25/04/2026
⚠️ ኩላሊትን የሚጎዱ 6 አደገኛ የእለት ተእለት ልማዶች
ለኩላሊት ጤና ጥንቃቄ ማድረግ በየቀኑ ከምንወስናቸው ትናንሽ ውሳኔዎች ጋር የተያያዘ ነው። አንዳንድ ልማዶች በጊዜ ሂደት ኩላሊት ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ
ለኩላሊት ጉዳት ሊዳርጉ የሚችሉ የዕለት ተዕለት ልማዶች የሚከተሉት ናቸው ፦
🧂 ጨው ማብዛት
ከመጠን ያለፈ የጨው አጠቃቀም የደም ግፊትን ይጨምራል። ከፍተኛ የደም ግፊት ደግሞ ለኩላሊት መጎዳት ዋነኛው መንስኤ ሲሆን፣ ኩላሊቶቹ ትርፍ ጨውን ለማስወገድ ጠንክረው እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል
💊 የህመም ማስታገሻዎችን ማዘውተር
እንደ አይቡፕሮፌን ያሉ የህመም ማስታገሻዎችን ያለ ገደብ መውሰድ ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም ፍሰት በመቀነስ በሂደት ለኩላሊት ህብረ ህዋሳት መጎዳት ምክንያት ይሆናል
🍭 ስኳር ማብዛት
ስኳር ለከፍተኛ ውፍረትና ለስኳር በሽታ ይዳርጋል፤ እነዚህ ደግሞ ለከባድ የኩላሊት በሽታዎች መከሰት ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው። በመጠጦችና በተለያዩ ማጣፈጫዎች ውስጥ የሚገኙ "ድብቅ" ስኳሮችን ማስተዋል ያስፈልጋል
🍟 የታሸጉና የተቀነባበሩ ምግቦችን ማዘውተር
እነዚህ ምግቦች አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ የጨውና የፎስፈረስ መጠን ይይዛሉ። ከፍተኛ የፎስፈረስ መጠን ደግሞ በኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል
💧 በቂ ውሃ አለመጠጣት
ውሃ ኩላሊቶች ጨውና መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት ውስጥ እንዲያጸዱ ይረዳል። በቂ ውሃ አለመጠጣት ኩላሊቶች ቆሻሻን የማጣራት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ ከማድረጉም በላይ ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ እድልን ይጨምራል
🍺 ከመጠን ያለፈ የአልኮል መጠጥ
አዘውትሮ አልኮልን ከመጠን በላይ መጠጣት ለከባድ የኩላሊት በሽታ የመጋለጥ እድልን በእጥፍ እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ
የእርሶ ልማድ የትኛው ነው❓ እኔ ውሀ መጠጣት ሰነፍ ነኝ
Ethio Hakim
Hakim Mereja ሀኪም መረጃ
Digital Hakim