Health ful የቤት ለቤት ህክምና

Health ful የቤት ለቤት ህክምና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Health ful የቤት ለቤት ህክምና, Medical and health, Addis Ababa.

👉 ወገብ ህመም ህመም አለዋት ፍቱንመፍትሄ ከ ኝጋ አለ ➡የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ...
08/10/2025

👉 ወገብ ህመም ህመም አለዋት ፍቱንመፍትሄ ከ ኝጋ አለ

➡የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ። ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚቋቋሙ ክፍሎች ናቸው። ዲስክ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ አለው ።

የዲስክ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውስጥ ፈሳሽ መውጣት ነው። ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው። ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል።

አንዳንድ ግዜ በእጅ ላይ የመደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም ስሜት አይኖረውም። የተንሸራተተው ዲስክ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማንም።

➡ የዲስክ መንሸራተት ህመም ምልክቶች

የዲስክ መንሸራተት ስለመከሰቱ ምንም እዉቅና ሳይኖርዎ ወይም ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳይኖር ችግሩ ሊኖር/ሊከሰት/ ይችላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳያሳዩ በምርመራ ወቅት በራጅ ላይ የዲስክ መንሸራተት መኖሩ ሊታወቅ ይችላል፡፡

➡የዲስክ መንሸራተት በሚኖርበት ወቅት የሚኖሩ የህመም ምልክቶች:-

• የእጅ/የእግር ላይ ህመም፡- የዲስክ መንሸራተቱ ያጋጠመዉ በታችኛዉ የጀርባ አጥንቶች አካባቢ ከሆነ ከፍተኛ ህመም በመቀመጫዎ፣ በጭንዎና በባትዎ አካበቢ እንዲሁም መርገጫዎ/የእግር መዳፉ ላይ ሊሰማዎ ይችላል፡፡ የዲስክ መንሸራተት ያጋጠመዎ አንገትዎ ላይ ከሆነ ህመሙ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰማዎ በትከሻና በእጅዎ ላይ ነዉ፡፡ ሕመሙ በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበት ወቅት ወይም ወደ ተወሰነ አቅጣጫ የጀርባ አጥንቶችዎን በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡

• የእጅ/ እግር መስነፍ፡- በዲስክ መንሸራተት ምክንያት የተጎዳ ነርቭ ካለ ያ የተጎዳዉ ነርቭ እንዲሰራ የሚያደርገዉ ጡንቻ ሊደክም ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ መራመድ መቸገር፣እቃ ማንሳት ያለመቻል ወይም መያዝ ያለመቻል ሊከሰት ይችላል፡፡

• የመደንዘዝ ወይም የመጠቅጠቅ ስሜት

• የማቃጠል ስሜት

• የጡንቻ ህመም

• የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች አየባሱከሔዱ እና ወዳው ካልታከሙ ህመሙ አየባሰ
እስከ ሰረጀሪ ከዛም አልፎ ለስቃይና ሞት ሊዳርግ ይችላል
➡ መንስኤዎች

የዲስክ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከጊዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ዲስክ ከእድሜ ጋር ውሃማ ይዘቱን ያጣል። ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል::

➡ለዲስክ መንሸራተት ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች

♦ እድሜ
♦ ትክክል ያለሆና ያተኝኘት እና ያቀማመጥ ፖዚሺን
♦ትክክል ያለሆና የስልክ ቴሌቪዢን computer አጠቃቀም
♦የሰዉነት ክብደት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላይ የጨመረ ከሆነ በጀርባ አጥንተትዎና ዲስኩ ላይ ጫና ይፈጥራል፡፡

♦ የስራዎ ሁኔታ፡- የስራቸዉ ፀባይ ጉልበት የሚጠይቅ ስራ የሚሰሩ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡

♦ በተደጋጋሚ ከባድ ነገር የሚያነሱ፣ የሚጎትቱ፣ የሚገፉ፣ ወደ ጎን መታጠፍና መጠማዘዝ የሚያበዙ ሰዎች ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡

♦ በዘር የሚመጣ፡- አንዳንድ ሰዎች ለመሰል ችግር ተጋላጭነታቸዉ መጨመር በዘር ሊወረስ ይችላል፡፡

➡ የዲስክ መንሸራተት ህክምና

👉 የጀርባዎ ህመምዎ ወደ እጅዎና እግርዎ የሚሰራጭ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና

1 💊የፊዚዮቴራፒ ህክምና ማድረግ

-የህመም ማስታገሻ፡- ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንደ አይቡፕሮፌን/አድቪል/ መዉሰድ

2. 💊 ሙቀት/ቀዝቃዛ ነገር መጠቀም፡- በመጀመሪያ ቀዝቃዛ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ ህመሙንና መቆጥቆጡን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ከተወሰኑ ቀናት በኃላ ሙቅ ነገር መያዝ ምቾትና የህመም ፈዉስ እንዲሰማዎ ስለሚያደርግ በቦታዉ ላይ መያዝ

3. 💊 ከመጠን ያለፈ እረፍት ያለማድረግ/ማስወገድ፡- ከመጠን ያለፈ እረፍት የመገጣጠሚያዎች መጠንከር/መተሳሰር እና ጡንቻዎች መስነፍ እንዲመጣ ስለሚያደርግ የፈዉሱን ጊዜ አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ይልቁንም በሚመችዎ አቅጣጫ ለ30 ደቂቃዎች እረፍት ማድረግና ከዚያን ለአጭር ጊዜ ወክ ማድረግ አሊያም የተወሰኑ ስራዎችን ማከናወን፡፡

ከህመምዎ እያገገሙ ባሉበት ወቅት ህመሙን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች/እንቅስቃሴዎች መቆጠብ፡፡

ከዲስክ መንሸራተት እንዴት መከላከል ይቻላል?
👉የአቀማመጥ እና የአተተኛኘት ሁኔታችንማስተካከል
👉የኮፒዮተር የእጅ ሰልካችንአጠቃቀም ፖዚሺን ማስተካከል
👉 ከፍተኛ የሰውነት ክብደት እንዳይኖርዎ ተጠንቀቁ
👉 ክብደት ሲያነሱ የሰውነት አቋምን ማስተካከል
👉 የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ካዩ በቂ እረፍት መውሰድ እና ተገቢውን ህክምና ማከናወን
👉 በቀን አድ ጌዜ የመሳሳብ እቅስቃሴ ማድረግ
👉 ማንኛወንም እቅስቃሴ ከመስራታችን ቀድመን የመሳሳብ እቅስቃሴ መስራት

ለበለጠ መረጃ 👉 📞 0919008097

🌹መላው የኦርቶዶክስ  እምነት ተከታዬች                     እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ  🌹                መልካም  ፋሲካ  በዓል                         ...
20/04/2025

🌹መላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዬች
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ 🌹

መልካም ፋሲካ በዓል
ይሁንልን!! 🙏

እንደተናገረ ተነሥቶአል
በዚህ የለም።
ማቴ 28፡6 🙏🙏🙏

20/12/2024

ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ክፍል የፍየል ስጦታ ተበረከተ

ነገሩ እንዲህ ነው:-

| በምሥራቅ ኢትዮጵያ አፋር ክልል ገዋኔ ተወላጅ የሆኑት አቶ ሳሊህ አሊ እድሜያቸው 38 አመት አርሶ አደርና የአራት ልጆች አባት ከሰባት ሳምንታት በፊት ህይወታቸውን የሚቀይር አደጋ አጋጥሟቸው ነበር ።

አቶ ሳሊህ አሊ አደጋው የደረሰባቸው በስራ ላይ አንዳሉ ከአምስት ሜትር ከፍታ ካለው ላይ ወድቀው ጉዳቱ የደረሰባቸው ሲሆን ጉዳታቸውም በጣም ከፍተኛ ነበር ፡፡ በአደጋውም ምክንያት በደም-ጋን (Pelvis) አጥንታቸው ላይ ከባድ ስብራቶች እንዲሁም በኮቴያቸው (Calcaneous) ላይ ከባድ ስብራት ደርሶባቸዋል።

ታካሚው አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ክፍል ክትትል ከሚያድጉበት ሆስፒታል በሪፈር መጥተው ክትትል አንዲያደርጉ ይደረጋል ፡፡ በአጥንት ህክምና ክፍል ሀኪም ዶክተር ገመቺስ ረጋሳ የሚመራው የቀዶ ህክምና ቡድን ፈጣንና ውጤታማ ውስብስብ ቀዶ ህክምናና እንክብካቤ ያደርግላቸዋል ።

በቀዶ ህክምና ቡድን የተሳካና ውጤታማ ቀዶ ሕክምና ስለተደረገላቸው በማገገምና የህክምና ቡድኑም ክትትል እያደረገላቸው በሳምንታት ውስጥ በሳዩት ለውጥ ምክንያት አቶ ሳሊህ አሊ ጤንንታቸው በተሳካ ሁኔታ ተመልሶላቸው አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ። የህክም ክትትል ሲያደረጉ የነበሩት ታካሚ አቶ ሳሊህ አሊ ከሆስፒታል ህክምናቸውን ጨርሰው (discharged with appointment) በቀጠሮ ወደ መጡበት አፋር ክልል አንዲመለሱ ተደርጓል ።

አገራቸው አፋር ጥቂት ሳምንታት ቆይተው ያገገሙት ታካሚ ሳሊህ አሊ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን ለመግለጽና ለማሳየት አቶ ሳሊህ አሊ ለተከታታይ ምርመራ (Follow up) ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲመለሱ ለህክምና ቡድኑ እንደ ምስጋና የሚሆንላቸውን የፍየል ጠቦት ከአፋር ድረስ ይዘው መጥተው ከምስጋና ጋር ለህክምና ቡድኑ አበርክተዋል ።

ይህን ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን ለሚያንፀባርቅ ብቻ ሳይሆን በአፋር ክልል ውስጥ እንዲህ ያሉ የምስጋና ተግባራት በጣም ዋጋ እንዳላቸውና ቦታ እንደሚሰጣቸው አንዲሁም የፍቅራቸው የሚያሳይ እንደሆነ የአፋር ባህላቸውንና አከባቢያቸውን የሚያውቁ ሰዎች አጫውውናል ።

የአቶ ሳሊህ አሊ ታሪክ ርኅራኄ እና ችሎታ ያለው የህክምና እንክብካቤ በታካሚዎች ህይወት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን በጎ ሀሳብን የሚያሳይና ሙያችንን የሚያስከብር ትልቅ ማሳሰቢያ ነው ፡፡ አቶ ሳህሊ አሊን በትምህርት ከፍላችን ስም እያመሰገንን ።

የአ.አ.ዩ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአጥንት እና የትራውማ ህክምና ክፍል በሰራተኞቹ ቁርጠኝነትና ስነ -ምግባርን በተላበሰ ሀኪሞች በተሰጠው የህክምና አገልግሎት ምክንያት ወደፊትም ለብዙዎች የተስፋ እና የፈውስ መብራት ሆኖ ማህበረሰቡን በማገልገል አንደሚቀጥል ቃል እየገባን ።

በዚህ የህክምና አገልግሎት የተሳተፉና የተደሰቱት የአጥንት ህክምና ክፍል ሐላፊና የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ አርሶ አደሩን ለማበረታታት፣ ማገገሚያና ትራንስፖርት የሚሆን 10ሺህ ብር በአጥንት ህክምና ትምህርት ከፍልና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስም ለአቶ ሳህሊ አሊ አበርክተውላቸዋል።

(ከዶ/ር ሳምሶን (ሬዚደንት) ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)

በአዲስ አበባ ከተማ ለተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የሚደረግ ጥንቃቄ በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ  በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል...
09/11/2023

በአዲስ አበባ ከተማ ለተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የሚደረግ ጥንቃቄ

በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ስንሻው አባይ ገለፁ።

ጉንፋን መሰል ህመም ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣ ሳል፣ ራስ ምታት፣ ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣ ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡

እንደ ዶክተሩ ገለፃ፤ ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የላይኛውን የመተንፈሻ አካል ክፍል የሚያጠቃ ነው ብለዋል፡፡ ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፈሳሽ መውሰድ፣ ከቅዝቃዜ ራስን ማራቅ (ሙቀቱን የተመጣጠነ ማድረግ)፣ መኖሪያ ቤትን አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣ በቂ የሆነ እረፍት መውሰድ እና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ፡፡

በሌላ በኩል በቤት ውስጥ የእፅዋት ዝርያዎችን በፍም (እሳት) ላይ በማጨስ ጭሱን መታጠን ሳንባ እንዲያብጥ ወይም እንዲቆጣ በማድረግ ለጉዳት እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡

ዶክተሩ አክለውም፤ማህበረሰቡ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት፣ በንግድ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣ የእጅን ንፅህና በአግባቡ በመጠበቅ እንዲሁም አስም ያለባቸው ምልክቶቹ እንደታዩባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ሄደው መታየት እንዳለባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በ2 ሺህ ያህል ናሙናዎች ላይ ባደረገው ምርመራ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

የዝናብ ወራት ማለፉን ተከትሎ በጥቅምትና ህዳር ወቅት ላይ አብዛኛውን ጊዜ የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ይከሰታል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ-ሃይል ዋና አስተባባሪ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ተከስቷል፡፡

እጅን በመታጠብ፣ አፍና አፍንጫን በመሸፈን በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል፡፡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቂ እረፍት በመውሰድ፣ ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች በመጠቀምና ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክረ-ሀሳቦች በመተግበር፣ በርና መስኮቶችን በመክፈት፤ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግ መከላከል እንደሚቻል ነው የገለፁት፡፡

(ኤ ኤም ኤን)

ጊላይን-ባሬ ሲንድረም (ጂቢኤስ) GBSጊላይን-ባሬ ሲንድረም (ጂቢኤስ) ያልተለመደ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት በሽታ የመከላከል ስርዓት የጡንቻ እንቅስቃሴን እና ስሜትን የሚቆጣጠሩትን ...
30/04/2023

ጊላይን-ባሬ ሲንድረም (ጂቢኤስ) GBS

ጊላይን-ባሬ ሲንድረም (ጂቢኤስ) ያልተለመደ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት በሽታ የመከላከል ስርዓት የጡንቻ እንቅስቃሴን እና ስሜትን የሚቆጣጠሩትን ነርቭ : የነርቪ ሰራዐት ና ነርቮችን የሚያጠቃ ነው።

ይህ ወደ ድክመቶች: የመደንዘዝ እና የእጅ እግር መወጠርን ያመጣል : ይህም ከባድ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ወደ ሽባነት ሊሸጋገር ይችላል.

የጂቢኤስ ትክክለኛ መንስኤ ሙሉ በሙሉ አልተረዳም ነገር ግን እንደ ቫይራል ወይም የባክቴሪያ ኢንፌክሽን በመሳሰሉት ኢንፌክሽኖች እንደቀሰቀሰ ይታሰባል።
የሕመሙ ምልክቶች ድንገተኛ ሊሆኑ ይችላሉ እና በሰዓታት ወይም ቀናት ውስጥ ሊዳብሩ ይችላሉ።

በጣም የተለመዱት የጂቢኤስ ምልክቶች የጡንቻ ድክመት፣ የመደንዘዝ ወይም የእጅ እግር መወጠር፣ እና የማስተባበር እና ሚዛናዊነት ችግር ያካትታሉ።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ድክመቱ የተጎዳው ሰው በራሱ መንቀሳቀስ ወይም መተንፈስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል.

ለጂቢኤስ የሚሰጠው ሕክምና ሰውነት በሚድንበት ጊዜ ምልክቶችን ለመቆጣጠር እንደ አካላዊ ሕክምና እና የመተንፈሻ አካላት ድጋፍን የመሳሰሉ ደጋፊ እንክብካቤን ያካትታል።

በአንዳንድ አጋጣሚዎች የፕላዝማፌሬሲስ ወይም የደም ሥር ኢሚውኖግሎቡሊን ሕክምና የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ለመቀነስ እና መልሶ ማገገምን ለማፋጠን ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል.

አብዛኛዎቹ የጂቢኤስ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ያገግማሉ ወይም ትንሽ ቀሪ ውጤቶች ብቻ ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን አልፎ አልፎ፣ ሁኔታው ​​ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል።

Call 👉 0919008097

በቅንነት ሸር ላይክ ፎሎ አድርጉ

Like sher follow please

Health ful የቤት ለቤት ህክምና
በሆስፒታለም ህክምነውን አንሠጣለን

👉 ዒድ ሙባረክ Eid Mubarak عيد مباركለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1444’ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!መልካም በዓል!     Health ...
21/04/2023

👉 ዒድ ሙባረክ

Eid Mubarak عيد مبارك

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1444’ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል! Health ful የቤትለቤት ህክምነ ቤተሰቦች call 👉0919008097

†✝† እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝††✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝††✝† ብርሃነ ትንሣኤ †✝††✝† የዓለማት ...
16/04/2023

†✝† እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†

†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†

†✝† ብርሃነ ትንሣኤ †✝†

†✝† የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ : የዘለዓለም አምላክ ወልድ ዋሕድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዕለት መግነዝ ፍቱልኝ : መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ሥልጣኑ ተነስቷልና እንኳን ደስ አለን::

††† ከዚህ በኋላ ለ50 ቀናት እንዲህ እያልን ሰላምታ እንለዋወጣለን:-
††† ክርስቶስ ተንስአ እሙታን!
¤በዐቢይ ኃይል ወስልጣን!
††† አሠሮ ለሰይጣን!
¤አግዐዞ ለአዳም!
††† ሰላም!
¤እምይእዜሰ!
††† ኮነ!
¤ፍሥሐ ወሰላም!

በእርግጥም አምላካችን በሞቱ ሞትን ገድሎ : በትንሣኤው ሕይወትን አድሎናልና ደስታ ይገባናል:: መድኃኔ ዓለም በኅቱም ድንግልና እንደ ተወለደ በኅቱም መቃብር ተነስቷል:: ለደቀ መዛሙርቱም "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ሲል በዝግ ደጅ ገብቷል::

በዕለተ ትንሣኤው የመጀመሪያውን ደስታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተካፍላለች:: የእርሷን ያህል በሃዘን የተጐዳ የለምና:: ቀጥለው ቅዱሳት አንስት እነ ማርያም መግደላዊት ትንሣኤውን አይተዋል:: ሰብከዋልም::

††† በዚሕች ቀን ማዘን አይገባም:: በትንሣኤው የደነገጡና የታወኩ የአጋንንትና የአይሁድ ወገኖች ብቻ ናቸውና::

††† አምላካችን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በረከት አይለየን:: በዓሉንም የሰላም : የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::

††† የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን::

††† "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም:: 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል: በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ::" †††
(ሉቃ. ፳፬፥፭-፰)

††† "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል:: ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና:: ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና::" †††
(፩ቆሮ. ፲፭፥፳)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

15/03/2023
➡የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ...
15/03/2023

➡የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ። ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚቋቋሙ ክፍሎች ናቸው። ዲስክ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ አለው ።

የዲስክ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውስጥ ፈሳሽ መውጣት ነው። ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው። ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል።

አንዳንድ ግዜ በእጅ ላይ የመደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም ስሜት አይኖረውም። የተንሸራተተው ዲስክ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማንም።

➡ የዲስክ መንሸራተት ህመም ምልክቶች

የዲስክ መንሸራተት ስለመከሰቱ ምንም እዉቅና ሳይኖርዎ ወይም ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳይኖር ችግሩ ሊኖር/ሊከሰት/ ይችላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳያሳዩ በምርመራ ወቅት በራጅ ላይ የዲስክ መንሸራተት መኖሩ ሊታወቅ ይችላል፡፡

➡የዲስክ መንሸራተት በሚኖርበት ወቅት የሚኖሩ የህመም ምልክቶች:-

• የእጅ/የእግር ላይ ህመም፡- የዲስክ መንሸራተቱ ያጋጠመዉ በታችኛዉ የጀርባ አጥንቶች አካባቢ ከሆነ ከፍተኛ ህመም በመቀመጫዎ፣ በጭንዎና በባትዎ አካበቢ እንዲሁም መርገጫዎ/የእግር መዳፉ ላይ ሊሰማዎ ይችላል፡፡ የዲስክ መንሸራተት ያጋጠመዎ አንገትዎ ላይ ከሆነ ህመሙ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰማዎ በትከሻና በእጅዎ ላይ ነዉ፡፡ ሕመሙ በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበት ወቅት ወይም ወደ ተወሰነ አቅጣጫ የጀርባ አጥንቶችዎን በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡

• የእጅ/ እግር መስነፍ፡- በዲስክ መንሸራተት ምክንያት የተጎዳ ነርቭ ካለ ያ የተጎዳዉ ነርቭ እንዲሰራ የሚያደርገዉ ጡንቻ ሊደክም ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ መራመድ መቸገር፣እቃ ማንሳት ያለመቻል ወይም መያዝ ያለመቻል ሊከሰት ይችላል፡፡

• የመደንዘዝ ወይም የመጠቅጠቅ ስሜት

• የማቃጠል ስሜት

• የጡንቻ ህመም

• የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች አየባሱከሔዱ እና ወዳው ካልታከሙ ህመሙ አየባሰ
እስከ ሰረጀሪ ከዛም አልፎ ለስቃይና ሞት ሊዳርግ ይችላል
➡ መንስኤዎች

የዲስክ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከጊዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ዲስክ ከእድሜ ጋር ውሃማ ይዘቱን ያጣል። ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል::

➡ለዲስክ መንሸራተት ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች

♦ እድሜ
♦ ትክክል ያለሆና ያተኝኘት እና ያቀማመጥ ፖዚሺን
♦ትክክል ያለሆና የስልክ ቴሌቪዢን computer አጠቃቀም
♦የሰዉነት ክብደት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላይ የጨመረ ከሆነ በጀርባ አጥንተትዎና ዲስኩ ላይ ጫና ይፈጥራል፡፡

♦ የስራዎ ሁኔታ፡- የስራቸዉ ፀባይ ጉልበት የሚጠይቅ ስራ የሚሰሩ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡

♦ በተደጋጋሚ ከባድ ነገር የሚያነሱ፣ የሚጎትቱ፣ የሚገፉ፣ ወደ ጎን መታጠፍና መጠማዘዝ የሚያበዙ ሰዎች ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡

♦ በዘር የሚመጣ፡- አንዳንድ ሰዎች ለመሰል ችግር ተጋላጭነታቸዉ መጨመር በዘር ሊወረስ ይችላል፡፡

➡ የዲስክ መንሸራተት ህክምና

👉 የጀርባዎ ህመምዎ ወደ እጅዎና እግርዎ የሚሰራጭ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና

1 💊የፊዚዮቴራፒ ህክምና ማድረግ

-የህመም ማስታገሻ፡- ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንደ አይቡፕሮፌን/አድቪል/ መዉሰድ

2. 💊 ሙቀት/ቀዝቃዛ ነገር መጠቀም፡- በመጀመሪያ ቀዝቃዛ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ ህመሙንና መቆጥቆጡን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ከተወሰኑ ቀናት በኃላ ሙቅ ነገር መያዝ ምቾትና የህመም ፈዉስ እንዲሰማዎ ስለሚያደርግ በቦታዉ ላይ መያዝ

3. 💊 ከመጠን ያለፈ እረፍት ያለማድረግ/ማስወገድ፡- ከመጠን ያለፈ እረፍት የመገጣጠሚያዎች መጠንከር/መተሳሰር እና ጡንቻዎች መስነፍ እንዲመጣ ስለሚያደርግ የፈዉሱን ጊዜ አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ይልቁንም በሚመችዎ አቅጣጫ ለ30 ደቂቃዎች እረፍት ማድረግና ከዚያን ለአጭር ጊዜ ወክ ማድረግ አሊያም የተወሰኑ ስራዎችን ማከናወን፡፡

ከህመምዎ እያገገሙ ባሉበት ወቅት ህመሙን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች/እንቅስቃሴዎች መቆጠብ፡፡

ከዲስክ መንሸራተት እንዴት መከላከል ይቻላል?
👉የአቀማመጥ እና የአተተኛኘት ሁኔታችንማስተካከል
👉የኮፒዮተር የእጅ ሰልካችንአጠቃቀም ፖዚሺን ማስተካከል
👉 ከፍተኛ የሰውነት ክብደት እንዳይኖርዎ ተጠንቀቁ
👉 ክብደት ሲያነሱ የሰውነት አቋምን ማስተካከል
👉 የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ካዩ በቂ እረፍት መውሰድ እና ተገቢውን ህክምና ማከናወን
👉 በቀን አድ ጌዜ የመሳሳብ እቅስቃሴ ማድረግ
👉 ማንኛወንም እቅስቃሴ ከመስራታችን ቀድመን የመሳሳብ እቅስቃሴ መስራት

ለበለጠ መረጃ 👉 📞 0919008097

ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች…ዛሬ በዳዊት ከተማ…  መድኃኒት እርሱ ክርስቶስ ጌታ የሆነው ተወልዶላችኋልና።【 ሉቃ :- 2:10·11】እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስ...
07/01/2023

ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች…ዛሬ በዳዊት ከተማ… መድኃኒት እርሱ ክርስቶስ ጌታ የሆነው ተወልዶላችኋልና።
【 ሉቃ :- 2:10·11】

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ባዓል በሰላም አደረሳችው አደረሰን 💒🙏🙏🙏

Address

Addis Ababa

Telephone

+251919008097

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health ful የቤት ለቤት ህክምና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram