13/05/2023
✍️ #እርግዝና #በወርአበባ በየትኞች ቀናት ይፈጠራ?በየትኞቹ ደሞ አይፈጠርም?
👉 #ውድ #የዶክተር #ሸምሴ ተከታታዮች እርግዝና እንዴትና መቼ እንደሚከሰት ማወቅ ማርገዝ ለሚፈልጉም ሆነ ለማይፈልጉ ጠቀሜታው የላቀ ነው፡፡ ማርገዝ ለሚፈልጉ ጊዜና ሁኔታዎችን አመቻችቶ ለመሞከር ሲረዳ ለማይፈልጉ ደግሞ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ለመጠንቀቅ ያግዛቸዋል፡፡ ይሁንና ካልተፈለገ እርግዝና ለመጠበቅ ወይም አራርቆ መዉለድ ለሚሹ የእርግዝና መከላከያ መውሰድ ዋነኛው መፍትሄ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
👉በአንድ የወር አበባ ኡደት ውስጥ ለፈርቲላይዜሽን(ለእርግዝና) የደረሰ የሴት እንቁላል ከመቀመጫው ከኦቫሪ ወጥቶ በማህጸን ቱቦ አድርጎ ወደ ማህጸን ይጓዛል፡፡ ይህ ሂደት ኦቩሌሽን ይባላል፡፡ በመደበኛነት አንድ ሴት ኦቩሌት የምታደርገው በአንድ የወር አበባ ኡደት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከኦቫሪ የወጣው እንቁላል ለፈርቲላይዜሽን(ለእርግዝና) ብቁ ሆኖ በማህጸን ቱቦ ውስጥ የሚቆየው ከ12 እስከ 24 ሰአት ብቻ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከወንድ ዘር ጋር ተገናኝቶ እርግዝና ካልተፈጠረ እንቁላሉ ከማህጸን ግድግዳ ጋር አብሮ በወር አበባ መልክ ይወገዳል፡፡
👉ኦቩሌት የሚደረግበትን ጊዜ ማወቅ ቶሎ ለማርገዝ ይረዳል፡፡ አንዲት ሴት ኦቩሌት የምታደርግበትን ጊዜ በእርግጠኛነት መናገር ባይቻልም ለመገመት የሚያስችሉ የተለያዩ ምልክቶችን ማወቅና ለማርገዝ የሚደረገውን ሙከራ በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ማድረግ የማርገዝን እድል ይጨምራል።፡ይህንን ጊዜ መገመት ከሚያስችሉት ዘዴዎች አንዱና ቀለል ያለው ቀን መቁጠር ነው፡፡
👉እንደ የወር አበባ ኡደት ሁሉ የኦቩሌሽን ጊዜም ከሴት ሴት እንዲሁም አንድ ሴት ላይ ከወር ወር የተለያየ ስለሆነ ይህ ነው ብሎ አንድን ቀን መጠቆም አይቻልም። በአማካይ የወር አበባቸዉ ኡደት ከ28-32 ቀን ለሆነ ሴቶች ኦቩሌት ያደርጋሉ ተብሎ የሚገመተው ያለፈው የወር አበባቸው ከጀመረበት ቀን በኋላ ከ11ኛው እስከ 21ኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ጊዜ ለእርግዝና ምቹ ጊዜ ተብሎ ይታወቃል።
👉ከላይ እንደተገለጸው ከኦቩሌሽን በኋላ እንቁላሉ ለፈርቲላይዜሽ (ለእርግዝና) ብቁ ሆኖ የሚቆየው ከ12-24 ሰአት ያህል ቢሆንም የወንድ ዘር ግን ከግብረስጋ ግንኙነት በኋላ በሴቷ ሰውነት ውስጥ ከሶስት እስከ አምስት ቀን መቆየት ስለሚችል እርግዝና ሊፈጠር የሚችልባቸውን ቀናት ሰፋ ያደርገዋል፡፡ ለእርግዝና ምቹ ነዉ ተብሎ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ዉስጥ በየቀኑ አሊያም አንድ ቀን እየዘለሉ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ የማርገዝን እድል ያሰፋል፡፡ ከግንኙነት በኋላ በጀርባ ተኝቶ ከ10-15 ደቂቃ መቆየት የወንዱ ዘር ወደ ማህጸን በር ለመግባት በቂ ጊዜ ይሰጠዋል።
👉በተቃራኒዉ ማርገዝ ለማይፈልጉ ደግሞ ኦቩሌሽን ከሚጠበቅበት 3-5 ቀናት በፊት ጀምሮ በኦቩሌሽን ወቅትም ግንኙነት አለማድረግ ይመረጣል። ኮንዶም ወይም ሌሎች የእርግዝና መከላከያ መንገዶችም ጥሩ አማራጭ ናቸው፡፡
👉ጤናማ የወንድ ዘር የእርግዝናን እድል ለመጨመር ስለሚረዳ ለማርገዝ ሙከራ በሚደረግበት ጊዜ ወንዱም አልኮል መጠጥን በመቀነስ፤ ሲጃራ በማቆምና የሰውነት ክብደትን በመቆጣጠር የበኩሉን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
🛑ሌላስ ጊዜ ቢሆን ባይጠጣና ባይጨስ አይሻልም?
ሌሎች ኦቩሌሽንን ሊጠቁሙ የሚችሉ ምልክቶች ደግሞ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት መካከል የማህጸን ፈሳሽ መጠን መጨመር፤ ባንዳንድ ሴቶች ላይ በኦቩሌሽን ወቅት በአንደኛው ጎናቸው ህመም ቢጤ መሰማት፣ በሌሎች ደግሞ ከሚቀጥለው የወር አበባ በፊት መሀከለኛው ቀን አካባቢ ትንሽ ደም መፍሰስ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ መረገዝ አለመረ