Hakim Mereja ሀኪም መረጃ

Hakim Mereja ሀኪም መረጃ Sometimes take a LOSS for a bigger WIN.
(1)

ከአሰቃቂ የጅብ ጥቃት መትረፍ፡ የተቀናጀ የህክምና እርዳታ ውጤትአንድ ህጻን በጅብ ጥቃት ምክንያት በደረሰበት ከፍተኛ የፊት አካል መጎዳት ምክንያት ወደ አለርት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል...
25/03/2026

ከአሰቃቂ የጅብ ጥቃት መትረፍ፡ የተቀናጀ የህክምና እርዳታ ውጤት

አንድ ህጻን በጅብ ጥቃት ምክንያት በደረሰበት ከፍተኛ የፊት አካል መጎዳት ምክንያት ወደ አለርት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መጣ።

በጥቃቱ ወቅት ህጻኑ ሁለቱንም ዓይኖቹን ያጣ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ማየት አይችልም። ከዚህም በተጨማሪ በዓይኖቹ ዙሪያ፣ በግንባሩ እና በሁለቱም ጉንጮቹ ላይ ያለው ቆዳ ተገሽልጦ ተወስዷል። የላይኛው መንጋጋው (maxilla) ከፊል አካል በጥቃቱ ምክንያት ሲጠፋ፣ የቀሩት አጥንቶች ደግሞ ተሰባብረው ነበር።

ህጻኑ ወዲያውኑ ወደ ህጻናት ጽኑ ህክምና ክፍል (PICU) በመግባት የህይወት አድን እርዳታ የተደረገለት ሲሆን ፣ በአንገቱ በኩል ቀዳዳ በመክፈት እንዲተነፍስ (tracheostomy) ተደርጓል። በቀጣዮቹ ቀናትም የቀዶ ጥገና ቡድኑ ኢንፌክሽንን ለመከላከልና የሞቱ አካላትን ለማስወገድ ተከታታይ የጽዳት ስራዎችን አከናውነዋል።

ቁስሉ ለቀጣይ ህክምና ዝግጁ ሲሆን የተሃድሶ ቀዶ ጥገና ተጀመረ፦

የቆዳና ቲሹ ንቅለ ተከላ፦ የፕላስቲክ እና ተሃድሶ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶች ከህጻኑ ጭን ላይ ስጋና ቆዳ 7 ሴሜ በ 17 ሴሜ የሆነ ከነ ደም ስሩ በመውሰድ በፊቱ ላይ የጠፋውን ክፍል ለመተካት የነጻ ቲሹ ዝውውር/ ንቅለ ተከላ (free tissue transfer) ተደርጓል። ይህ ስራ በጥቃቅን የደም ስር የቀዶ ጥገና ጥበብ (microsurgery) ከጆሮው አጠገብ ካሉ የደም ስሮች ጋር እንዲገናኝ ተደርጓል።

የአጥንት ተሃድሶ፦ በመቀጠልም የጠፋውን የፊት ቅርጽ ለመመለስ፣ የተሰባበሩትን የመንጋጋ አጥንቶች በማስተካከል በታይታኒየም እንዲደገፉ ተደርጓል።

እስካሁን ድረስ ህጻኑ ቢያንስ 8 ቀዶ ጥገናዎችን ያከናወነ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ የፊት ማስተካከያ ስራዎች ይጠብቁታል። በአሁኑ ወቅት ህጻኑ በማገገም ላይ ይገኛል።

ይህ አጋጣሚ የተቀናጀ የህክምና ቡድን (Multidisciplinary care) ያለውን ፋይዳ ያሳያል። የህጻናት ሐኪሞች፣ የጽኑ ህክምና ባለሙያዎች፣ ጠቅላላ ቀዶ ጥገና እና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶች የህጻኑን ህይወት ለማዳንና ፊቱን ለመጠገን በጋራ ሰርተዋል።

ይሁን እንጂ ይህ አሳዛኝ ክስተት ብቸኛው አይደለም። በአሁኑ ሰዓት ሌላ ግማሽ ፊቱን በጅብ የተበላ ህጻን በተመሳሳይ ሆስፒታላችን ውስጥ ቀዶ ጥገናውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

እነዚህ አደጋዎች በማህበረሰባችን ውስጥ እየደረሰ ያለውን የጅብ ጥቃት አስከፊነት የሚያስታውሱ ናቸው። ልጆቻችንን ለመጠበቅ ንቁ መሆን፣ ማህበረሰባዊ ጥንቃቄ ማድረግ እና ተጋላጭነትን የሚቀንሱ የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል።

የተሃድሶ ቀዶ ጥገና (reconstructive microsurgery) የጠፋን መልክና ተግባር ሊመልስ ቢችልም፣ ዋናው መፍትሄ ግን አደጋው ሳይደርስ መከላከል ነው።

በተሃድሶ ቀዶ ጥገና (reconstructive microsurgery) ወቅት የተሳትፉ ባለሙያዎች

1. ዶ/ር አብዱረዛቅ አሊ (መሪ ሃኪም) - የፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ እና ማይክሮሰርጅን

2. ዶ/ር አታክልቲ ባራኪ (ኮንሰልታንት ዋና ሃኪም) - የፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ እና የ እጅ ሰርጅን

3. ዶ/ር ዘቢባ መካ (ኮንሰልታንት ዋና ሃኪም) - የፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጅን

4. ዶ/ር ተስፋሁን አሊ (ረዳት ሃኪም) - ሬዚደንት

5. ዶ/ር ዮሃንስ ኤሊያስ (ረዳት ሃኪም) - ፌሎው

6. ሲራጅ ሙሼ - ማደንዝዣ እና ሰመመን ሰጪ ባለሙያ

7. ናትናኤል ብርሃኑ - የቀዶ ህክምና ክፍል ነርስ

8. ጫልቱ ተገኔ - የቀዶ ህክምና ክፍል ነርስ

9. አለሙ ቦጋለ - የቀዶ ህክምና ክፍል ነርስ

10. ኪሩቤል እሸቱ አለማየሁ - ፖርተር

11. አባይነው ሰውነት ተገኘ - ፖርተር

12. ዘቢደር ፈንቴ ደምለው - ጽዳት
እና ሌሎች በርካታ ባለሙያዎች ተሳትፋውበታል

First batch General Surgery graduates of Wolkite University, 2026.
25/03/2026

First batch General Surgery graduates of Wolkite University, 2026.

የሆስፒታሉን ስራ-አስኪያጅ ስትጠይቀው " ችግሩ የወረዳው ፋይናንስ ነው " ይልሀል ። የወረዳውን ፋይናንስ ስትጠይቀው " ችግሩ እኮ ጤና ቢሮው በጀት አለመመደቡ ነው¡ " ይልሀል ። የክልሉን ...
25/03/2026

የሆስፒታሉን ስራ-አስኪያጅ ስትጠይቀው " ችግሩ የወረዳው ፋይናንስ ነው " ይልሀል ። የወረዳውን ፋይናንስ ስትጠይቀው " ችግሩ እኮ ጤና ቢሮው በጀት አለመመደቡ ነው¡ " ይልሀል ። የክልሉን ጤና ቢሮ ደግሞ " ለምን የደከምኩበትን የዲዩቲ የላብ ክፍያ ትቀማኛለህ?, ለምን በወቅቱ አትከፍለኝም? ለምን እኔንም ልጆቼንም ለችግርና ለርሀብ ትዳርጋለህ? አስረዳኝ " ስትለው " አይ እኛ እኮ እያሰብንበት ነው, በጀት ገና ልንመድብ ነው ; ተጠይቋል ,ሊመጣ ነው, ታገሱ " እያሉ ቡጊ ቡጊ ጨዋታ ይጫወቱብናል ። ኧረ ተው እንደማመጥ ወገን? የእናንተ ፊት " ፅጌረዳ አበባ መስሎ የእኛ ፊት የአበባ ማስቀመጫ ጣሳ መስሎ እስከመቼ ነው? ወይንስ እናንተ በየቢሮውና በየሀላፊነት ቦታው ተቀምጣችሁ ጤና ባለሙያውን እንደቆሎ እንድትቆሉ የፈቀደላችሁ ማነው? ወይንስ እናንተን ፈላጭ ቆራጭ የሀገሪቱ አንደኛ ዜጋና ሁሉን አድራጊ እኛን ደግሞ 2ኛ ዜጎችና ጩኸት ሰሚ የሌለን አድርጎ ያስቀመጣችሁ ማነው? ነገ ቀን ሲወጣ ከምንተዛዘዘብ ሒሳብም ከምንተሳሰብ ምናለ ብንደማመጥ? ዲዩቲ ክፍያ የተነጠቃችሁ, የዘገየባችሁ, ( ብራችሁ ኤክስፓየርድ ያደረገባችሁ እንዴት ናችሁ? ( ኤክስፓየርድ አደረገ ማለትም ለምሳሌ የዛሬ 5 ወር ገደማ መከፈል የነበረበት 10,000 ብር ቢኖራችሁ ዛሬ ላይ ምናልባት ቢከፈላችሁ የሚኖረው ዋጋ የ 6000 ብር ያህል ይሆናል ።ለምን? ከተባለ የዛሬ 5 ወር ገደማ የዘይት ዋጋ የሳሙና ዋጋ የክሰልና የእንጨት ዋጋ እንዲሁም የልብስ ዋጋ ዛሬ ላይ ግሽበት አሳይቷልና ነው ። ስንቱ ብር ኤክስፓየርድ አደረገባችሁ ማለት ነው ? 4000 ብር ።
እንዴው በሞቴ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ ይህንን ምስጢር አንብቡትማ ይጠቅማችሗል ።እንበልና ህፃን ልጅህ ዳቦ በሻይ እያለ እየለመነህ ነው ። እያለቀሰ እየጠየቀህ ነው ። አንተ ግን ዝምብለህ ስትሰማው ትቆይና ትታገሰዋለህ ; ነገር ግን ህፃኑ እለቅሶውንም ሆነ ልመናውን በፍፁም ሊተው አልቻለም ; ከዚያ በሗላ በጣም በቁጣ ትነሳና ህፃኑን ይዘህ ቅጥቅጥ አድርገህ ትገርፈዋለህ ። ህፃኑ ከጠየቀው ጥያቄ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ነገር ትፈፅምበታለህ! ! ህፃኑ ምርር ብሎ እሪ ብሎ ያለቅሳል ብሶቱን ያሰማል :: ከዚያ ወዲያውኑ ቶሎ ለቅሶውን ሳያቋርጠው ህፃኑን ወደ አንተ ሳብ ታደርገውና ወደ ጉያህ በጣም አስጠግተህ በደንብ ትስመዋለህ ፍፁም ፍቅር መልሰህ ትሰጠዋለህ ። በጣም ጥብቅ አድርገህ ይዘህ ፍፁም ከመጀመሪያው ተቃራኒ የሆነ እንክብካቤ መስጠት ። ከዚያ ይህ ህፃን ምን ይሆናል? ? አዲስ ባህርይ ይዞ ቁጭ ይላል! ! ( ህፃን ልጅ ካላችሁ ሞክሩትማ ?)
( የአለም ነገስታት የሚመሩበት አንድ መመሪያ አላቸው ; Theisiss Anti thesis >>> Synthesis! ! ይህ ምን ማለት ነው? ?
2 እርስ በርሳቸው ፍፁም ተቃራኒ የሆኑ ሀሳቦች እርስበርሳቸው ተጣፍተው ሌላ አዲስ ሀሳብ ይፈልቃል ማለት ነው ። ለምሳሌ ህዝቡን ሰላማዊ ሰልፍ ይቻላል, ዲሞክራሲ መብት አለህ ,በነፃነት መኖር ተፈቅዷል! ! ብለው በየሚዲያቸው ከነገሩት በሗላ ህዝቡ የሆነ ጉዳይና ጥያቄ ይዞ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ሰልፉን በጭስ ቦምብ መበታተን ማለት ነው ። በፖሊስ ዱላ እየወቀጡ ወደ ቤቱ መመለስ ማለት ነው ። ይህ አንድ ምሳሌ ነው እንጅ ሁሉንም ስራ የሚሰሩት በዚህ መልኩ ነው ። " ቲሲስ አንታይ ቲሲስስ ሴንቴሲስ! !! ልክ ጤና ባለሙያው ላይ የተፈፀመውም ይኸው መመሪያ ነው! ! ከዚህ ቀደም ጤና ባለሙያው የጠየቀው ጥያቄ " ኑሮ ከበደኝ, መኖር አቃተኝ ,ደሞዝ ይጨመረኝ, የትራንስፖርት ,የቤት አበልና የተጋላጭነት ክፍያ ይፈፀምልኝ? ? "

ናፍጣ የለም" በሚል ሰበብ ህይወቷን አደጋ ላይ የጣሉት እናት ጉዳይ....ቤተሰቦቿ በጭንቅ ላይ ሳሉ "ናፍጣ የለም" በሚል ሰበብ ህይወቷን አደጋ ላይ የጣሉት እናት ጉዳይ፦ የሙያ ስነ-ምግባር ...
25/03/2026

ናፍጣ የለም" በሚል ሰበብ ህይወቷን አደጋ ላይ የጣሉት እናት ጉዳይ....

ቤተሰቦቿ በጭንቅ ላይ ሳሉ "ናፍጣ የለም" በሚል ሰበብ ህይወቷን አደጋ ላይ የጣሉት እናት ጉዳይ፦ የሙያ ስነ-ምግባር ወይንስ የሃላፊነት መሸሽ?

ልዩ የመረጃ ዘገባ - ከጫጎ ጤና ጣቢያ

በዛሬው ዕለት ሸካ ዞን በጫጎ ጤና ጣቢያ የተከሰተው እጅግ አሳዛኝ ክስተት፣ የጤና ተቋማቱ ለሰው ህይወት የሚሰጡትን ዋጋ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ሆኗል።

በአስቸኳይ ምጥ ላይ የነበሩ አንዲት እናት ለተሻለ ህክምና ወደ ማሻ ሆስፒታል ሪፈር ቢደረጉም፣ በአካባቢው የሚገኘው አምቡላንስ "ናፍጣ የለኝም" በሚል አስደንጋጭ ምላሽ አገልግሎት ሊሰጥ አልቻለም።

በዚህም ምክንያት፣ እናቲቱ በከፍተኛ የጤና ስጋትና በምጥ ስቃይ ላይ እንዳሉ በሞተር ሳይክል ተጭነው ለከፋ አደጋ ተጋልጠው እንዲጓዙ ተገደዋል።

የዘገባው ዋና ነጥቦች፦

* ለድንገተኛ አደጋና ለህይወት አድን የተመደበ ተሽከርካሪ "ናፍጣ የለም" በሚል ምክንያት ስራ ማቆሙ።

* በህክምና የታዘዘላቸውን አምቡላንስ አጥተው በሞተር ሳይክል ለአደጋ ተጋልጠው እንዲሄዱ መደረጋቸው።

* የዞኑና የወረዳው የጤና መምሪያ፣ እንዲሁም የአካባቢው አስተዳደር ይህንን ተደጋጋሚ የነዳጅ እጥረት ሰበብ በአስቸኳይ በመፍታት የተጠያቂነት አሰራር እንዲዘረጉ በጽኑ እናሳስባለን።

የሰው ህይወት በቸልተኝነትና በናፍጣ ሰበብ መጥፋት የለበትም! ድርጊቱ እጅግ አስነዋሪና በእናቶችና ህጻናት ህይወት ላይ እንደመቆመር የሚቆጠር ነው። የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

Via ጫጎ ጤና ጣቢያ

ከጉርሻ page ላይ የተወሰደ

First batch OBGYN graduates of Wolkite University, 2026.
25/03/2026

First batch OBGYN graduates of Wolkite University, 2026.

Class of 2026: Obstetrics and Gynecology Graduates of St. Paul’s Hospital Millennium Medical College . Congratulations!
25/03/2026

Class of 2026: Obstetrics and Gynecology Graduates of St. Paul’s Hospital Millennium Medical College . Congratulations!

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል የኦፕራሲዮን ማገገሚያ ክፍል ላይ በተፈጠረው አለመግባባት የሆስፒታሉ ዳይሬክተሩ እና የኮሌጁ ዳይሬክተሩ ያሳለፉት አሰራር ከህግ እና ከጤ...
24/03/2026

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል የኦፕራሲዮን ማገገሚያ ክፍል ላይ በተፈጠረው አለመግባባት የሆስፒታሉ ዳይሬክተሩ እና የኮሌጁ ዳይሬክተሩ ያሳለፉት አሰራር ከህግ እና ከጤና ተቋማት አሰራር መመሪያዎች ጋር የተቃረነ መሆኑን ከኦፕራሲዮን ማገገሚያ ክፍል ሐላፊ(ፒን) ቅሬታ ቀረበ።

ከዚህ በታች በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ትንታኔ እና አስተያየት ቀርቧል።

1. የክስተቱ መነሻ እና የአመራር ሥልጣን ጣልቃገብነትና የክፍሉ ሐላፊ ሥልጣን አለመከበር

አንድ ታማሚ ከካኑላ(ግሉኮስ መስጫ መርፌ) ጋር በተያያዘ በባለሙያዎች እና በአስታማሚው በተፈጠረ አለመግባባት የክፍሉን ሐላፊ ነርስ(ፒንን) አስታማሚዎች በስድብ፣ በዛቻ እና በአካላዊ ጥቃት አድርሷታል። በማንኛውም የጤና ተቋም ውስጥ የሥራ ክፍል ሐላፊ (Head Nurse/Unit Manager) ለክፍሉ ሥርዓት፣ ለሠራተኞች ደህንነት እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ሙሉ ሥልጣን እና ኃላፊነት ያለው አካል መሆኑ እሙን ነው።

ትንታኔ፡-አስታማሚው በታካሚው ሕክምና አገልግሎት ላይ ቅሬታውን ለክፍሉ ሐላፊ ማቅረብ ሲገባው ወዲያውኑ ሐላፊውን ከመደብደብ እስከ ወደ ውስጣዊ አሰራር ደረጃውን ባልጠበቀ መልኩ ቀጥታ የኮሌጅ ሐላፊና ሆስፒታል ዳይሬክተር ውስጣዊ ጣልቃገብነት እስከ ውጫዊ ጣልቃገብነት መሄዱ የሆስፒታሉን የውስጥ ቅሬታ አፈታት መዋቅር ችላ ማለት ነው። ይህ አሰራር የክፍሉን ሐላፊ ሥልጣን ማቃለል፣መናቅና ከማዳከም ባለፈ በሌሎች አስታማሚዎች ሕግ አለማክበርና በሙያተኞች ዘንድ የሥራ ሥነ ምግባር እንዲበላሽ መንገድ ይከፍታል።

2. የበላይ አመራሮች ጣልቃ ገብነት እና የሕግ ተግባር ላይ ያለው ጉድለት

የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎች( ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተሩ እና የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሩ) በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት የክፍሉን ሐላፊ አሳልፈው በፌዴራል ፖሊስ አሳጅበው በውጪ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ እንድትታሰር አድርገዋል።

ትንታኔ፡-

✍️ የሥልጣን ተላላፊነት ጥሰት፡- በማንኛውም ተቋም ውስጥ አለመግባባት ሲፈጠር ቀጥተኛ ኃላፊውን ሳይጠይቁ ወይም ሳያሳትፉ ከፍተኛ አመራሮች ወዲያውኑ ጣልቃ መግባት የተዋረድ አስተዳደርን ያዳክማል። ክፍሉ ሐላፊ የሆነችው ነርስ ጉዳዩን የመፍታት ሥልጣን ሳይሰጥ/አገልግሎት ተቀባዩ እስከ ሰጪው ባለሙያዎች በሥልጣን ከአገልግሎት ጋር በተያያዘ ጉዳይ በክፍሏ ሐላፊ ሙሉ ሥርና ከሐላፊዋ በላይ እንደሆነ ከእሷ በላይ ያሉ አካላት ማስተላለፍ ሐላፊነትና ሥልጣን ውጩ ከእሷ ውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ መወሰን የሚገባው አካል ከበዳይና አጥቂ ሀሳብ በመውሰድ ውሳኔ ማሳለፋቸው የሆስፒታሉና ኮሌጁ ሥራ አመራር ከባድ ክፍተት ነው።
✍️ "Informal" የግንኙነት አጠቃቀም፡- ጉዳዩን በተቋሙ መደበኛ አሰራር መዋቅር ሲስተም ሳይፈቱ በስልክ በሚደረግ "Informal" ግንኙነት መፍታት እና የፖሊስ ጣልቃ ገብነትን ማምጣት የሕግ አሰራርን አላግባብ መጠቀም ነው።

3. የጤና ተቋማት አሰራር ሕግጋት እና መመሪያዎች መጣስ

የጤና ተቋማት ሕግ እና የሙያ ሥነ-ምግባር ደንቦች እንደሚከተለው ያዛሉ፦

1. የቅሬታ አፈታት ሂደት፡- ታካሚ ወይም አስታማሚ ቅሬታ ካለው መጀመሪያ ለክፍሉ ሐላፊ ማቅረብ ይጠበቅበታል። መፍትሔ ካላገኘ በኋላ ወደ ላይኛው ደረጃ (Clinical Director, Hospital Administrator) መሄድ አለበት። እዚህ ጉዳይ ላይ አስታማሚው በታካሚው ጉዳይ ቀጥታ ወደ ከፍተኛ አመራሮች በመድረስ ሂደቱን አጭበርብሯል።
2. የሠራተኛ ደህንነት ጥበቃ፡- በአገልግሎት ላይ ላሉ የጤና ባለሙያዎች ደህንነት ማረጋገጥ የተቋሙ ኃላፊነት ነው። በሥራ ላይ ለሚደርስ ጥቃት ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ሠራተኛውን መጠበቅ ነው፣ እንጂ ተጠቂውን አሳልፎ መስጠት አይደለም።
3. የጥበቃ አሠራር፡- ታካሚ ወይም አስታማሚ ተባባሪ ካልሆነ፣ ሕግን ከጣሰ እና ለሠራተኞች አደጋ ከፈጠረ፣ ሆስፒታሉ የራሱ የጥበቃ ክፍል በማስተባበር ሰውየውን ከግቢው ለጊዜው የማስወጣት ሥልጣን አለው። ይህ በሕግ የተሰጠ የተቋሙ መብት ነው። ይሁን እንጂ እዚህ ላይ ተቋሙ የራሱን ሕጋዊ ሥልጣን ተጠቅሞ ታካሚውን ከማስወጣት ይልቅ የራሱን ሠራተኛ አሳስሯል።

4. የተሳሳተ የውሳኔ አሰጣጥ ምክንያት ያስከተለው ውጤት

በዚህ ጉዳይ ምክንያት፦

✍️ የሥራ ሥነ-ምግባር መጓደል፡- አመራሮች በሕገ-ወጥ መንገድ በመግባባት ተጠቂዋን ማሳሰራቸው ለሌሎች ሠራተኞች "በሥራ ቦታ ጥቃት ከደረሰብህ አንተ ትቀጣለህ" የሚል አሉታዊ ሥነልቦናዊ ጥቃት እና አለመተማመን መልእክት ይልካል።
✍️ የሕክምና አገልግሎት መስተጓጎል፡- የክፍሉ ሐላፊ በእስር ላይ መቆየቷ በክፍሉ ውስጥ የአመራር ክፍተት በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጡን አሉታዊ በሆነ መልኩ ሊነካ ይችላል።
✍️ የሕግ የበላይነት ተጠያቂነት መጓደል፡- ከፍተኛ አመራሮች ራሳቸው ሕግን እና መመሪያን በመጣስ ውሳኔ ማሳለፋቸው ተቋሙ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን አላግባብ መጠቀም ነው።

5. የሚመከሩ መፍትሄዎች

1. ፈጣን እርምጃ፡- የታሰረችው የክፍሉ ሐላፊ ነርስ ወዲያውኑ ከእስር እንድትፈታ እና ወደ ሥራዋ እንድትመለስ እንደገና ተጣርቶ አሰራር ደንቡ ላይ ማስተካከያና እንዳይደገም መምከር መደረግ አለበት። እስር የመጨረሻ አማራጭ እንጂ የመጀመሪያ እርምጃ መሆን የለበትም።
2. ገለልተኛ ምርመራ፡- ጉዳዩን ለማጣራት ከሆስፒታሉ እና ከኮሌጁ አመራር ውጪ የሆነ ገለልተኛ ኮሚቴ (ወይም የክልል ጤና ቢሮ ወይም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን) ተቋቁሞ የአመራሮችን የሥልጣን አላግባብ አጠቃቀም እና የሕግ ጥሰት መመርመር ይኖርበታል።
3. የዲሲፕሊን እርምጃ፡- በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት የሕግ አሰራርን ያጣመሙት ከፍተኛ አመራሮች (Chief Clinical Director, Chief Executive Director) እና የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎች በሥልጣን አላግባብ መጠቀም ክስ ተመስርቶባቸው በሥራ ዲሲፕሊን እንዲቀጡ ማድረግ።
4. የአሠራር ማሻሻያ፡- በተቋሙ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታት ግልጽ የሆነ የውስጥ ቅሬታ አፈታት ሥርዓት መዘርጋት፣ ለክፍል ሐላፊዎች የሥልጣን ሽግግር ማረጋገጥ እና የሠራተኛ ደህንነት መመሪያዎችን ማጠናከር ይገባል።
5. የሥነ-ልቦና ድጋፍ፡- ጥቃት ለደረሰባት እና በሂደቱም አሳልፎ ለተሰጠችው ነርስ የሥነ-ልቦና ድጋፍ እንዲደረግላት መደረግ አለበት።

ማጠቃለያ

በዚህ ጉዳይ ላይ የተፈጸመው ነገር የጤና ተቋማት አስተዳደር ሕግጋትን፣ የሙያ ሥነ-ምግባርን እና የሠራተኛ ደህንነት መመሪያዎችን በግልጽ የሚጥስ ነው። ከፍተኛ አመራሮች ከሥራ ክፍል ሐላፊ ይልቅ አስታማሚውን(ታካሚውን) በማስተናገድ እና በሕግ መንገድ ችግሩን በመፍታት ሳይሆን በግላዊ ትውውቅ እና በስልክ ግንኙነት ውሳኔ በማሳለፍ የተቋሙን ሕጋዊ ሰውነት አጥፍተዋል። ይህ አሰራር ተጠቂዋን ከመጠበቅ ይልቅ አሳልፎ በመስጠት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው።

ስለዚህ ተገቢው መፍትሔ ከላይ እንደተገለጸው ነርሲቱን ከእስር መፍታት፣ አመራሮችን ተጠያቂ ማድረግ እና የተሳሳተውን አሰራር ማስተካከል ነው።

Via Inbox

Obstetric and gynecology graduates of Saint Pauls hospital mellinium medical college class of  2026🎉🎉🎉congratulations
24/03/2026

Obstetric and gynecology graduates of Saint Pauls hospital mellinium medical college class of 2026
🎉🎉🎉congratulations

Anesthesiology, Critical Care and Pain Medicine graduates of bahrdar university 2026
24/03/2026

Anesthesiology, Critical Care and Pain Medicine graduates of bahrdar university 2026

Internal Medicine graduates of Arsi University 2026
24/03/2026

Internal Medicine graduates of Arsi University 2026

23/03/2026

hello hakim mereja
እንዴት ናችሁ??እኛ አለን ጥሎ ማይጥል አምላክ ክብሩ ይስፋ።ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ሠራተኞች የዲውቲ ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት ዛሬ ሥራ ቆሟል።ካቢኔዎች ማስፈራራታቸውን ቀጥለውበታል እባካችሁ ለመላው ለኢትዮጵያ ህዝብ አድርሱልን።በነሱ ምክንያት ታካሚዎች እየተጉላሉ እየሞቱ ነው ሃይ ባይ ጠፈ።

‎በተሳሳተ የብልጽግና ፖሊሲ ምክንያት ታክሞ መዳን እና ህይወትን ማራዘም በሚቻል በሽታዎች ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸው በእየወሩ እየተቀጠፈ ይገኛሉ ‼️‎=============...
23/03/2026

‎በተሳሳተ የብልጽግና ፖሊሲ ምክንያት ታክሞ መዳን እና ህይወትን ማራዘም በሚቻል በሽታዎች ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸው በእየወሩ እየተቀጠፈ ይገኛሉ ‼️
‎===================================
‎በቢሊዮን የሚቆጠር መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ በማድረግ የቅንጦት ሪዞርቶችን እና ሎጅዎችን እየገነባ የሚገኘው አገዛዙ፤ በሌላ በኩል ግን ታካሚዎች በሆስፒታል ኮሪደር፣ ለህክምና ወረፋ እየጠበቁ ባሉበት በቤታቸው ውስጥ ህክምና ሳያገኙ ህይወታቸው እያለፈ ይገኛል።

‎ይህ የሀብት እጥረት ብቻ አይደለም፤ ቅድሚያ የሚሰጠውን ሴክተር አለማወቅ እንጂ። የቅንጦት ሎጅ ወይስ የህዝብ መገልገያ ሆስፒታል ይቅደም የሚለውን አለመለየት ነው።

‎ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለባት አገር ውስጥ፦

‎⛓ አንድ የልብ ቀዶ ህክምና ማዕከል ብቻ ይገኛል፤
‎⛓ የካንሰር ታካሚዎች ለTACE፣ ኬሞቴራፒ እና ሬዲዮቴራፒ ረጅም ጊዜ ወረፋ ይጠብቃሉ፣
‎⛓ የኒዮሮሰርጀሪ (የቅንጭላት ቀዶ-ህክምና) ፤ የኩላሊት ዕጥበት (Dialysis) እና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን ማግኘት ሀገራችን ውስጥ ቅንጦት ሆኖል።
‎⛓ እናቶችና አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት አሁን ድረስ ማከም በሚቻል በሽታ ህይወታቸው ይቀጠፋል።

‎⚙️ ይህ አልፎ አልፎ የሚከሰት ጉዳይ አይደለም፤ የቀን ተቀን የሀገራችን እውነታ እንጂ።

‎ታካሚዎች የሚሰጣቸው ቀጠሮ ረጅም በመሆኑ ምክንያት ለቀጠሮ ቀናቸው ሳይደርሱ ህይወታቸው ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ የሚያልፍ ዜጎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው።

‎በዚህን ጊዜ ግን በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በቅንጦት ፕሮጀክቶች ላይ እየተረጨ ፤የራስ ዜጋን ለመጨፍጨፊያ ድሮንን እና ተተኳሽ ላይ ፈሰስ እየተደረገ ይገኛል።

‎እውነታውን በደንብ ግልፅ ሳደርገው፦
‎🕸 ሪዞርት፦ የሆስፒታል አልጋን አይተካም !
‎🕸 ሎጅ፦ የሕይወት አድን ቀዶ ህክምና አይሰጥም!
‎🕸 የውበት ፕሮጀክት፣ ኮሪደር ልማት ፦ የካንሰር ህክምናን አይተካም!

‎ሕዝብ እየተሰቃየ፣ እየሞተ የሚከናወን ቅንጡ ፕሮጀክት ልማት አይደለም ፤ Ignorance ነው ‼️

‎እኔ ልማትን እየተቃወምኩ አይደለም፤ የተሳሳተ ፖሊሲን Criticized እያደረኩ ነው! ቅድሚያ የሚሰጠውን ችላ በማለት፤ የቅንጦት ፕሮጀክቶችን ማስቀደምን ፤ የርስ በርስ ጦርነት ላይ የሙጥኝ ማለትን እየተቃወምኩ ነው።

‎ሕዝቡ በእየቀኑ በሚድን በሽታ ህይወቱን እያጣ ባለበት ሰዓት የቅንጦት ፕሮጀክቶችን የሚገነባ መንግስት በደንብ መጠየቅ አለበት!

‎Healthcare is not a privilege. It is a right !

‎ህይወትን የሚያድኑ አገልግሎቶች በሰፊው እስኪሰራጩ ፣ Subspecialist & Specialist ሐኪሞች ቁጥራቸው በደንብ እስኪጨምር እና Brain drainage እስኪቀንስ፣ በቀጠሮ ዝርዝር ውስጥ ያሉ ታካሚዎች ቤታቸው መሞታቸው እስኪቆም ድረስ የሚገነቡ ቅንጡ ፕሮጀክቶች በየትኛውም መመዘኛ ምክንያታዊ ሊሆኑ አይችሉም !

©️Dr. Henok Abraham

Address

Addis Ababa

Telephone

+251934647389

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hakim Mereja ሀኪም መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Hakim Mereja ሀኪም መረጃ:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram