Mereb events

Mereb events Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mereb events, Addis Ababa.

 #የ፳፻፲፪ የልሳነ ግእዝ በልጆች የሁለተኛ ምዕራፍ መርሐ ግብር የመጀመሪያ ፈተና፡፡ ስም ______________________________________ትእዛዝ ፩፡ ከታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎ...
28/12/2019

#የ፳፻፲፪ የልሳነ ግእዝ በልጆች የሁለተኛ ምዕራፍ መርሐ ግብር የመጀመሪያ ፈተና፡፡
ስም ______________________________________

ትእዛዝ ፩፡ ከታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በሚገባ በማንበብ ትክክል የሆነውን ‹እውነት›፤ ስህተት የሆነውን ‹ሐሰት› በማለት መልሱ፡፡

ዓቢያን አናቅጽ ንባባቸው ሁል ጊዜ ተነሽና ወዳቂ ነው፡፡ ______
የግሥ መነሻ ፊደላት አምስት ናቸው፡፡ ________________
ከፈለ የሚለው ግሥ ንባቡ ተጣይ ነው፡፡ __________________
የግሦች ሁሉ መድረሻ ፊደል ግእዝ ነው፡፡ _________________

ትዕዛዝ ፪፡ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል አክብቡት፡፡
ሠረቀ የሚለው ግሥ ሲረባ ሁለተኛው አንቀት _________ ነው፡፡
ሀ. ይሥርቅ ለ. ይሠርቅ ሐ. ሠረቀ

ገነየ የሚለው ግሥ ሁለተኛ አንቀጽ የቱ ነው?
ሀ. ይገንይ ለ. ይግነይ ሐ. ይገኒ መ. ሁሉም መልስ ነው

ዘረወ ሲረባ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ዘረወ፣ ይዘርው፣ ይዝርው፣ ይዝርው
ለ. ዘረወ፣ ይዘሪ፣ ይዝሪ፣ ይዝሪ
ሐ. ዘረወ፣ ይዘሩ፣ ይዝሩ፣ ይዝሩ
መ. መልስ የለም

ትእዛዝ ፫፡ በ ‹ሀ› ሥር ያሉትን አናቅጽ በ ‹ለ› ካሉት ትርጉሞች ጋር አዛምዱ፡፡
ይሠርቅ ____________ ሀ/ ይወጣል
ሠረቀ ______________ ለ/ ይውጣ
ይሥርቅ ____________ ሐ/ ወጣ

ታኅሣሥ 16 በ2012 ዓ.ም ጠዋት በዐዲስ አበባ የታየው  #ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ እንደኛ ዕይታ ይሄን ይመስል ነበር፡፡
27/12/2019

ታኅሣሥ 16 በ2012 ዓ.ም ጠዋት በዐዲስ አበባ የታየው #ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ እንደኛ ዕይታ ይሄን ይመስል ነበር፡፡

21/12/2019

ሊቃውንት አባቶቻችንን ያፈራውን የአብነት ትምህርቶችን ልጆቻችንን ማስተማር ታላቅ ወዳደረገን ማንነታችን መመለስ ነው፡፡

Our   has launched the first satellite into space, as more sub-Saharan African nations strive to develop space programme...
20/12/2019

Our has launched the first satellite into space, as more sub-Saharan African nations strive to develop space programmes to advance their development goals and encourage scientific innovation.

17/12/2019

#የዓብይ ጾም ቀለም

በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት፡፡ አዘጋጅ ዶ/ር ውቤ ካሣዬ፡፡ አቅራቢዎች የታእካ ነገሥት በአታ ለማርያም ሊቃውንት፡፡ በ2011 ዓ.ም የቀረበ

 #መረብ ልዩ ልዩ ዝግጅት አስተናባሪ ኢትዮጵያዊ ዕውቀቶች ላይ መሠረት አድርጎ የሚሠራ ድርጅት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ዕውቀቶች በተለይ ደግሞ በድህነት ለሚኖር ማኅበረሰብ ለእድገት በሚያደርገው ጉ...
16/12/2019

#መረብ ልዩ ልዩ ዝግጅት አስተናባሪ ኢትዮጵያዊ ዕውቀቶች ላይ መሠረት አድርጎ የሚሠራ ድርጅት ነው፡፡

ኢትዮጵያዊ ዕውቀቶች በተለይ ደግሞ በድህነት ለሚኖር ማኅበረሰብ ለእድገት በሚያደርገው ጉዞ ወሳኙን ሚና ይጫወታሉ፡፡ የማንኛውም ሀገር የለውጥ መንገድ በሀገራዊ ዕውቀቶች ላይ የተነጠፈ ሲሆን የለውጥ ጉዞው በማኅበረሰቡ ዘንድ ተአማኒና ፈጣን ይሆናል፡፡ መረብ ልዩ ዝግጅት አስተናባሪ ሀገራዊ ዕውቀቶች ለማኅበረሰቡ ያላቸውን ጉልህ ሚና ተረድቶ እነዚህን እውቀቶች ለለውጥ ለሥልጣኔና ለእድገት በሚደረጉ ጉዞዎች ውስጥ በማካተት ለማኅበረሰቡ ቅርብ የሆኑ ሥልጣኔዎችን እንዴት ማምጣት ይቻላል የሚለውን ክፍተት የሚሞሉና ጠቋሚ የሆኑ ሥራዎችን ይሠራል፡፡

መረብ ልዩ ዝግጅት አስተናባሪ ሀገራዊ ዕውቀቶችን ወደ ግንባር እያመጣ በሚቀረጹት የመንግሥት ሕጎች፣ በማኅበረሰቡ የዕለት ተዕለት የኑሮ ሒደቶች ውስት፣ ለእድገት ለለውጣና ለታላቅነት በሚደረጉ ጉዞዎች ውስጥ ለማካተትና አገልግሎታቸውን ለማጉላት የተለያዩ መንገዶችን የሚጠቀም ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንዱ ሥልጠና መስጠት ነው::

 #ሀገሬ(ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)ሀገሬ ውበት ነውለምለምና ነፋስ የሚጫወትበትፀሐይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት፡፡ሀገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋእዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ፡፡ሀገ...
15/12/2019

#ሀገሬ

(ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)

ሀገሬ ውበት ነው
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት
ፀሐይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት፡፡
ሀገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ፡፡
ሀገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ
ሀገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፡፡
ውሸት ነው በበጋ ፀሐይ አትፋጅም
ክረምቱም አይበርድም
አይበርድም፣ አይበርድም፡፡

ሀገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት፡፡

እዚያ አለ ነጻነት
በሀገር መመካት
በተወላጅነት
በባለቤትነት
እዚያ አለ ነፃነት፡፡

ሀገሬ ሀብት ነው
ጐመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ሥጋ
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፡፡
ጠጁ ነው ወለላ
ከኮኛሽ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ፡፡
እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል
በዓሉ ይደምቃል
ሙዚቃው ያረካል
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል፡፡

እዚያ ዘመድ አለ…
ሁሉም የእናት ልጅ ነው
ሁሉም የአባት ልጅ ነው፡፡
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር
ባለጋራም ቸር ነው ‹የሀገር ልጅ› ሲቸገር፡፡

ገነት ነው ሀገሬ፡፡

ምነው ምን ሲደረግ!
ምነው! ለምን! እንዴት!
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ
ጥርኝ አፈር በእጁ ስንዝር ወሰን አልፎ
የተቀደሰውን የአፍሪቃ ላይ ደሴት
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት፡፡

እምቢኝ አሻፈረኝ!
አሻፈረኝ እንቢ!

መቅደስ ነው ሀገር
አድባር ነው ሀገሬ፤
እናትና አባቴ ድኸው ያደጉበት
ከአያት ከቅድም አያት የተረካከብኩት
አፈር የፈጩበት
ጥርስ የነቀሉበት፡፡

ሀገሬ ዓርማ ነው የነፃናት ወናጫ
በቀይ የተጌጠ በአርንጓዴ ብጫ፡፡
እሾህ ነው ሀገሬ
በጀግና ልጅ አጥንት የተከሰከሰ
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ፡፡
ሀገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት
ዘፈን የፈተነው በጠበል በጸሎት፡፡

ለምለም ነው ሀገሬ
ውበት ነው ሀገሬ
ገነት ነው ሀገሬ፡፡

ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ
እዛ ነው አፈሩ የማማ ያባባ፡፡
ስሳብ እሄዳለሁ ቢሰበርም እግሬ
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ ሀገሬ፡፡
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውለድ ሀገሬ ካሳደገኝ ጓሮ፡፡

  Decides to Inscribe   on the List of Cultural HeritageDecember 12/2019 The United Nations Educational, Scientific and ...
13/12/2019

Decides to Inscribe on the List of Cultural Heritage

December 12/2019 The United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO) decided to inscribe TIMKET, which is Ethiopian Epiphany, on the List of Representatives of the Intangible Cultural Heritage of Humanity.

UNESCO’s intergovernmental committee for the safeguarding of intangible cultural heritages made the decision in its meeting in Bogota, the capital of Colmbia.

According to UNESCO, inscription of Timiket festivity on the Representative List could enhance the visibility of intangible cultural heritage and promote inter-cultural dialogue among the multi-ethnic population of Ethiopia and other communities globally.

The festival of Timiket or Epiphany is celebrated across Ethiopia on January 19th or 20th in leap year, corresponding to the 10th day of Tirr in the Ethiopian calendar.

Timkat celebrates to commemorate the baptism of Jesus in the Jordan River. This festival is best known for its ritual reenactment of baptism.

The inscription of Timiket raised the number of Ethiopia’s world intangible cultural heritages to four after Meskel, the Geda System and Fichee-chambalaalla, New Year festival of the Sidama people.

[አይቼው የማላቀው የድንጋይ መጽሐፍ]✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ♥ ባለፈው እንዳስነበብኳችሁ በሰሜን አሜሪካ ኮንግረስ ቤተ መጻሕፍት በቶማስ ጄፈርሰን ሕንጻ ውስጥ ወደ 250 የሚጠጉ የ...
10/12/2019

[አይቼው የማላቀው የድንጋይ መጽሐፍ]
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥ ባለፈው እንዳስነበብኳችሁ በሰሜን አሜሪካ ኮንግረስ ቤተ መጻሕፍት በቶማስ ጄፈርሰን ሕንጻ ውስጥ ወደ 250 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍትን ተፈቅዶልኝ ካየሁ በኋላ የቀረጽኳቸውን መላልሼ በማየት በመደነቅ ጊዜዬን ማሳለፍ ጀመርኩ።

♥ ከልጅነት ጀምሮ በብራና መጻሕፍት ውስጥ ማደጌ ይመስለኛል ብራና መጻሕፍት ያሉበትን ክፍል በማሽተት ጭምር ሳለየው አልቀርም። እነዚህን የቀደምት ኢትዮጵያውያኑን መጻሕፍት ስለምወዳቸው ይመስለኛል መዋደድ የጋራ ነውና በምሄድበት ሀገራት ሁሉ በፍቅር ይጠብቁኛል።

♥ ኮንግረስ ላይብረሪ ባየሁት 250 መጻሕፍት ስደነቅ 800 የብራና መጻሕፍት ያሉበት ታላቅ ዪኒቨርሲቲ እንዳለ ይልቁኑ የድንጋይ የግእዝ መጽሐፍ እንዳለ መምህር ነጸረ አብ ቁጭ ብለን ስናወጋ በጆሮዬ ሹክ አለኝ። በመገረም በመደመም ውስጥ ሆኜ ለጥቂት ደቂቃዎች ጸጥ ካልኩ በኋላ ቦታውን ስጠይቀው በካቶሊክ ዪኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ እንደሆነ በቦታው 15 ዓመታት የሠራው መምህር ነጸረ ነገረኝ።

♥ ካቶሊክ ዪኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ የተመሠረተው በ1887 ዓ.ም ሲሆን ታላቅ ጥናትና የምርምር ሥራ የሚደረግበት ዪኒቨርሲቲ ነው። በስሩ ባሉት 12 ትምህርት ቤቶች ውስጥ በፒ ኤች ዲ ዶክትሬት (Doctor of Philosophy) 66 በማስተርስ ዲግሪ 103፤ በቅድመ ምረቃ 72 ፕሮግራሞችን በመስጠት ተመራማሪዎችን ለፕላኔቷ ያቀርባል።
የእኛው ቋንቋ ግእዝም እስከ ፒ ኤች ዲ የዶክትሬት ዲግሪ ከሚሰጥባቸው ታላላቅ ዓለም ዐቀፍ ዪኒቨርሲቲ ውስጥ አንደኛው ይህ ነው።

♥ በቅድመ ምረቃ 3332 በድኅረ ምረቃ 2624 በአጠቃላይ ወደ 5956 የዛሬ ተማሪዎች የነገ ተመራማሪዎች አሉት። ከUS Capitol በ3 ማይል ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ የምርምር ዪኒቨርሲቲ ሰፊና በ176 ሔክታር ላይ ያረፈ ለዐይን ማራኪ ነው። በዪኒቨርሲቲው ያለው የጆን ኬ ሙሌን መታሰቢያ ቤተ መጻሕፍት ከ1.3 ሚሊየን በላይ መጻሕፍት፤ በ10ሺዎች የሚጠጉ ኤሌክትሮኒክ ጆርናሎች ይገኙበታል።

♥ ይህን ታላቅ የምርምር ተቋምን ማየት እንድችል ይልቁኑ የምወዳቸው የኢትዮጵያን ጥንታውያት መጻሕፍት እንድመለከት ስለተፈቀደልኝ ኅዳር 28 እሑድ ወደ ዪኒቨርሲቲው ከመምህር ነጸረ ከካሜራ ማኖቼ ከኤርሚና ከደመኢየሱስ ጋር ሄድን።

♥ ወደ ውስጥ ዘልቀን ከገባን በኋላ የኢትዮጵያ ጥንታውያት የብራና ስብስብ ወዳለበት የምድር ቤቱ ክፍል ወረድን። ወደ ክፍሉ ስንቃረብ ዕውቀትን ያመቁ የብራና መጻሕፍት ሽታ ተሰማኝ፤ ገብቼ እስከምመለከታቸው ድረስ አላስቻለኝም፤ የክፍሉን መጥሪያ ስንነካው ከውስጥ የሲሪያክ፣ የአርመን፣ የጆርጂያ ቋንቋዎች ፕሮፌሰር የሆነችው የክፍሉ ሐላፊ ዶክተር ሞኒካ ብላንቻርድ በሩን ከፍታ በፈገግታ ተቀበለችን።

♥ ረጅሙን የሕይወት ዘመኗን በጥናት በምርምር እንዳሳለፈች ያስታውቃል፤ ወዲያውኑ ጊዜ አልወሰደችም በብራና መጻሕፍት ወደተሞላው በጥንቃቄ በንጽሕና በተቀመጡበት ክፍል ውስጥ አስገብታን ዕርፍ።

♥ የፈለጋችሁትን አውጥታችሁ እዩ ወደ 400 የሚጠጉ ታላላቅ የብራና መጻሕፍትና 400 ጥቅሎች አሉላችሁ አለችን እኔም እየመረጥኩ መመልከት ጀመርኩ። ብራናዎችን ሳነባቸው የኖሩኳቸው ወዳጆቼ በመሆናቸው ከእነርሱ ጋር ለተወሰነ ሰዓት የተመስጦ ቆይታ አድርጌ ወደ 400 ጥቅሎች አመራሁ ግን ስንቱ ተነቦ ያልቃል? ብቻ የምፈልጋቸውን ከተመለከትኩ በኋላ በድንጋይ ላይ የተቀረጹ የጥንታውያን ቋንቋዎች ጽሑፎችን አየሁ።

♥ የድንጋይ ላይ ጽሑፎችን ማን ይተረጉማቸዋል? እያልኩ ስቆዝም ዶክተር ሞኒካ ሳይገባት አልቀረም ፊደላት የተቀረጸበት በእጇ ቡናማ ወረቀት ይዛ ጠጋ ብላ አዲሱን ግኝት አስተዋወቀችኝ፤ ይኸውም በቀላሉ የድንጋይ ላይ ጽሑፍን ወደ ወረቀት ላይ ለውጦ በጉልሕ ያስነብባል፤ ለትርጓሜው ችግር የለም ቀንና ሌሊት ያለዕረፍት የሚመራመሩ የቋንቋዎች ሊቃውንት ይተረጉሙታል።

♥ ይህን በተመስጦ ስመለከት በኅሊናዬ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችን ጠራርጎ አሽቀንጥሮ ጥሎ ዓለም አሁን የደረሰበት ዕውቀት ሳይደርስበት የመደባደቢያ አውድማ የሆኑትን የሀገራችን የትምህርት ተቋማት ሳስብ ሐዘን ተሰማኝ።

♥ ነገር ግን ነገ ኢትዮጵያን የሚረከቧት ዛሬ ትውልዱ የዘነጋቸው ሕፃናት ትውልዱ በዝንጋኤ የጣለውን የኢትዮጵያን አልማዛዊ ዕውቀት በክብር አንሥተው ዓለም ከደረሰበት የሳይንስ ምርምር ጋር አስተባብረው ኢትዮጵያን በከፍታ ሰገነቷ ላይ እንደሚያስቀምጧት ስለማምን ሐዘኑ ከልቤ ብን ብሎ ወጣ።

♥ በመጨረሻም ዶክተር ሞኒካ ላየው የምፈልገውን የድንጋይ ላይ ተከፋች የግእዝ ጽሑፍን ያለበትን ይዛ መጣች፤ በሕይወቴ እንደዚህ ዓይነት አይቼ ስለማላውቅ በአድናቆት ተመላሁ።በድንጋይ ላይ ጽሑፍንና ሥዕልን መቅረጽ የሚችሉ ጥበቦች ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ አይቼ የበለጠ አከበርኳቸው። ጣቶቼም እነዚያን ጽሑፎች ዳሰሱ።

♥ ምስለ ፍቁር ወልዳና ሥዕለ ሥሉስ ቅዱስ ከታተመበት ከዚ የድንጋይ ጽሑፍን ስገልጥ ረዘም ያለ የዘንባባ ሥዕል ዳርና ዳር ያለው የአንዲት የንግሥት ሴት ከፊል ገጽ ና የአንድ ወንድ ተቀርጾ ይታያል።

♥ የሴቲቱ አቀራረጽና ሹሩባን ስመለከተው በጥንት የኢትዮጵያ ኑብያና ግብጽ ሥልጣኔ የምናያቸው ንግሥታትን ይመስላልና፤ የኢትዮጵያ ልዕልት አንድሮሜዳ ትሆን? ብዬ አሰብ አረኩና ረጃጅሞች የዛፍ ቅርጾች ግን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በመመርመር የጥንታውያን የኢትዮጵያን ከፍተኛ ሥልጣኔ ታሪክ የሚያውቁት ሐኪም አበበች ሽፈራውን እጠይቃቸዋለሁ በማለት ገጥሜ በነበረበት የክብር ስፍራ አስቀመጥኩት።

♥ ለ15 ዓመታት በዚህ ቤተ መጻሕፍት የሠሩት መምህር ነጸረ አብ በመጨረሻ ሲነግሩኝ ያሳዘነኝ ነገር እነዚህን መጻሕፍት ለመመርመር እጅግ ብዙዎች ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች ወደ ቤተ መጻሕፍቱ ዘወትር ሲመጡ በ16 ዓመት ውስጥ መጥቶ ያየው አንድ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው ሲለኝ መስማቴ ነው፤ አባቶች ሁሉን ሠርተው ፍሪጅ ውስጥ አስቀምጠው ቢሄዱም ከስንፍና ብዛት አውጥቶ አሙቆ መብላት ያቃተን ያህል እየተሰማኝ በቀዝቃዛው የማታው አየር ሰፊውን የዩኒቨርስቲውን ቅጽር ለቅቄ ስወጣ ልቤ ግን በውስጥ ካሉት ከ800 መጻሕፍት ጋር ነበር።

[ኅዳር 28/ 2012 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የካቶሊክ ዪኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ ቆይታዬ]
https://t.me/joinchat/AAAAAFTyR7tztt08pN9U-w
✍ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

07/12/2019
23/11/2019
 #ናታኒም አቤል  #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ    #ልሳነ ግእዝ  # ግእዝ ንባብ  #ያሬዳዊ ዜማ  #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል
23/11/2019

#ናታኒም አቤል #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ #ልሳነ ግእዝ # ግእዝ ንባብ #ያሬዳዊ ዜማ #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል

 #ኖላዊ አቤል  #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ    #ልሳነ ግእዝ  # ግእዝ ንባብ  #ያሬዳዊ ዜማ  #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል
23/11/2019

#ኖላዊ አቤል #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ #ልሳነ ግእዝ # ግእዝ ንባብ #ያሬዳዊ ዜማ #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል

 #ዳግም ጌታው  #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ    #ልሳነ ግእዝ  # ግእዝ ንባብ  #ያሬዳዊ ዜማ  #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል
23/11/2019

#ዳግም ጌታው #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ #ልሳነ ግእዝ # ግእዝ ንባብ #ያሬዳዊ ዜማ #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል

 #ቸርነት እና ምሕረት ሚሊዮን  #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ    #ልሳነ ግእዝ  # ግእዝ ንባብ  #ያሬዳዊ ዜማ  #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል
23/11/2019

#ቸርነት እና ምሕረት ሚሊዮን #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ #ልሳነ ግእዝ # ግእዝ ንባብ #ያሬዳዊ ዜማ #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል

 #ናታን ሮቤል  #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ    #ልሳነ ግእዝ  # ግእዝ ንባብ  #ያሬዳዊ ዜማ  #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል
23/11/2019

#ናታን ሮቤል #ክረምትን ለልጆች 2011 ዓ.ም ተማሪ #ልሳነ ግእዝ # ግእዝ ንባብ #ያሬዳዊ ዜማ #ኢትዮጵያዊ ሥነ-ሥዕል

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mereb events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram