Health Tips

Health Tips ሰለጤና እናወራለን እናማክራለን

02/02/2025

የሐዘን መግለጫ
============
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በተወለዱ በ37 አመታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።

ዶ/ር አንዷለም በዩኒቨርሲቲያችን፣ ብሎም በአገራችን አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ ያወግዛል። በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን አጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የማር ጥቅሞች፡- 1. የተፈጥሮ ማጣፈጫ፡- ማር ከተጣራ ስኳር የበለጠ ጤናማ አማራጭ ሊሆን ይችላል። 2. የሳል ማስታገሻ፡ ከአንድ አመት በላይ የሆናቸው ህጻናት ሳል እና የጉሮሮ መቁሰል ለማስ...
13/09/2024

የማር ጥቅሞች፡-
1. የተፈጥሮ ማጣፈጫ፡- ማር ከተጣራ ስኳር የበለጠ ጤናማ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

2. የሳል ማስታገሻ፡ ከአንድ አመት በላይ የሆናቸው ህጻናት ሳል እና የጉሮሮ መቁሰል ለማስታገስ ሊረዳ ይችላል።

3. *አንቲኦክሲዳንት*፡ ማር በአጠቃላይ ጤናን የሚደግፉ አንቲኦክሲዳንትስ በውስጡ ይዟል።

4. ለቁስል ፈውስ፡ ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪያት ስላለው ጥቃቅን ቁስሎችን ለማከም ይረዳል።

ቅድመ ጥንቃቄዎች፥

1. የእድሜ ገደብ፡ ማር ከ1 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት በቦቱሊዝም ስጋት ምክንያት መሰጠት የለበትም።

2. አለርጂዎች፡- አንዳንድ ልጆች ለማር ወይም ለክፍለ አካላት አለርጂ ሊሆኑ ይችላሉ።

3. የምንሰጠውን የማር መጠን መመጠን ያስፈልጋል።

የአጠቃቀም ምክሮች፡-
🍀- ማርን በሞቀ ሻይ ውስጥ ወይም ከሎሚ ጋር በመደባለቅ ሳል ለማስታገስ መጠቀም ይቻላል።

🌿እንደ እርጎ ወይም ኦትሜል ባሉ መክሰስ ወይም ቁርስ ላይ ማካተት ይቻላል።
tiktok.com/
https://t.me/btfree44

ማያሲስ ምንድን ነው?ማይያሲስ በዝንብ እጭ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በሞቃታማና በሐሩር ክልል ውስጥ የሚከሰት ነው። አንዳንድ ዝንቦች እንቁላሎቻቸውን በቁስል ወይም በቁስሉ...
22/07/2024

ማያሲስ ምንድን ነው?

ማይያሲስ በዝንብ እጭ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በሞቃታማና በሐሩር ክልል ውስጥ የሚከሰት ነው።

አንዳንድ ዝንቦች እንቁላሎቻቸውን በቁስል ወይም በቁስሉ አጠገብ ያስቀምጣሉ ወይም እንዲደርቅ በተንጠለጠሉ ልብሶች እና የአልጋ ልብሶች ላይ ይጥላል።ከእንቁላሉ የሚፈለፈሉ እጮች ወደ ቆዳ ውስጥ ይገባሉ። የአንዳንድ ዝርያዎች እጭ ወደ ሰውነት ውስጥ ዘልቀው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ.

የ myiasis ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድ ናቸው?

እጮቹ ሲያድግ በቆዳ ውስጥ አንደ እብጠት ይወጣሉ.።ከቆዳው ስር ያሉ እጮች አልፎ አልፎ ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ.።ብዙውን ጊዜ እጮች ከቆዳው በታች ይቀራሉ እና በሰውነት ውስጥ አይጓዙም።

ማዮሲስ እንዴት ይታከማል?

እጮቹ ብዙ ከሆነ በቀዶ ሕክምና ባለሙያ ማስወገድ ያስፈልጋል። እጮቹ ከተወገዱ በኋላ ቁስሉ በየቀኑ ይጸዳል። ብዙ ካልሆነ ቫዝሊን ቁስሉን በመቀባት እጩ እዲታፈን በማድረግ እንዲሞት ማድረግ ይቻላል።

ማዮሲስ እንዴት ያገኘናል?

በስህተት እጮችን በመምጠጥ፣ ዝንቦች እንቁላል በተከፈተ ቁስል ወይም በቁስል አጠገብ እንቁላል ሲጥሉ ወይም በአፍንጫዎ ወይም በጆሮዎ ውስጥ ኢንፌክሽን ገጥመውዎት ሊሆን ይችላል። ሰዎች ትንኞች ወይም እጭ በሚይዙ መዥገሮች ሊነከሱ ይችላሉ። ኢንፌክሽኑ ሊከሰት በሚችል ሞቃታማ አካባቢዎች አንዳንድ ዝንቦች በውጭ በተሰቀሉ ልብሶች ላይ እንቁላሎቻቸውን ይጥላሉ።

በማይያሲስ ኢንፌክሽን እንዴት መከላከል እችላለሁ?

ወደ ሞቃታማ አካባቢዎች በመሄድ እና ብዙ ጊዜ ለማሳለፍ የበለጠ ጥንቃቄ ያድርጉ። ክፍት ቦታውን ለዝንቦች፣ ትንኞች እና መዥገሮች ንክሻ ለመገደብ ቆዳዎን ይሸፍኑ። ፀረ-ተባይ መድሃኒቶችን ይጠቀሙ እና የተጓዦች ጤና መመሪያዎችን ይከተሉ

ማያሲስ በሚታወቅባቸው አካባቢዎች የወባ ትንኝ መረቦችን በመጠቀም እራስዎን ይጠብቁ።

በሞቃታማ አካባቢዎች, ልብሶችን ለማድረቅ ብረት ይጠቀሙ።.
ማያሲስ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም

01/07/2024

ችላ ሊሏቸው የማይገቡ 10 የማህፀን ካንሰር ምልክቶች
➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

1️⃣ ባልተለመደ ሁኔታ ከብልት ደም መፍሰስ
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

የማህፀን ህክምና የሚያደርጉ አብዛኛዎቹ ሴቶች የተዘበራረቀ የደም መፍሰስ ያጋጥማቸዋል።

ለአጭር ጊዜ የሚቆይ በተለመደ ጊዜ የሚከሰት የደም መፍሰስ አንዱ የማህፀን ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።

ይህ የደም መፍሰስ በሌሎች የጤና እክሎች ሊያጋጥም ይችላል።

👉👉👉 ከእነዚህም መካከል:-

🔸የሆርሞኖች አለመመጣጠን፣
🔸የዳሌ ህመምና
🔸የዳሌ አካባቢ አካሎች ኢንፌክሽን ናቸው።

ካንሰሩ በአቅራቢያ ወደሚገኙ የሰውነት ክፍሎች በሚዛመትበት ጊዜ በቀላሉ የሚቀደዱ ወይም የሚበጠሱ ትናንሽ የደም ቧንቧዎችን በመፍጠር በቀላሉ የደም መፍሰስ እንዲከሰት ያደርጋል።

ይህ የደም መፍሰስ በወር አበባ ዑደት መካከል፣ ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት በኋላ እና ከዘመነ እርጠት በኋላ ሊያጋጥም ይችላል።

በወር አበባ ዑደት መካከል ወይም ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት በኋላ የደም መፍሰስ የሚያጋጥምዎት ከሆነ ወደ ህክምና መስጫ ተቋም መሄድ ይኖርብዎታል።

2️⃣ ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

ሽታ የሌለው ንጹህ የብልት ፈሳሽ ጤናማ ሲሆን ይህ የብልት ፈሳሽ መጠን እየጨመረ ከሄደ፤ መጥፎ ሽታ ካለው ወይም ያልተለመደ ወይም የተለየ እይታ ወይም መልክ ካለው የኢንፌክሽን ወይም የማህፀን ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።

በማህፀን ካንሰር የተያዙ ከሆነ ፈሳሹ ከባድ ወይም ወፍራም፣ አመድ የመሰለ ቀለም፣ ውሃማ፣ ቡናማ ወይም ከደም ጋር የተቀላቀለ ሊሆን ይችላል፡፡

3️⃣ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት መሰማት
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

ህመም ያለው የግብረ ስጋ ግንኙነት አንዱና ዋነኛው የማህፀን ካንሰር ምልክት ነው፡፡

ይህ ምልክት ያለብን ያለብን የማህፀን ካንሰር በሽታ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል።

ይህ ማለት፤ ካንሰሩ በአቅራቢያ ወደሚገኙ የመራቢያ አካሎች ተዛምቷል ማለት ነው።

ከህመሙ በተጨማሪ፤ ወፍራምና መጥፎ ሽታ ያለው ፈሳሽ ይኖራል።

4️⃣ የዳሌ ህመም
🚤🚤🚤🚤🚤

የዳሌ ህመም በሴቶች ላይ የሚታይ የተለመደ ምልክት ነው።

በተጨማሪም በወር አበባ ጊዜ ቁርጠትና ህመም የሚታዩ ምልክቶች ስለሆኑ ካንሰር ወይም ሌላ ከባድ ችግር እንዳለብን አመላካች አይደሉም።

ነገር ግን ለረጂም ጊዜ የሚቆይና በተደጋጋሚ የሚከሰት ህመም የማህፀን ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።

በማህፀን ካንሰር የሚሰቃዩ ከሆነ ባልተለመደ ሠዓት የሚከሰትና በወሩ በማንኛውም ቀን ወይም ጊዜ የሚጀምር ድንገተኛ የዳሌ ህመም ያጋጥማል።

በተጨማሪም፤ የዚህ ዓይነት ህመም ካጋጠመን ያለብን የካንሰር ህመም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑን አመላካች ነው።

5️⃣ ሽንት በሚሸኑበት ጊዜ ምቾት ማጣት
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

የማህፀን ካንሰር ሽንት በሚሸኑበት ወቅት ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል።

ይህ በጣም የተለመደ የዚህ ገዳይ በሽታ ምልክት ነው፡፡

በሚሸኑበት ወቅት ምቾት ማጣት የሚከተሉትን ምልክቶች ያጠቃልላል:-

🔹ማቃጠል፣
🔹በስለት የመወጋት ዓይነት ስሜት ወይም
🔹በሚሸኑበት ወቅት የማጣበቅ ወይም
🔹የሽንት ቧንቧ መጥበብ ዓይነት ስሜት ናቸው።

እነዚህ ምልክቶች ካንሰሩ በቅርብ ወደሚገኙ አካሎች በሚዛመትበት ወቅት ይከሰታሉ።

ስለዚህ ሌሎች ጉዳቶች ከመድረሱ በፊት ጥንቃቄ ያሻዋል፡፡

ነገር ግን በሚሸኑበት ወቅት ምቾት ማጣት ሌሎች መነሻዎች ሊኖሩት ይችላሉ ከነዚህም መካከል:-

🔸የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን
🔸የሽንት ፊኛ ችግር
🔸የ ይስት ኢንፌክሽን ወይም
🔸በግብረ-ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ናቸው፡፡

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

6️⃣ ከባድና ለረጂም ጊዜ የሚቆይ የወር አበባ ዑደት
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

ከባድና ለረጂም ጊዜ የሚቆይ የወር አበባ ሌላኛው የተለመደ የማህፀን ካንሰር ምልክት ነው።

የማህፀን ካንሰር በሚዛመትበት ወይም በሚራባበት ጊዜ የማህፀን መቆጣት ይከሰታል።

የሚፈስዎት የወር አበባ ወይም ደም ከባድ ሊባል የሚችለው በሁለት (2) ሠዓት ልዩነት ሞዴስ የሚቀይሩ ከሆነ ነው።

ከካንሰሩ በተጨማሪ፤ ከፍተኛ ወይም ከባድ የደም መፍሰስ በሆርሞኖች አለመመጣጠን፣ የዳሌ ኢንፍላሜሽን ህመም፣ የታይሮይድ በሽታ፣ የጉበት በሽታ እና የኩላሊት በሽታ ሲሆኑ በአንዳንድ መድሃኒቶችም ሊከሰት ይችላል፡፡

7️⃣ የሽንት ፊኛን አለመቆጣጠር
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

እርጉዝ ሴቶች እና በብዛት ፈሳሽ ነገር የጠጣ ሰው ወደ ሽንት ቤት መመላለስ የተለመደ ነው።

ምንም በማያውቁት ምክንያት ይህ ችግር ካጋጠምዎት ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልግዎታል ማለት ነው።

በማህፀን ካንሰር የሚሰቃዩ ሴቶች የሽንት ፊኛ መዘጋት የመጀመሪያ አንገብጋቢ ችግር ነው።

ይህ ችግር የሚያሳየው ያለብን የማህፀን ችግር ከማህፀን አልፎ ወደ ሽንት ፊኛና በአቅራቢያ ወደሚገኙ የሽንት ቧንቧዎች መዛመቱን ነው።

የማህፀን ካንሰር ህመም ኖሮባቸው ህክምና እየወሰዱ የሚገኙ ሰዎች የሽንት ፊኛ መቆጣጠር ችግርና በሽንት ውስጥ ደም ይታይባቸዋል።

8️⃣ የሰውነት ክብደት መቀነስ
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

በካንሰር በሚያዙበት ወቅት በሽታ የመከላከል ስርዓታችን ካንሰሩን ለመዋጋት በከፍተኛ ሁኔታ ይሰራል።

ሰውነታችን ሳይቶኪን (Cytokines) የተባሉ ትናንሽ ፕሮቲኖችን ያመርታል።

እነዚህ ሳይቶኪኖች ፋትን ወይም ቅባትን ከተለመደው ፍጥነት በላይ ይሰባብሩታል።

ይህም ከአመጋገብዎ ሁኔታ አንፃር የክብደት መቀነስ እንዲከሰት ያደርጋሉ።

በፍጥነት ክብደት የሚቀንሱ ከሆነና በዚህ ጽሁፎች ውስጥ የተካተቱ ሌሎች ምልክቶች የሚታይብዎት ከሆነ፤ የማህፀን ካንሰር አጋጥሞዎት ሊሆን ስለሚችል የህክምና ቼክአፕ ወይም ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው።

9️⃣ ዘወትር የድካም ስሜት መሰማት
🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤

ስራ በሚበዛብን ቀን ማንኛውም ሰው በጣም ይደክመዋል፤ ነገር ግን ትንሽ እረፍት በሚያደርጉበት ጊዜ መንፈስዎ ታድሶና ሃይል አግኝተው ይነቃሉ።

በቂ እረፍት አድረገው አብዛኛውን ጊዜ የድካም ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ ጉዳዩ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል።

በካንሰር በሚያዙበት ጊዜ ጤናማ የሆኑ ቀይ የደም ሴሎች በሽታውን ለመከላከል በነጭ የደም ሴሎች ይተካሉ።

ይህ ሁኔታ የደም ማነስ በማስከተል ድካም፣ የሃይል መቀነስና የምግብ ፍላጎት መቀነስ እንዲፈጠር ያደርጋል።

በተጨማሪም ለሰውነታችን የሚደርሰው ኦክስጅን እንዲቀንስ ያደርጋል።

ደም ማነስ የሚከሰት ከሆነ ካንሰሩ በፍጥነት እየተራባ መሆኑን የሚያሳይ የማስጠንቀቂያ ምልክት ስለሆነ በጣም በፍጥነት መታከም አለብዎት።

🔟 የእግር ህመም
🚤🚤🚤🚤🚤🚤

የማህፀን ካንሰር ህመም ያለባቸው ሴቶች የእግር ማበጥና ህመም ይታይባቸዋል።

ካንሰሩ በሚዛመትበት ጊዜ የደም ዝውውርን ይዘጋል ይህም እግር እንዲያብጥ ያደርጋል።

ያበጠው እግር ቁስልና ከፍተኛ የህመም ስሜት በመፍጠር የቀን ከቀን ሥራችንን ወይም ተግባራችንን ለመወጣት እንዲያዳግተን ያደርጋል።

በካንሰር ምክንያት የተከሰተ ከሆነ ህመሙ ቀጣይነት ያለውና ከቀን ወደቀን እየጨመረ የሚሄድ ነው። አንዳንድ ጊዜ የጀርባ ህመም ሊኖር ይችላል።

ማስታወስ የሚገባን ጉዳይ እግራችንን አመመን ማለት ካንሰር አለብን ማለት አይደለም።

የእግር ህመም ካለብዎትና ከላይ ከተጠቀሱት ጥቂት ምልክቶች ለጥቂት ሳምንታት የሚታይብዎት ከሆነ በሃኪም ምርመራ ቢደርግልዎት መልካም ነው።

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

✅ የመከላከያ መንገዶች
🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️

🍑 እድሜያቸው ከ20-30 አመት ላይ የሚገኙ ሴቶች በሶስት (3) ዓመት ልዩነት የጤና ምርመራ ማድረግ አለባቸው።

እድሜያቸው ከ30-65 አመት ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ደግሞ ከ3-5 ዓመት ልዩነት የጤና ምርመራ ማድረግ አለባቸው።

🍑 እድሜሽ 20 ዎቹ ውስጥ ከመግባቱ በፊት የሄፓታይተስ ቫይረስ ክትባት ይውሰዱ።

🍑 ሲጋራ ማጨስሽን አቁሚ ከሁለተኛ ወገን የሲጋራ ጭስ እራስሽን አርቂ።

🍑 በግብረ-ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ውሰጂ።

🟪 ጠቃሚ መረጃ ነውና ለወዳጆችዎ ያካፍሉ 🟪

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️
ምንጮች:- Daily Mail, WebMD & Health-line.
➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️

ጽሑፉን ከወደዱት (Like) በማድረግ ለሌሎችም (Share) ያድርጉት፡፡ ቸር እንሰንብት

#ኢትዮጤና

➖〰️➖〰️➖〰️
መልካም ጤንነት!!
➖〰️➖〰️➖〰️

ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት፤ የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይከታተሉ።

Facebook🚦https://www.facebook.com/EthioTena
YouTube🚦https://youtube.com/
TikTok🚦https://tiktok.com/
Telegram🚦https://t.me/ethiotenadaniel
Instagram🚦https://instagram.com/ethiotena
Facebook Group🚦https://m.facebook.com/groups/EthioTena/

01/07/2024

የአዕምሮ ጤና እና የኛ ህብረተሰብ

ህዝባችን (እኔን ጨምሮ) ለአእምሮ ህመም ያለው ግንዛቤ በጣም አናሳ ነው። አንዱ ተነስቶ በጫማ ጥፊ ሴጣንህን ዘረኩት ሲልህ "ና ወንድሜ ታከመው" ማለትህን ትተህ አሜን ትልለታልህ።

እኔ በዓሎችን በራሴ ነው ማከብረው ንግስትም ነኝ ስትልክ "እህቴ ነይ ታከሚው" ከማለት ይልቅ ትከተላታለህ ወይ ቀልደህ ታልፋታለህ።

የፍቅር አምላክ ሁለቴ የተለያየ ቦታ ይፈጥርሃል ሲልህ "ታከመው ወንድሜ" ማለትህን ትተህ ታላግጥበታለህ።

'ችግር' የሚለውን ቃል የፈጠሩት ፊደላት 6ኛ ፊደል ስለሆኑ 666 ነው ሲልህ ታከመው ማለትህን ትተህ "ቃለ ህይወት ያሰማልን" ትላለህ።

እና አንድ እህትህ "ህይወት መሮኛል፣ መኖር ደክሞኛል፣ ደብሮኛል" ስትልህ... አይዞሽ ባክሽ ሁሉም እንደዛው ነው ብለህ ታልፋለህ እንጂ ነይ እስኪ ታይው ታከሚው አትልም። ስለምታውቀው ስለማታውቀው ገጠመኞችህ ዘባርቀህላት፣ "አይዞሽ ፈታ ማለት ነው" ብለህ ታልፋለህ።

ትኩሳት ብታይበት፣ ደም ቢፈሰው፣ እራሱን ቢስት እኮ ይዘህ ወደ ሆስፒታል ትሮጣለህ። የአዕምሮ ህመምን እና ምልክቶቹን ግን የሂወት አጋጣሚ አርጋ እንድትቆጥረው አርገህ ታልፋታለህ ወይም "ሴት ወዶ ኮ ነው እንዲህ የሆነው" ወይንም "አስደግመውባት ኮ ነው እንዲ ምታረገው" ብለህ ከንፈርህን ትመጣለህ እንጂ ታከሚው እናሳክማት አትልም።

በዚህም ምክንያት ለሚመጡ መዘሶችም ሁሉ በማወቅም ባለማወቅም፣ በቸልተኝነትም ባለመገንዘብም ተጠያቂ አንተ እራስህ፣ እኔ እራሴ፣ እኛ ሁላችንም ነን።

ለአዕምሮ ህመም ክብደት እንስጠው፣ ግንዛቤ ይኑረን፣ አደገኛ እንደሆኑ እንገንዘብ! በጓደኞቻችን፣ በቤተሰብ አባሎቻችን የምናየውን የባህሪ ለውጦችን እንደቀላል ነገር ችላ አንበል። እንታከም! እናሳክም! ስቃያቸውን እናስታግስላቸው!

ያለ አዕምሮ ጤና ጤና የለም!
ስለአዕምሮ ህመም ጥልቅ ግንዛቤን ለማግኘት በባለሙያዎች የሚተላለፉልንን እንደ ' Mental wellness የአእምሮ ጤና ' የመሳሰሉ ገፆች እንከታተል!

ዶ/ር መላኩ አባይ የስነ ደዌ ስፔሻሊስት

01/07/2024

Wiixataa hanga Sanbata xiqqaa!

Magaalaa Jimmaa
Hoteela Boonii Cinaa!

01/07/2024

የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ፍቅሬ ወርቅነህ

በህጻናት ላይ   ምልክቶች ምንድን ናቸው?1.በጎን እና በጎን ያለ ህመም (flank pain)2.የሽንት ከለር ቀይ መሆን3.የሽንት መጠን መቀነስ ወይም አለመኖር4.የሰውነት ማበጥ __በተለይ ከ...
01/07/2024

በህጻናት ላይ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

1.በጎን እና በጎን ያለ ህመም (flank pain)
2.የሽንት ከለር ቀይ መሆን
3.የሽንት መጠን መቀነስ ወይም አለመኖር
4.የሰውነት ማበጥ __በተለይ ከፊት የጀመረ እብጠት
5.በጎን በኩል የሚዳሰስ እብጠት( flank mass)
6.የደም ግፊት መጨመር
እኒህን የመስሉ የህመም ምልክቶች ሲያዩ የህጻናት ሀኪም ያማክሩ
የቴሌግራም ቻናላችንን በዚህ https://t.me/+vG_CAkvv7mQ0NWZk ያገኛሉ

ሰላም  ፤ ዛሬ በተለምዶ  ጭርት (Tinea corporis) ስለሚባለው በሽታ ይዤላቹ ቀርቢያለሁጭርት ምንድን ነው?- ጭርት (tinea corporis) የምንለው በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ፣ ...
11/06/2024

ሰላም ፤ ዛሬ በተለምዶ ጭርት (Tinea corporis) ስለሚባለው በሽታ ይዤላቹ ቀርቢያለሁ

ጭርት ምንድን ነው?

- ጭርት (tinea corporis) የምንለው በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ፣ በሁሉም የእድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን ከሰው ወደ ሰው፣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ፣ በንክኪ የሚተላለፍ የላይኛውን የቆዳ ክፍል የሚያጠቃ በሽታ ነው።

ከየት ሊይዘን ይችላል?

-በበሽታው ከተያዙ ሰዎች፣ከተለያዩ የቤት እና የዱር እንስሳቶች፣ ከአፈር ሊሆን ይችላል። በተለይ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተጠቀመበትን እንደ ፎጣ፣ አልጋ ልብስ፣ ካልሲ፣ የፀጉር ማበጠሪያ በጋራ መጠቀም እና ንክኪ መፍጠር ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።

አጋላጭ ምክንያቶቹስ ምንድን ናቸው?

-ሞቃታማ እና እርጥበታማ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች፣ ሰውነትን የሚያጣብቁ ልብሶችን መልበስ፣ ደካማ የበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች፣ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ ከመጠን በላይ ላብ የሚያልባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምልክቶቹስ?

-አንድ ሰው ተጋላጭ ከሆነ በዃላ ከ4-14 ቀን ምልክት ሊያሳይ ይችላል። በሰውነት ላይ ክብ ክብ የሆነ ፣ ጠርዝ ጠርዙ ቀላ ያለ (erythematous)፣ የማሳከክ ስሜት ሊኖረው የሚችል እየሰፋ የሚሄድ እንደ ቅርፊት (scaly)፣ የተሰነጠቀ (cracked) የሚመሰስል ነገር ሊወጣ ይችላል።

ምርመራዎቹስ

-የህክምና ባለሙያው በቆዳ ላይ የወጣውን ነገር አይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ከቆዳ ላይ ናሙና በመውሰድ በቤተ ሙከራ በmicroscope በመታገዝ ፈንገስ መኖር አለመኖሩን ሊያረጋግጥ ይችላል።

የሚያመጣውስ መዘዝ?

-በተለይ ደካማ ዠበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች ለምሳሌ (HIV ህመምተኞች፣ የካንሰር ህክምና የሚወስዱ) በቶሎ በሽታውን ለማስወገድ ሊቸገሩ ይችላል።

-የሚያሳክክ፣ የተቆጣ እና የቆዳ መሰንጠቅ ሲኖር ለሌላ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን (secondary bacterial infection) ሊጋለጡ ይችላሉ።

አእዴት መከላከል እንችላለን?

-የግል እና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ

-ሰውነታችነንን ከታጠብን በዃላ በንፁህ ፎጣ ወይም ጨርቅ በደንብ ማድረቅ

-የግል መጠቀም ያልብንን ነገሮች በጋራ አለመጠቀም

-በተቻለ መጠን በዚህ በሽታ ከተበከሉ እንስሳት ንክኪ አለመፍጠር፣ በአካባቢያችን የታመሙም እንስሳት ካሉ የእንስሳት ሀኪም ጋር በመውሰድ ማሳከም ተገቢ ነው።

ህክምናውስ?

-እነደ ወጣበት ቦታ እና ስፋት የሚወሰን ሲሆን በቦታው ላይ የሚቀባ ፀረ ፈንገስ ወይም የሚዋጥ ፀረ ፈንገስ በሀኪም ሊታዘዝ ይችላል።

ለወገንዎ ያጋሩ ፤ ጤና ይብዛላቹ
ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ

የህፃናት የሩማቲክ የልብ በሽታ መከላከልየሩማቲክ የልብ ሕመም (RHD) በልጆች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል, ነገር ግን በአብዛኛው መከላከል ይቻላል. የልጆች የሩማቲክ የልብ በሽታን...
30/05/2024

የህፃናት የሩማቲክ የልብ በሽታ መከላከል

የሩማቲክ የልብ ሕመም (RHD) በልጆች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል, ነገር ግን በአብዛኛው መከላከል ይቻላል. የልጆች የሩማቲክ የልብ በሽታን ለመከላከል አንዳንድ ቁልፍ ስልቶች እዚህ አሉ

1. የጉሮሮ እንፌክሽን በፍጥነት መታከም:-

* የስትሮፕቶኮካል ጉሮሮ ኢንፌክሽኖች ህክምና ካልተደረገላቸው ወደ (Rheumatic fever) ሊያመራ ይችላል ይህም ለሩማቲክ የልብ ሕመም ትልቅ አደጋ ነው:: የ (Rheumatic fever) ለመከላከል የጉሮሮ እንፌክሽን በተመጣጣኝ አንቲባዮቲኮች በፍጥነት መመርመር እና መታከም አስፈላጊ ነው::

2. ፕሮፊላቲክ አንቲባዮቲኮች፡-

* የሩማቲክ ትኩሳት ክፍል ያጋጠማቸው ወይም የሩማቲክ የልብ ሕመም ያለባቸው ሕፃናት ለረጅም ጊዜ የሚከላከሉ አንቲባዮቲኮችን መውሰድ አለባቸው። ይህ ተደጋጋሚ የጉሮሮ በሽታን ለመከላከል ይረዳል, ይህም ተጨማሪ የ (Rheumatic fever) ያስከትላል.

3. በቂ የጤና ትምህርት እና ለማግኘትም መዘጋጀት:-

* ልጆችን እና ቤተሰቦቻቸውን የአፍ ንጽህናን የመጠበቅን አስፈላጊነት እና ለማንኛውም የጉሮሮ ህመም ምልክቶች አፋጣኝ የሕክምና ክትትል እንዲደረግ ማስተማር። ይህ መደበኛ የጥርስ እንክብካቤን፣ የትምባሆ ጭስ መጋለጥን ማስወገድ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ማስተዋወቅን ይጨምራል።

4. የጤና እንክብካቤ ማግኘት፡-

* መደበኛ ምርመራዎችን እና ክትባቶችን ጨምሮ ህጻናት ጥራት ያለው የጤና አጠባበቅ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ። የጉሮሮ እና ሌሎች ኢንፌክሽኖችን አስቀድሞ ማወቅ እና መቆጣጠር የሩማቲክ የልብ በሽታን ለመከላከል ይረዳል።

5. የተሻሻለ የኑሮ ሁኔታ መፍጠር እና ማመቻቸት:-

* እንደ መጨናነቅ፣ ድህነት እና ንፁህ ውሃ እና ንፅህና አጠባበቅ አለመሟላት ያሉ ማህበራዊ የጤና ጉዳዮችን መፍታት። እነዚህ ምክንያቶች ከሩማቲክ የልብ ሕመም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ኢንፌክሽኖች እንዲስፋፉ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ.

6. ህክምናን ማክበር እና መከታተል:-

* በተደጋጋሚ የጉሮሮ እንፌክሽን ለመከላከል እና የሩማቲክ Fever ስጋትን ለመቀነስ የታዘዙትን አንቲባዮቲኮች እና የሕክምና ዘዴዎችን በጥብቅ መከተልን ማበረታታት.

7. ማህበረሰብ አቀፍ የመከላከያ ፕሮግራሞች ላይ መሳተፍ እና የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር መሞከር

* ስለ ሪህማቲክ የልብ ሕመም ግንዛቤን ለማሳደግ፣ ጤናማ ኑሮን ለማስፋፋት እና የጉሮሮ እና የቁርጥማት ምልክቶች አስቀድሞ ለማወቅ እና ለመቆጣጠር የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን ለማግኘት ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ ፕሮግራሞችን መተግበር እና መሳተፍ::

#ማሳሰቢያ:- በልጁ ልዩ ፍላጎቶች እና ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ለህፃናት የሩማቲክ የልብ በሽታ አጠቃላይ የመከላከያ እቅድ ለማዘጋጀት እንደ የሕፃናት ሐኪሞች ወይም የልብ ሐኪሞች ካሉ የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች ጋር በቅርበት መስራት አስፈላጊ ነው::

ዶ/ር ሳቦና ለሜሳ (የህፃናት ስፔሻሊስት ሃኪም)

ጅማ ዩኒቨርሲቲ

ጥያቄ 5 ህጻናትን ማስገሳት የምናቆመው መቼ ነው?መልስ: ማስገሳት የምናቆመው በራሳቸው ማግስት እስኪችሉ ድረስ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ከ6ወር በላይ ሲሆኑ የጉሮሮ እና የምግብ መውረጃ ጡንቻዋቻ...
27/05/2024

ጥያቄ 5
ህጻናትን ማስገሳት የምናቆመው መቼ ነው?

መልስ: ማስገሳት የምናቆመው በራሳቸው ማግስት እስኪችሉ ድረስ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ከ6ወር በላይ ሲሆኑ የጉሮሮ እና የምግብ መውረጃ ጡንቻዋቻቸው ሰለሚጠነክሩ በራሳቸው ማጋሳት ይጀምራሉ።

ጥያቄ 4ጡት ለሚጠቡ ህጻናት መቼ ነው ውሀ መስጠት የምንጀምረው?መልስ: የእናት ወተት በቂ የውሀ መጠን ስላለው ከ6 ወር በታች ላሉ ህጻናት ውሀ መስጠት አያስፈልግም።ከስድስት ወር በሀላ ግን ...
25/05/2024

ጥያቄ 4
ጡት ለሚጠቡ ህጻናት መቼ ነው ውሀ መስጠት የምንጀምረው?
መልስ: የእናት ወተት በቂ የውሀ መጠን ስላለው ከ6 ወር በታች ላሉ ህጻናት ውሀ መስጠት አያስፈልግም።ከስድስት ወር በሀላ ግን ጠጣር ምግቦች ሰለሚጀምሩ መስጠት ይገባል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251923599030

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health Tips posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Health Tips:

Share