Dr yimer

Dr yimer Pediatrics Resident

13/04/2025

✅ Scoliosis: Lateral curvature of the spine >10°, often with vertebral rotation.

Etiology
✔️ Idiopathic (most common) – Especially in adolescents (F > M)
✔️ Congenital – Vertebral anomalies (e.g., hemivertebra)
✔️ Neuromuscular – Cerebral palsy, muscular dystrophy
✔️ Syndromic – Marfan syndrome, neurofibromatosis

Clinical Features
✔️ Asymmetry in shoulder or hip height
✔️ Rib hump on forward bend test (Adam’s test)
✔️ Usually painless
✔️ Severe cases → Restrictive lung disease

Diagnosis
✔️ Standing spinal X-ray
✔️ Cobb angle measurement (≥10° diagnostic)

Management
✔️ 40–50°: Surgical correction (spinal fusion)

✅ Kyphosis: Excessive forward curvature of thoracic spine (>40–45°)

Etiology
✔️ Postural kyphosis – Common, flexible, correctable
✔️ Scheuermann disease – Juvenile structural kyphosis (wedge-shaped vertebrae)
✔️ Osteoporotic compression fractures – Elderly
✔️ Congenital or traumatic causes

Clinical Features
✔️ Hunchback appearance
✔️ Back pain (variable)
✔️ Decreased height in elderly
✔️ Severe kyphosis → Restrictive lung pattern

Diagnosis
✔️ Lateral spinal X-ray – Measures kyphotic angle
✔️ MRI – If neurologic symptoms or atypical presentation

Management
✔️ Postural – Physical therapy
✔️ Scheuermann’s – Bracing, surgery if severe
✔️ Osteoporotic – Bisphosphonates, vertebroplasty for fractures

10/04/2025

#ለምፅ (Vitiligo)
====
👉ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት (acquired) የቆዳ ቀለም ባለመመረቱ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው

👉ለምፅ በንክኪ አይተላለፍም

👉ለምፅ ከህጻናት ጀምሮ በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ሊታይ ይችላል

?
======
👉ምክንያቱ ይሄ ነው ተብሎ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ፤ የተለያዩ መላምቶች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፤ከነዚህም መካከል "የሰውነታችን በሽታ የመከላከያ ስርአት (immunity system) የራሳችንን የቆዳ ቀለም አምራችህዋሳትን (melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው" የሚለው መላምት በይበልጥ ተቀባይነት አለው።

በዚህም ምክንያት ለምጽ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚከሰቱ ሌሎች ህመሞች (autoimmune diseases) ጋር ተያያዥነት አለው ተብሎ ይታሰባል ፤ ለምሳሌ ከየስኳር ህመም፣ የእንቅርት ህመም (autoimmune type)፣ ላሽ (alopecia areata)....

👉ለምፅ ከጭንቀት (emotional stress)፣ ከእርግዝና፣ ከአደጋ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል


======
👉ለምጽ ያለበት ቦታ ወደ ነጭነት የሚያደላ ቀለም ሲኖረው ከዚህ ውጪ ማሳከክ ወይም ቦታው ላይ ቅርፍቶች መኖር የለምጽ ባህሪ አደለም

👉በማንኛውም የቆዳችን ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

👉ለምፅ አንድ ቦታ ላይ ብቻ (focal)፣ በግራ ወይም በቀኝ የሰውነት ክፍል ብቻ (segmental) ወይም አብዛኛው የቆዳችኝ ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል


=====
👉የህክምናውን አይነት የሚወስኑ ሁኔታዎች ፦
🔹የህመሙ ጥንካሬ (severity)
🔹እየተስፋፋ መሆኑ ወይም ባለበት መቆሙ
🔹የህክምናው በቀላሉ መገኘት እና የህመምተኛው የመክፈል አቅም...


=====
🔹የሚዋጥ
🔹 የሚቀባ
🔹 Phototherapy (ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ ብርሀንን በመጠቀም የሚሰጥ ህክምና)
🔹የቀዶ-ጥገና (surgery) ህክምና
🔹የማንጣት ህክምና (depigmentation)
አብዛኛው የሰውነት ክፍል በለምፅ ከተጠቃ እና ለማከም አስቸጋሪ ከሆነ ጤነኛውን የቆዳ ክፍል በማንጣት የማመሳሰል ሂደት ነው (Michael Jackson ይህ ህክምና ተደርጎለታል)


======
👉አብዛኛውን ጊዜ በህክምና ሙሉ ለሙሉ አይጠፋም። ህክምናውም አጥጋቢ የሚባል አይደለም።

👉የህክምናው ዓላማ መስፋፋቱን ለመቀነስ እና ቆዳ በተወሰነ መልኩ ወደ ቀድሞ ቀለሙ እንድመለስ ማድረግ ነው።

👉ህክምናውን ከጀመርን በኋላ የህክምናውን ውጤት ለማየት ከ 2-3 ወር ሊፈጅ ይችላል

👉ጠቅላላ ህክምናው ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ያለማቋረጥ መከታተል ያስፈልጋል

👉ህክምናው ከተጠናቀቀ በኋላ ለምፁ እንደገና ሊመለስ ይችላል

👉ከንፈር ላይ፣ጣት ላይ እንዲሁም ከቆዳው በተጨማሪ ፀጉርም አብሮ ነጭ ከሆነ የመዳን እድሉ ዝቅተኛ ነው

?
=====
🔹ለምፅ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ጫና ያሳድራል
🔹እየሰፋ ሊሄድ ይችላል
🔹ቆዳችን በፀሐይ ጨረር እንዲጠቃ ሊያረግ ይችላል (ፀሐይ መከላከያ/sunscreen መጠቀም ያስፈልጋል)

#በመጨረሻም

ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል‼️

#ምንጮች
1. American Acadamy of Dermatology
2. DermNet
3. Yale Medicine

09/04/2025

✅ Vitamin B12 Deficiency Causes
Vitamin B12 deficiency occurs when the body lacks adequate levels of vitamin B12, essential for red blood cell formation, neurological function, and DNA synthesis. It can result from various dietary, absorption, and medical factors.

✔️ Dietary Causes:
→ Inadequate Intake: Common in vegetarians and vegans as B12 is primarily found in animal products like meat, fish, eggs, and dairy.

✔️ Malabsorption Issues:
→ Pernicious Anemia: An autoimmune condition that impairs vitamin B12 absorption due to lack of intrinsic factor.
→ Gastrointestinal Disorders: Conditions like Crohn’s disease, celiac disease, or bacterial overgrowth affecting the small intestine.
→ Gastrointestinal Surgeries: Procedures like gastric bypass, gastrectomy, or bowel resection that reduce absorption.

✔️ Medication-Related Causes:
→ Proton Pump Inhibitors (PPIs) and H2 Blockers: Long-term use reduces stomach acid, necessary for B12 absorption.
→ Metformin: Commonly prescribed for type 2 diabetes; may interfere with B12 absorption.

✔️ Other Causes:
→ Alcoholism: Can interfere with vitamin absorption and utilization.
→ Aging: Reduced stomach acid production in older adults affects B12 absorption.

⭐ Untreated vitamin B12 deficiency can lead to anemia, nerve damage, and cognitive impairment. Early diagnosis and management are essential.

✅ Guillain-Barré Syndrome (GBS): Acute, immune-mediated demyelinating polyneuropathy affecting peripheral nerves.Most co...
07/04/2025

✅ Guillain-Barré Syndrome (GBS): Acute, immune-mediated demyelinating polyneuropathy affecting peripheral nerves.

Most common cause of acute flaccid paralysis in developed countries.

🔹 Etiology
✔️ Often preceded by respiratory or gastrointestinal infection (e.g., Campylobacter jejuni, CMV, EBV, Mycoplasma pneumoniae).
✔️ Post-vaccination (rare).
✔️ Molecular mimicry: Immune system attacks myelin or axons of peripheral nerves.

🔹 Pathophysiology
✔️ Autoimmune attack on peripheral nerve myelin (AIDP - most common subtype) or axons (AMAN, AMSAN subtypes).
✔️ Segmental demyelination and inflammation of peripheral nerves and nerve roots.

🔹 Clinical Features
✔️ Ascending symmetric muscle weakness (lower limbs → upper limbs).
✔️ Absent or decreased deep tendon reflexes (areflexia).
✔️ Paresthesia and numbness.
✔️ Autonomic dysfunction (e.g., tachycardia, BP fluctuations, urinary retention).
✔️ Respiratory muscle involvement (severe cases).

🔹 Diagnosis
✔️ Clinical presentation (progressive, symmetric weakness with areflexia).
✔️ CSF Analysis (Albuminocytologic dissociation):

↑ Protein, Normal cell count.
✔️ Electrophysiological studies (Nerve conduction study):

- Decreased conduction velocity, prolonged distal latency.

🔹 Management
✔️ Supportive care (e.g., respiratory support if needed).
✔️ IVIG or Plasma exchange (plasmapheresis):

- Effective in reducing recovery time.
✔️ Avoid corticosteroids (ineffective).

🔹 Complications
✔️ Respiratory failure (most serious).
✔️ Autonomic instability.
✔️ Persistent weakness or residual neurological deficit (rare).

✅ Sturge-Weber Syndrome (SWS): Congenital, non-inherited neurocutaneous disorder with vascular malformations affecting s...
06/04/2025

✅ Sturge-Weber Syndrome (SWS): Congenital, non-inherited neurocutaneous disorder with vascular malformations affecting skin, brain, and eyes.

Sporadic mutation in GNAQ gene.

🔹 Pathophysiology
✔️ Somatic mosaic mutation in GNAQ gene → Abnormal development of small blood vessels (capillary malformations).
✔️ Affects leptomeninges (meninges covering the brain), skin (especially face), and eyes.

🔹 Clinical Features (Mnemonic: STURGE)
S - Seizures (often focal, early childhood).

T - Tram-track calcifications (seen on brain imaging, especially parietal-occipital region).

U - Unilateral Port-Wine Stain (facial capillary malformation, commonly V1/V2 distribution of trigeminal nerve).

R - Retardation (Intellectual disability) (variable).

G - Glaucoma (early-onset, ipsilateral eye).

E - Epilepsy (often refractory).

🔹 Diagnosis
✔️ Clinical presentation + Imaging (CT/MRI):

Tram-track calcifications (gyriform calcifications) on CT.

Leptomeningeal angiomas on MRI with contrast.

✔️ Ophthalmologic examination: For glaucoma screening.

🔹 Management
✔️ Symptomatic treatment:

* Anticonvulsants for seizures.

* Intraocular pressure management for glaucoma.
✔️ Laser therapy: For port-wine stain (cosmetic).

🔹 Complications
✔️ Refractory epilepsy.
✔️ Visual impairment (from glaucoma).
✔️ Cognitive impairment.

11/12/2024

ልጆች እሚያለቅሱባቸው 10 ምክንያቶች
1 ረሃብ_ማጥባት
2 እንቅልፍ ማጣት_ ጫጫታ መቀነስ፣ የጎብኚ ቁጥር መቀነስ
3 ምቾት ማጣት _ መኝታቸው መርጠቡነ መወዝቀዙን ወይ ሙቆ ከሆነ ቸክ ማረግ
4 እንድናስገሳቸው ሲፈልጉ_ በተለይ ህጻንከጠባ በኋላ ካለቀሰ ሆዱንስላልተመቸው አስገሽኝ እያለ ነው
5 ህመም _ የምጡ ሂደት በራሱህጻኑ ላይ ህመም ሊያመጣ ይችላል
6 ትኩረትሲሹ _ሃጻኑ የተረሳ ከመሰለው ሊያለቅስይችላል
7በሽታ
8 ቁርጠት —ያለ ማቋረጥ ለረጅም ደቂቃ እንዲያለቅሱ ያደርጋል
9 ጨጓራቸው በአየር ሲሞላ ህጻኑን በግራ በኩል ማስተኛት ጋዙ እንዲወጣ ያግዛል
10 ጥርስ ማውጣት

18/04/2024

የአእምሮ ሞት እና የትንፈሳ እጥረት ምርመራ(Brain death and apnea test)
=====================
አንድ ሰው ፅኑ ህክምና ክፍል (ICU) ሲታከም ከፍተኛ ክትትል ይደረግለታል በተጨማሪም የሰውነቱ ክፍሎች መስራት የሚገባቸውን ስራ የሚተኩ ማሽኖች ሊኖሩ ይችላሉ።

አንድ ሰው አእምሮው ሙሉለሙሉ ሞቶ ነፍሱ ግን ላትወጣ ትችላለች። ሳንባውን አእምሮው ማዘዝ ሲያቆም በማሺን እንዲተነፍስ (Mechanical ventilation) ማድረግ ይቻላል። ልብ ያለ አእምሮ ትእዛዝ መምታት ትችላለች። ስለዚህ ግለሰቡ ልቡ ይመታል፤ ይተነፍሳል ግን አእምሮው ሞቷል። መስተካከል የሚችል ህመም ሳይኖር የአእምሮ ሞት ላይ ከደረሰ በህክምናው እንደሞት ስለሚቆጠር የመተንፈሻ ማሽኑ ሌላ የሚተርፍ ታካሚ እንዲጠቀምበት ይነቀላል። (መስተካከል የሚችል ማንኛውም አይነት ነገር ከመሞከር ግን ወደ ኋላ አይባልም።)

ውሳኔው እጅግ ትልቅ ውሳኔ ስለሆነ አእምሮው መሞቱን በሚገባ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ስለዚህ የአእምሮ ሞትን ቢያንስ በሁለት የተለያዩ ሀኪሞች ለየብቻ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው። በተጨማሪም የሚያስፈራ ምርመራ አለው። የትንፈሳ እጥረት ምርመራ (Apnea test)።

የትንፋሽ ምርመራውን ለመስራት በቅድሚያ 100% ኦክስጅን በደንብ ለታካሚው በማሽኑ አማካኝነት ይሰጠዋል። ከዛ ማሽኑ ይነቀላል። ግለሰቡ ምንም የመተንፈስ ምልክት ሳያሳይ ለ6-8 ደቂቃዎች ከቆየ በደሙ ውስጥ ያለው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ይለካል። ከ60mm Hg በላይ ከሆነ አእምሮው ሞቷል ማለት ነው። አንድ ሰው ትንፋሽን የሚቆጣጠረው ወሳኝ የአእምሮ ክፍል ሳይሞት ግለሰቡ ቢፈልግ እንኳን ትንፋሹን መያዝ አይችልም። የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መጠን ከፍ ሲል ሳይወድ በግድ አእምሮው ያስተነፍሰዋል። ይህን ካላደረገ አእምሮው መሞቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

05/04/2024

ተጣብቀዉ ስለሚወለዱ ልጆች መንስኤዎቹ | conjoined twins

ከአንድ በላይ ፅንስ መፈጠር (multifetal pregnancy) ከአጠቃላይ እርግዝና ከ90 ወሊዶች አንድ የሚከሰት ሲሆን በአብዛኛዉ ሁለት (twins መንታ) ሆነዉ ሲፈጠሩ በጥቂት ቁጥር 3 (triplets) , 4 (quadruplets) ,5 (quintuplets) ወይም 6 (sextuplets) እርግዝና በአንዴ ሊከሰት ይችላል።

የመንታ አፈጣጠር አይነቶች

በአብዛኛዉ መንታ የሚፈጠረዉ (ከመቶ መንታዎች ሰማንያ የሚደርሱት-80%) በሁለት እንቁላሎች በአንድ የወር አበባ ኡደት ዉስጥ አድገዉ በአንዴ ሲወጡና እርግዝና ሲካሄድ ሲሆን የሚፈጠሩትም ልጆች በመልክ የማይመሳሰሉ በፆታም ሊመሳሰሉ ወይ ላይመሳሰሉ ይችላሉ። (Dizygotic twins) በእንደዚህ አይነት የመንታ አፈጣጠር ተጣብቀዉ የመፈጠር እድል አይኖራቸዉም።

ሁለተኛዉ አይነት የመንታ አፈጣጠርና በተለያዩ የሰዉነት ክፍላቸዉ ተጣብቀዉ እንዲፈጠሩ የሚያደርገዉ አይነት ሲሆን ይህም በአንድ የወር አበባ ኡደት ዉስጥ ከአንድ እንቁላል ወደ ሁለት ፅንስ የመፈጠር ሂደት ዉስጥ የሚከሰት ነዉ።

ይህ ከአንድ እንቁላለል ወደ ሁለት ፅንስ የመፈጠር ሂደት (monozygotic twins) ከመንታ አፈጣጠር ዉስጥ 20% የሚይዝ ሲሆን ፅንሶችም በመልክም በፆታም ተመሳሳይ ሆነዉ ይፈጠራሉ።

በአብዛኛዉ ጌዜ (99%) በእንቁላል የሚከፈልበት ጌዜ ከአንድ ሳምንት በታች ሲሆን በአንድ ወይ በሁለት እንግዴ ልጅና በአንድ ወይ በሁለት ግድግዳ ዉስጥ የድጋሉ። የመጣበቅ እድልም አይኖራቸዉም።

ተጣብቀዉ የሚፈጠሩ ፅንሶች የሚከሰተዉ አንዱ እንቁላል ከወንድ የዘር ፍሬ ከተዋህደ በኋላ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ሁለት ፅንስ ሲከፈል በሚያደርገዉ ሂደት ዉስጥ ሲሆን ተጣብቆ የመወለድ እድል ከመቶ ከአንድ እንቁላል መንታ አፈጣጠር ዉስጥ ከአንደ ባነሰ (

23/03/2024

ውሀ ሰውነት ውስጥ ማነስ (ዲሀይድሬሽን)

🍀የሕፃናት ሰውነት በቀላሉ ውሀ ስለሚያጣ የሰውነት ውሀ ማጠር ለሕፃናት አደገኛ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል

ምክንያቱ

🍁ተቅማጥ

🍁ትውከት

🍁ከሁለት እስከ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ አለማጥባት

🍁የእናት ጡት ያልሆነ ወተት መመገብ (እንደ ፎርሙላ፣ ወተት፣ ወይንም ውሀ)

🍁ሙቅ የአየር ጠባይ

ምልክት

🍁ትንሽ መሽናት፣ጠቆር ያለ ሽንት፣ ሀይለኛ ሽታ ያለው

🍁ደረቅ አፍ እና ደረቅ ምላስ

🍁የፈዘዘ ዓይን ወይንም ከተለመደው ውጭ የሆነ አይነት ቆዳ

🍁ሀይለኛ ውሀ ማጠር የጐደጐዱ ዓይን፣ ለስላሳ እና የጐደጐዱ ቦታዎች ጭንቅላት ላይ መታየት፣ የኪሎ ማነስ፣ ወይንም ብዙ አለመነቃነቅ/ያለመንቃት ሊያስከትል ይችላል።

ህክምና

🍁🍁የሰውነት የፈሳሽ ማጠር ምልክት ሲታይ፣ ሕፃኑ ተቅማጥ ካለው ወይንም እያስታወከ ከሆነ ሕፃኑ እሺ እስካለ ድረስ በየ ሁለት ሰዓት ቶሎ ቶሎ እየቀሰቀሳችሁ አጥቡ።
በምግብ እጥረት ላልተጓዱ ህጻናት ORS መስጠት።

🍀የሰውነት ፈሳሽ ያጠረው ሕፃኑ እየተሻለው ካልሄደ በትንሽ ሰዓት ውስጥ የልጁ ሰውነት ውስጥ በቂ ውሀ እንዲኖር የሚያስፈልገውን ለማድረግ አፋጣኝ ህክምና ያስፈልገዋል።

15/03/2024

ደረት አካባቢ የሚሰማ ጭምድድ የሚያደረግ የደረት ህመም እና ከወትሮው የተለየ የትንፋሽ ማጠር አደገኛ የልብ ድካምን የሚያሰከትለው የCoronary Artery Disease(CAD) ምልክት ሊሆን እንደሚችል ያውቃሉ?

ይህ አይነት የህመም ስሜት ከወትሮ በተለየ መልኩ የሚሰማዎት ከኾነ እጅግ በጣም አደገኛ የልብ ድካም ምልክት ሊሆን ይችላል። ሰዎች እንደዚህ አይነት ስሜት ሲሰማቸው ብርድ መቶኝ ነው የሚል የተሳሳተ አመለካከት አላቸው። ይህ የደረት ህመም በተለይ የህመም ስሜቱ ሄድ መለስ የሚል እስከ ትከሻ፣ አነገት፣ እጅ እና የመነጋጭላ አካባቢ ድረስ የህመም ስሜት ሊሰማን ይችላል።

አንድ ማወቅ ያለብን ነገር ምንጊዜም ቢሆን የሰው ልጅ ልብ በማነኛውም ሰአት ልትደክም እንደምትችል ማሰብ ተገቢ ነው።ይህ ሊሆን የሚችለው የደም ስሮች በተለያየ ምክንያት ለምሳሌ በኮሌስትሮል ሲዘጉ፣ልብ ውስጥ ደም መተላለፊያ ቱቦ መዘጋት ወይም በተለያዩ ኢንፌክሽን ምክንያት ወደ ልብ የሚሄደው የደም ፍሰት ሲስተጓጎል ወይም ሲቆም ነው።

በዚህ ጊዜ የልብ ጡንቻዎች በቂ የሆነ ኦክስጅን ያለው ደም ሳያገኙ በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ መስራት ሲያቅታቸው በቶሎ ህክምና እርዳታ ካላገኙ እስከ ምት ሚዳርግ አደገኛ በሽታ ነው። ይህ አይነቱ የልብ ህመም የሚያስከትለው Coronary Artery Disease (CAD) እንለዋለን።

ከዚህ በተጨማሪ እንቅስቃሴ ስናደርግ ከወትሮ የተለየ የድካም ስሜት፣የትፋሽ ማጠር በተለይ ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ ትነፋሽ ማጠር ከሆነ፣እግር እና ሆድ አካባቢ እብጠት፣ፈጣን የሆነ የልብ ምት ለእራሳችን መሰማት፣ላብ ማላብ፣ እና የማዞር ስሜት ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ አደገኛ ምልክቶች በሚከሰቱበት ጊዜ ጊዜ በአፋጣኝ ወደ ህከምና ተቋም መሄድ እንዳለብን መዘነጋት የለብንም።

ይህ በሽታ በአለም አቀፍ ደረጃ በ2020 አመተ ምህረት የCDC ሪፖርት እንደሚያሳየው ወደ 400,000 ህዝብ የሚጠጋ ህዝብ ህይወት ለህልፈት ዳርጓል። በአብዛኛው ለዚህ በሽታ ተጋላጭ የሚሆኑት በተለይ እድሜያቸው ገፋ ያሉ ሰዎች ፣የትንባኾ ውጤቶችን መጠቀም ፣የደም ግፊት፣ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ያላቸው ሰዎች፣ከመጠን በላይ ውፍረት፣ስኳር በሽታ፣ቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ የልብ በሽታ ካለ፣ቅባት የበዛባቸው ምግቦች መጠቀም፣ህገወጥ መድሀኒቶች ለምሳሌ ኮኬይን መጠቀም እና ጫት መቃም ተጋላጭነትን ይጨመራል። ከዚህ በተጨማሪ ከመጠን በላይ ብስጭት እና ጭንቀትም ለዚህ ችግር ይዳርገል።

ስለዚህ አንድ ልባችንን ለመታደግ በተቻለ መጠን የሰውነት ክብደታችንን ማመጣጠን ፣የደም ግፊት፣ ስኳር እና ከመጠን በላይ ኮሌሰትሮል ካለብን በአግባቡ መታከም፣በቂ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ቅባታማ ምግቦችን በተቻለ መጠን መቀነስ አትክልት እና ፍራፍሬ ማዘውተር፣ ጨው መቀነስ፣ ጭንቀትን መቀነስ፣ ትንባሆ በፍፁም አለማጨስ እና ከሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች መቆጠብ ይጠበቅበናል። በተለይ ሁልጊዜ የሰውነት ክብደት ቀንሱ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት መዘዙ ከባድ ነው ስንል በምክንያት ስለሆነ በተቻለ መጠን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ይህ ህመም መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የተለያዩ ምርመራዎች ለምሳሌ የተለያዩ ከደም ላይ የሚሰሩ ምርመራዎች ፣ECG፣ Echocardiography፣ Exercise stress test፣ cardiac cathetherization and angiogram ፣የደረት X ray፣ የልብ CT Scan ሊደረጉ ይችላሉ።

ወደ ህክምናው ስንሄድ ደግሞ መድሀኒቶች ለምሳሌ የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሀኒቶች፣ Asprin፣ B-blockers፣ ACE inhibitors፣ calcium channel blockers፣ Nitroglycerin ሁሉም እንደአስፈላጊነቱ ታይቶ ሊታዘዝ ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ የተዘጋውን የደም ቧንቧ ለማሰተካከል Coronary angioplasty and stent replacment ፣Coronary artery bypass graft surgery የሚባሉ የልብ ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ይችላል።

13/03/2024

***
በርካቶቻችን በብዛት የምንጠቀመው እና በተለይም በረመዳን ጾም ወቅት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድየሚዘወተረው ቴምር በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።

በቫይታሚን፣ ማዕድናትና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዲኖሩት አስችሎታል፡፡…ለምሳሌ ያህል…

ቴምር የጤና ጥቅም አለው?

1. ስብና ኮልስትሮል፡ ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡

2. ፕሮቲን፡ ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡

3. ቫይታሚን፡ በቫይታሚን የበለጸገ ነው ቴምር፡፡ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 እና ሲ ንም አካትቶ ይዟል፡፡

4. ሀይል እና ጉልበት፡ ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡

5. ፖታሲየምና ካልሲየም፡ ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ቴምር በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠን ነው ያለው፡፡ ብዙ ፖታሲየምና ትንሽ ሶዲየም ደግሞ ለጤናማ የነርቭ ስርዐት ወሳኝ ነው፡፡

6. ብረት፡ ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት ማዕድን እጥረት ላለባቸው ሰዎች፣ ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ ይከላከላል፡፡

7. ድርቀት፡ ለድርቀትም ቢሆን ውሀ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

8. ሰውነትን ማጽዳት፡ በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም ይረዳል – ቴምር !

9. ካንሰር እና የዓይን ችግር፡ የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ነቀርሳ (ካንሰር)ን ለማከምም ብቃት እንዳለው ይታወቃል – ቴምር፡፡

10. (የቆዳ ችግር) ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና አለው፡፡ ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡

በርከት ያሉ ቪታሚኖችን እና ሚኔራሎች በመያዙ ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገርለታል። ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ እንዲሁም ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ እና ዚንክ ሚኔራሎች በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል።

ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን መመገብ ለጤናችን ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች ውስጥም፦

· የሆድ ድርቀትን ይከላከላል

o ቴምር በባህሪው የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ ቴምሩን በውሃ ውስጥ ዘፍዝፈን በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።

· ለአጥንት ጤንነት እና ጥንካሬ

o በቴምር ውስጥ የሚገኙት ሚኔራሎች ለአጥንታችን ጥንካሬ እና ጤነነት እጅጉን ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል። ቴምር እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ ኮፐር እና ማግኒዚየም ማእድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና ጥንካሬ ጠቃሚ ነው።

· ደም ማነስን ይከላከላል

o ቴምር በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የምግብ ማእድናት ንጥረ ነገቾች ክምችት የደም ማነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች እጅጉን ጠቃሚ ነው።

· አለርጂን ይከላከላል

o ቴምርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው አለርጂን ለመከላከል የሚረዳውን ሰልፈር ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ነው። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን የምንመገብ ሰዎች ለተለያዩ አይነት አለርጂዎች የመጋለጥ እድላችን እጅጉን እንዲቀንስ እንደሚያደርገው ይነገርለታል።

· ለነርቭ ጤንነት

o በቴምር ውስጥ የሚገኙት ቪታሚኖች የተስተካከለ እና ጤናማ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ስለሚያደርግም ለጤናችን ጠቃሚ ያደርገዋል።

· ለልብ ጤንነት

o ቴምር ለልባችን ጤንነት በርካታ ጠቀሜታዎች ስላሉት ተመራጭ ያደርገዋል።ቴምር የልብ ጤንነትን ይጎዳል የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ እቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ በመርዳትም ለልባችን ጤንነት ጠቀሜታ አለው።

· ስንፈተ ወሲብን ይከላከላል

o ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ቴምር በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሰዎችን የወሲብ ፍላጎት ከፍ እንዲል እና የወሲብ ፍራቻ ላለባቸው ሰዎች ድፍረትን እንዲያገኙ በማድረግ ስንፈተ ወሲብን ለመከላከል ይረዳል።

· በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ተመራጭ ምግብ ነው

o ቴምር በእርግዝና ወቅት ለጽንሱ ጤንነት ብሎም በወሊድ ጊዜ ምጥ አስቸጋሪ እንዳይሆንና የተሻለ የማማጥ አቅም እንዲኖረን ያስችላል።

· የአዕምሯችንን ጤንነት ያሳድጋል

o ጥናቶች በቴምር የምናገኘው ቫይታሚን ቢ6 የተሻለ የአዕምሮ ተግባራት እንዲኖርና ሰዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘገቡ ማገዙን ተናግረዋል።

07/03/2024

Does Donating Blood have any Benefits for The Donors?
Blood donation can have health benefits for the donors as well. It can help in:

5. Reducing iron levels in the body,
6. Knowing one’s blood group,
7. Promoting the production of fresh red blood cells
8. Stimulating the body to replenish its blood supply.
9. Donors often receive a basic health check-up, including screening for certain diseases, which can provide valuable insights into their well-being.

10. Donating blood is a selfless act of giving that can provide a deep sense of fulfillment and satisfaction. Knowing that you have played a part in positively impacting someone’s life and well-being can be incredibly rewarding.

Address

Addis Ababa

Telephone

+251994864805

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr yimer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr yimer:

Share

Category