
07/11/2020
የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ (ኢ.መ.ፋ.) አ .ማ ማህበራዊ ግዴታውን በመወጣት
የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ (ኢ.መ.ፋ) ግንባር ቀደም የመድሃኒት አምራች በመሆን ላለፉት 56 አመታት የህብረተሰቡን የመድሃኒት ፍላጎት ለሟሟላት በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡
ፋብሪካችን ማህበራዊ ግዴታውን ለመወጣት ለገጠሩ ህዝባችን የውሃ ጉድጓድ በማስቆፈር፣ ለኦቲዝም ማዕከላት ቋሚ በጀት በመመደብ ፣ለተወሰኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በቋሚነት የምሳ ምገባ በማድረግና ሌሎች የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ጉልህ አስተዋፆ እያደረገ ይገኛል፡፡
ኮቪድ -19 ን በመካላከል የኢ.መ.ፋ አስተዋፆ
በአሁኑ ወቅትም በአገራችን ብሎም በ ዓለማችን ላይ እጅግ አሳሳቢ በሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ላይ ሁሌም ለ ማህበረሰቡን ችግር ፈጣን ምላሽ በመስጠት የሚታወቀው የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚጠቅም የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ከኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መ/ቤት ፈቃድ በማግኘት የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት(WHO recommended Alcohol Based hand rub solution -sanitizer ) በማምረት ለገበያ አውሏል፡፡
የምርቱ አመራረት የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መመሪያ (Guide to Local Production: WHO-recommended Handrub Formulations) መሰረት ሲሆን በውስጡ • Ethanol 80% (v/v), • Glycerol 1.45% (v/v), • Hydrogen peroxide 0.125% D.water q.s የያዘ ሲሆን በምርት ሂደት ላይ እያለ የጥራት ማረጋገጫ ምርመራዎች የተደረጉለትና መስፈርቶቹን ያሟላ ቢሆንም በገለልተኛና በሶስተኛ አካል (National Conformity Assessment) በተደረገ የጥራት ማረጋገጫ ምርመራም ሙሉበሙሉ መስፈርቶቹን ያሟላ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
የአ.መ.ፋ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር በማምረት ያለበትን ሃገራዊ እና ማኅበራዊ ሃላፊነት እየተወጣ ከመሆኑም በተጨማሪ ከሚመረተው ምርትም እስከ 20% የሚሆነውን ለበጎ አድራጎት ተግባር እያዋለ ይገኛል፡፡ ድጋፍ ከተደረገላቸው ውስጥም ለአብነት የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ለአረጋውያን እና ለአእምሮ ህሙማን መንከባከቢያዎች (መቄዶንያ ፣ ለጌርጌሶን ፣ለስሊዮንየ አረጋውያን ለአእምሮ ህሙማን መንከባከቢያ)
ለኦቲዝም ማዕከላት
ለአካል ጉዳተኞች ማዕከላት
ለፌዴራል ፖሊስና ለሌሎችም ፖሊስ ጣቢያዎች
ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም
ለማረምያ ቤቶች (ለቃሊቲ፤ ለቂሊንጦ እና ሌሎችም) እና
ለሰላም ሚኒስቴር እና ሌሎችም
በተጨማሪም ለCOVID-19 ብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በጥሬ ገንዘብ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ዕርዳታ አድርጓል፡፡
እንደሚታወቀው በአሁኑ ወቅት ኮቪድ-19 ባስከተለው ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ምክንያት ብዙ ድርጅቶች ጫና ውስጥ ገብተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ (ኢ.መ.ፋ) ይህንን ጫና በመቋቋም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያደርሰውን የኑሮ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሰራተኞቹ የ 1000 ብር አና ለበዓል የሚሆን 700ብር በመስጠት ሰራተኞቹን ደጉሟል ፡፡
የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ (ኢ.መ.ፋ) የሚያደርገውን ድጋፍ በመቀጠል ከቶታል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ብዛቱ ከ90 ሺ በላይ ባለ 500ሚሊ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር በማምረት በእርዳታ መልክ ለማበርከት በዚህ ሳምንት ለማስረከብ ዝግጁነቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ለወደፊቱም ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በቀጣይም የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች (Surgical Face Mask) አምርቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል ፡፡