24/10/2025
የሳምንቱ የጤና ምክር፡ ክብደት መቀነሻ መድኃኒቶች
✅ ጥቅሞች
• የምግብ ፍላጎትና የረሃብ ስሜትን ይቀንሳሉ።
• ከአመጋገብና እንቅስቃሴ ጋር ሲሄዱ ቋሚ ክብደት ለመቀነስ ይረዳሉ።
• የደም ስኳር፣ ግፊትና ኮሌስትሮልን ጨምሮ አጠቃላይ ጤናን ሊያሻሽሉ ይችላሉ።
⚠️ ጉዳቶች
• ማቅለሽለሽ፣ ተቅማጥ ወይም የልብ ምት መጨመር የመሳሰሉ የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላሉ።
• የአኗኗር ለውጥ ሳይደረግ መድኃኒቱ ከተቋረጠ ክብደቱ ብዙ ጊዜ ይመለሳል።
አስቸኳይ የሕክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች
• የልብ ችግሮች: የልብ ምት መዛባት ወይም መጨመር።
• የሐሞት ከረጢት ችግሮች: በላይኛው ቀኝ ሆድ ላይ ህመም።
• ጣፊያ መቆጣት (Pancreatitis): ወደ ጀርባ የሚወነጨፍ ከባድ የሆድ ህመም።
• ኩላሊት ላይ ጉዳት: የሽንት መጠን መቀነስ፣ በእግር ላይ እብጠት።
• የስነ ልቦና ለውጦች: የስሜት መለዋወጥ፣ ጭንቀት
• አለርጂ: ሽፍታ፣ የሰውነት ማበጥ፣ ወይም የመተንፈስ ችግር።
የተሻሉ እና አስተማማኝ ዘላቂ መፍትሔዎች
• ሚዛናዊ አመጋገብ: ሙሉ ምግቦች፣ ፋይበር እና ስስ ፕሮቲን ላይ ማተኮር፤ የተቀነባበሩ ስኳሮችን መገደብ።
• ቋሚ እንቅስቃሴ: በሳምንት ቢያንስ 150 ደቂቃ ስፖርት።
• እንቅልፍና ጭንቀትን መቆጣጠር
• በቂ ውኃ መጠጣት
• አለመሰልቸት (ቋሚነት)
ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል
በሀኪምች ህብረት ለህብረተሰብ ጤና የቆመ
Weekly Health Tip: Weight Loss Medications (General Overview)
✅ Benefits:
• Help reduce appetite and food cravings
• Support steady weight loss when combined with diet and exercise
• May improve blood sugar, blood pressure, and cholesterol
⚠️ Disadvantages:
• Can cause side effects like nausea, diarrhea, or increased heart rate
• Some are expensive or require injections
• Weight often returns if stopped without lifestyle changes
Serious Side Effects (Require Medical Attention):
• Heart problems: Increased heart rate, high blood pressure, or irregular heartbeat
• Gallbladder issues: Pain in the upper right abdomen, nausea, or vomiting
• Pancreatitis: Severe stomach pain radiating to the back
• Kidney injury: Reduced urine output, swelling in legs
• Mental health effects: Mood changes, anxiety, or suicidal thoughts (rare)
• Allergic reactions: Rash, swelling, or breathing difficulty
Better and Safer Long-Term Strategies:
• Balanced eating: Focus on whole foods, fiber, lean proteins, and fewer processed sugars
• Regular exercise: At least 150 minutes/week of walking, cardio, or strength training
• Sleep & stress control: Poor sleep and stress hormones make weight loss harder
• Hydration: Water before meals can reduce overeating
• Consistency: Small, steady changes are more sustainable than quick fixes
Connect with us for updates and more:
Telegram | Facebook | LinkedIn | TikTok | Website |Youtube