
21/07/2025
Sinusitis
በአፍንጫና በቅንድብ ስር በሚገኙ አጥንት ቀዳዳዎች ላይ የሚፈጠር እብጠት ወይም መቆጣት ነው።
ምክንያቶች
✔ በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ
✔ አለርጂ
✔ የአፍንጫ አፈጣጠር ችግር
✔ የተዳከመ በሽታ መከላከል አቅም እና ሲጋራ ማጨስ ሊሆኑ ይችላሉ።
ምልክቶች
✔ የአፍንጫ መታፈን
✔ ጉንጭ፣ አይን እና ራስ ህመም
✔ ትኩሳት እና ሳል እንዲሁም ማስነጠስ የመሳሰሉት ናቸው።
በቤት ውስጥ ማድረግ የምንችለው ህክምና
✔ በቂ እረፍት ማድረግ
✔ በቂ ውሃ መጠጣት እና ቀላል የህመም ማስታገሻ መውሰድ።
ተደጋጋሚ የሳይነስ ኢንፌክሽን ካለ ግን የህክምና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው።
አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
የሁሉም ሰው ህይወት ዋጋ የሚሰጥበት ቦታ
ለበለጠ መረጃ ወደ 7560 ይደውሉ።