
28/07/2025
የትኛውም መሥሪያ ቤት ብትሰራ፣ የትኛውም ዓይነት ሙያ ቢኖርህ፣ እጅግ ብዙ ሰራተኞችን ብትመራ፣ አንድ ቀን በሌላ ሰው ትተካለህ። ወይም ያንተ ቦታ ምንም ለውጥ አያመጣም። አንድ ቀን ትተካለህ። የአንተ መጉደል ለዚያ መሥሪያ ቤት ቅንጣት አያጎድልም።
አንተ እኮ እናትና አባትህን፣ ወይም ልጅና ሚስትህን፣ ወይም ሌሎች የምትወዳቸውን ቤተሰቦች ትተህ ስንት ቀን በስራ ጉዳይ ተወጥረህ አብረሀቸው አልሆንክም። ስንት ጊዜስ አልጠየካቸውም። በእርግጥ አንዳንዴ ከአሁን አሁን የኑሮህን ሁኔታ ፈቀቅ ለማድረግ ብለህ ነው የምትለፋው። ይህን እንደዚህ ያንን እንደዚያ ባደርገው ኑሮየን አሻሽላለሁ ብለህ ነው የምትደክመው። ግን እንደጠበከው ሆኖልሃል? ያሰብከውን እድገት አግኝተሃል? አገኘዋለሁ ያልከውን መሻሻልስ ደርሰህበታል? መልሱን ለአንተ ትተንዋል።
ሆኖም ግን ሁልጊዜ እያስታወስክ መሥራት ያለብህ ነገር ቢኖር ጊዜው መቼ እንደሆነ አታውቀው ይሆናል እንጂ ትተካለህ። ወይም የአንተ በሥራ ቦታህ ላይ አለመገኘት ያን ያህል አያከስርም። አዎ፣ ተተኪ ነህ።
እናም ወዳጄ፣
አንተን በቅጽበት ለሚተካህ እና ዋጋህን ከኢምንት ለሚቆጥረው መሥሪያቤትስ ምን ያህል ዋጋ ትሰጠዋለህ? ነገር ግን የቤተሰብ ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል። በቀላሉ አትተካም። በቀላሉ አትረሳም። ለማን ትኩረትና ጊዜ መስጠት እንዳለብህ ታውቃለህ። በነገራችን ላይ የምንልህ ገብቶሃል።
በተለይ የአንተ መጉደል ምንም ተጽዕኖ ለማያደርስ መሥሪያ ቤት ራስህን፣ ቤተሰብህን፣ ጊዜህን አትሰዋ። ምክንያቱም አንድ ቀን በሌላ ትተካለህ። እናም ሁልጊዜ ዋጋህን ከፍ ከሚያደርግልህ፣ አንተ ባትኖር የሆነ ተጽዕኖ ማድረስ ከምትችልበት ጋር ተጣበቅ። አለበለዚያ አታጎድልም!
ይህ ማለት በሥራህ ቀልድ ማለት አይደለም፣ ይልቁንም ሥራህን በአግባቡ ከሚረዱ ጋር ሁን ማለት እንጂ!
ይልቁንስ ተከተለን👇
https://www.youtube.com/