08/11/2025
🚨የጥርስ ብሩሽዎን በየስንት ጊዜ መቀየር አለብዎት?
🦷💦ጥርሶዎን መቦረሽ የአፍ ጤናዎን ለማሻሻል ፣ ጥርስ ላይ የሚኖር ቆሻሻን ለማስወገድ እንዲሁም ለድድ በሽታዎች የመጋለጥ እድሎን ለመቀነስ የሚረዳ ወሳኝ መንገድ ነው።
🦠🩸ነገር ግን የጥርስ ብሩሽ በየጊዜው ካልተቀየረ በባክቴሪያ፣ በቆሻሻ፣ በደም እና በምራቅ ሊበከል ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ የጥርስ ብሩሽዎ ሳይቀየር በቆየ ቁጥር ብሩሾቹ መበታተን ስለሚጀምሩ ጥርስ ላይ የተለጠፉ ቆሻሻዎችን በአግባቡ ማስወገድ አይችልም። ስለዚህ የጥርስ ብሩሽዎን ውጤታማነት ለመጨመር በወቅቱ መቀየር አስፈላጊ ነው።
🌍የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል (CDC) እና የአሜሪካ የጥርስ ሕክምና ማህበር (American Dental Association) እንደሚመክሩት የጥርስ ብሩሽዎን ቢያንስ በየሶስት ወይም በየአራት ወሩ መቀየር ይኖርቦታል። የጥርስ ብሩሾቹ መበላሸት እና ጥርስን የማጽዳት አቅማቸው መቀነስ የሚጀምረው በእነዚህ ጊዜያት ስለሆነ።
👉👉ነገር ግን የሚከተሉት ሁኔታዎች ካጋጠምዎ ቀደም ብለው መቀየር ይኖርቦታል
🪥የጥርስ ብሩሽዎ የተጎዳ ወይም የተበላሸ ከመሰልዎት
🤧ታመው ከነበሩ
🚽የጥርስ ብሩሽዎ ለመበከል አደጋ ከተጋለጠ ለምሳሌ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ከወደቀ፣ በቦርሳዎ ውስጥ ተከፍቶ ከተቀመጠ፣ የቤት እንስሳት ጋር ንክኪ ከነበረው ወይም ለረጅም ጊዜ በዕቃው ውስጥ ችላ ተብሎ ከቆየ
🦷ከቦረሹ በኋላ ጥርስዎ እንደጸዳ የማይሰሞት ከሆነ
🪥ለመጨረሻ ጊዜ የጥርስ ብሩሽዎን የቀየሩበት ጊዜ መቼ እንደሆነ የማያስታውሱ ከሆነ
👃🏼ሽታ ማምጣት ከጀመረ
🦠እንዲሁም የቀለም መቀየር ካመጣ የጥርስ ቡርሽዎን መቀየር ይኖርቦታል።
📱የ WeCareET የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ስመጥር የጥርስ ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ቢያሻዎት በቪዲዮ ፣ በስልክ ወይም በፅሁፍ መልዕክት ስለ እርሶ እና ስለ ወዳጆ ጤና ይመካከሩ !!!
መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ እና ይሞክሩት ።
👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
👨🏽⚕️👩⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።
#9394