Doc Book

Doc Book � Writer only

የደመወዛችሁን 6% ለጤና መድን ትከፍላላችሁ!ይህ ማለት ሙያችሁን በደመወዛችሁ 6% ትገዛላችሁ🤔🤔🤔ቆይ ባለፈዉ እኔ ነኝ የባረቀብኝ  ወይስ MOH ነዉ???     🤔🤔🤔🤔
18/10/2025

የደመወዛችሁን 6% ለጤና መድን ትከፍላላችሁ!
ይህ ማለት ሙያችሁን በደመወዛችሁ 6% ትገዛላችሁ🤔🤔🤔

ቆይ ባለፈዉ እኔ ነኝ የባረቀብኝ ወይስ MOH ነዉ???
🤔🤔🤔🤔

" የወላዷን ስቃይ ሳይ ግን አልቻልኩም፣ በጣም ደከመኝ እንባዋን ሳይ እኔም ባለሁበት ቁጭ ብየ አለቀስኩ ፤ የእኔ ማልቀስ ግን ህፃኑን ማትረፍ አልቻለም፣ በዚህም በጣም አዝኛለሁ " - የአምቡ...
17/10/2025

" የወላዷን ስቃይ ሳይ ግን አልቻልኩም፣ በጣም ደከመኝ እንባዋን ሳይ እኔም ባለሁበት ቁጭ ብየ አለቀስኩ ፤ የእኔ ማልቀስ ግን ህፃኑን ማትረፍ አልቻለም፣ በዚህም በጣም አዝኛለሁ " - የአምቡላንስ ሹፌር

በጎፋ ዞን መሎ ጋዳ አካባቢ አንድ የአምቡላንስ ሹፌር አንዲት ወላድ እናትን ወደ ሆስፒታል ይዞ ሲጓዝ አምቡላንሷ በጭቃ ተውጣ እና ሹፌሩ መኪናዋን ለማውጣት የቻለውን በሙሉ አድርጎ ሲያቅተው በጭቃው ላይ ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ የሚያሳይ ምስል በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ላይ ተዘዋውሮ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንን የአምቡላንስ ሹፌር በስልክ አግኝቶ ስለተፈጠረው ነገር አነጋግሯል።

ይህ ሹፌር ሀብታሙ ደርጉ ደረሰ ይባላል።

ሹፌር ሀብታሙ ደርጉ ደረሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

" ችግሩ የተፈጠረው ከመሎ ጋዳ ወረዳ አንዲት ወላድ እናት በወሊድ ምክንያት ሪፈር ተጽፎላት ወደ ጎፋ ዞን ሆስፒታል ይዤ እየሄድኩ እያለ ልዩ ስሙ ጃውላ መንገድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8 ስአት ላይ ነው።

ከወላዷ ጋር የነበሩ ሰዎች ከእኔ ጋር በመሆን መኪናዋን ከጭቃው ለማውጣት እየታገልን እያለ ወላዷ በዚሁ ቦታ ላይ ወለደች፣ የሚያሳዝነው ግን የተወለደው ህጻን ሞቷል።

በመቀጠልም ስለተፈጠረው ነገር ለሃላፊዬ ደወልኩና ነገርኩት፣ እናትየዋ የደም ካንሰር ስላለባት በህይወት ለመቆየት ወደ ሆስፒታል መድረስ አለባት አልኩት። ከዛም ከቡልቄ ወረዳ ሌላ አምብላንስ መጥቶ እናትየዋን እንድወስዳት ተደረገ።

ይህ ነገር ከመሆኑ በፊት ግን እናትየዋን እና ህፃኑን በህይወት ለማዳን የግድ አምብላንሷን ከጭቃው ማላቀቅ ስለነበረብኝ ብዙ ስቆፍር ነበር። ነገር ግን አልሆነም፣ እኔም በዚያ ብርድ ላይ ስቆፍር አድሬ ሰኞ እለት ጠዋት 2:30 አካባቢ ላይ ወደ ጋዳ ተመልስኩ።

በሰአቱ የተሰማኝ ስሜት ከባድ ነው፣ ቆፍሬ፣ ቆፍሬ ሲደክመኝ በአካባቢው ያሉ ሰዎች እንዲረዱን አምቡላንሷን ሳስጮሀት ነበር። ግን መጀመሪያ ላይ ማንም አልመጣልንም። አብረውኝ የህክምና ባለሙያን ጨምሮ የወላዷ ባለቤት እና አማቿ ነበሩ።

በሰአቱ የወላዷን ስቃይ ሳይ አልቻልኩም፣ በጣም ደከመኝ፣ እንባዋን ሳይ እኔም ባለሁበት ቁጭ ብየ አለቀስኩ ፤ የእኔ ማልቀስ ግን ህፃኑን ማትረፍ አልቻለም፣ በዚህም በጣም አዝኛለሁ።

በህይወት የሌለ ልጅ የወለደችው እናት በስአቱ በጣም ደክሟት ነበር፣ ምክንያቱም የደም ካንሰር አለባት። ሌለኛው አምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ወስዶ ካደረሳት በሗላ ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎላታል፣ ነገር ግን ለህክምናው የተጠየቀችው ገንዘብ ወደ 800 ሺህ ብር ስለሆነ ገና እርዳታ እያሰባሰብን ነው።

በአምቡላንስ ሹፍርና እያገለገልኩ ሁለት አመት ቆይቻለሁ፣ ብዙ ጊዜም ተመሳሳይ ችግር ይገጥመኛል፣ ሁለት እና ሶስት ቀን መንገድ ላይ የማድርባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ። በተደጋጋሚ የእናቶችን ከፍተኛ የሆነ ሲቃይ አይቻለሁ። በዚህኛው ግን በጣም ተስፋ ቆርጨ ከዚህ በሗላ መኪና ላለማሽከርከር አስቤ ነበር። በፌስቡክ የእኔን ምስል ብዙዎች ሲቀባበሉት ስመለከት እና ብዙዎች ለእናቶች ያላቸውን ፍቅር ሲገልፁ ሳይ ግን በጣም ደስ ብሎኛል።

ሁሌም በመንገድ ጉዳይ እንደተሰቃየን ነው፣ ችግሩ ጫፍ የወጣ ነው። የእናቶችን እና የህፃናቶችን ሞት ለማቆም ሁሉም ሰው ለመሎ ጋዳ መንገድ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል " ሲል ተናግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

painful story 🥲🥲🥲🥲

17/10/2025

ጥቅምት ወር/October የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው!

ለጡት ካንሰር ተጋላጭ የሚያደርጉ/ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች

🎀 (ከ50 አመት በላይ መሆን)
🎀የተቀየረ ጂን ከቤተሰብ መውረስ
🎀BRCA1እና BRCA2 የሚባሉ ጂኖች)
🎀 የወር አበባ ጊዜ:የመጀመርያ የወር አበባ ከ12 አመት በታች ማየት እና የወር አበባ የቆመበት ጊዜ ከ55 አመት በኋላ መሆን
🎀 አባላት ውስት የጡት ወይም የማህፀን እና ዘር ፍሬ ካንሰር ታሪክ መኖር
🎀 ህክምና (radiation therapy)
🎀ከልክ ያለፈ ውፍረት
🎀ኦስትሮጅንእና ፕሮጀስተሮን የተባሉ ሆርሞኖች የያዙ መድሃኒቶችን መውሰድ(ብዙ ጊዜ ከወሊድ መከላከያዎች ጋር)
🎀የመጀመርያ ልጅን ከ30 አመት በኋላ መውለድ እና ጡት አለማጥባት,
🎀አልኮል መጠጦችን መጠጣት, ማጨስ …

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ነገሮች ተጋላጭነትን ይጨምራሉ ማለት ነው እንጂ ቀጥታ ከጡት ካንሰር ጋር ይያያዛሉ ወይም የጡት ካንሰር ያመጣሉ ማለት አይደለም።

👉🏽ስለዚህም የምንላቸውን ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ማስተካከል, በየጊዜው ጡታችንን መፈተሽና ከሃኪም ጋር በመመካከር ምርመራዎችን ማድረግ ተገቢ ነው።

15/10/2025
አዲሱ ታርጋ 30,000 ብር ያስከፍላል።30000 ብር X 1,800,000 መኪና = 54 ቢሊዮን ብርይመችህ መንግስት😏😏😏❤️
10/10/2025

አዲሱ ታርጋ 30,000 ብር ያስከፍላል።
30000 ብር X 1,800,000 መኪና = 54 ቢሊዮን ብር
ይመችህ መንግስት

😏😏😏❤️

 #ተራዝሟልየጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የአገልግሎት ጊዜዉ ባለፈበት የሙያ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ጤና ባለሞያዎች ማሳደስ እንዳለባቸውና የሞያ ፍቃድ የ...
10/10/2025

#ተራዝሟል

የጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የአገልግሎት ጊዜዉ ባለፈበት የሙያ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ጤና ባለሞያዎች ማሳደስ እንዳለባቸውና የሞያ ፍቃድ የሌላቸው ደግሞ አዲስ እንዲያወጡ ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰርኩላር አውርዶ ነበር።

ነገር ግን በተባለው ጊዜ ለማደስ የIhris-HrI ስርዓት እያስቸገረ መሆኑን ጠቅሶ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለ1 ወር ጤና ሚኒስቴር ያራዘመ መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም በኃላ " no license, no practice " በሚል መሪ ቃል የሙያ ፍቃድ ያላወጡ እና ያላሳደሰ ባለሞያዎች በሞያዉ መስራት እንደማይችሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

08/10/2025

Big shout out to my newest top fans! Gerawerk Tale, Tesfaye Alemu, Xalale Toitole, ቢተዉማማሩ ደስታው, Hawi Tadesse, Nuhamin Yeshmebet, የሆነው እየሆነ ያለው, Hirut Kassa, Gadissa Olana Dhaba, Qano Dib, Derbe Aschalew, Abdul Mejid, Dawit Tesfaye, Asfaw Fisa, Aberach Admassu, Heranu Hero Beker, Eyoba Abay, Mequanint Asefa, Dilu Dessie, Fentaye Zelelew Mera, Desu Terefe, Rahel Gebreyesus, Yonas Esseye, Afework Weldemichael, Geremew Bantirgu, Shimallis F Imaanaa, Biruk Seyfe, Lidya Shemsu, Selamawit Tesfaye, Selam Arega, Kibrework Bezabih, Etsegenet Etsegenet, Gumataw Abate, Esseyina Hailu, Tarekegn Murezha, ዝም አልልህም, Naod Baye, Alembrahan Beyene Wedikeshi, Zerihun Moges

07/10/2025

Scene at the Emergency department🙄🙄🙄

አዲሱ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ደመወዝ!             ***//***
04/10/2025

አዲሱ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ደመወዝ!
***//***

 #ይህ የቀን ውሎ አበል ስሌት በደሞዝ ደረጃና በክልል ከተማ  #ለካቢኔ ና ቢሮ ሰራተኞች እንደዚህ ተሻሽሏል ነገር ግን በ1990ዓ.ም የወጣው አዋጅ  #የሀኪሞች  #የ house allowanc...
03/10/2025

#ይህ የቀን ውሎ አበል ስሌት በደሞዝ ደረጃና በክልል ከተማ #ለካቢኔ ና ቢሮ ሰራተኞች እንደዚህ ተሻሽሏል
ነገር ግን በ1990ዓ.ም የወጣው አዋጅ
#የሀኪሞች
#የ house allowance=1000 ብር
=1225 ብር
መቼ ይሻሻላል ቆይ በ1000 ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ቤት ይኖር ይሁን?

Share share share,
Loading

አዲስ አበባ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ምአዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል።Share
02/10/2025

አዲስ አበባ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል።

Share

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doc Book posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Doc Book:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category