Umma' Clinic

Umma' Clinic Quality Diagnostic and Therapy Service , Integrity, Empathy, and Teamwork is our Difference

የፀሐይ ግርዶሽ እና ዓይናችን(ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው ፤ የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት)በሰኔ 14, 2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ ...
19/06/2020

የፀሐይ ግርዶሽ እና ዓይናችን

(ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው ፤ የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት)

በሰኔ 14, 2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ግርዶሹን ለማየት ሲባል ቀጥታ ወደ ፀሐይ ማየት ስለሚያስከትለው ጕዳትና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማብራሪያ ለመስጠት እሞክራለሁ።
በፀሐይ ጨረር የሚመጣ የሬቲና (የብርሃን መቀበያ) ጉዳት በእንግሊዝኛ, solar retinopathy, photic retinopathy, foveomacular retinitis, solar retinitis, and eclipse retinopathy ይባላል።

ይኽ ጉዳት የሚከሰተው በቀጥታ ፀሐይን ወይም የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ሲሞከር የሚከሰት ችግር ሲሆን የብርሃን መቀበያችን (ሬቲና) ላይ ጉዳት በማድረስ ዕይታችንን ይቀንሳል፡፡ ጨረሩን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደ ቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። የዚህ ችግር ዋና መንስዔ ከፀሐይ የሚወጣው ጨረር ቢሆንም በብረት ብየዳ ጊዜ ከሚወጣ ጨረር ፣ ከትክክለኛው ኃይል በላይ የሚለቀቁ ሌሎች የብርሃንና የሌዘር ምንጮችም ሊከሰት ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለ ሐምራዊ-ለ Ultraviolet-B ) በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።

🔹አጋላጭ ሁኔታዎች፡-

- ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ፡፡
- ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡

- ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡
- የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡

- ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- ነጮች ከጥቁሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- በብየዳ ጊዜ ተገቢውን መነጽርና የፊት ጋሻ አለመጠቀም ለተመሳሳይ ጉዳት ይደርጋል።

🔹ምልክቶቹ፦

በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በሁለቱም ዓይን ላይ፦
- የዕይታ መቀነስ
- በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ
- የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል)
- በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡

ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በማይክሮስኮፕ በማየት ወይም ሬቲናውን ፎቶ በማንሳት ወይም OCT በሚባል መሳሪያ በማየት ችግሩ መከሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

🔹ህክምናው፦

ምንም እንኳን ይህን ችግር ለማከም የተለያዩ መድኃኒቶች (ስቴሮይድን ጨምሮ) ቢሞክሩም አጥጋቢ ውጤት አላመጡም፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ነገር ችግሩ እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል ነው ።

🔹መከላከያ መንገዶች፦

⛔ ፀሐይን ፣ ፀሐይ ግርዶሽን ፣ የብየዳ ጨረርና ሌሎች ኃይለኛ ብርሃን የሚረጩ ነገሮችን በቀጥታ አለማየት ፣
በፀሐይ ግርዶሽ በዓመታት አንዴ የሚታይ በመሆኑና ብርሃኑም የቀነሰ ስለሚመስለን ለማየት ሊያጓጓን ይችላል... ሆኖም በፍጹም በቀጥታ ማየት የለብንም።

⚠️ ህጻናት፣ የአዕምሮ ህመምና ውስንነት ያለባቸውን ሰዎች ወደ ፀሐይ እንዳያዩ መከላከል ፣ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ መርዳት
✅ የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ዓላማ የተሰሩ ISO እና CE ሰርቲፊኬት ያላቸው ልዕለሐምራዊ (UV) ንዑሰ - ቀይ (Infrared) ጨረሮችን 99 - 1ዐዐ% የሚከላከሉ ጥቁረታቸው (shade no 12) የሆኑ መነጽሮችን ብቻ መጠቀም ይቻላል። ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት መነጽሮች በሀገራችን ስለመግባታቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቱሪስቶች ወደ እኛ ሀገር ሲመጡ ይዘው ይመጡ ይሆናል፡፡

🔹የተለመዱትን የፀሐይ መነጽሮች ማድረግ ይቻላል?

❌ በፍጹም! ምንም እንኳን የፀሐይ መነጽሮች ጐጂ ጨረሮችን መቀነስ ቢችሉም በቀጥታ ወደ ፀሐይ ለማየት ተብሎ ስላልተሰሩ ተጨማሪ ጨረሮችን ወደ ዓይን ያስተላልፋሉና በፍጹም እነዚህን መነጽሮች ተማምነው ወደ ፀሐይ/ ፀሐይ ግርዶሽ ማየት የለብዎትም፡፡ ጥቁር መነጽር መሆኑ ብቻ ጨረሮቹን ይከላከላል ማለት አይደለም።

ጥላሸት የተቀባ መነጽር፣ የራጅ ፊልም፣ የተለመደ የፀሐይ መነጽር፣ ካሜራዎች ወዘተ የሚታዩ የብርሃን ጨረሮችን ቢቀንሱም አደገኛ የሆኑትን ልዕለሐምራዊና ንዑስቀይ ጨረሮችን መከላከል አቅም ስለሌላቸው በነሱ መተማመን አይገባም፡፡

መንግስት ይኽን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መነጽሮች እንዳይሸጡ ቁጥጥር ማድረግ ይገባዋል።

30/05/2020

There is already a community spread. Consider everyone potentially infectious! I want to emphasize this point, because this was the mistake we made here. Once there is an established community spread, don’t fool yourself into thinking that COVID-19 patients will only have cough/fever or other symptoms.
Stay safe my dear colleagues and God be with you!

Stay home,safe live
17/04/2020

Stay home,safe live

17/04/2020
"የኮሮና ጠባሳ!"የሰው ልጅ ሳንባ በአማካይ 500 ሚለየን የሚሆኑ ትናንሽ አየር መሳቢያ ፊኛ (alveoli) አሉት ::  የነዚህ ፊኛዎች ጤና የምንስበውን የአየር ብሎም የምናገኘውን ኦክስጂን...
15/04/2020

"የኮሮና ጠባሳ!"
የሰው ልጅ ሳንባ በአማካይ 500 ሚለየን የሚሆኑ ትናንሽ አየር መሳቢያ ፊኛ (alveoli) አሉት :: የነዚህ ፊኛዎች ጤና የምንስበውን የአየር ብሎም የምናገኘውን ኦክስጂን መጠን (gas exchange) ይወስነዋል:: አየር ወደ ውስጥ ስንስብ እኚህ ፊኛዎች እስከሚለጠጡ ይሞላሉ፡፡ ከነዚሀ ፊኛዎች ጀርባ የሚገኝ ቀጭን የደም ስር (perialveolar capillary) የአየር ፊኛዎቹ ሲሞሉ (ሲለጠጡ) በግድግዳቸው ላይ አምልጦ (diffusion) የሚተንለትን አክሲጅን ተቀብሎ ወደ ሰውነት ይገባል... እግረ መንገዱንም የያዘውን የተቃጠለ ጋዝ (CO2) ወደ አየር ፊኛ ያተናል፡፡ በዚህ ሒደት አክሲጂን አገኘን ህይወትም ቀጠለች ማለት ነው፡፡
በሰው ልጅ ተፈጥሮ በአየር ፊኛ (alveoli) እና ኦክሲጂን ተቀብሎ በሚወስደው የደም ስር (Capillary) መካከል ያለው ግድግዳ እጅግ እጅግ ሲበዛ ቀጭን ነው፡፡ ኦክስጂን ወደ ሰውነት መግባትም ሆነ ጒጂ የሆነ ጋዝ መውጣት (gas exchange) ሊካሔድ የሚችለው ቅጥነቱ እንደተጠበቀ ከኖረ ብቻ ነው። ከወፈረ እንደ መታነቅ ቁጠሩት!
የኮሮና በሽታ ሲከፋ ( Severe form) ይህ ወሳኝ አካባቢ በሰውነት መከላከያ ይደበደባል። በጥቃቱም የአየር ፊኛውም ሆነ የደም ስሩ ግድግዳ ይቆስላል(Collateral damage) ፡፡ የአየር ፊኛው ጀርባ ያለው የደም ስሩ ግድግዳ ስለሚቀደድ በደምስሩ ውስጥ የነበረው ፈሳሽ እና ፕሮቲን (plasma protein) ደምስሩን ለቆ ይፈሳል... የአየር ፊኛው በፈሳሽ ይጥለቀለቃል (proteinaceous excudates in alveolar space) :: አካባቢው በፈሳሽ, በሞቱ ወታደሮች እና በቆሻሻ ይሞላል፡፡ የፈነዳውን የአየር ፊኛም ለመድፈን በሚደረገው የጥገና ስራ በጠባሳ ይሞላል (pneumocyte hyperplasia)፡፡ ጠባሳው ወፍራም ስለሚሆን ቀዳዳው ቢጠገንም ግድግዳዉ ኦክስጅን አያሳለፍም ወይም በቀላል ቋንቋ ስስ የነበረው ፊኛ የዘይት ጀሪካን ሆነ ማለት ነው። አይለጠጥም.... አየር ብንስብበት እንኳ አክሲጂን አያሳልፍም ...ዋጋ የለውም፡፡ በዚህም አየር ማስተላለፍ ኖሮበት የማያስተላልፍ ሰነፍ ክፍል በሳንባችን ይጨምራል (rise in physiologic dead space)፡፡ የዚሀ አይነት ሳንባ ክፍል እንደሞተ ይቆጠራል። ሰውነት እና የአየር ፊኛው .እንደተለያዩ ይቀራሉ!

ሰውየው ከኮሮና ከዳነ የተረፈ ቢመስልም ካሉት 500 ሚሊየን አየር መሳቢያ ፊኛ (alveoli) ውስጥ ምናልባት 300 ሚለየን ገብሮ ሞተውበት ሊሆን ይችላል ...ቀሪ ህይወቱን በ200 ሚለየን ፊኛ ይጋፈጣል እንደማለት ነው። በሌላ ቋንቋ ስድስት ሲለንደር መኪናን ባለ ሁለት ቢደረግ ችግሩ ምን ይሆናል ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ...V8 ወደ ላዳነት ቢቀየር ለውጡ የሚታወቀው ዳገት ላይ ሊሆን ይችላል ...መዳኑ ያለ ኪሳራ አይደለም፡፡ የእድሜ ልክ ችግር ጥሎ የሚሔድ በሽታ ነው።
ሌላ ጊዜ ኮሮና ኩላሊትን እንዴት እንዳሚጐዳ እነግራችራዋለሁ::
የዚህ ፅሁፍ የተፃፈበት አላማ የባህሪ ለውጥን ለማፋጠን ነው .... According to cognitive behavior change model... አንዳንድ ሰዎች የሚጠነቀቁት ነገሩን በትክክል ካወቁት/ከ ተረዱት ብቻ ነው...በተፈጥሮ በቀላሉ አያምኑምና፡፡ እናም በዚህ መረጃ ተመርቶ ራሱን ለመጠበቅ የሚወስን አይጠፋም ብየ ተስፋ አደርጋሁ፡፡
ከኮኖና ራስዎን ቤተሰብዎን አገርዎን ይጠብቁ!
Dr. Kalkidan Hassen, Associate Professor Jimma University.

08/04/2020

የኖቬል ኮሮና ህመም
ታሪክ
ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሮና የተገኘው በ1937 ሲሆን ሰዎችን እንደሚያጠቃ የታወቀው ግን እአአ በ1960 መጨረሻ መሆኑ በታሪክ ይታወሳል። በ1970ዎቹ አካባቢ ደግሞ ስለ ኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች እና ስያሜ በደንብ የታወቀበተ ወቅት እና ሰፊ ጥናት የተደረገበት ጊዜ ነበር።
ሥያሜ
ኮሮና ማለት ከላቲን የተወረሰ ቃል ሲሆን ዘውድ ማለት ነው። ምክንያቱም በረቂቅ አጉይ መነፅር ሲታይ ክብ የሉል ቅርፅ ያለው ዙሪያውን ጥቃቅን ዘውድ የሚመስሉ ነገሮች ስላሉበት ነው። mid 6th century n corona : from Latin, ‘wreath, crown’.
ዝርያ
ኮሮና ቫይረስ ብዙ አይነት ዝርያዎች አሉት ። በግሪክ ፊደላት ዐልፋ ፡ ቤታ ፡ ጋማ እና ዴልታ የተመደቡ ዓይነቶች ሲኖሩ በብዛት በቀላል ጉንፋን አምጭነታቸው ይተወቃሉ። አስከፊ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች በቤታ ክፍል የሚመደቡ ሲሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ወረርሽኝ በማምጣት የሚታወቁት ኮሮና ቫይረሶች
የተቀሰቀሱበት ሀገር ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ይመስላል ፡
1 ፡ ሳርስ (SARS) 2003 እአአ ቻይና ፣
2 ፡ መርስ {MERS) 2012 እአአ ሳውዲ አረቢያ
3 ፡ ሳርስ 2 (COVID-19 ) 2019 እአአ ቻይና
ኮሮና ቫይረስ ብዙ እንስሳትን በተለይም የአጥቢ ዝርያዎችን፣ አእዋፋት እና ሰውን ጨምሮ ያጠቃል። በብዛት የሚታወቀው የሰው ጉንፋን አምጪ ኮሮና አብሮን የኖረ ሲሆን የከፋ የጤና እክል የማያስከትል ነው።
የከፋ የኮሮና ወረርሽኝ አምጪ ቫይረስ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፈው ከአጥቢ እንስሳት ጋር በተያያዘ ንክኪ (በተለይም የሌሊት ወፍ ) እና ጥሬ ስጋቸውን በመብላት መሆኑ ይታመናል። ቫይረሱ ራሱን መለዋወጥ እና እንደገና ማዋሃድ ስለሚችል በቀላሉ ከእንስሳት ወደ ሰው ይተላለፋል።
የበሽታው መነሻ ሂደትና የህመም ምልክቶች
መነሻ
ክፉ እና አጣዳፊ የመተንፈሻ ህመም 2
በሳርስ ኮሮና ቫይረስ 2 (SARS 2 COVID-19) ምክንያት የሚከሰት የሳንባ ህመም ሲሆን ከአጥቢ እንስሳት ወደ ሰው በውሀን ቻይና መተላለፍ ጀመረ በመቀጠልም ከሰው መደ ሰው መተላለፍ ቀጠለ። ከዚያም ህመሙ ያለበት ሰው በሚያስል፣ በሚያስነጠስ ወይም በሚያወራ ሰዓት በሚፈጠሩ ውሃ አዘል ብናኞች ( aerosols) ወደ ሌላ ሰው አፍ፣ አፍንጫ፣ እና አይን ይገባል ከዚያም የቫይረሱ ተቀበይ ህዋሳት ባሉበት ከላይኛው ወደ ታችኛው የአየር መተላለፊያ ቱቦ ይወርድና በመጨረሻም የሳንባ የአየር ማጣሪያ ክፍልን ማጥቃት ይጀመራል።
ለኮሮና የሚጠቁ የሰውነት ክፍሎች
1 ፡ የመተንፈሻ አካላት
2 ፡ አንጀት እና ጉበት
3 ፡ የደም ስሮች
4 ፡ ኩላሊት
5 ፡ ስርዓተ ነርቭ
የበሽታው ምልክቶች መታየት የሚጀምሩበት ጊዜ

የኮሮና ህመም ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ከህመምተኛ ጋር ከተደረገ ንክኪ በኋላ ከ2 እስከ 14 ባሉት ቀናት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ እስክ 21 ቀናት ሊዘገዩ ይችላል። በአብዛኛው እስከ 5- 8 ቀን ድረስ ምልክት ማሳየት የጀምራሉ።
በብዛት የሚታዩ የህመም ምልክቶች
1 ፡ ከፍተኛ ትኩሳት 58% (አወቂ ላይ 81%)
2 ፡ ደረቅ ሳል 54% (አወቂ ላይ71%)
3 ፡ የትንፋሽ ማጠር 13% (አወቂ ላይ43%)
4 ፡ የድካም ስሜት ፡ የሰውነት መዛል
5 ፡ የሆድ ህመም
ብዙ ሕፃናት የህመም ምልክት አያሳዩም ምልክት ያለባቸውም ቢሆን መጠነኛ የሆነ የበሽታው ስሜት ይኖራቸዋል እንጂ አስጊ ምልክቶችን አያሳዩም። ሁሉም በሚያስብል ደረጃ ሕፃናት መታመማቸው የሚታወቀው በህመሙ የተጠቃ ቤተሰብ ሲኖር በጥርጣሬ የላቦራቶሪ ምርመራ ሲደረግላቸው ነው።
ለኮሮና በጣም ተጋላጭ እና ህመሙ የሚፀናባቸው ሕፃናት የትኞቹ ናቸው?
1 ፡ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት
2 ፡ የቆየ የልብ ፣ የሳንባ እና የስኳር ህመም ያለባቸው ሕፃናት
3 ፡ በሽታን የመከላከል አቅማቸው የቀነሰ ህፃናት
4 ፡ በምግብ እጥረት የተጎዱ
5 ፡ የካንሰር ታማሚዎች
ህፃናት ላይ የህመም ምልክቶች ለምን ቀለል ይላሉ?
1 ፡ ሕፃናት በዓመት ውስጥ ቢያንስ ከ4-6 ጊዜ በጉንፋን ይያዛሉ ከጉንፋን ቫይረሶቸ ውስጥ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ይገኙበታል ይህም ከኖቬል ኮሮና ቫይረስ በጥቂቱም ቢሆንም በሽታ የመከላከያ አቅም ይፈጥርላቸዋል።
2 ፡ ሕፃናት የኮሮና ቫይረስን የሚያከስሙ ንጥረ ቅመሞች በብዛት ስለሚያመርቱ።
3 ፡ ህፃናት በአየር ያልተበከለ እና ጠባሳ የሌለበት በሽታን የሚቋቋም የመተንፈሻ አካል ስላላቸው።
4 ፡ ንቁ የሆነ የበሽታን የመከላከያ ክፍል ስላላቸው።
5 ፡ የቆዩ እና ተጓዳኝ የጤና ችግሮች በህፃናት ላይ አለመብዛታቸው። ☺️
የላቦራቶሪ ምርመራ
1 ፡ ከአፍንጫ፣ ከአፍ እና ከመተንፈሻ አካላት ላይ ተጠርጎ የሚወስድ ፈሳሽ እና የአክታ ምርመራ
3 ፡ የራጅ ምርመራ
4 ፡ የሲቲ ስካን ምርመራ
5 ፡ እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ምርመራ ሊደረግ ይችላል።
የኮሮና በሽታ ህክምና
ክትባት ወይም መድሃኒት የለውም ግን አንደ ህመሙ ቅለት እና ክብደት የሚሰጥ የህክምና አርዳታ አለ።
80% የሚሆኑት ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፋ ከሰው መለየት ጓንት እና ጭንብል መጠቀም እና የከፋ የህመም ምልክት እስካላሳዩ ድረስ ረፍት ማድረግ ብቻ በቂ ነው።
ተዛማጅ ለሆኑ የጤና እክሎች ህክምና ይደረጋል። የሙቀት መቀነሻ የኦክስጅን እርዳታ እና የመተንፈሻ አካላቸው ለተጎዱ ጽኑ ሕሙማን ሳንባን የሚያግዝ ወይም የሳንባን ስራ ተክቶ የሚሰራ ማሽን ያስፈልጋል።
በየእለቱ የሚያስፈልገውን ምግብ እና የጎደለ /የሚያስፈል ፈሳሽ መተካት።
የፀረ ተዋህስያን መድሃኒት።
ሞት
የህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመሞት እድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911004364

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Umma' Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Umma' Clinic:

Share