
20/04/2023
የአጥንት መሳሳት(Osteoporosis)
የሰው ልጅ አጥንት የሚገባውን ያክል የካልሲየም ክምችት ሳይኖረው ሲቀር እና ደካማ ሲሆን የአጥንት መሳሳት(Osteoporosis) ይባላል። በዚህ ጊዜ አጥንት በቀላሉ ተሰባሪ ይሆናል።
• ሁሉንም የሰው ዘሮች እና ሁለቱንም ጾታዎች የሚያጠቃ ሲሆን በተለዬ ተጠቂ የሆኑ አካላት አሉ፦
-አፍሪቃዊያን
-ኤሲያዊያን
-እና ሴቶች የበለጠ ተጠቂ ናቸው
• መንስዔዎቹ
-እርጅና
-ሴት መሆን
-ከቤተሰብ ተመሳሳይ ታሪክ መኖር
-በጣም ቀጭን መሆን
-የሆርሞን መዛባት(የመራቢያ ሆርሞን፣የጎይተር ሆርሞን)
-የአመጋገብ ሥርአት መዛባት(በጣም ቀጭን ለመሆን ራስን ማስራብ፣ካልሲዬም ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ)
-የአኗኗር ዘይቤ( እንቅስቃሴ አለማድረግ፣አልኮል ማብዛት፣ሲጋራ ማጨስ)
-በህክምና የሚታዘዙ መድሐኒቶች(ለሚጥል በሽታ፣ለካንሰር ወዘተ)
መቼ ወደ ህክምና ልሂድ?
-ከቤተሰብ ውስጥ በአጥንት መሳሳት ምክንያት ስብራት ተከስቶ ከነበር
-የወር አበባ ከ45 እድሜ በፊት ከቀረ
-እድሜ ሲገፋ ወንድ ከ70 ዓመት ሴት ከ50 ዓመት እድሜ በላይ
-የአጥንት መሳሳት ሊያመጡ የሚችሉ መድሐኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ
ምን ችግርን ያስከትላል?
-በቀላሉ የመሰበር እድል ከሌሎች ከፍ ያለ ይሆናል
-የጀርባ አጥንት(Vertebral bone #)፣የዳሌ አጥንት ሥብራት፣የመዳፍና የክርን አጥንት ሥብራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
-የዳሌ የአጥንት ሥብራትን ተከትሎ በሽተኛውን ለተጨማሪ እንገልትና ስቃይ ብሎም ቶሎ ካለረታከመ ለሞት ይዳርጋል።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
-የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
-የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል
ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ 0934539128 ይደውሉ።