07/03/2025
ሜኒንጅዮማ በአንጎል እና ህብረ ሰረሰር ዙሪያ ካለው ሽፋን የሚነሳ እጢ ነው።
[ ] አብዛኛው ሜኒንጅዮማ የህመም ምልክቶችን ሳያስከትሉ ለብዙ አመታ በጣም በዝግታ ሊያድጉ ይችላሉ። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ፣ በአቅራቢያው ባሉ የአንጎል ህዋሶች ፣ ነርቮች ወይም ደም ስሮት ላይ የሚኖራቸው ተጽእኖ ከባድ ህመምንና የአካል ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል።
🇪🇹ምልክቶቹ እጢው እንዳለበት የአንጎል ክፍል ይለያያል። ዋና ዋና ምልክቶቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ🇪🇹
[ ] የእይታ ለውጦች, መደብዘዝ, ሁለት ሆኖ መታየት
[ ] የከፋ ራስ ምታት, ጠዋት ልይ የሚብስ
[ ] የመስማት ችግር ወይም የጆሮ ውስጥ የመደወል ድምፅ
[ ] የማስታወስ ችሎታ ማጣት/መቀነስ
[ ] የማሽተት ማጣት/መቀነስ
[ ] የሚጥል ህመም
[ ] በእጆቹ ወይም በእግሮቹ ላይ ድክመት/አልታዘዝ ማለት
[ ] የመናገር ችግር/መናገር አለመቻል/መደበላለቅ
🇪🇹 የሕክምና አማራጮችን ለመወሰን የሚከተሉትን ነገሮች ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል🇪🇹
[ ] የእጢው መጠንና ያለበት ቦታ
[ ] የዕጢው የእድገት ሁኔታ
[ ] የእርስዎ ዕድሜ እና አጠቃላይ የጤና ሁኔታ
[ ] የህክምና አማራጩ ሊፈጥር የሚችለው ለውጥ/ግብ
🇪🇹የሕክምና አማራጮች🇪🇹
[ ] ወቅቱን ጠብቆ ክትትል ማድረግ
[ ] የቀዶ ህክምና
[ ] የጨረር ህክምና
[ ] የመድሀኒት ህክምና
Image- ALERT comprehensive Specialized Hospital, operating right spheno orbital meningioma.
28/06/2017E.C
ዶ/ር ተመስገን ሹሜ የአንጎልና ህብረ-ሰረሰር ቀዶ ህክምና ሬዚዴንት
አድስ አበባ ዩኒቨርስቲ, ኢትዮጵያ