Aki Speech Therapy

Aki Speech Therapy Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aki Speech Therapy, Alternative & holistic health service, Addis Ababa.

26/03/2025
አኬ የስነ ልሳን(speech therapy clinlic )ደረጃውን ከፍ በማረግ ቁጥር ( 2 ) SPEECH THERAPY CLINLICመክፈቱን በደስታ ይገልፃል  በተጨማሪም የህፃናት መዋያም መክፈ...
05/11/2024

አኬ የስነ ልሳን(speech therapy clinlic )ደረጃውን ከፍ በማረግ ቁጥር ( 2 ) SPEECH THERAPY CLINLIC
መክፈቱን በደስታ ይገልፃል በተጨማሪም የህፃናት መዋያም መክፈታችንን በደስታ እንገልፃለን !!!👏👏👏👏
አድራሻችን:-

-ቁጥር 1 ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ በሚወስደው መንገድ በስተ ግራ በኩል ዳሽን ባንክ ህንፃ ላይ 2ፎቅ ላይ
-ቁጥር 2 24 40/60 ኮንዶሚኒይም ገባ ቡሎ
ስልክ ቁጥር 0903242838/0985365590/0978806778 ይደዉሉ ማንኛዉንም የንግግር ችግሮችን መፍትሄ እንስጣለን የብዙ አመት ልምድ ባላቸው ባለ ሀኪሞች መፍትሄ እንሰጣለን!!!
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፡-
* የህፃናት ማቆያ (ከ6ወር ጀምሮ)
*ማንኛዉም የህፃናት የንግግር ችግር(speech Therapy)
*ማንኛዉም የአዋቂ የንግግር ችግር(speech Therapy)
*የባህሪ ህክምና(ABA Therapy )
*Art Therapy
*ቤት ለቤት speech Therapy
*የአምሮ ህክምና (Psychiatriy )
# የሚሰጥበት ቋንቋ፡-
አማርኛ
ኦሮምኛ
እንግሊዘኛ

በልጆች ላይ የትኩረት ማነስ እና እረፍት የለሽ እንቅሰቃሴ ወይም Attention deficit hyperactive disorder (ADHD) ምንድን ነው? -ADHD ልጆች ላይ በጣም በብዛት የሚ...
03/06/2024

በልጆች ላይ የትኩረት ማነስ እና እረፍት የለሽ እንቅሰቃሴ ወይም Attention deficit hyperactive disorder (ADHD) ምንድን ነው?

-ADHD ልጆች ላይ በጣም በብዛት የሚስተዋል የአእምሮ ጤና እክል ሲሆን ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች በአለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሲሆኑ በአብዛኛው በልጆች ላይ ይስተዋላል እስከ ጎልማሳነት እድሜ ሊቀጥል የሚችል ችግር ነው።

አይነቶቹስ?

-ይህ ችግር ከፍተኛ የሆነ የትኩረት ማነስ ወይም ማጣት (inattention) እና እረፍት የለሽ እንቅስቃሴ ማሳየት (hyperactivity)፣ የሚያስከትለውን ችግር ወይም ብዙ ሳያስቡ ግብታዊ መሆን (impulsivity)፣ ወይም የሁለቱ ውህድ ሊሆን ይችላል።

ማንን ያጠቃል?
-ከሴቶች ይልቅ ወንዶችን በብዛት የሚስተዋል ችግር ነው።

ምልክቶቹስ?

-በአካባቢያቸው ወይም በሌላ ሀሳብ መረበሽ
-ለጥቃቅን ነጠሮች ትኩረት መስጠት አለመቻል

-በግድየለሽነት ስህተት መስራት
-አንዳንድ ተግባራትን ከጀመሩ በዃላ የማስቀጠል ፣ የመጨረስ ችግር ለምሳሌ በክፍል ውስጥ አሰተማሪ እያስተማረ መከታተል ጀምረው ወዲያውኑ ሀሳባቸው መበተን

-ትእዛዝ ያለመቀበል ችግር
-አእምሮን ከሚፈትሹ ስራዎች መራቅ

-ንብረቶቻቸው በአግባቡ መያዝ አለመቻል፣የመጣል ችግር
-የእለት ተእለት እቅስቃሴ የሚደረጉ ነገሮችን የመርሳት ሁኔታ

-እረፍት የለሽ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ማሳየት ወይም ከመጠን በላይ መወራጨት ፣ አርፎ አለመቀመጥ፣ መቅበጥበጥ፣ ማውራት መቆም አለመቻል፣ ረጋ ብሎ ለመጫወት መቸገር፣ በሰው ወሬ፣ በጨዋታ መሀል ያለ ፍቃድ ጣልቃ መግባት፣

አጋላጭ ምክንያቶቹስ?

-ተመራማሪዎች ይህ ነው የሚባል መንሰኤ ባያሰቀምጡም ነገር ግን በዘረመል (genetics) አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል።

-ያለ ጊዜ የተወለዱ ልጆች ፣ በእርግዝና ጊዜ የሚያጨሱ ፣ አልኮል መጠጥ የሚጠጡ እናቶች ፣ በእርግዝና ጊዜ ከመጠን በላይ ጭንቀት

-በአካባቢ የሚገኙ መርዛማ ኬሚካል ተጋላጭ መሆን
-በአንጎል ላይ የሚደርስ ጉዳት

የሚያመጣውስ መዘዝ?

-ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች በቂ እርዳታ ካላገኙ ውሳኔዎችን ለመወሰን መቸገር፣ በትምህርት እና ስራ ላይ ደካማ መሆን፣ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ መሆን፣ ስራ ማጣት፣ ገንዘብን በአግባቡ መጠቀም አለመቻል፣ ለሱስ ተጋላጭ መሆን፣ ራስን ማጥፋት፣ ደካማ የሆነ ማህበራዊ ሂወት ሊያመጣ ይችላል።

ህክምናውስ?

-የአሰተሳሰብን እና የባህርይ ህክምና ይህ ህክምና እንዴት እነዚህን ልጆች መንከባከብ እንደምችል ቤተሰብን እና መምህራን ማስተማርን ያካትታል። ይህ ህክምና ልጆች እዴት ባህሪያቸውን መቆጣጣር እንደሚችሉ፣ ይረዳል ተብሎ ይታሰባል።

-መድሀኒቶች ለምሳሌ stimulants እና non stimulants የሚባሉ ምልክቶቹን ለመቀነስ ይረዳሉ። stimulants መድሀኒቶች የሚሰሩት አንጎል ውስጥ የሚገኙ Dopamine እና Norepinephrine የሚባሉ ኬሚካሎች መጠን በመጨመር ነው። non stimulants የሚሰሩት ደግሞ የNorepinephrine መጠን በመጨመር ነው።

ከወላጅ እና መምህራን ምን ይጠበቃል?

-ADHD ያለባቸው ልጆች ለማስተካከል አጫጭር እና ትኩረት የሚጠይቁ ጨዋታዎችን እና ተግባራትን ማዘጋጀት ፣ ማሳተፍ እና ማበረታታት ከወላጆች እና ከመመህራን የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው።

-ልጆችን በቅጣት ሳይሆን በምክር ለማስተካከል መሞከር፣ ቁጣ እና ስድብ ማስወገድ ለልጆች ስነ ልቦና የተሻለ ነው።

-የልጆቹን ትኩረት ሊበትኑ የሚችሉ ነገሮችን ከአካባቢያቸው ማራቅ እና የጭንቀት መንፈስ ሲታይባቸው ረጋ ባለ መንፈስ ማወያየት የተረጋጉ እና አስተዋይ እንዲሆኑ ያግዛል።

-በሞባይል ስልክ ፣ቴሌቪዥን፣ እና ኮምፒዩተር ላይ የሚያሳልፋትን ጊዜ መቀነስ

-በቂ እንቅልፍ እንዲያገኙ ማገዝ፣የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ የተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴ ለምሳሌ ዮጋ፣ ታይ ቺ የሚባሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የመርሳት በሽታን ለመከላከል የሚረዱ 5 ነጥቦች==========================1) እግርን ሸራ ጫማ ወይም እስኒከር ውስጥ መክተት። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አእምሮ ውስጥ የሚዘዋወረ...
23/05/2024

የመርሳት በሽታን ለመከላከል የሚረዱ 5 ነጥቦች
==========================
1) እግርን ሸራ ጫማ ወይም እስኒከር ውስጥ መክተት። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አእምሮ ውስጥ የሚዘዋወረውን የደም መጠን እና ኦክስጅን ስለሚጨምር አእምሮ እንዳያረጅ ይረዳል።

2) የአእምሮ እንቅስቃሴ ማድረግ። ስፖርት ስንሰራ አካላችን እንደሚፈረጥመውና እንደሚጠነክረው አእምሯችንም እንደዚሁ ነው። አዳዲስ ነገሮችን ስንማር አእምሯችንን ስፖርት እያሰራን ነው።

3) አመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ። እድሜያቸው 65 አመት ከሆናቸው አስር ሰዎች አንዱ የመርሳት በሽታ ይይዘዋል። አንዳንዶቹ የመርሳት በሽታ መንስኤዎች በቀላሉ የሚድኑ አካላዊ ህመሞች ናቸው። ስለዚህ አመታዊ ምርመራ በማድረግ እነዚህን ህመሞች በጊዜ መለየትና ታክሞ መዳን ይቻላል።

4) ስኳርና የደም ግፊትን መቆጣጠር። ከአልዛይመር ህመም ቀጥሎ የመርሳት ህመምን የሚመጣው አእምሮ ውስጥ ደም ሲፈስ ነው።ለዚህ ዋነኛ አጋላጮቹ የስኳር ህመም እና የደም ግፊት ስለሆኑ የደም ግፊትና የስኳር ህመምን መቆጣጠር የመርሳት ህመም እንዳይከሰት ይከላከላል።

5) በእድሜ የገፉ ሰዎች ድባቴ ወይም የእንቅልፍ ችግር ሲያጋጥማቸው የአእምሮ ሀኪም ማማከር። በእድሜ የገፉ ሰዎች ብስጭት ወይም ድብርት ሲሰማቸው ወይም እንቅልፋቸው ሲቀንስ "እርጅና ነው" ብሎ ችላ ከማለት ይልቅ የአእምሮ ሀኪም ማማከር

ያለ አእምሮ ጤና፤ጤና የለም!!!!

11/01/2024

አኪ የስነ ልሳን ሕክምና ክሊኒክ አሁን ደሞ ደረጃውን ከፍ በማድረግ
በ speech therapy nተጨማሪ የብዙ አመት ልምድ ባላቸዉ ሐኪሞች እና ነርሶች
ልዩ እንክብካቤ በሚያደርጉ ነርሶ
ቤት ለቤት የነርስግ አገልግሎት መጀመራችንን በደስታ እንገልፃለን !!! 0903242838 በመደወል ያናግሩን

09/12/2023

ታዲያስ ሁሉም ሰው በቀላል ጊዜ ውስጥ 'የንግግር ሕክምና' ምን እንደሆነ ይረዱ.
በንግግር ሕክምና ውስጥ ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች ንግግር, ቋንቋዎች እና መግባባት በመገንባት ላይ እናተኩራለን. እኛ እነዚህን ነገሮች ለማሳካት ቀላል አዝናኝ አፍቃሪ ተግባሮችን እና የአፍ የሞተር እንቅስቃሴ እናደርጋለን.

Aki Speech TherapyHow to prevent Stroke easily1. Know ur blood pressure2. Eat healthy diet🍎3. Maintain healthy weight🏋4....
29/10/2023

Aki Speech Therapy
How to prevent Stroke easily
1. Know ur blood pressure
2. Eat healthy diet🍎
3. Maintain healthy weight🏋
4. Quit smoking🚭
5. Stay active👟
6. Avoid drinking too much alcohol

October 29 world stroke day

የመንተባተብ እክልየመንተባተብ እክል ምንድነው?🗣የመንተባተብ እክል በመደበኛ ቅልጥፍና እና የንግግር ፍሰት ላይ ተደጋጋሚ እና ትልቅ ችግርን የሚፈጥር የንግግር እክል ነው።🗣 የሚንተባተቡ ሰዎች...
13/09/2023

የመንተባተብ እክል

የመንተባተብ እክል ምንድነው?

🗣የመንተባተብ እክል በመደበኛ ቅልጥፍና እና የንግግር ፍሰት ላይ ተደጋጋሚ እና ትልቅ ችግርን የሚፈጥር የንግግር እክል ነው።

🗣 የሚንተባተቡ ሰዎች መናገር የሚፈልጉትን ያውቃሉ፤ ግን ለመናገር ይቸገራሉ። ለምሳሌ ፣ አንድን ቃል ፣ የሰዋሰው ቃል፣ ተነባቢ ወይም አናባቢ ድምጽን ሊድገሙ ወይም ሊራዘሙ ይችላሉ። በተጨማሪም በንግግር ጊዜ የሚቸገሩበት ቃል ወይም ድምጽ ጋር ሲደረሱ ሊያቆሙ ይችላሉ ፡፡

🗣መንተባተብ በትናንሽ ልጆች ዘንድ የተለመደ ለመናገር የመማሪያ ክፍል ነው።

✔️የንግግራቸውን እና የቋንቋ ችሎታቸውን ለማዳበር እስኪያድጉ ድረስ ትናንሽ ልጆች ሊንተባተቡ ይችላሉ ፡፡ሆኖም አንዳንድ ጊዜ መንተባተብ እስከ ጉርምስና ድረስ የሚቆይ ሥር የሰደደ እክል ነው።

🗣ይህ ዓይነቱ የመንተባተብ እክል በራስ መተማመን እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል ፡፡

የመንተባተብ ምልክቶች

የመንተባተብ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ-
🗣ቃል ፣ ሐረግ ወይም ዓረፍተ ነገር ለመጀመር መቸገር፤

🗣በአንድ ቃል ውስጥ አንድ ቃል ወይም ድምጾች ማራዘም፤

🗣የድምፅ ፣ የቃላት ወይም ሀረጎችን መድገም

🗣ለአንዳንድ ቃላቶች አጭር ዝምታ ፣ ወይም በቃላት ውስጥ ለአፍታ ያቆማል (የተሰበረ ቃል)
ወደ ቀጣዩ ቃል ለመዛወር መቸገር ለምሳሌ"እ" "እንትን"ማለት፤

🗣አንድ ቃል ለማፍራት ፊት ላይ ወይም በላይኛው የሰውነት ክፍል ከልክ ያለፈ ውጥረት ፣ ጭንቀት ወይም በፊት ላይ እንቅስቃሴ፤

🗣ለማውራት መጨነቅ፤

🗣በብቃት የመግባባት ውስን ችሎታ፤

🗣ፈጣን የዓይን ብልጭ ድርግም ማድረግ፤

🗣የከንፈር ወይም መንጋጋ መንቀጥቀጥ፤

🗣የጭንቅላት መነቅነቅ፤

🗣ግለሰቡ በሚደሰትበት ፣ በሚደክምበት ወይም ውጥረት በሚኖርበት ጊዜ ፣ ​​ወይም በራስ የመተማመን ስሜት ሲሰማው ፣ በድንገት ወይም ጫና ሲሰማው መንቀጥቀጥ ሊባባስ ይችላል።

🗣በቡድን ፊት መነጋገር ወይም በስልክ መነጋገር ያሉ ሁኔታዎች በተለይ ለሚንተባተቡ ሰዎች ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

📌ሆኖም የሚንተባተቡ ብዙ ሰዎች ከእራሳቸው ጋር ሲያወሩ እና ከሌላ ሰው ጋር በአንድነት ሲዘምሩ ወይም ሲናገሩ ሳይንተባተባተቡ መናገር ይችላሉ።

👉ለመንተባተብ እክል ሐኪም ወይም የንግግር ቋንቋ ፓቶሎጂስት ጋር መቼ መሄድ አለብዎት?

🔘ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 5 ዓመት ለሆኑት ልጆች ሊንተባተብ የሚችልባቸውን ጊዜያት ማለፍ የተለመደ ነው ፡፡ ለአብዛኛዎቹ ልጆች ፣ ይህ የመናገር የመማር ክፍል ነው ፣ እናም በራሱ ይሻሻላል።

🔘ልጁ እያደገ ሲሄድ በበለጠ እየተደጋገመ ሊቀጥል ይችላል። በዚህ ጊዜ በትምህርት ቤት ፣ በሥራ ቦታ ወይም በማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ውጤታማ የመግባባት ችሎታን ማድረግ ከባድ ይሆናል። በተጨማሪ ጭንቀተና ፍርሀትን ያስከትላል።

🔷 መንተባተብን እንዴት ማከም ይቻላል?

👉 ይህን አይነት እክል ማከም ወይም መከታተል የሚችለዉ የስነ- ልሳን ሀኪም ወይም እስፒች ላንጉጅ ቴራፒሰት (Speech therapy) Akalu assefa (speech pathologist )

ስልክ: 0978806778 / 0903242838
Aki Speech Therapy

14/06/2023

በእስትሮክ ምክንይት ለሚመጡ የንግግር ችግሮች መፈትሔ አላቸዉ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251978806778

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aki Speech Therapy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Aki Speech Therapy:

Share