Hayat General Hospital

Hayat General Hospital Hayat General Hospital is a privately owned health institution providing quality health care services for more than 25 years.

Hayat General Hospital
:
To be the first choice in health care for our communities and be the leader in providing quality, compassionate patient-centered care that seeks physical cures and comfort, as well as peace of mind and peace of heart. Also to improve health by providing high-quality medical education.

:
Hayat General Hospital is a for-profit medical institution dedicated

at providing quality patient care and medical education with bold attention to clinical excellence, patient safety, passion and commitment, so as to provide the very best healthcare for the community we serve.

Committed to provide the best health Care Services
10/12/2024

Committed to provide the best health Care Services

25/11/2024
Dr. Gelane Lelissa•Specialized In Obstetrics and Gynecology in Addis Ababa University Medical faculty•Subspecializing In...
14/11/2024

Dr. Gelane Lelissa
•Specialized In Obstetrics and Gynecology in Addis Ababa University Medical faculty
•Subspecializing In Reproductive Endocrinology and Infertility In Saint Paul’s Hospital Millennium Medical College
Areas Of Expertise
•Evaluation And Management of Couple With Infertility
•Evaluation And Management Of Pelvic And Gynecologic problems
•Evaluation And Management Of Endocrine Problem Of the Reproductive System
•Evaluation And Management Of Male And Female Sexual Dysfunction
•Provision Of Routine Gynecologic Screening

 #የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ...
24/10/2024

#የዲስክ መንሸራተት ምንድን ነው?
የጀርባ አጥንት የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው። የጀርባ አጥንት መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ክፍሎች የጀርባ አጥንት ዲስኮች ይባላሉ። እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ። ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚቋቋሙ ክፍሎች ናቸው። ዲስክ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ አለው።
የዲስክ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውስጥ ፈሳሽ መውጣት ነው። ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው። ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል።
አንዳንድ ግዜ በእጅ ላይ የመደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም ስሜት አይኖረውም። የተንሸራተተው ዲስክ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማንም።
የዲስክ መንሸራተት ህመም ምልክቶች
የዲስክ መንሸራተት ስለመከሰቱ ምንም እዉቅና ሳይኖርዎ ወይም ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳይኖር ችግሩ ሊኖር/ሊከሰት/ ይችላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳያሳዩ በምርመራ ወቅት በራጅ ላይ የዲስክ መንሸራተት መኖሩ ሊታወቅ ይችላል፡፡
የዲስክ መንሸራተት በሚኖርበት ወቅት የሚኖሩ የህመም ምልክቶች:-
• የእጅ/የእግር ላይ ህመም፡- የዲስክ መንሸራተቱ ያጋጠመዉ በታችኛዉ የጀርባ አጥንቶች አካባቢ ከሆነ ከፍተኛ ህመም በመቀመጫዎ፣ በጭንዎና በባትዎ አካበቢ እንዲሁም መርገጫዎ/የእግር መዳፉ ላይ ሊሰማዎ ይችላል፡፡ የዲስክ መንሸራተት ያጋጠመዎ አንገትዎ ላይ ከሆነ ህመሙ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰማዎ በትከሻና በእጅዎ ላይ ነዉ፡፡ ሕመሙ በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበት ወቅት ወይም ወደ ተወሰነ አቅጣጫ የጀርባ አጥንቶችዎን በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡
• የእጅ/ እግር መስነፍ፡- በዲስክ መንሸራተት ምክንያት የተጎዳ ነርቭ ካለ ያ የተጎዳዉ ነርቭ እንዲሰራ የሚያደርገዉ ጡንቻ ሊደክም ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ መራመድ መቸገር፣እቃ ማንሳት ያለመቻል ወይም መያዝ ያለመቻል ሊከሰት ይችላል፡፡
• የመደንዘዝ ወይም የመጠቅጠቅ ስሜት
• የማቃጠል ስሜት
• የጡንቻ ህመም
• የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ በራሳቸው ግዜ ሊጠፉ ይችላሉ።
መንስኤዎች
የዲስክ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከጊዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው። ዲስክ ከእድሜ ጋር ውሃማ ይዘቱን ያጣል። ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል።
ለዲስክ መንሸራተት ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች
• እድሜ
• የሰዉነት ክብደት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላይ የጨመረ ከሆነ በጀርባ አጥንተትዎና ዲስኩ ላይ ጫና ይፈጥራል፡፡
• የስራዎ ሁኔታ፡- የስራቸዉ ፀባይ ጉልበት የሚጠይቅ ስራ የሚሰሩ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡
• በተደጋጋሚ ከባድ ነገር የሚያነሱ፣ የሚጎትቱ፣ የሚገፉ፣ ወደ ጎን መታጠፍና መጠማዘዝ የሚያበዙ ሰዎች ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡
• በዘር የሚመጣ፡- አንዳንድ ሰዎች ለመሰል ችግር ተጋላጭነታቸዉ መጨመር በዘር ሊወረስ ይችላል፡፡
• የዲስክ መንሸራተት ህክምና
• የጀርባዎ ህመምዎ ወደ እጅዎና እግርዎ የሚሰራጭ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና
1. የህመም ማስታገሻ፡- ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንደ አይቡፕሮፌን/አድቪል/ መዉሰድ
2. ሙቀት/ቀዝቃዛ ነገር መጠቀም፡- በመጀመሪያ ቀዝቃዛ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ ህመሙንና መቆጥቆጡን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ከተወሰኑ ቀናት በኃላ ሙቅ ነገር መያዝ ምቾትና የህመም ፈዉስ እንዲሰማዎ ስለሚያደርግ በቦታዉ ላይ መያዝ
3. ከመጠን ያለፈ እረፍት ያለማድረግ/ማስወገድ፡- ከመጠን ያለፈ እረፍት የመገጣጠሚያዎች መጠንከር/መተሳሰር እና ጡንቻዎች መስነፍ እንዲመጣ ስለሚያደርግ የፈዉሱን ጊዜ አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ይልቁንም በሚመችዎ አቅጣጫ ለ30 ደቂቃዎች እረፍት ማድረግና ከዚያን ለአጭር ጊዜ ወክ ማድረግ አሊያም የተወሰኑ ስራዎችን ማከናወን፡፡
ከህመምዎ እያገገሙ ባሉበት ወቅት ህመሙን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች/እንቅስቃሴዎች መቆጠብ፡፡
ከዲስክ መንሸራተት እንዴት መከላከል ይቻላል?
• ከፍተኛ የሰውነት ክብደት እንዳይኖርዎ ተጠንቀቁ
• ክብደት ሲያነሱ የሰውነት አቋምን ማስተካከል
• የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ካዩ በቂ እረፍት መውሰድ እና ተገቢውን ህክምና ማከናወን

Source:- Info Health Center

  graduate  ....Adis Abeba University GCMS      the degree of  the Doctor of Medicine Post  graduate Adis Abeba Universi...
23/10/2024

graduate ....Adis Abeba University GCMS
the degree of the Doctor of Medicine Post graduate Adis Abeba University MF..School of graduate
in Orthopaedics & Traumatology Surgery
medical working experience for a total of almost 40 yrs at different health institutions

06/09/2024

HAYAT HOSPITA
መልካም አዲስ አመት

13/07/2024


• እርግዝና የወንድ የዘር ፍሬና የሴቷ እንቁላል ውህደት ሲፈጥሩ የሚፈጠር ክስተት ሲሆን በሴቶች ማህፀን ውስጥ እስከ ሚወለድ ጊዜ የራሱን እድገት ማከናወን ሲጀምር ነው።
• አንድት ሴት የወር አበባ ማየት የጀመረችበትን የመጀመሪያ ቀን አንድ ብለን ቆጥረን 12ኛው፡ 13ኛው፡ 14ኛው፡ 15ኛውና 16ኛው ቀን በተለይ 14ኛው ቀን የምትፀንስባቸው ቀናት ናቸው።
• እርግዝና 280 ቀናትን ወይም 40 ሳምንታትን ይወስዳል።
#የእርግዝና የመጀመሪያ ምልክቶች
የወር አበባ መቅረት፡ ማቅለሽለሽና ማስታወክ፡ የጡት ጫፍ መጠጠርና መጥቆር እንድሁም ፈሳሽ መልቀቅ፡ ክብደት መጨመር፡ የጡት መጠን መጨመር፡ ቶሎቶሎ ሽንት መሽናት፡ የሆድ መጠን መጨመር፡ በምርመራ ወቅት HCG መገኘት። በመቀጠል በተለያዩ ምርመራዎች ይረጋገጣል።
#አደገኛ የእርግዝና ምልክቶች
የምጥ አይነት ስሜት፡ ውሀ መሳይ ፈሳሽ፡ ከባድ የሆድ ቁርጠት፡ ደማቅ ደም መፍሰስ፡ አጣደፊና ተደጋጋሚ ትውከት፡ በጣም ከፍተኛ የደም ግፊት፡ ፈጣን ክብደት መጨመር፡ ከባድ የራስ ምታት፡ የእይታ ችግር፡ ከፍ ያለ የእግር እብጠት፡ የደረት ህመም፡ ተደጋጋሚ መደንዘዝ ስሜትና የጀርባ ቁርጥማት ሲታዩ በፍጥነት ወደሚከታተሉበት ጤና ተቋም ይሂዱ።
ቅድመ ወሊድ ክትትል
#ለአንዲት እናት እርጉዝ መሆኗ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ እስክትወልድ ድረስ የሚሰጥ የጤና ክትትልና እንክብካቤ ነው
ማንኛዋም እርጉዝ ሴት ለምን ቅድመ ወሊድ ክትትል ያስፈልጋታል?
1: ከእርግዝና ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና ችግሮችን ለመከላከል
2: ጤናማ ልጅን እንድትወልድ ለማድረግ
3: በፅንስ ላይ በተለያየ ምክንያት ወይም መከላከል በማይቻል መልኩ የሚፈጠር ችግር ካለ ቀድሞ ለማወቅና ለእናት ጤና ጥንቃቄ ለማድረግ
4: እናትን ስለ እርግዝና ምጥና ሌሎች ጉዳዩች ትምህርት ወይም ግንዛቤ ለማስጨበጥና ሌሎችም ናቸው።
#አንድት እርጉዝ ሴት ማወቅና መተግበር ያሉባት ነገሮች
1. በቀን 2 ሰአት እንቅልፍ
2. በማታ 10 ሰአት እንቅልፍ
3. በቂ እረፍትና መዝናናት
4. የተመጣጠነ ምግብና ተጨማሪ መቅመስ
5. የአካል እንቅስቃሴ እስከ አንድ ሰአት የሚሆን ወክ ጧት/ማታ
6. ጭንቀት፡ ውጥረትና ፍራቻን ማስወገድ
7. ከባድ ስራን(ማንሳት መጣልን) መቀነስ
8. የማይቆረጥ ቅድመ ወሊድ ክትትል
9. በቂ ፈሳሽ መውሰድ
10. በግራ ጎን መተኛት
11. ውፍረትን መቆጣጠር
12. አነስተኛ ስብ
13. በቂ ፕሮቲን
14. በቄ ፍራፍሬ፡ ቅጠላቅጠልና ጥራጥሬ
15. አደገኛ ምልክቶችን ማወቅና ካለ ቶሎ መታየት
16. ክትባት መከታተልና መጨረስ
17. ተጨማሪ ቫይታሚንና ፎሊክ አሲድ መውሰድ
18. የፅንስ እንቅስቃሴ መከታተል
19. የምጥ ምልክቶችን ማወቅ
#የተለየ ክትትል የሚያስፈልጋቸው
1. ቁመት 1:50 በታች የሆኑ
2. ከ 18 አመት በታች የሆኑ
3. ሳያረግዙ 35 አመት የሞላቸውና አሁን ያረገዙ
4. ደም ግፌት፡ ስኳር፡ የልብ፡ የኩላሊትና ሌሎችም ችግር ያለባቸው
5. ተላላፌ በሽታ እንደ HIV አይነት ያለባቸው
6. ቀድሞ የውርጃ ታሪክ ያላቸው
7. መንታ ያረገዙ
8. በዘር የሚተላለፍ ችግር ያለባቸውና ሌሎችም ናቸው።
Hayat Hospital
Source:-info health center
ለተጨማሪ መረጃ እና ምርመራ ካስፈለገዎ
ዶ/ር ታጠቅ ተስፋዬ
የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

13/07/2024

Our physiotherapy unit is ready to serve you
From Monday - Saturday
Come & Visit
Call:-0909 46 46 46
Hayat General Hospital
We always prioritize your care & safety

Address

Bole
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hayat General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Hayat General Hospital:

Share