Ethio-Telehealth

Ethio-Telehealth የቴሌሄልዝ አገልግሎት (ባሉበት የጤና ማማከርና ህክምና) በዶ/ር ጋሻው ሶለላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት) https://t.me/Ethiotelehealth

ድባቴ ለልብ ድካም 14 በመቶ የበለጠ አጋላጭ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተመቅድም• ድባቴ ወይም ድብርት (depression) 4.4 ከመቶ አካባቢ የዓለም ህዝብ ላይ የሚታይ ሲሆን የአካላዊ ...
15/06/2025

ድባቴ ለልብ ድካም 14 በመቶ የበለጠ አጋላጭ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ

መቅድም

• ድባቴ ወይም ድብርት (depression) 4.4 ከመቶ አካባቢ የዓለም ህዝብ ላይ የሚታይ ሲሆን የአካላዊ ውስንነት ከሚያመጡ ህመሞች ግንባር ቀደም እንደሆነ ይታወቃል።

• የልብ ድካም (heart failure) ካለባቸው ሰዎቸ ውስጥ ቢያንሱ አንድ ሰው ላይ ድባቴ ይታያል። ይህም ሆስፒታል ተኝቶ የመታከም እና የመሞት እድልን ከፍ ያደርጋል።

• ይሁን እንጅ ድባቴ ለልብ ድካም ያለው አጋላጭነት በደንብ ሳይጠና ቆይቷል።

የጥናቱ ተሳታፊዎች

• ጥናቱ ላይ የተካተቱት ሰዎች 2.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዜጎች ሲሆኑ አማካይ እድሜያቸው 54 ዓመት ነበር። አብዛኞቹ ነጮች እና አንድ አራተኛ አካባቢ (24 በመቶ) የሚሆኑት ደግሞ ጥቁሮች እንደነበሩ ተመላክቷል። እንዲሁም 94 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወንዶች ነበሩ።

የጥናቱ ዋና ዋና ውጤቶች

• ድባቴ ያለባቸው ሰዎቸ ለልብ ድካም የመጋለጥ እድላቸው ድባቴ ከሌላቸው አንፃር 14 በመቶ እንደሚበልጥ ታይቷል።

• እንዲሁም ድባቴ ካለባቸው ሰዎቸ ውስጥ ወንዶች ለልብ ድካም የመጋለጥ እድላቸው ከሴቶች እንፃር 30 በመቶ በልጦ ታይቷል።

የጥናቱ ምንጭ: https://jamanetwork.com/journals/jamanetworkopen/fullarticle/2833714

🦠የዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤም ፖክስ) [ ]የበሽታው ምንነት📌 ኤም ፖክስ በሽታ በዝንጀሮ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከተያዙ እንስ...
14/06/2025

🦠የዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤም ፖክስ) [ ]

የበሽታው ምንነት

📌 ኤም ፖክስ በሽታ በዝንጀሮ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከተያዙ እንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፍ እና በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡

የበሽታው ምልክቶች

• ሽፍታ
• ሳል
• ትኩሳት
• የራስ ምታት
• የእጢ እብጠት
• የቆዳ ቁስለትና ድካም
• የጡንቻና የጀርባ ህመም

መከላከያ መንገዶች

😷 የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን በመጠቀም

🚫🤝 የኤም ፖክስ መሰል ሽፍታ የሚታይባቸው ሰዎች ጋር ባለመነካካት

🧽 ታማሚዎቹ የተጠቀሙባቸውን ቁሳቁሶች በአግባቡ ሳያጸዱ ባለመጠቀም

🙌 የግል እና የእጅ ንፅህና በመጠበቅ

🏥 በሽታው በቀጥታ ከሰው ወደ ሰው በንክኪ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛዉም ሰዉ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

📢 Mpox (Monkeypox) Awareness 🦠🔷 What is Mpox?A contagious viral disease from the Orthopoxvirus family (like smallpox). M...
14/06/2025

📢 Mpox (Monkeypox) Awareness 🦠

🔷 What is Mpox?

A contagious viral disease from the Orthopoxvirus family (like smallpox). Most recover, but some may get seriously ill.

🔷 Signs & Symptoms:

🤒 Fever
😖 Headache
🔴 Rashes
🦠 Swollen lymph nodes
💪 Muscle aches
😣 Back pain

🔷 How is it Transmitted?

🤝 Close contact with infected persons (skin-to-skin, face-to-face)
🧴 Contaminated items (clothes, needles, bedding)
🐒 Animal bites, scratches, or handling infected animals

🔷 Prevention:

🚫 Avoid close contact with infected persons
🧼 Wash hands frequently
😷 Wear a mask
🙅‍♂️ Don't touch rashes
🚫 No sharing of personal items
🐾 Avoid wild animals (rodents, monkeys)
✅ Maintain good hygiene
🩺 Seek medical advice if exposed

🔷 Treatment:

🏥 Isolate the patient
🧤 Use PPE
💧 Stay hydrated
🧽 Clean lesions
👀 Monitor for complications
💊 Supportive care

📌 Stay Safe! Spread Awareness, Not the Virus. ✅

ነስር (Epistaxis) ምንድነው?Epistaxis (ነስር) የምንለው ከአፍንጫ ደም በሚፈስበት ጊዜ ነዉ። ነስር የተለመደ የጤና ችግር ሲሆን በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ ሊከሰት ይችላል። ...
10/06/2025

ነስር (Epistaxis) ምንድነው?

Epistaxis (ነስር) የምንለው ከአፍንጫ ደም በሚፈስበት ጊዜ ነዉ። ነስር የተለመደ የጤና ችግር ሲሆን በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ ሊከሰት ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ የሚነሳው በቀላል ችግር ቢሆንም ፣ አንዳንድ ጊዜ ከባድ በሽታ ልያመለክት ይችላል።

ምን ምክንያቶች አሉት?

Epistaxis (ነስር) ብዙ ምክንያቶች አሉት። ከእነዚህ መካከል የተለመዱት የደረቀ አየር መተንፈስ፣ በጣቶች አፍንጫ መጎርጎር ፣ አለርጂ እና ጉንፋን ናቸው ። ከነዚህ በተጨማሪ የደም ግፊት እና የደም ማቅጠኛ መድሃኒቶችን መውሰድ ይጠቀሳሉ።

የመጀመሪያ እርዳታ

ነስር ሲከሰት በቀጥታ መቀመጥና በትንሹ ወደ ፊት ዝቅ በማለት አፍንጫን መሃል አንጓ ላይ ይዞ መጫን ያስፈልጋል። ይህን ለ10-15 ደቂቃ ይቀጥል ። ራስን ወደ ኋላ ማረግ ኣያስፈልግም ፣ ይህ ደም ወደ ሆድ እንዲወርድ እና ትውከትን በመፍጠር እንዲባባስ ያደርጋል።

ነስርን ለመከላከል እርጥበት ቦታ ላይ መሆን ይመረጣል። የእርጥበት መሳሪያ (humidifier) በቤት ውስጥ በመጠቀም መቆጣጠር ይቻላል ። ከሚያስነሱብን ተግባሮች ራስን ማራቅም ሌላኛው መከላከያ መንገድ ነው።

ወደ ህክምና ተቋም መቼ በሄድ አለብኝ ?

ደም ከ20 ደቂቃ በላይ ከፈሰሰ፣ ብዛቱ ከጨመረ፣ ወይም በተደጋጋሚ ከመጣ ሐኪም ማማከር ይኖርብዎታል። በተጨማሪም ጭንቅላት ላይ ጉዳት ካጋጠሞት እና በኣፍንጫዎት ደም መፍሰስ ከመጣ አስቸኳይ የህኪም እርዳታ ይፈልጋል።

What Is a  ?A pacemaker is a small, implantable electronic device that helps regulate the heartbeat.The heart’s rhythm i...
06/06/2025

What Is a ?

A pacemaker is a small, implantable electronic device that helps regulate the heartbeat.

The heart’s rhythm is controlled by a natural pacemaker called the sinus node, which sends electrical signals to the lower chambers of the heart through a pathway called the cardiac conduction system. Damage to this system can result in slow or unreliable heartbeats, which can occur gradually with age or be caused by medical conditions such as infection, inflammatory diseases, or blockages in the arteries of the heart.

Who Needs a Pacemaker?

Pacemakers are commonly used for people who have a heart rate that is too slow (bradycardia) or who have disorders that interfere with the heart’s normal electrical pathways.1 A pacemaker prevents slow heart rates that may cause shortness of breath, fatigue, lightheadedness, or even sudden death. In some patients, damage to the heart’s conduction system causes no symptoms at first but can lead to dangerous events like fainting or even sudden death.

For patients with or at risk of heart failure, a specialized pacemaker may be used to help coordinate the heart’s contractions. This can involve placing an extra lead to pace both sides of the heart or positioning a lead deeper in the heart’s conduction system to help prevent or reverse weakening of the heart muscle.

What Does a Pacemaker Do?

A pacemaker monitors the heart’s electrical signals and sends small, painless electrical impulses to make the heart contract when needed, maintaining a steady, reliable rhythm. A conventional pacemaker consists of a battery connected to leads (wires) that attach to the heart, allowing the device to both monitor and pace the heart.

How Are Pacemakers Implanted?

Implanting a conventional pacemaker involves a minor surgery, usually done under sedation. A small incision is made under the collarbone to place the battery under the skin. Leads are then threaded through a nearby vein into the heart under x-ray guidance and connected to the battery.

Recently, “leadless” pacemakers—small, capsule-sized devices—have been developed that are inserted into the heart after being passed through a vein in the groin. These pacemakers are a good option for people with blockages in their upper body veins or in those at higher risk of infection. However, compared with standard pacemakers, leadless pacemakers have more limited programming options, and when the battery runs low, leadless pacemakers need to be replaced or a second pacemaker needs to be placed.

Living With a Pacemaker

Most people with a pacemaker can live healthy, active lives after a few weeks of limited activity to prevent lead dislodgement after implantation. Individuals with modern pacemakers can undergo magnetic resonance imaging (MRI) but should avoid deepwater diving or arc welding. Regular checkups in a pacemaker clinic can ensure a pacemaker is working well. The pacemaker battery is typically replaced every 8 to 12 years with a minor surgical procedure in which the pacemaker generator containing the battery is replaced with a new device.

🔴  #በትንፋሽ ለሚወሰዱ  #የአስም መድሃኒቶች የአጠቃቀም መመሪያ  (Steps for Appropriate Use of Inhalers)1️⃣ ክዳኑን መክፈት 2️⃣ የመድሃኒት እቃውን በደንብ መነቅ...
06/05/2025

🔴 #በትንፋሽ ለሚወሰዱ #የአስም መድሃኒቶች የአጠቃቀም መመሪያ (Steps for Appropriate Use of Inhalers)

1️⃣ ክዳኑን መክፈት

2️⃣ የመድሃኒት እቃውን በደንብ መነቅነቅ

3️⃣ አየር ወደ ውጭ ማስወጣት

4️⃣ ዕቃውን ወደ አፍ በማስገባት ዙሪያውን በከንፈር ግጥም አድርጎ መዝጋት

5️⃣ በቀስታ ወደ ውስጥ መተንፈስ መጀመር ከዛም የመድሀኒት መስጫውን አንዴ በደንብ መጫን እና በዝግታ ወደ ውስጥ መተንፈስ (ልብ ይበሉ መዋጥ ሳይሆን መተንፈስ ነው።)

6️⃣ ዕቃውን ከአፍ ማስወጣት እና ለ 10 ሰኮንድ ያህል አፍን ግጥም በማድረግ ትንፋሽን ያዝ አድርጎ መቆየት

ተጨማሪ ካስፈለገ ከ 1 ደቂቃ በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ መድገም።

ማስታወሻ፡ ልብ ይበሉ በአንድ ትንፋሽ ከአንድ ጊዜ በላይ መድሀኒት መስጫውን መጫን አይመከረም።

አስም ለመቆጣጠር የሚረዳ መድሃኒት ከሳቡ በኋላ አፍን በውሀ መጉመጥመጥ ይመከራል።

🔴   (Asthma)  • የታችኛው የአየር ቧንቧ በሚቆጣበት እና በሚጠብበት ወቅት የሚከሰት የሳንባ በሽታ ነው።• በሽታው ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርሱ ምልክቶችን ሲያሳይ የመሻልና የመበባስ ...
06/05/2025

🔴 (Asthma)



• የታችኛው የአየር ቧንቧ በሚቆጣበት እና በሚጠብበት ወቅት የሚከሰት የሳንባ በሽታ ነው።
• በሽታው ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርሱ ምልክቶችን ሲያሳይ የመሻልና የመበባስ ባህሪ አለው።



√ ሲር ሲር የሚል የትንፋሽ ድምፅ
√ ሳል
√ ደረትን ጭብጥ አድርጎ መያዝ
√ ትንፋሽ ማጠር
• አስም በሚነሳ ወቅት እስከ ሞት የሚያደርስ ትንፋሽ ማጠር ሊያመጣ ይችላል።



• የሳንባ ስራ መፈተኛ ምርመራ (Spirometry) - በሽታውን ለማወቅ ሊያስፈልግ ይችላል።
• የአለርጅ ምርመራ - በኛ ሀገር ባይኖርም አስሙን የሚቀሰቅሱት አለርጅዎች ካሉ እነሱን ለመለየት ይረዳል።



• በሚሳቡ እና በሚዋጡ መድሃኒቶች የሚታከም ሲሆን የሚዋጡት በተለይ ፕሪዲኒሶሎን ለብዙ ጊዜ እንዲወሰዱ አይመከርም።
• ሁለት ዓይነት የሚሳቡ መድሃኒቶች አሉ።
√ ቶሎ የሚያሽሉ - ከ 5 እስከ 15 ደቂቃ ውስጥ ለውጥ ያሳያሉ። ለምሳሌ ሳልቡታሞል ይጠቀሳል።
√ ለረጅም ጊዜ አስሙን የሚቆጣጠሩ - አስሙ ቶሎ ቶሎ እንይባባስ ያደርጋሉ። ለምሳሌ ቤክሎሜታሶን ይጠቀሳል።
√ አንዳንድ መድሃኒቶች ደግሞ ሁለቱንም ስራ የሚሰሩ አሉ። ለምሳሌ ሲምቢኮርት ይጠቀሳል።

?

√ አስም ቀስቃሾችን ማስወገድ፦ ለምሳሌ የአየር ብክለት፣ አቧራ፣ የአበባ ብናኝ፣ የኬሚካል ሽታ እና የአየር በጣም መሞቅ ወይም መቀዝቀዝ ይጠቀሳሉ።
• የመታመም እድልን መቀነስ፦ አንዳንድ ኢንፌክሽኖች የአስምን ምልክቶችን ያባብሳሉ። ለምሳሌ ጉንፋን እና ኮቪድ 19 ይጠቀሳሉ። ስለዚህ የኮቪድ 19 ክትባት መውሰድ ያስፈልጋል።
• የአስም ታማሚዎች ጥብቅ የሆነ ክትትል ማድረግ ይገባቸዋል።

🔴     የጨጓራ በሽታ ማለት በተለያዩ ምክንያቶች አሲድ ከተፈለገው በላይ በማመንጨት በጨጓራ የላይኛው ንጣፍ ላይ የሚከሰት ቁስለት ወይም ቁስለት መሰል ነገሮች የሚያመጡት ስሜት መሆኑን የሕክ...
27/04/2025

🔴

የጨጓራ በሽታ ማለት በተለያዩ ምክንያቶች አሲድ ከተፈለገው በላይ በማመንጨት በጨጓራ የላይኛው ንጣፍ ላይ የሚከሰት ቁስለት ወይም ቁስለት መሰል ነገሮች የሚያመጡት ስሜት መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የጨጓራ በሽታ ምንነት

የጨጓራ ሕመም ከአሲድ መመንጨት ጋር በተገናኘ የሚከሰትና ከምግብ ሥርዓት ጋር ግንኙነት ያለው ነው። በተለምዶ ሕመሙ ከመጀመሪያው የምግብ መውረጃ ቱቦ ጀምሮ ሙሉ የጨጓራ መውረጃ ቱቦዎችን በማጠቃለል የጨጓራ በሽታ ተብሎ በአንድ ላይ ይጠራል። ነገር ግን ራሳቸውን የቻሉ የተለያዩ በሽታዎች ናቸው።

የጨጓራ በሽታ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አሲድ ከአቅም በላይ ሲመነጭ፣ አልሰር ሲፈጠር ወይም ሌላ ምክንያት ኖሮ ለዚህ ተጋላጭ የሚያደርጉ ምክንያቶች ሲኖሩ አንድ ሰው ስሜት ይኖረዋል። ይህ ስሜትም በተለያየ መንገድ ሊገለጽ ይችላል። ጤናማ ወይም የተለመደ አይነት አገላለጽ አንደኛው ነው።
ከጨጓራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሰውነት ክፍሎች የሚያሳዩአቸው ምልክቶች በአሲድ መብዛት ወይም ደግሞ ቁስለት በመፈጠሩ ምክንያት የሚታዩ ምልክቶችም አሉ። ማቃር፣ ማቃጠል፣ ምግብ አለመፈጨት፣ አንዳንዴ ማስታወክ፣ የአይነምድር መጥቆር ወይም ሬንጅ መምሰል ነገሮች ይከሰታሉ። ይህ ክስተት ከጨጓራ፣ ከምግብ መውረጃ ቧንቧ እና በአንጀት የመጀመሪያ ክፍል ከአሲድ ጋር በተገናኘ የተፈጠረ ነው።

የጨጓራ ሕመም የሚባሉት ከላይ የተዘረዘሩት ናቸው። ነገር ግን የበሽታው መገለጫ አንድ አይነት ቢሆንም፤ ችግሩን የሚያመጡት መሰረታዊ ምክንያቶች ከሰው ሰው ይለያያል። ለምሳሌ አንድ ሰው የጨጓራ ባክቴሪያ ኖሮት በዛ ምክንያት የሚመነጨው የባክቴሪያ አሲድ ስለሚጨምር አልሰር (ቁስለት) ሊፈጥር ይችላል። ሲጋራ የሚያጨሱ፣ ምግብ በሥነ-ስርዓት የማይመገቡ፣ የሥራ ጫና ወይም ጭንቀት ያለባቸው ከሲጋራ ማጨሱ ጋር ተዳምሮ አሲድ ያመነጭና አልሰር ሊፈጥርባቸው ይችላል። ይህ ራሱን የቻለ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

አንዳንድ ሰው ደግሞ በሕመም ምክንያት ከሶስት እና ከአራት በላይ መድሃኒቶችን (የስኳር፣ የግፊት፣ የኮሌስትሮል፣ የአስም እና የተለያዩ መድሃኒቶችን) እንዲወስድ ሊገደድ ይችላል።እነዚህ መድሃኒቶች በራሳቸው የጨጓራ በሽታ ያመጣሉ። ይህ ማለት የጨጓራውን አካል በቀጥተኛ ሁኔታ ስለሚፈጩ ቁስል ያመጣሉ። ቁስሉ ደግሞ በአሲድ ይባባሳል። እነዚህና መሰል ተጋላጭ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶቹ ብዙ ናቸው።

በአጠቃላይ የጨጓራ በሽታ ማለት በተለያዩ ምክንያቶች አሲድ ከተፈለገው በላይ በማመንጨት በጨጓራ የላይኛው ንጣፍ ላይ የሚከሰት ቁስለት ወይም ቁስለት መሰል ነገሮች የሚያመጡት ስሜት ነው።

የጨጓራ ሕመም እና ሕክምና

የጨጓራ ሕመም ብዙ አይነት እንደመሆኑ ሕክምናውም ይለያያል። ለምሳሌ በምግብ መውረጃ ቧንቧ ላይ አሲድ በብዛት ወደ ጉሮሮ መውጣት ሕመም በመድሃኒት ወይም ምግብ በማስተካከል ይታከማል። ስሜቱም ጥሩ ወደሚባል ደረጃ ይመለሳል። ሆኖም ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተመልሶ የመምጣት እድል ሊኖረው ይችላል።

ዋና ጨጓራ በሚባለው ቦታ ውስጥ የሚፈጠሩ አልሰሮች ለምሳሌ ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ሲጋራ ማጨሱን ካቆመ፣ ባክቴሪያ ከሆነ ደግሞ ባክቴሪያው ከታከመ በተጨማሪም የአሲድ መድሃኒት ከወሰደ እና የሚሰጣቸውን ምክር የሚያሟሉ ታካሚዎች ከሆኑ አልሰሩ በሂደት ይድናል። ስሜቱም ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል።

ነገር ግን አንዳንዴ ጨጓራ ውስጥ ያለ ቁስል ሁሉ የጨጓራ አሲድ መድሃኒት ብቻ ላያድነው ይችላል። መልኩን ወደእጢ ወይም ወደካንሰር የቀየረ ሊሆን ይችላል። እንደዚህ በሚሆንበት ጊዜ ታካሚዎቹ ክብደት ይቀንሳሉ፣ ደም ማነስ ይይዛቸዋል፣ አይናቸው ቢጫ ይሆናል፣ ሰገራቸው ይጠቁራል፤ እነዚህና መሰል ነገሮች ይታያሉ። በጨጓራ መድሃኒት የማይመለስ ሕመም ይኖራቸዋል።

በዚህ ጊዜ በኢንዶስኮፒ ምርመራ ናሙና ተወስዶ ናሙናው የቁስልነት ወይም የካንሰርነት ባሕሪ እንዳለው ከተረጋገጠ በኋላ የቁስል ከሆነ ይድናል። ካንሰር ከሆነ ደግሞ ደረጃውን ወደ መወሰን ይኬዳል፤ ደረጃው በቀዶ ጥገና የሚሰራ ሆኖ ከተገኘ እዛ ቦታ በቀዶ ጥገና ይሰራል። ተዛማጅ የሆኑ የጨረር ሕክምና ወይም ኬሞ ቴራፒ ሕክምና የሚያስፈልገው ከሆነ ሊሰጥ ይችላል። ሁለተኛው ነገር ወጣ ያለ እና ያልተለመደው የጨጓራ ችግር ነው ማለት ነው።

አብዛኞቹ የጨጓራ በሽታዎች በሥርዓት ከታከሙ ይድናሉ። የተወሰኑት ደግሞ መልካቸውን ከቀየሩ መዳን በማይችሉበት ደረጃ ላይ ሊሆን ይችላል።

የጨጓራ ሕመምና የሕብረተሰቡ ግንዛቤ

ማሕበረሰቡ ስለጨጓራ በሽታ ግንዛቤዎች አሉት። ነገር ግን ትልቁ ችግር የሚሆነው እና ብዙ ሰው ሲቸገር የሚስተዋለው ታክሞ የሚድን እና ታክሞ የማይድንን የጨጓራ በሽታን መለየት ላይ ነው። በጊዜው እና በአግባቡ ቢታከም የሚድነውን በሽታ ከፍ ወዳለ ደረጃ መቀየሩን አለማወቅ እና ምርመራዎችን የመፍራት ስጋት አለ። አንድ ሕመምተኛ ታክሞ መዳን በሚችልበት ሂደት ባለመታከሙ በሽታው ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሊሸጋገር ይችላል። ብዙ ጊዜ ያለው ችግር ሰዎች ግንዛቤ ቢኖራቸውም ወደ ሕክም ተቋም አይሄዱም።

አንዳንዶች ወደ መድሃኒት መደብር ሄደው በራሳቸው መድሃኒት ይጠቀማሉ። መድሃኒት በሚውጡበት ጊዜ ጊዜያዊ መፍትሄ ሲያገኙ ሃኪም ማየት የነበረበት አንዳንድ መሰረታዊ የበሽታው መገለጫዎች ታክሞ የሚድነውን ከማይድነው ጋር የሚለይበትን ጊዜ ያሳልፋል። ታካሚው ያንን ጊዜ በከንቱ በማባከኑ በኋላ ላይ በሽታው መልኩን ቀይሮ የመምጣት ሁኔታ ያጋጥማል። ይህ ብዙ ጊዜ በሕክምና ተቋማት የሚያጋጥም ነው።

ስለሕመሙ በሕብረተሰቡ ዘንድ ሙሉ ለሙሉ ግንዛቤ አለ ማለት ባያስደፍርም ብዙ ሰው የጨጓራ በሽታን በስሜት ያውቀዋል። ሆኖም ግን ትልቁ ችግር የሚሆነው የጨጓራ በሽታ ሁሉ ሁሌም ስሜት ላይኖረው ይችላል። አንድ ሰው ውስጥ ትልቅ ቁስል ኖሮት ካንሰር ደረጃ ደርሶም ክብደት ብቻ ሊቀንስ ይችላል። ማቃር ሳይኖረው፣ ማቃጠል ሳይሰማ፣ አለመፈጨት ሳያጋጥም በኋላ፤ ክብደትህ አነሰ፣ ደም ማነስ አለብህ ተመርመር ተብሎ ወደ ሕክምና ሲመጣ ጨጓራው ላይ አልሰሩ ወደ ካንሰር ተቀይሮ ሊሆን ይችላል።

ከግንዛቤ ጋር በተያያዘ ሌላው ጉዳይ የአመጋገብ ስርዓትን ይመለከታል። በኢትዮጵያ የአመጋገብ ስርዓት እንጀራ ነገርና መሰሎች፣ ፓስታ ማካሮኒ የሚዘወተሩ ናቸው። አሁን አሁን ጥራጥሬ የመመገብ ልምድ ቀንሷል። በዚህ ላይ ደግሞ ከአቅም በላይ የበሰሉ ተዘጋጅተው የሚሸጡ ምግቦችንም መመገብ ተለምዷል።
ምግብ የሚዘጋጀው በመቀቀል፣ በማብሰል እና በመጋገር ነው። በጤና ለአመጋገብ ጥሩ ነው የሚባለው በመጀመሪያ የተቀቀለ፣ በመቀጠል ደግሞ የተጋገረው፣ በመጨረሻ ረድፍ የሚቀመጠው ደግሞ የተቁላላው ወይም የበሰለ ምግብ ነው።

የበሰለ ምግብ ለጤና ጥሩ አይደለም። ብዙ ጊዜ የምንጠቀማቸው ምግቦች ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ላይ ዘይት የተደረገበት ከአንድ ሰዓት በላይ (ከሚገባው በላይ) በስሎ የምግብነት ንጥረ ነገሩን ያጣ ነው። የተወሰኑ ንጥረ ነገሮች በእሳት ተቃጥለው፣ ዘይቱ መልካቸውን ቀይሮት ነው የምንጠቀመው። አጠቃቀሙም ሁሉም ምግብ ላይ ዘይት ገብቶ ቅባት በዝቶበት በመሆኑ ጨጓራ ለመፍጨት ይቸገራል፤ በዚህ ሰዓትም ስሜት ይኖራል። ከአሲዱ ጋር የጠለሉ ቅባቶችና ኬሚካሎች ስሜት ያመጣሉ።
ግንዛቤን በተመለከተ በከፊል ቢኖርም፤ በከፊል ደግሞ ሰው የሚመጣው ስሜት ሲኖረው ነው። ሲያቃጥላቸው ወይም አላስበላ ሲላቸው ወይም ሥራ ሲከለክላቸው ወደ ሕክምና ይመጣሉ። በዚህ ጊዜ ጤናማ የአመጋገብ ስርአት እንዲከተሉ ይመከራል።

ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት

የሚመከሩ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት ከምንላቸው መካከል፤ ሆድ በጣም ሳይሞላ መብላት፣ ብዙ ያልበሰሉ ምግቦች መመገብ፣ ሲጋራ ማጨስ ካለ ማቆም ወይም መቀነስ እና መድሃኒቶችን ያላግባብ አለመውሰድ ይጠቀሳል። አልኮል በብዛት አለመጠጣት፣ በልቶ ወዲያው አለመተኛት፣ የሚስማሙ የምግብ አይነቶች ለይቶ ማወቅ፣ ምግብ በአግባብ መጠን በአግባብ ጊዜ መውሰድም ይመከራል።

ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች የአእምሮም የጉልበት ሥራም እየሰሩ ቁርስ ሳይበሉ ውለው ማታ 12፡00 ሰዓት የሚመገቡ አሉ። ይህ ሊሆን አይችልም። ይህ ሲሆን ጨጓራ ውስጥ ከአቅም በላይ አሲድ ይመነጫል። ከመነጨ ደግሞ ለስሜት፣ ለአልሰር ያጋልጣል። ስለዚህ ሰዎች በተገቢው ሰዓትና በተገቢው መጠን ምግባቸውን ተረጋግተው አኝከው፣ አላምጠው አዋህደው መዋጥ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ለጨጓራ ጥሩ ስሜት ይፈጥራል።

የጨጓራ በሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ተጋላጭ የሚያደርጉ እና የመከላከያ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል መጨናነቅ፣ ከአቅም በላይ ሥራን ለመወጣት መሞከር፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል በብዛት መጠቀም፣ ከአቅም በላይ መወፈር፣ ተደጋጋሚ ተገቢ ያልሆኑ መድሃኒቶች መውሰድ፣ ምግብ በሰዓት አለመብላት ለጨጓራ ጫና ይፈጥራል።

እነዚህ ሁሉ አሲድ በማብዛት የመከላከያ ስልቶቹን በማጥቃት የጨጓራውን ንጣፍ ለአሲድ ተጋላጭ ያደርጉታል። መከላከያ ስልቶቹ በተፈጥሮ የጨጓራ የላይኛው ንጣፍ ሙከስ የሚባል ንፍጥ የሚመስል ነገር አለው። ከቁስለት አሲዱን ይከላከላል።

ጨጓራ ላይ የተፈጠረ ቁስለት በኢንዶስከኮፒ ክትትል ይፈልጋል። የአንጀት የመጀመሪያ ክፍል ላይ የተፈጠረ ቁስለት ቶሎ ይድናል። ጨጓራ ላይ የተፈጠረ ቁስለት ግን ቶሎ ላይድን ስለሚችል ተገቢ ለሆነ ጊዜ መድሃኒት ወስደው ትልቅ ቁስለቶች ከሆኑ ከሶስት እስከ ስድስት ወራት ባሉ ጊዜያቶች በኢንዶስኮፒ ታይቶ የመዳናቸውን አቅጣጫ አይቶ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የበዓል ሰሞን አመጋገብ ሥርዓት

የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የተለያየ ሃይማኖት ይከተላሉ፣ የተለያየ አጽዋማት አላቸው። እንደየእምነቱ ለምሳሌ በኦርቶዶክስ እምነት ከጾም በኋላ ከጾም ምግብ ወይም ቅባት ነክና ስጋ ነክ ካልሆኑ ምግቦች ወደ ቅባት እና ስጋ ነክ ወደ ሆኑ ምግቦች ይሻገራሉ። በሙስሊም ቢጾሙም ቅባት ነክ ምግብ ነገር ማታ ላይ ስለሚፈቀድ ያን ያህል አንጀታቸውን አይከብዳቸውም። ለረጅም ጊዜ ቅባት የረሳ፣ በመጠኑ መብላት የለመደ አንጀት ወይም ጨጓራ በአንዴ ከፍተኛ አመጋገብ እና ካሎሪ ሲወስድ ይጨናነቃል።

ብዙ ጊዜ ቅባት የሚያበዙ ሰዎች የሃሞት ጠጠር ይኖርባቸዋል። የሃሞት ጠጠር የሚባለው ጠጠር ሳይሆን የረጋ ቅቤ እንደማለት ነው። የሃሞት ጠጠር የሚኖረው ሰው እንደጨጓራ ሕመም ስሜት ይኖረዋል። በላይኛው የሆድ ክፍል ውስጥ ማቃጠል፣ አለመፈጨት፣ መቁረጥ፣ የሆድ መነፋት፣ ማስታወክ እና የመሳሰሉ ነገሮች ያጋጥማሉ።

እነዚህ ነገሮች ለጨጓራ ስሜት እንደሰጠ ሁሉ ለሃሞት ከረጢት ላለ ጠጠር ስሜት ይሆናል። በመሆኑም በበዓል ጊዜ ማሕበረሰቡ የሚጠቀማቸው ከአቅም በላይ ቅባትና ዘይት ተኮር ናቸው። ዶሮ ወጥን በአብነት ብንመለከት ለመብሰል ቢያንስ እስከ ሶስት ሰዓት እሳት ላይ ይቆያል። እንደዚህ አይነት ምግቦች አንጀት አይቋቋማቸውም፤ ይከብዳሉ።

በመሆኑም መጠን ቢቀንስ ጥሩ ነው። አንድ ሰው ከአንድ ዶሮ ወጥ እስከ ዘጠኝ ጊዜ የሚጎርስ ቢሆን አምስት ጊዜ ብቻ ቢጎርስ ይመከራል። በጎን ደግሞ እንደቆስጣ፣ ሰላጣ፣ የተቀቀለ ድንች፣ ያሉ አትክልቶችን ተልባ መቀላቀልና ተመጣጣኝ የሆኑ ምግቦችን መጠቀም መልካም ነው።
ሁሉንም ምግቦች በጣም አጣፍጦ፣ ቆልቶ አለመመገብ ይመከራል። ቀቅለን ብንመገብ የተሻለ ነው። በዓመት በዓል ሰሞን ስጋ እስኪያልቅ ባንጠቀም ጥሩ ነው። ስጋ አብዝቶ መጠቀም አንጀትን ለከፍተኛ (የቅባት) የፕሮቲን መጠን ያጋልጣል።

ይህ ደግሞ የሰውነት ቅርጽና የክብደት መጠንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያዛባል። የስኳር መጠን እና ክብደት እስከ ስድስት ኪሎ ይጨምራል። ክብደት መጨመር በራሱ ለጤና ትልቅ ችግር አለው። ለመቀነስ ብዙ ጊዜ ይወስዳል። በዓመት በዓል ጊዜ አልኮልና ጣፋጮች ይወሰዳሉ። እነዚህን ከአቅም በላይ ከመጠቀም መቆጠብና በሂደት ሰውነትን አስለምዶ ቀስ በቀስ መጥኖ መጠቀም አግባብ ነው።

የአመጋገብ ስርዓት ከመጥገብ አንጻር መቃኘት የለበትም። ሰዎች በጣም እስኪጠግቡ መመገብ የለባቸውም። የሚያስፈልገውን መጠነኛ አመጋገብ መጠቀም ጥሩ ነው። ስንመገብ መጠንን መቀነስም አስፈላጊ ነው።

ምግብን ከአቅም በላይ አለማብሰል፣ ሌሎች ተለዋጭ ምግቦች አትክልትና አትክልት መሰል ነገሮችን ከስጋ ጋር በተመጣጠነ መልኩ በማዕዳችን ማቅረብ፣ ከምግብ በኋላ ተገቢ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ (ወጣ ብሎ መመለስ)፣ ራትን መዝለል ለሰውነት ረፍት ይሰጣል እንዲሁም አልኮል በብዛት አለመጠቀም ተገቢ ነው የዶ/ር መንግሥቱ እርቄ መልእክት ነው።

ዶ/ር መንግሥቱ እርቄ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ሕክምና ትምህርት ክፍል መምህርና የጨጓራ፤ የአንጀትና የጉበት በሽታ ሰብ ስፔሻሊስት)

🔥 #የማይግሬን (መርዘን) ራስ ምታት (Migraine Headache)የማይግሬን ራስ ምታት ምንድን ነው?🔸የማይግሬን ራስ ምታት ከራስ ምታት አይነቶች አንዱ ሲሆን ሌሎች ምልክቶችንም ሊያሳይ ይ...
23/02/2025

🔥 #የማይግሬን (መርዘን) ራስ ምታት (Migraine Headache)

የማይግሬን ራስ ምታት ምንድን ነው?

🔸የማይግሬን ራስ ምታት ከራስ ምታት አይነቶች አንዱ ሲሆን ሌሎች ምልክቶችንም ሊያሳይ ይችላል።
🔸በሽታው በብዛት ሴቶች ላይ ሲታይ በማንኛውም እድሜ ላይ ያለን ሰው ሊያጠቃ ይችላል።

የማይግሬን ራስ ምታት ማስነሻዎች

💥 መጨናነቅ
💥 የሆርሞን ለውጦች
💥 ምግብ በሰዓቱ አለመመገብ ወይም በደንብ አለመብላት
💥 የአየር ንብረት መቀያየር
💥 ከበቂ ባላይ መተኛት ወይም በቂ እንቅልፍ አለማግኘት
💥 ከፍተኛ ወይም አንፀባራቂ ብርሃን
💥 አልኮል መጠጣት
💥 ሲጋራ ማጨስ ወይም የሚያጨስ ሰው አጠገብ መሆን

ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?

➡️ ራስ ምታት፦ ከጀመረ በኋላ እየተባባሰ የሚሄድ ሲሆን ግምሽ አናትን ከፍሎ ሊያም ይችላል።
➡️ ማቅለሽለሽና አልፎ አልፎ ማስመለስ
➡️ ከፍተኛ ድምፅና ብርሃንን የመቋቋም ችግር
➡️ የአይን እይታ ችግር፣ የፊት አካባቢ መደንዘዝና የመሳሰሉ ምልክቶች ("Auras") ከራስ ምታቱ በፊት ወይም አብረው ሊመጡ ይችላሉ።

ህክምናው ምንድን ነው?

🔑 ቀለል ያለ ራስ ምታት ከሆነ ፓራሲታሞል፣ አይቡፕሮፌን እና የመሳሰሉ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ።
🔑 በተጨማሪም የፓራሲታሞልና የካፌን ቅይጥ መድሃኒት ሊታዘዝ ይችላል።
🔑 ከፍተኛ ራስ ምታት ሲኖር ደግሞ ትሪፕታንስ የሚባሉ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ።
🔑 ለማቅለሽለሽና ለማስታዎክ የሚረዱ መድሃኒቶችም ሊሰጡ ይችላሉ።
🔑 እንዲሁም ድግግሞሽ እንዳይኖር የሚረዱ መድሃኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ።
🔑 ከመድሃኒቶች ባሻገር ለመዝናናት መሞከር እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስነሻዎች ማስወገድ ተገቢ ነው።

❤️ #የልብ እና  #የደምስር ጤናን ለመጠበቅ የሚረዱ  #8ቱ መንገዶች1ኛ - አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ (መካከለኛ ስፖርት ከሆነ በሳምንት ውስጥ ለ 150 ደቂቃ እና ከበድ ያለ ስፖርት  ከሆ...
16/02/2025

❤️ #የልብ እና #የደምስር ጤናን ለመጠበቅ የሚረዱ #8ቱ መንገዶች

1ኛ - አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ (መካከለኛ ስፖርት ከሆነ በሳምንት ውስጥ ለ 150 ደቂቃ እና ከበድ ያለ ስፖርት ከሆነ በሳምንት ውስጥ ለ 75 ደቂቃ መስራት)

2ኛ - ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት መከተል

3ኛ - ክብደትን መቆጣጠር (Body Mass Index ከ25 በታች እንዲሆን ማድረግ)

4ኛ - ሲጋራ አለማጨስ

5ኛ - አጠቃላይ የኮሌስትሮል መጠንን ከ 200 mg/dL በታች ማድረግ

6ኛ - የደም ግፊት መጠንን ከ 120/80 mm Hg በታች ማድረግ

7ኛ - በባዶ ሆድ የተለካን የስኳር መጠን ከ 100 mg/dL በታች ማውረድ

8ኛ - በቂ እንቅልፍ መተኛት (በቀን ውስጥ ከ7 - 9 ሰዓት)

ከላይ የተዘረዘሩትን መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ከ 90% በላይ የሚደርስን የስትሮክና የልብ ደም ስር መዘጋት መከላከል ይቻላል❗️

የመረጃ ምንጭ - የአሜሪካ የልብ ማህበር (American Heart Association)

🔴 !
15/02/2025

🔴 !

Check out gashawsolela’s video.

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Telehealth posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethio-Telehealth:

Share