪን እንዲደረጉ ይመከራል። HPV ክትባት በመዉሰድ በሽታዉንም በቀላሉ መከላከልም ይቻላል።
ለ ማህጸን በር ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች
#ከ አንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ ማብዛት
#በልጅነት/በለጋነት እድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት መጀመር/ከ 20 አመት በፊት
#ከዚ ቀደም ለተለያዩ ለአባላዘር በሽታ ተጋልጠው ከሆነ ምሳሌ ቂጢኝ ፤ጨብጥ
#የበሽታ መከላከል አቅሞ በተለያዩ ምክንያቶች ተዳክሞ ከሆነ ለምሳሌ HIV
# ብዙ ልጅ መውለድ /7 ጊዜ አርግዛ የወለደች እናት አራት እጥፍ በካንሰሩ የመያዝ እድል አላት ምንም ካልወለደችው ሴት ጋር ሲነጻጸር
#ማጨስ
#ለረጅም ጊዜ ድብልቅ የወሊድ መቆጣጠርያ ክኒን መጠቀም
::::::::::::::::::::///:::::::::::::::/::::::::::::::::::///////
የማህጸን በር ካንሰር ምልክቶች
#አብዛኛውን ጊዜ ካንሰሩ ወደከፋ ደረጃ እስኪደርስ ምንም አይነት ምልክት ላይኖረው ይችላል።ነገር ግን ደረጃው ከፍ እያለ ሲሄድ እታች ያሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል
#በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት/በኋላ ደም መፍሰስ/ማየት
#ወር አበባ ሳይደርስ/ በመሃል ደም መፍሰስ
#ከብልት ዉስጥ ሚወጡ የተለያዩ ፈሳሾች ለምሳሌ ዉሃ መሰል፤ደም የቀላቀለ እና ሽታ ያለው ማያሳክክ ፈሳሽ
#በዳሌ አካባቢ የ ሚፈጠር ህመም በተለየ በአንድ በኩል እንዲሁም ከ ዳሌው ተነስቶ ወደ ጭን ሚሰራጭ
#በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚፈጠር ህመም/አለመመቸት
#ክብደት መቀነስ ፤መደካከም እና ደም ማነስ
#ሽንት ፤ ጽዳጅ መቆጣጠር አለመቻል/ከቁጥጥርዉጭ መሆን
እንዴት መከላከል ይቻላል
ክትባት መዉሰድ/መከተብ
#በአመት አንዴ የ ማህጸን በር ካንሰር ምርመራ ማድረግ ።ካንሰሩ ለህክምና አዳጋች ወደ ሆነ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ከተገኘ ሊድን ይችላል።
#ጥንቃቄ ባለው መንገድ ግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ለምሳሌ ኮንዶም መጠቀም ወይም ዘግየት ብሎ የገብረ ስጋ ግንኙነት መጀመር
#ሲጋራ አለማጨስ
መቼ በ ዶክተር ማየት አለብን??
#የትኛዉም ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች ካስጨነቅዎ ወደ ሃኪም ቤት በመሄድ ምርመራ ማድረግ አለብዎ/ይመከራል።

04/12/2020

✍ Facts for your soul!!👌

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

👉 Dealing with Anger

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

✅ Women are 2.5 times more likely than men to turn to food as a way to calm down when angry

✅ According to surveys, men are 3 times more likely than women to use s*x as a way to calm down when angry

✅ Women are 56% more likely than men to "yell a lot" when angry

✅ Men are 35% more likely than women to "seethe quietly" when angry

📥(Zoellner, 2000) from Comer's fundamentals of abnormal psychology

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ለ አፍንጫ መድማት(ነስር)መንስሄዎች1 ለ ረጅም ሰአት ደረቅ ና ሞቃት በ ሆነ የአየር ንብረት ዉስጥ መቆየት2 አፍንጫ ዉስጥ የሚፈጠር ኢንፌክሽን(infection)3 አለርጂ(allergy rhin...
04/12/2020

ለ አፍንጫ መድማት(ነስር)መንስሄዎች
1 ለ ረጅም ሰአት ደረቅ ና ሞቃት በ ሆነ የአየር ንብረት ዉስጥ መቆየት
2 አፍንጫ ዉስጥ የሚፈጠር ኢንፌክሽን(infection)
3 አለርጂ(allergy rhinitis)
4 አደጋ :ድንገተኛ ወይም በማወቅ ሚፈጠር ለምሳሌ ህጻናት አብዛኛውን ጊዜ ደጋግመው አፍንጫቸውን በ መነካካት/በመጎርጎር ያደማሉ
5 ከዚ በፊት ሰርጀሪ ወደ ፊት አካባቢ ተሰርቶ ሚያቅ ከሆነ
6 ደም ግፊት
7 በ አፍንጫ ዉስት ያለ እጢ
8 ለተለያዩ ምክንያት የሚሰጡ መድሃኒቶች ለምሳሌ Aspirin ,warfarin

ነስር በሚነስራቸው ሰዎች መወሰድ ያለባቸው የምግብ ኣይነት የቱ ነው??
1 በ potassium ንጥረ ነገር የበለጸጉ የፍራፍሬ እንዲሁም የኣትክልት ምግብ ኣይነቶችን መመገብ ለምሳሌ :ሙዝ:ኣቮካዶ እና ድንች
2 በ vitamin C የበለጸጉ ፍራፍሬዎችን መመገብ ለምሳሌ:ብርቱካን እና የመሳሰሉት
3 የ iron መጠን በ ሰዉነታችን ዉስት የሚጨምሩ የምግብ ኣይነቶችን መመገብ ለምሳሌ :ጥሬ ስጋ :ባቄላ :ኣተር ወዘተ
4 የ vitamin K መጠን በ ሰዉነታችን ዉስት የሚጨምሩ ኣረንጓዴ ኣትክልቶችን መመገብ
5 ከዚ በተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ መዉሰድ ይህ ማለት ከ protein, carbohydrate… የመሳሰሉት
እነዚህን የ ምግብ ኣይነቶችን ሁሉንም ላናገኝ እንቺላለን ነገር ግን በ ኣካባቢያቺን ያለዉን ፍራፍሬዎች ሆነ ኣትክልት ብንጠቀም እራሳቺንን ከከፋ አደጋ ልንጠብቅ እንችላለን በቀላሉ::በተጨማሪ በነስር መልክ የወጣውን ደም ሊተኩልን ይችላሉ::

ነስር በሚነስራቸው ሰዎች መወሰድ የሌለባቸው የምግብ ኣይነት የቱ ነው??
1 ቅባት የበዛባቸው ምግብ….(Oily and greasy foods)
2 ሚያቃጥሉ ወይም በርበሬ የ በዛባቸው
3 caffeinated መጠጦች ለምሳሌ ቡና :ሻይ
~~~~~~~~~~~~continue ~~~~~~

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Minladrgilih Dele posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Minladrgilih Dele:

Share