ኢንፎ ሔልዝ ሴንተር

ኢንፎ ሔልዝ ሴንተር ሁሉ በጤና ይሆናል!!! 0932338485

21/11/2025

የተመረዘ ምግብ በልተዉ ከታመሙ 8 የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ የ7ቱ ህይወት አለፈ

ምግቡ በማንና እንዴት ተመረዘ?

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በአብሮነት እራት ተመግበዉ በጠና ከታመሙ ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ አባወራዉ ከስድስት ልጆቹ ጋር ሰባት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸዉ ማለፉን ፖሊስ ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለዉ ተመስገን እንደገለፁት በወረዳዉ መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት ስምንቱ የቤተሰብ አባላት አብረዉ እራት ከተመገቡ በኋላ በድንገት መታመማቸዉ ተናግረዋል።

በአብሮነት እራት እንደተመገቡ ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ህመም መዳረጋቸዉን መረጃ የደረሳቸዉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ ተረባርበዉ ወደ ሆስፒታል ማድረሳቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

ቢሆንም ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት የ5 ዓመቱ መንግስቱ ኃይሌ ፣የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ ተክሉ ኃይሌ የተባሉት ሶስቱ ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸዉ ማለፉን ነዉ የተገለፀዉ።

የተቀሩ ተጎጂዎችን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ሀኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም የ14 ዓመቷ መቅደስ ኃይሌ እና የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱ እህትና ወንድም ህይወት ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 11:00 ሰዓት ሲያልፍ የሟቾች ቁጥር ወደ አምስት አሻቀበ።

ከተቀሩት ተጎጂዎች ደግሞ የ1ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን ሲሳይ ኃይሌ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የስድስቱ ሟች ልጆች አባት የሆነዉ አቶ ኃይሌ አበራ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሰመመን ዉስጥ ሆኖ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ህልፈቱ እዉን ሆኖ ልብ ሰባሪና አሳዛኝ የሆነ ዜና ተደመጠ።

የባለቤቷንና የስድስት ልጆችዋን ህልፈት ለማወቅ ያልታደለችዉ ወይዘሮ ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል በከፍተኛ የጥንቃቄ ክፍል ዉስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች በህወት መኖሯን ነዉ ፖሊስ የተገለፀዉ።

ተጎጂዋ ቤተሰቡን በጅምላ ወደ ሞት ያወረደዉን ጉዳይ ልትተርክ በህይወት ትተርፍ ይሆን?ወይስ እሷም የባለቤቷና የልጆችዋ እጣ ገጥሟት ከቤተሰቡ መሀል አንድም ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ በጅምላ እቺን አለም የመሰናበታቸዉ አሳዛኝ ዜና ይደመጣል? የሚለዉን ለመገመት ይከብዳል።

ፖሊስ ተጎጂዎች የተመገቡት ምግብ የተመረዘዉ በማንና እንዴት?የሚለዉን እዉነታ ለማረጋገጥና የተፈፀመዉን ድርጊት አጣርቶ እዉነታዉ ለማረጋገጥ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል አዋቅሮ ምርመራ የማጣራቱን ስራ መጀመሩን የተናገሩት ኮማንደር ያለዉ ተመስገን የምርመራ ግብረ ኃይሉ በድርጊቱ የሌሎች እጅ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ አስር ሰዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተጎጂዎች በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ህክምና ተከታትለዋል ያለዉ ፖሊስ የሟቾች የአስክሬን ምርመራ ዉጤት እየተጠበቀ መሆኑንና ስለጉዳዩ የተሻለ ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል መረጃ ሊገኝ እንደሚችል ይገመታል።

የክልሉ ፖሊስ ሚድያ ክፍል ይህ ዜና በሚድያ ይፋ እስካደረገበት ሰዓት ድረስ ከስምንቱ ተጎጂዎች ዉስጥ አንዷ የሆነችዉ የቤቱ እማወራ በአዲስ አበባ ምንሊክ ሆስፒታል በህክምና እየተረዳች መሆኑን አረጋግጧል።

በተለያየ ጊዜ እቺን አለም የተቀላቀሉት ከ46 ዓመቱ አባት እስከ 1 ዓመት አ7 ወር እድሜ ያለዉ ህፃን እቺን አለም በተመሳሳይ ሰአት ለመሰናበት የተገደዱበት ተግባር የተለየ ግኝት ካለ መረጃዉን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል።

(ኮማንደር ታጁ ነጋሽ -ማ.ኢ.ፖ.ኮ)

19/11/2025

Check out ETHIO MEDICAL TRAINING CENTER’s video.

16/11/2025

ETHIO MEDICAL TRAINING CENTER

#0921785903

16/11/2025



1) በሽታው ምንድን ነው?

#የቫይረሱ አይነት: ማርበርግ ቫይረስ የፋይሎቫይረስ (Filoviridae) ቤተሰብ አባል ሲሆን ይህም ኢቦላ ቫይረስ የሚገኝበት ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ሁለቱም በሽታዎች ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶች እና የሞት መጠን ያላቸው።

#ክብደት: በሽታው ከባድ እና ከፍተኛ የሞት መጠን ያለው ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ወረርሽኞች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ እስከ 88% የሚደርስ ሰዎች ሞተዋል (እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል)።
#ታሪክ: በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተሞች ተከስቷል። ቫይረሱ የመጣው ከዩጋንዳ በመጡ የላብራቶሪ ምርምር ዝንጀሮዎች አማካኝነት ነው ይባላል።

2) ስርጭት (በሽታው እንዴት ይተላለፋል?)
+++ ዋናው #ምንጭ: የማርበርግ ቫይረስ ተሸካሚዎች ፍራፍሬ ላይ የሚያዘወትሩ የሌሊት ወፎች (Rousettus bats) ናቸው። ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት በእነዚህ የሌሊት ወፎች ባሉበት ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ በመገኘት ነው።

+++ ከሰው ወደ ሰው የሚኖረው #ስርጭት: ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ወይም እንስሳት በሚወጡ ፈሳሾች (ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ የዘር ፈሳሽ እና ሌሎች) ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው።
3) #ምልክቶች
የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያሉ።

የሚከተሉትን እንመልከት
#የመጀመሪያ ደረጃ ላይ : ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት።
#ሁለተኛ ደረጃ (ከጥቂት ቀናት በኋላ): ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም።
#የከፋ ደረጃ (ከ5-7 ቀናት በኋላ) ከባድ የደም መፍሰስ (ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር)፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ስራ መቆም (Multi-organ failure) እና ሞት። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ (በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ)።

4)የሚሰጠው ህክምና እና መከላከያ መንገዶች
#ፈውስ: ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት የለም።
#ህክምና: የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ (Supportive Care) ነው።
#ፈሳሽ መተካት (IV fluids): በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ነው።
#የደም መፍሰስ ቁጥጥር: የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል/ማከም።
#የተጎዱትን የአካል ክፍሎች (ኩላሊት፣ ጉበት) ድጋፍ መስጠት።

በጣም #አስፈላጊው ነጥብ
-) የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE): የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው።
_) ንጽህና: እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለይ የታመመ ሰው የነካን ወይም የጎበኘን ከሆነ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ
1) የዓለም ጤና ድርጅት (World Health Organization - WHO): Marburg Virus Disease (MVD)

2) የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (Centers for Disease Control and Prevention - CDC : Marburg Hemorrhagic Fever (Marburg HF)

ባምላኩ አበባው
ፕሮፌሽናል ነርስ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል

15/11/2025
ሙያ ፈቃድዎን ለማሳደስ ከመሄደዎ በፊት የCPD ስልጠና በመውሰድ የሚጠበቅበዎትን CEU በእጅዎ ይያዙ !!! ETHIO MEDICAL TRAINING CENTER    1. 👉   STEWARDSHIP ...
10/11/2025

ሙያ ፈቃድዎን ለማሳደስ ከመሄደዎ በፊት የCPD ስልጠና በመውሰድ የሚጠበቅበዎትን CEU በእጅዎ ይያዙ !!!

ETHIO MEDICAL TRAINING CENTER




1. 👉 STEWARDSHIP
2. 👉 (MOTIVATED, COMPASSIONATE AND COMPETENT CARE)
3. BASIC LIFE SUPPORT (BLS)

ስልጠናውን ጤና ባለሙያ የሆነ ሁሉ መውሰድ ይችላል።

ስልጠናውን እንደጨረሱ በእያንዳንዳቸው 15CEU የሚሸፍን ሰርተፍኬት ያገኛሉ።

ኮርሶቹ ከነፊታችን ሰኞ ህዳር 1/2018 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 8 ቀናት ይሰጣሉ።

👉 Registration:- Ongoing
አሁኑኑ ደውለው ይመዝገቡ
👇 👇👇👇👇👇
👉 0921785903
👉 0913744598/0932338485
በአካል ለመመዝገብ ንፉስ ስልክ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ
ፊትለፊት ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
https://t.me/jossiale2022

      TRAINING በየትኛውም አካባቢ ያላችሁ  የጤና ባለሙያዎች የCPD ስልጠና ስትፈልጉ ተወዳጁና ተመራጩ   አለላችሁ። #አስታውሱ :- ሁል ጊዜ በሳምንት ሁለት ዙር ስልጠና እንሰጣላን...
29/07/2025



TRAINING

በየትኛውም አካባቢ ያላችሁ የጤና ባለሙያዎች የCPD ስልጠና ስትፈልጉ ተወዳጁና ተመራጩ አለላችሁ።

#አስታውሱ :- ሁል ጊዜ በሳምንት ሁለት ዙር ስልጠና እንሰጣላን።

👉 የሚጀምረው ዋናው ሳምንታዊ ፕሮግራማችን ሲሆን የሚጀምረው ደግሞ ተጨማሪና በስራ ቀናት ለሚመቻቸው የሚዘጋጅ ነው።
በተጨማሪም
➯✍️ ONLINE (E-LEARNING) CPD
➯✍️ Webinar Training (አነስተኛ CEU የያዘ) እየሰጠን እንገኛለን።
ደውለው ይመዝገቡ!!!
👇👇👇👇👇
0921785903
አድራሻችን ሳሪስ መስመር ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ሰፈር
ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
ወይም
ንፋስ ስልክ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት
ባቡር ፌርማታ አጠገብ ራሚ ህንፃ!!!
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢንፎ ሔልዝ ሴንተር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ኢንፎ ሔልዝ ሴንተር:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram