
13/03/2024
አርትራይተስ(የመገጣጠሚያ ህመም)
ቁርጥማት የአንድ ወይም ከዚያ በላይ መገጣጠሚያዎች እብጠት ነው። የአርትራይተስ ዋና ምልክቶች የመገጣጠሚያ ህመም እና መገተር ነው ፣ ይህ ህመም ከእድሜ ሲገፋ እየባሰ ይሄዳል። በጣም የተለመዱት የአርትራይተስ ዓይነቶች የአርትሮሲስ እና የሩማቶይድ አርትራይተስ ናቸው። አርትራይተስ ከ200 ከሚበልጡ የተለያዩ የቁርጥማት በሽታ አይነቶች ጋር ተዛማጅነት ያለው ነው ከእነዚህ መካከል ኦስትዮአርትራይተስ፣ ሩማቶይድ አርትራይተስ፣ ሲስተሚክ ሉፐስ ኤራይቲማቶሰስ፣ ሪህ ፣ በርሳይተስ፣ ሩማቲክ ፊቨር፣ ላይም በሽታ፣ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
መንስኤዎቹ
ለሁሉም የአርትራይተስ በሽታ አንድ ዓይነት ምክንያት የለውም ፡፡ መንስኤው እንደየበሽታው አይነት ይለያያል ነገር ግን እንዳጠቃላይ የሚቀመጡ ምክንያቶች ፡-
📌 ጉዳት (አደጋ)
📌 በቤተሰብ ይህ ዓይነት ችግር ካለ
📌 በተለያዩ ተዋሲያን መጠቃት (infection)
📌 በምንመገባቸው የምግብ ዓይነቶች ተያይዘው የሚመጣ
📌 የሪህ በሽታ
ምልክቶቹ
📌 በእንቅስቃሴ እና በቅዝቃዜ ሰዓት የሚባባስ ህመም
📌 ጠዋት ጠዋት የመገጣጠሚ አከባቢ ያለ የመጨምደድ ስሜት
📌 የመገጣጠሚያ እብጠት
በአርትራይተስ የመያዝ ሰፊ አጋጣሚ ያላቸው እነማን ናቸው?
📌 ከዕድሜ መግፋት
📌 በሰውነት ክብደት መጨመር
📌 ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ተጋላጭ ናቸው
📌 የቫይታሚን ሲ እና ዲ እጥረትን
📌 በዘር ለበሽታው የመጋለጥ አጋጣሚ
የአርትራይተስ በሽታ ህክምና
📌 አካላዊ እንቅስቃሴና የአኗኗር ለውጥ ማድረግ
📌 ፊዚካልቴራፒ ወይም ጤናን ለማሻሻል የሚረዱ የሰውነት እንቅስቃሴዋችን ማድረግ
📌 ክብደት መቀነስ
📌 ጠቆር ያለ አረንጓዴ ቀለም ያላቸውን በካልስየም የበለጸጉ ቅጠላ ቅጠሎችን፣ ትኩስ ፍራፍሬዎችን፣ ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ የሚባለው ንጥረ ምግብ የሚገኝባቸውን ምግቦች አዘውትሮ መመገብ
📌 የተለያዩ መድሃኒቶች (Analgesics, Non-steroidal, anti-inflammatory drugs (NSAIDs), Corticosteroids) እንዲሁም ሌሎች መድሀኒቶች