Ethio.Medical news

Ethio.Medical news This pagee advise more about health related to drugs

05/06/2023

WhatsApp Group Invite

25/05/2023

ማንኛውንም ያስጨነቆትን የጤና ጉዳይ እንዲሁም የሚፈልጉትን የምክር አገልግሎት በውስጥ መስመርም ሆነ በበዚሁ መልስ ማግኘት የሚችሉበት ፔጅ ነው።

ይጠይቁ፣ይወቁ፣ከጭንቀቶ ይገላገሉ!!

25/05/2023

በማንኛውም እድሜ ክልል ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች
የስነ- ምግብ ምክር
የስነ-ልቦና ምክር
ጤና ነክ የሆኑ ጉዳዮችን እንዲሁም መድሀኒት ነክ የሆኑ ነገሮችን በስልክ ፣በzoom፣እንዲሁም በአካል የማማከር ስራዎችን እንሰራለን።
አገልግሎት ለማግኘት እና በፈለጉት ጉዳይ አገልግሎት ለማግኘት
በ0941970284
በ0704930670 ይደውሉ

11/03/2023
01/07/2022

Over-the-counter (OTC) medicines

01/07/2022

ልጆች መቼ ነው አልጋ ላይ መሽናት የሚያቆሙት?
አብዛኞቹ ህፃናት 5 ዓመት ሲሆናቸው ሌሊት ላይ ሽንታቸውን መቆጣጠር ይችላሉ:: ሆኖም 10-15% የሚሆኑ ህፃናት እስከ 7 አመታቸው ድረስ ይቸገራሉ፡፡ ሽንት ለሊት ሊያመልጣቸው ይችላል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ይህ ችግር ያለባቸው ህፃናት እድሜያቸው በ 1 ዓመት በጨመረ ቁጥር ቺግሩ በ15% እየቀነሰ ይሄድና እድሜያቸው 15 ዓመት ሲሞላ 99 በመቶ ህፃናት ከዚህ አይነቱ ችግር ሙሉ ለሙሉ ነፃ ይሆናሉ፡፡
::
ሆኖም አንድ ሕጻን 6 አመት እና ከዛ በላይ ሆኖ ሽንትን ለመቆጣጠር ካልቻለ ወላጆች ሐኪም መማከር አለባቸው፡፡ ሽንትን መቆጠጠር ያለመቻል ችግር በወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ላይ ከሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊና ማሕበራዊ ተፅዕኖ ይልቅ በልጆች ላይ የሚፈጥረዉ ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖ እጅግ የበረታ ነው፡፡
ወላጆች ሊያወቁት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ልጆች ሆነ ብለው አሰበውና አቅደው ወይም በእነርሱ ግድ የለሽነትና ሥንፍና የሚመጣ ችግር እንዳልሆነ ልረዱ ይገባል፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነት ቺግር ያለባቸውን ህፃናት ማሸማቀቅ ማናደድ እንዲሁም በሰዉ ፊት ʺለሊት አልጋ ላይ ሸንቷል!ʺ ብሎ ማሳፈር በፍፁም ተገቢ አይደለም፡፡

ሽንትን ሌሊት ያለመቆጣጠር ችግር መንስኤው ምንድነው? ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የምከተሉት ናቸው
1. ትልቅ የሆነ እንቅልፍ እና የሽንት ፊኛ ከመጠን በላይ ሲወጠር መንቃት አለመቻል
2. የጉሮሮ መጥበብ እና ትንፋሽ መቆራረጥ እና ማንኮራፋት (obstructive sleep apnea)
3. በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ(በተለይ እናት እና አባት ላይ በ ልጅነታ ቸው አጋጥሞቸው ከሆነ)
4. የሆርሞን መዛባት በተለይ የቫሶፕሬሲን (ADH) የሚባለው ሆርምን ማታ ላይ በአግባቡ የማይመረት ከሆነ
5. የሽንት ፊኛ ተገቢውን የሽንት መጠን መያዝ ወይም መሸከም አለመቻል(በነርቭ ቺግር ወይም የአፈጣጠር ችግር ምክንያት)
6. የአይምሮ ጭንቀት
7. አስቸጋሪና አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ እና ያን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሃት
8. አሰቃቂ አካላዊ ድብደባና ቅጣት
ወሲባዊ ጥቃት/የአስገድዶ መደፈር በተለይ ሴት ታዳጊዎች ላይ
10. የነርቭ ዘንግ(spinal cord) ችግሮች(spina bifida)
11. ከፍተኛ የሺንት መጠን ማምረት - polyuria (በስኳር ፣ በኩላሊት ችግሮች ወይም በሌሎች ምክንያቶች)
12. ረጅም ጊዜ የቆየ ሆድ ድርቀት
13. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

+251941970284

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio.Medical news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethio.Medical news:

Share