
06/07/2024
ዛሬ ፌስቡክ ላይ ዞር ዞር ስል ይሄንን ጥያቄ አየሁት ። እንደሴትነቴ ይሄን በደንብ ስለሚገባኝ መናገር ፈለጉ። 😭
በነገራችን ላይ ትንሽ ጡት ያላችሁ ሴቶች እናንተን አይመለከትም ይቅርታ !!! 😄
ጡታችን ወደታች እንዳይሆን የሚሰሩ ስፖርቶች አሉ።
ዋናው ነገር ጡቶች ወደታች የሚሆኑት የደርታችን እና የጀርባችን ጡንቻዎች ጡታችንን ለመሸከም ደካማ ሲሆኑ ነው።
ምን ማለቴ ነው ፣ በተለይ ክብደት ስንጨምር ጡቶቻችን ውስጥ የሚጠራቀም ስብ ስላለ ትልቅ ይሆናል።
የጀርባችን ጡንቻዎች እና የደረታችን ጡንቻዎች ግን ያንን መሸከም ስላማይችሉ ጡት ወደታች ይወድቃል።
አስሬ ጡት ስል ግራ ገባኝ እኮ ።
ለማነኛውም ክብደት ማንሳት እና ጡንቻዎቻችሁን በማጠንከር ፣ ቀጥ ብሎ መቀመጥ ጡታችሁን ለመደገፍ ስለሚችል ጡንቻችሁ ወደነበረበት ይመለሳል።
ጡት የምታጠቡ እናቶችም ተመሳሳይ ነገር ይሰራል።
ባጠቃላይ
1. የጀርባ እና ደረት ጡንቻችሁን የሚያጠነክር ስፖርት ስሩ
2. ቅጥ ብላችሁ የሆድ ጡንቻችሁን በመጠቀም ተቀመጡ
3. የሚበቃችሁን ጡት መያዢያ አደርጉ። ያረጀውን ጣሉት
4. ጡታችሁ የትም ቦታ ላይ ቢሆን በጣም ነው የሚያምረው።