
21/05/2025
ቨርቹዋል ኦቲዝም ምንድነው?
👉🏽 ቨርቹዋል ኦቲዝም ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በብዛት ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት በመጠቀም የሚፈጥረ ሁኔታ ነው።
👉🏽 ከሁለት አመት በታች የሆኑ ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት የሚጠቀሙ ልጆች የተለያዩ የባህርይ እክሎች እና የተግባቦት እክሎች ያጋጥማቸዋል። በሀገራችንም አሁን ላይ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች እየታዩባቸው ያሉ ህፃናት እየበዙ ነው ይህም ብዙ ልጆች ከወራት እድሜያቸው ጀምሮ ቲቪና ስልክ ላይ በተለያየ ቋንቋ የተለያዩ ነገሮችን ማየታቸው እና ከእኩዮቻቸው ጋር ተግባቦት አለመኖሩ ለዚህ እክል ተጠቂ እንዲሆኑ እያደረጋቸው ይገኛል ።
የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች
የቨርቸዋል ኦቲዝም ምልክቶች ከአንድ ልጅ አንድ ልጅበየተለያየ ሊሆን ይችላል ። ሆኖም ምልከቶች ከምንላቸው ውስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።
🧩 ከፍተኛ እንቅስቃሴ (እረፍት የለሽ መሆን)
🧩ትኩረት ማድረግ አለመቻል ወየረም አጭር ትኩረት መስጠት
🧩 ጨዋታዎች ላይ ፍላጎት መቀነስ
🧩ማህበራዊ መስተጋብር ወይም ተግባቦት አለመኖር
🧩ተለዋዋጭ ስሜት
🧩 የመረዳት እክል
🧩 የንግግር እና ቋንቋ መዘግየት
🧩 የተገደበ የአይን ግንኙነት እና ማህበራዊ መስተጋብር
🧩ተደጋጋሚ ባህሪያት ወይም የተገደበ ፍላጎት
🧩ስሜትን የማቋቋም እክል
🧩ለነገሮች ስሜታዊነት (sensitive)
🧩ተደጋጋሚ እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ፡ እጅ መጠቅለል፣ መሽከርከር)
🧩 ብስጭትና ቁጣዎች ከምልክቶቹ ውስጥ ይጠቀሳሉ።
የቪርቹዋል ኦቲዝም መንስኤ
👉🏽ቪርቹዋል ኦቲዝም ህፃናት በሞባይሎች፣ በታብሌት፣ በቴሌቭዥን፣ በኮምፒውተሮች እና በላፕቶፕ ስክሪን ላይ የረዘመ ጊዜ ሲያሳልፉ የሚፈጠር ሁኔታ ነው
ይህም
1. ከመጠን በላይ የስክሪን ጊዜ፡ ከ 3 አመት በፊት ለዲጂታል ስክሪኖች ለረጅም ጊዜ መጋለጥ በተለይም ያለአዋቂዎች መስተጋብር።
2. የማህበራዊ መስተጋብር እጦት፡ የወላጅ እና የልጆች ውይይት፣ የአካል ጨዋታ እና መስተጋብር መቀነስ።
3. የአካባቢ እንቅስቃሴ አለመኖር ፡ የገሃዱ አለም የስሜት ህዋሳት ልምዶችን የሚገድቡ ስልክና ቲቪ አጠቃቀም ያካትታል ።
ቨርቸዋል ኦቲዝምን መከላከል፡-
🧩 ቲቪ እና ስልክ የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ
• ከ 2 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የስክሪን ጊዜ አለማድረግ።
• ከ2-5 አመት ለሆኑ ህጻናት ቢበዛ 1 ሰአት/ቀን (በክትትል)።
🧩 ማህበራዊ ተግባቦትና መስተጋብርን ማበረታታት።
• በመናገር፣ በማንበብ፣ በመዘመር እና በአካላዊ ጨዋታ እንዲሳተፉ ማድረግ።
🧩አነቃቂ አካባቢን መስጠት፡-
• አሻንጉሊቶችን፣ የስሜት ህዋሳትን እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ ልምዶችን ለልጆች ማሳየትና መአስተማር ።
🧩ጤናማ የስክሪን አጠቃቀም ሞዴል፡
ወላጆች ቲቪና ስልክ አጠቃቀምን በመገደብ ረገድ በምሳሌነት መምራት አለባቸው።
የቪርቹዋል ኦቲዝም ቴራፒዎች
👉🏽በዋነኛነት የባህርይ ቴራፒ እና የስፒች ቴራፒ
👉🏽የስክሪን ጊዜን ማቆም ወይም መገደብ
👉🏽የአካል እንቅስቃሴዎችን መጨመር
👉🏽ፊት ለፊት የሚናገሩበትን መንገድ መፍጠርና ማስተዋወቅ
👉🏽 ምቹና ደጋፊ አካባቢ መፍጠር
ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒ ካስፈለጎ
ይደውሉ 👇👇👇
+251940103047
+251954999933
📍 አድራሻ : መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
ጃዚኤል( ማህሌት) ሰፒች ቴራፒ
በማህሌት አዘነ
ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒስት
Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy
Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic
ፍላሽ ካርዶችንና የቴራፒ መጫወቻ እቃዎች ለማግኘት
https://t.me/JoMaFlashcards
☎️0978396662
0991239091
📍ኦንላይን (ዴሊቨሪ መሪ አያትና መገናኛ)