ALERT Comprehensive Specialized Hospital

ALERT Comprehensive Specialized Hospital This is the official Facebook account of ALERT Comprehensive Specialized Hospital

በ አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኩላሊት የፊኛ እና ሽንት ቱቦ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር መሀመድ ጀማል ; ስለ ኩላሊት ጠጠር ከ EBC ጋር ቆይታ አድርገዋል። ይከ...
02/02/2026

በ አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኩላሊት የፊኛ እና ሽንት ቱቦ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር መሀመድ ጀማል ; ስለ ኩላሊት ጠጠር ከ EBC ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ይከታተሉ።

Watch 🎥:
https://youtu.be/aIUaeN18pXk?si=2MIIJUpSfbfVkWaK

ከጥር 23–24 ፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ስጋደዌ ቀን በዓለም ለ72ኛ ጊዜ፣ በአገራችን ለ27ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ “የስጋደዌን በሽታ አንዘንጋው” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝ...
02/02/2026

ከጥር 23–24 ፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ስጋደዌ ቀን በዓለም ለ72ኛ ጊዜ፣ በአገራችን ለ27ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ “የስጋደዌን በሽታ አንዘንጋው” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ዋለ።

በዚህ የበዓል አከባበር ላይ የአለርት ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዝግጅቱ ድጋፍ፣ በህክምና አገልግሎት እና ለተጠቂዎች በኢኮኖሚ እርዳታና ማህበራዊ ድጋፍ በማበርከት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጎ ለሌሎች ተቋማት አርአያ መሆኑ ተጠቅሶ ከተሳታፊዎች ከፍተኛ ምስጋና ተቀብሏል።

በተጨማሪም በዝግጅቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የመንግስት ተቋማት፣ የህብረተሰብ አመራሮች እና አጋር ድርጅቶች ተሳትፈው ስለ ስጋደዌ በሽታ ምንነት፣ ቅድመ መከላከል እና ህክምና ጠቃሚ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

አስደሳች ዜና!የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ Smile train  ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር  የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ላለባቸው ሕጻናት እና አዋቂዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና አገ...
02/02/2026

አስደሳች ዜና!

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ Smile train ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ላለባቸው ሕጻናት እና አዋቂዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመደበኛነት ሳምንቱን ሙሉ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?

እንግዲያውስ የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ችግር Cleft lip እና Cleft palate ያለባችሁ በመሉ በ 0948898284 በመደወል ወይም ወደ አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመሔድ መመዝገብ ይችላሉ::

ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ ታካሚዎች የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት እንዲሁም ለሚያድሩት ;የአልጋ (መኝታ ) ወጪ ይሸፈናል፡፡
***
Oduu gammachiisaa!

Hospitaalli ALERT Comprehensive specialized, Smile train Ethiopia waliin ta’uun, daa’immanii fi ga’eessota baqaqa laagaa fi hidhii qabaniif tajaajila baqaqsanii yaaluutiin sirreessuu bilisaan kennaa Jira.

Kanaafuu, yoo namoota rakkoo baqaqa laagaa fi hidhii qabaniif yaala tolaa barbaaddan lakkoofsa bilbilla: 0948898284 irratti bilbiluun ykn Hospitaala ALERT Comprehensive specialized dhaquun tajaajila argachuu ni dandeessu.

Maamiltoota Finfinneen ala dhufaniif kaffaltiin geejjibaa fi nyaataa ni kaffalama, akkasumas warra siree qabatanii buluu isaan barbaachisuuf baasiin siree ni kaffalamaaf.

ቀደም ሲል 8 በመቶ ብቻ የነበረው የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት ድርሻ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ወደ 41 በመቶ ማደጉ ተገለፀ።  ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ; የጤና...
31/01/2026

ቀደም ሲል 8 በመቶ ብቻ የነበረው የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት ድርሻ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ወደ 41 በመቶ ማደጉ ተገለፀ።

ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ; የጤና ሚኒስትር ደኤታ

ዛሬ ጥር 23/2018 ዓ.ም በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማኔጅመንት አባላት፣የአስተዳድር ሰራተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እና የጽዳት ሰራተኞች የተሳተፉበት ሳምንታዊ የጽዳት ዘ...
31/01/2026

ዛሬ ጥር 23/2018 ዓ.ም በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማኔጅመንት አባላት፣የአስተዳድር ሰራተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እና የጽዳት ሰራተኞች የተሳተፉበት ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ መርሃ-ግብር ተካሄዷል!

Today, January 23, 2018, E.C aweekly cleaning campaign program was held at Alert Comprehensive Specialized Hospital, with the participation of management members, administrative staffs, health professionals, and cleaning staffs!
Follow us for more updates:
https://linktr.ee/Alert_Hospital

ሆስፒታሉን የተለያዩ የስዕል ስራዎችን ላሳመሩ አርቲስቶችና የጥበብ ባለሙያዎች የምስጋና ፕሮግራም ተከናወነ!                                                     ...
30/01/2026

ሆስፒታሉን የተለያዩ የስዕል ስራዎችን ላሳመሩ አርቲስቶችና የጥበብ ባለሙያዎች የምስጋና ፕሮግራም ተከናወነ!
አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን በስዕል ስራ ላስጌጡና ላሳመሩ አርቲስቶች ምስጋና አቅርቦላቸዋል፡፡
ሆስፒታሉን በጥበብ ስራዎች ምቹ፣ውብና ማራኪ በማድረግ የሚሰሩ ተግባራትን በቀጣይነት በትኩረት መስራት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጥር 21 እና 22/2018 ዓ.ም  ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተደረገ የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ከ70 ዩኒት ደም በላይ መሰብሰብ ተችሏል፡፡🩸🩸   ...
30/01/2026

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጥር 21 እና 22/2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተደረገ የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ከ70 ዩኒት ደም በላይ መሰብሰብ ተችሏል፡፡🩸🩸
በዚህ የበጎ አድራጎት መርሃ-ግብር ላይ ተሳትፎ ላደረጉ ሰራተኞችና ተገልጋዮች ልባዊ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡
የእርስዎ የደም ልገሳ የወገንዎን ሕይወት ይታደጋል! ❤️

የሀዘን መግለጫ የሆስፒታላችን ባልደረባ የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት መንግስቱ፣ የፋርማሲ ቴክኒሺያን፣ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የሆስ...
29/01/2026

የሀዘን መግለጫ

የሆስፒታላችን ባልደረባ የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት መንግስቱ፣ የፋርማሲ ቴክኒሺያን፣ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የሆስፒታላችን ማህበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጥራትና ኢኖቬሽን ዳይሬክቶሬት የሁለተኛውን ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፅም ግምገማ አካሄደ።በግምገማው ወቅት የሆስፒታሉን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻ...
29/01/2026

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጥራትና ኢኖቬሽን ዳይሬክቶሬት የሁለተኛውን ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፅም ግምገማ አካሄደ።

በግምገማው ወቅት የሆስፒታሉን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል በሁሉም የስራ ክፍሎች ከ30 በላይ የጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች መተግበራቸው፣ የክሊኒካል ኦዲት፣ የአገልግሎት ፕሮሰስ ዲዛይን፣ የታካሚ ደህንነት ክትትል እና ከካችመንት ጤና ተቋማት ጋር የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በቀጣይ ዘመን በጠንካራ ጎኖች ላይ በመቀጠል እና የማሻሻያ መስኮቶችን በመተግበር፣ ሆስፒታሉ በሀገራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን እንዲሁም በእውቅና እና አክሪዲቴሽን ሂደት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚቀጥል ተገልጿል።

The Quality and Innovation Directorate of ALERT Comprehensive Specialized Hospital conducted its second-quarter performance review.

During the review, more than 30 quality improvement projects implemented across all departments were presented and discussed. Key focus areas included clinical audits, service process redesign, patient safety monitoring, and collaborative activities with catchment health centers and hospitals.

The Directorate reaffirmed its commitment to strengthening service quality and positioning the hospital as a nationally and internationally competitive center of excellence, with particular emphasis on accreditation and institutional recognition.

🩸 የደም ልገሳ ተሳትፎ በአለርት ሆስፒታል!🩸ዛሬ ጥር 21/2018 ዓ.ም በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የደም ልገሳ ስራ ከ40 ዩኒት ደም በላይ ሰብስበናል።❤️ የእርስዎ ደም ...
29/01/2026

🩸 የደም ልገሳ ተሳትፎ በአለርት ሆስፒታል!🩸

ዛሬ ጥር 21/2018 ዓ.ም በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የደም ልገሳ ስራ ከ40 ዩኒት ደም በላይ ሰብስበናል።

❤️ የእርስዎ ደም ስጦታ የሌላው ሕይወት ነው!

🙌 ይሳተፉ እና ከእኛ ጋር ሕይወት ይስጡ።

🩸 Blood Donation campaign at ALERT Hospital! 🩸

Today, over 40 units of blood were collected at ALERT Comprehensive Specialized Hospital.

❤️ Your blood donation could be someone else’s hope for life!

🙌 Join us and help save lives today!

አለርት ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሲቢኤም ኢንተርናሽናል ዋና ስራ አስፈፃሚ በሆኑት ፕ/ር ራይንን ተጎብኘጉብኝቱ በአለርት ሆስፒታል ውስጥ በሲ ቢ ኤም ፕሮጀክት የተገነቡ እንደ ኦፕ...
29/01/2026

አለርት ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሲቢኤም ኢንተርናሽናል ዋና ስራ አስፈፃሚ በሆኑት ፕ/ር ራይንን ተጎብኘ

ጉብኝቱ በአለርት ሆስፒታል ውስጥ በሲ ቢ ኤም ፕሮጀክት የተገነቡ እንደ ኦፕቲካል ወርክሾፕ፣ በቅርቡ ተመርቆ ስራ የጀመረውን የ ህፃናት የአይን ህክምናን ላይ ያተኮረ ሲሆን በወቅቱም ከሆስፒታሉ ከፍተኛ አመራሮች እና በሲ ቢ ኤም ስፖስንሰርነት ከተማሩ የአይን ሐኪሞች ጋር ውጤታማ ውይይት ተደርጓል።

ጉብኝቱ ጥራቱን የጠበቀ የዓይን ህክምና አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና ተደራሽነት ለማስፋት በ አለርት ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በ ሲቢኤም ኢንተርናሽናል መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት እንደገና አረጋግጧል።

ALERT Comprehensive Specialized Hospital hosted Prof. Rainer Brockhaus, CEO of CBM, during his visit on 27 January 2026. The visit included discussions with hospital leadership, a tour of the Pediatric Eye Unit, and visits to the Optical Workshop and Optical Shop, showcasing inclusive service delivery and employment initiatives. Prof. Rainer also engaged with ophthalmologists trained through CBM-supported sub-specialty programs.

The visit reaffirmed the strong partnership between ALERT Hospital and CBM in advancing quality and inclusive eye care services.

Address

Kolfe Keranyo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ALERT Comprehensive Specialized Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category