
27/09/2025
ፈተና ከሰኞ-አርብ የምናደርግ መሆኑን እንድታውቁ! የቃለ መጠይቅ ፈተና የምናደርገው ለቀጣይ ፈተና ላለፉት ብቻ ነው።
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞችም ሆነ በአዲስ አበባ የድርጅታችን ሰራተኞች ለመሆን የሚያመለክቱትን ስራ ስለሆነ የፈለጉት ሁሉንም እናከብራለን። በእውነትም ችለን ለሁሉም ስራ ብንሰጣቸው ደስ ባለን ነበር። የሀገራችን ዜጎች የስራ ማጣት ችግር ምን ያህል እንደሆነ እናውቃለን። ተምረው በየቤቱ ሞራላቸው ተነክቶ የተቀመጡ እልፍ ወጣቶች እንዳሉም እናውቃለን። ይሁንና ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ ምክር ስልጠናና የአስተሳሰብ መቀየሪያ የስነ-ልቦና ሳይንስ ካውንስሊንግ ያስፈልጋል።
ድርጅታችን በሀገር ደረጃ ከ50,000 በላይ ተቋማት ጋር የተለያየ የስራ ግንኙነቶች አለው። በዚህ ሒደት ካለን መረጃ በመነሳት ስራ ፈላጊ የመብዛቱን ያክል ስራ ፈላጊዎች ለሚፈልጉት ስራ ብቁ የሚያደርጋቸው ሁለንተናዊ ብቃት የሌላቸው ናቸው። በየማህበራዊ ሚዲያው ስድብና አሉባልታ ሲመለከቱ የሚውሉት በርካቶች ለመሳሌ ይህን ፅሁፍ ከላይ እስከታች ጨርሰው ለማንበብ ይታክታሉ።
በመሆኑም የእኛ ምክር ስራ ፈላጊዎች ብቁ ለመሆን የሚያስችላችሁን እውቀት(30%) ፣ ክህሎት (50%) እና ስነምግባር (20%) ይዛችሁ ለመገኘት እንድትጥሩ እንመክራለን።
ድርጅታችን የሚሰራው ጥራትና የሽልማት ምዘና ላይ ነው። ደንበኞቻችን የእኛ ሰራተኞች ይሆናሉ ብለው የሚጠብቋቸው ፍፁም የሆኑ ፣ ከተለየ አለም የመጡ ፣ በርካታ ሙያዎች ላይ የተለየ አለም አቀፋዊ እውቀት ያላቸው ፣ በንፅህናቸውና አለባበሳቸው ልዩ የሆኑና ምሳሌ የሚሆኑ ፣ የተለየ የስነምግባር ልክ ያላቸው አድርገው ነው የሚጠብቁት።
ደንበኞቻችን ድርጅቶችና የድርጅት ባለቤቶችና አመራሮች ናቸው።
ስለዚህ እኛም የምንጥረው ደንበኞቻችን የሚጠብቁትን አይነት ሰራተኞች መልምለን መቅጠር ነው።
የኛ ደርጅቶች ዝርዝር
1. World Class Quality Award Organization
2. World Class Excellence Center
3. Grand African Organizational and leadership Award Organization
4. Abyssinia Higher Honor Award Organization
ናቸው።
እነዚህ ድርጅቶቻችን ውስጥ በመላው ሀገራችን መስራት የሚሻ ሁሉ ለድርጅታችን ብቁ የሚያደርጉትን ለማወቅ መጣርና ከላይ የዘረዘርናቸውን ብቃቶች ባለቤት ለመሆን መጣር ይኖርበታል።
በአሁኑ ዙር ፈተና ያላለፋችሁ ሁሉ በዩ ቱዪብ አካውንታችን በመግባትና በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ ያሉ እውቀቶችን በሚገባ በማየት ድርጅታችንንና ደንበበኞቻችንን በማወቅ ላራሳችሁም እውቀት እንድትገበዩ እና እንደምርጫችሁም ከድርጅታችን ጋር እንድትሰሩ እንመክራለን።
ለክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የመስቀል እንመኛለን!
የአቢሲኒያ የኢንደስትሪ ሽልማት የ2016 ዓ/ም ተሸላሚ ተቋማት የሽልማት ስነ ስርዓት | ክፍል 1