Lenat-MOM

Lenat-MOM Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lenat-MOM, Health & Wellness Website, adwa Street, Addis Ababa.

💖💖💖💖💖💖💖💖
ውድ የ ለእናት ቤተሰቦች 🤰
የእርግዝና ጉዞ በችግሮች እና እርግጠኛ ባልሆኑ ሁኔታዎች ሊሞላ እንደሚችል እንረዳለን ነገርግን ብቻዎን እንዳልሆኑ እንዲያውቁ እንፈልጋለን። ወደዚህ ዓለም አዲስ ሕይወት የማምጣት አስደናቂ ጉዞ ላይ ሲገቡ፣ በእያንዳንዱ እርምጃዎ የእኛን የማያወላውል ድጋፍ እና ምክር ልንሰጦ እዚህ ተገኝተናል።

🤰🏾ናብሊስ የእርግዝና አልባሳት መሸጫ!         *አዳዲስ          *ጥራት ያላቸው      *ዘመናዊ      ከ ሺን (SHEIN) የሚመጡ የእርግዝና አልባሳት**ለመግዛት እና ለተጨማሪ...
23/10/2025

🤰🏾ናብሊስ የእርግዝና አልባሳት መሸጫ!
*አዳዲስ *ጥራት ያላቸው *ዘመናዊ
ከ ሺን (SHEIN) የሚመጡ የእርግዝና አልባሳት
**ለመግዛት እና ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ይደውሉ (0908031515)
👉 https://t.me/nablismaternity
👉ለማዘዝ https://t.me/rechoooo ይጠቀሙ!
አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከሄመን የእናቶችና የህፃናት ሆስፒታል ዝቅብሎ - ኢክላስ ህንፃ ምድር ላይ ሱቅ.ቁ. 15
ስልክ፡ 0908031515

ጠቃሚ መረጃለሃኪም ከምንሰጣቸው እጅግ ጠቃሚ መረጃዎች መካከል አንዱና ዋነኛው የእናት ትክክለኛ እድሜ ነው፡፡ ከ35 አመት በላይ የሆኑ እናቶች ከእርግዝና ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ውስብስብ ችግሮ...
20/10/2025

ጠቃሚ መረጃለሃኪም ከምንሰጣቸው እጅግ ጠቃሚ መረጃዎች መካከል አንዱና ዋነኛው የእናት ትክክለኛ እድሜ ነው፡፡ ከ35 አመት በላይ የሆኑ እናቶች ከእርግዝና ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ውስብስብ ችግሮች በይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ ስለዚህም ትክክለኛ እድሜያቸውን በማሳወቅ ሃኪሙ የነዚህን ውስብስብ ችግሮች ጉዳት ለመቀነስ አስፈላጊውን ክትትልና ጥንቃቄ እንዲያደርግ ይረዳዋል፡፡ ከእርግዝና በፊት ያለ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ከብደት(BMI > 30 kg/m2 ) በእርግዝና ወቅት አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያስከትል በሳይንስ የተረጋገጠ ነው። ከነዚህም መካከል የደም ግፊት፣ስኳር እና ከባድ ምጥ ተጠቃሽ ናቸው።ከእርግዝና በፊት እና በእርግዝና ወቅት ያለ ጤናማ የአመጋገብ ስርዐት ለጤናማ ጽንስ እጅጉን አስፈላጊ ነው። በሰውነት ውስጥ ፎሌት(Folate) የተባለው ንጥረ ነገር በበቂ ሁኔታ ከሌለ በጽንሱ ላይ የተለያዩ የአፈጣጠር ችግሮችን ያስከትላል። ስለዚህም እርግዝና ከመታቀዱ 3 ወር ቀደም ብሎ ለእርጉዝ ሴቶች የሚዘጋጁና በሃኪም የሚታዘዙ የፎሌት ማሟያ ኪኒኖች(supplements) መውሰድ አስፈላጊ ነው። አዮዲን የተባለ ንጥረ ነገር ለጽንሱ የአእምሮ እድገት ጠቃሚ እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህም በአዮዲን የበለጸገ ጨው በምግብ ውስጥ በመጠቀም የጽንሱን ጤናማ እድገት ማስቀጠል ይቻላል።በተለምዶ ሾተላይ በመባል የሚታወቀው የጽንስ መጨንገፍ ችግር አር-ኤች ኔጋቲቭ(Rh-negative) የደም አይነት ያለቸው ሴቶች ላይ በተደጋጋሚ ውርጃን ያስከተላል። ይሁን እንጂ የህክምና ክትትል በማድረግና በሃኪሙ በሚታዘዝ መርፌ ጽንሱ እንዳይወርድ መከላከል ይቻላል።በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር ማቅለሽለሽና በተደጋጋሚ ማስታወክ አንድ አንድ ነፍሰ ጡሮች ላይ ሊበረታ ይችላል። የዝንጅብል ሻይ መጠጣት እነዚህን ስሜቶች በእጅጉ እንደሚቀንስ ሳይንሱ ያመለክታል።በተለምዶ የሽርት ውሃ ተብሎ የሚጠራው ፈሳሽ አብዛኛው ከጽንሱ በሚወጣ ሽንት እንደሚዘጋጅ ያውቃሉ? ጽንሱ ይህንን ፈሳሽ በተደጋጋሚ በመጠጣትና በመሽናት የሳንባ እና የሆድ እቃ አፈጣጠር እንዲጎለብት ያደርጋል።በእርግዝና ወቅት የጨጓራ ህመም ስሜቶች እንደ ቃር፣ ማቅለሽለሽ እና ጨጓራ አካባቢ የውጋት ወይም የቁርጠት ስሜት ሊባባሱ ይችላሉ። እነዚህንም የህመም ስሜቶች ለመቀነስ በመጠኑ በመመገብ እና በቀን ሶስት ጊዜ ከመብላት ይልቅ በትንሽ በትንሹ አራርቆ 6 ጊዜ መብላት ይመረጣል።አንድ ጽንስ በ7ኛው ሳምንት እንቅስቃሴ ቢጀምርም ነፍሰ ጡር ግን ይህንን እንቅስቃሴ ማስተዋል የምትጀምረው ከ 16 እንከ 18 ኛው ባሉ ሳምንታት ውስጥ ነው።በእርግዝና ወቅት የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ? አንዲት ነፍሰጡር በቀን ውስጥ መጠነኛ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርባታል። ነገር ግን ሩጫና የሰውነት ሚዛን የሚያዛቡ እንቅስቃሴዎች በእርግዝና ወቅት አይመከሩም።አንዲት ነፍሰጡር የመውለድ ቀኗ ደርሷል የሚባለው ከ 37ኛ ሳምንት በኋላ ነው። ከ40 ሳምንት በላይ የሚገፋ እርግዝና በጽንሱ ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊኖረው ይችላል። ስለዚህም እንደ ነፍሰ ጡሯ እና አንደ ጽንሱ ሁኔታ የምጥ መርፌ ወይም ኦፕሬሽን በሃኪሟ ሊታዘዝ ይችላል።የመጀመሪያ እርግዝናቸው የሆኑ ወላዶች አብዛኛውን ጊዜ ምጣቸው ይረዝማል። ሁለተኛው ምጥ ግን ከመጀመሪያው ጋር ሲነጻጸር አጠርና ቀለል ያለ ነው።በእርግዝና ወቅት እና ከወሊድ በኋላ የእንቅልፍ መረበሽ ብዙ ሴቶች ላይ የተለመደ ክስተት ነው። ነገር ግን አንዳንድ እናቶች ላይ ከወሊድ በኋላ በይበልጥ ሊስተዋል ይችላል።

የመጨረሻ ክፍል* በምጥ ጊዜ ግላይሴሚክ ወይም የደም ስኳር መጠን  ቁጥጥር  ትኩረት መሰጠቱ በሁለት ዋና ዋና የጤና እክሎች የመያዝን አጋጣሚ ይቀንሳል፤ እነዚህም የፅንስ ኦክስጅን እጥረት እና...
08/10/2025

የመጨረሻ ክፍል
* በምጥ ጊዜ ግላይሴሚክ ወይም የደም ስኳር መጠን ቁጥጥር ትኩረት መሰጠቱ በሁለት ዋና ዋና የጤና እክሎች የመያዝን አጋጣሚ ይቀንሳል፤ እነዚህም የፅንስ ኦክስጅን እጥረት እና ከወሊድ በዃላ በህፃኑ ላይ የደም የስኳር መጠን ማነስ ናቸው።

* ከወሊድ በኋላ የኢንሱሊን ፍላጎት በእርግዝና ወቅት ከነበረው በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል ። ስለዚህም በእርግዝና ወቅት የነበረው የደም ስኳር መጠን ቁጥጥር ለመጀመሪያዎቹ ከ24 እስከ 48 የእርግዝና ሰዓታት ውስጥ ላላ እንዲል ይደረጋል ።
* የእርግዝና የስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች የሚደረገው ዋናው ህክምና የአመጋገብ ምክክር እና የአመጋገብ ማስተካከያ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው ። አንድ ሕመምተኛ በተደጋጋሚ የደም ስኳር መጠን ከተቀመጠው ልክ በላይ ከሆነ የመድሀኒት ሕክምና እንዲጀመር ይመከራል።
* የእርግዝና የስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች ላይ አመጋገብን በማስተካከል ብቻ አጥጋቢ የደም ስኳር መጠን ቁጥጥር ማድረግ ከተቻለ የቅድመ ወሊድ የፅንስ ምርመራዎች በአብዛኛው አያስፈልጉም። እነዚህን ምርመራዎች በ40ኛው የእርግዝና ሳምንት ላይ መጀምር ይቻላል።

* የደም የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር የመድሀኒት ሕክምና ካስፈለገ፣ ታማሚዋ እናት የታዘዙ ሕክምናዎችን የማትተገብር ከሆነ እና የስኳር በሽታው ቁጥጥር አጥጋቢ ካልሆነ የቅድመ ወሊድ የፅንስ ምርመራዎች ከዚህ 40ኛው የእርግዝና ሳምንት ጊዜ ቀደም ብሎ እንዲጀመር ይመከራል።
* የእርግዝና የስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች አመጋገብን በማስተካከል ውይም በመድሃኒት ሕክምና በሽታው በሚገባ ቁጥጥር ውስጥ እስከሆነ ድረስ የመውለጃ ጊዜ ከ39 የእርግዝና ሳምንት በፊት መሆን የለበትም። ቁጥጥሩ አጥጋቢ ካልሆነ ግን የመውለጃ ጊዜ እንደየሁኔታው ይወሰናል።
* የእርግዝና የስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች በእርግዝና ወቅት የስኳር በሽታ ከሌለባቸው ሴቶች ጋር ሲነፃፀር በዓይነት 2 የስኳር በሽታ የመያዝ አጋጣሚያቸው 7 እጥፍ ይጨምራል ። በተጨማሪም ወደፊት በእርግዝና ወቅት በድጋሚ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
* የእርግዝና የስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች ከወሊድ በኋላ ከ6 እስከ 12 ሳምንታት ውስጥ የደም ስኳር መጠን ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከልክ ያለፈ የስኳር መጠን ይኖራቸዋል። ስለዚህ ለእነዚህ እናቶች ከወሊድ በኋላ ከ6 እስከ 12 ሳምንታት ውስጥ የደም ስኳር መጠን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል ።
* በቅድሚያ የእርግዝና የስኳር በሽታ ኖሯቸው ከወሊድ በኋላ ከ6 እስከ 12 ሳምንታት ውስጥ የሚደረገው የደም ስኳር መጠን ምርመራ መደበኛ ወይም ነፃ ከሆነ በየ3 ዓመቱ የደም ስኳር መጠን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል ።
* የስኳር በሽታ የሚያስከትለው ዘላቂ ውጤት በእናት ላይ ለዓይነት 2 የስኳር በሽታ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ መኖር (50% የእርግዝና የስኳር በሽታ ህመምተኞች ውሎ አድሮ በዓይነት 2 የስኳር በሽታ ይያዛሉ)፣ በሜታቦሊክ ሲንድሮም የመያዝ አጋጣሚያቸው መጨመር እና የደም ወሳጅ ቧንቧ በሽታ ና የመሳሰሉትን የልብና የደም ዝውውር መዛባት እና የስትሮክ አደጋ መጨመር ናቸው። የስኳር በሽታ የሚያስከትለው ዘላቂ ውጤት በፅንስ ላይ ደግሞ በስኳር በሽታ፣ በውፍረትና በሜታቦሊክ ሲንድሮም የመያዝ አጋጣሚያቸው መጨመር ናቸው።
* ከእርግዝና በፊት የስኳር ህመም ያለባቸው ሴቶች ከእናት ስኳር በሽታ ጋር በተያያዘ የፅንሱ ተዛማጅ የልብ፣ ኩላሊት፣ እና ማዕከላዊ የነርቭ ስርዓቶች ጉዳቶች በመጀመሪያዎቹ 7 ሳምንታት ውስጥ ስለሚከሰቱ እነዚህን ለማስቀረት ከእርግዝና በፊት የስኳር ህመም ያለባቸው ሴቶች ከመፀነስ በፊት ቅድመ እርግዝና ምክር እና አገልግሎቶት መጀመር አለባቸው።

* በዚህ ቅድመ እርግዝና ምክር እና አገልግሎቶት ላይም ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎት ይደረጋል። እንሂም የደም ዝውውር ችግሮች ምርመራ(የአይን እና የኩላሊት ተግባርን በመመርመር) ፣ የልብ ምርመራ (የደም ግፊት ምርመራ እና ኢኮካርዲዎግራፊ ወይም የልብ አልትራሳውንድን ምርመራ)፣ የመድህኒት ማሻሽያ ማድረግ (የተለያዩ በእርግዝና ወቅት የሚከለከሉ መድሀኒቶችን መቀየር እና የፎሌት መድሀኒት አስቀድሞ መጀመር) ፣ የደም ስኳር መጠን ቁጥጥርን መገምገም( በተገቢ ሁኔታ ቁጥጥር ውስጥ እስኪሆን የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም ያስፈልጋል) እና የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል (የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በቋሚነት ማድረግ፣ አመጋገብን ማስተካከል፣ ውፍረት ካለ ክብደት መቀነስ እና ሲጋራ ማጨስ ማቆም ) ናቸው።

… ካለፈው ሳምንት የቀጠለ* በእርግዝና ወቅት የስኳር በሽታ ህክምና  ለእርግዝና ስኳር በሽታ እና ለቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ይለያያል። ለቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ የህክምና መንገዶች...
03/10/2025

… ካለፈው ሳምንት የቀጠለ

* በእርግዝና ወቅት የስኳር በሽታ ህክምና ለእርግዝና ስኳር በሽታ እና ለቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ይለያያል። ለቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ የህክምና መንገዶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አመጋገብ ማስተካከል፣ የደም የስኳር መጠን መቆጣጠር ፣ እና የኢንሱሊን መድሀኒት መጠቀም ነው።
* እንቅስቃሴ የሚከለክሉ ችግሮች ከሌሉ በቀር ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለ30 – 60 ደቂቃ በሳምንት 3 ጊዜ ማድረግ ያስፈልጋል። አመጋገብም 40% ካርቦሃይድሬት ፣ 40% ስብ እና 20% ፕሮቲን መሆን አለበት። በዚህ መሰረት በቀን 3 ጊዜ ዋና ምግብ እና 2 ወይም 3 መክሰሶች ተከፍሎ መመገብ አለባቸው። የመተኛ ጊዜ ላይ መክሰስ ሌሊት ላይ የሚከሰት የደም ስኳር መጠን ማነስን ለመከላከል አስፈላጊ ነው።
* በእርግዝና ወቅት የደም ግሉኮስን በራስ መቆጣጠር እና በእርግዝና ወቅት የተሻለ የግሉኮስ መጠን ላይ መቆየት ያስፈልጋል ።
* የኢንሱሊን ሕክምና በደህንነቱ ምክንያት በእርግዝና ወቅት የመጀመሪያው ሕክምና ሆኖ ቀጥሏል። በእርግዝና ወቅት የስኳር በሽታ የሚዋጡ መድሀኒቶች በተሳካ ሁኔታ ጥቅም ላይ የዋሉ ቢሆንም ለቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ አይመከሩም ። የኢንሱሊን ፍላጎት መጠን በእርግዝና ጊዜ እየጨመረ ይሄዳል። በአብዛኛው ከ28 እስከ 32 ሳምንት ባለው ጊዜ የእርግዝና ወቅት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
* ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ላለባቹው እናቶች ፅንሱን ለመከታተል የተሟላ የአልትራሳውንድ ምርመራ በ18 እስከ 20 ሳምንት ላይ ሲደረግ የፅንሱ የልብ ኢኮካርዲዮግራፊ ደግሞ በ20 እስከ 22 ሳምንት ላይ ምርመራ ይደረጋል ።
* የቅድመ ወሊድ የፅንስ ምርመራ በእርግዝና ወቅት እንዳስፈላጊነቱ ይደረጋል ። እርግዝናው 6 ወር ካለፈ በኋላ እናቶች በየቀኑ የፅንሱን እንቅስቃሴ በመቁጠር እንዲከታተሉ ይደረጋል ። የፅንሱን ሁኔታ አልትራሳውንድን በመጠቀም የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ ይከታተሉታል።
* ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ላለባቹው እናቶች በአብዛኛው ከ28 እስከ 32 ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ የእርግዝና ወቅት ላይ የቅድመ ወሊድ የፅንስ ምርመራዎች ማድረግ ይጀመራል።
* ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ላለባቹው እናቶች የስኳር በሽታው በሚገባ ቁጥጥር ስር ከሆነ እና የቅድመ ወሊድ የፅንስ ክትትል ውጤት ጥሩ ከሆነ ፅንሱ እስኪዳብር እርግዝናው እንዲገፋ ይደረጋል ።
* የደም ቧንቧ በሽታ የሌለባቸው የስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች እርግዝናው እስከ 39 ሳምንት ድረስ እንዲቀጥል ይፈለጋል።
* የደም ቧንቧ በሽታ ያለባቸው የስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች ከ37 እስከ 39 ሳምንታት ውስጥ እንዲወልዱ ይመከራል ። እነዚህ እናቶች የደም ግፊት በሽታ እየተባባሰ ከሆነ፣ ጉልህ የፅንስ መቀንጨር ካለ፣ ወይም የቅድመ ወሊድ የፅንስ ክትትል ባዮፊዚካል ምርመራ ውጤት አስገዳጅ ከሆነ ብቻ ቀደም ብሎ ከ37 ሳምንት በፊት እንዲወልዱ ይደረጋል።
* በቂ የግላይሴሚክ ወይንም የደም ስኳር መጠን ቁጥጥር በሌላቸው እናቶች ላይ የወሊድ ጊዜ እንደየግለሰብ ደረጃ መወሰን ይኖርበታል ። ከወሊድ በፊት የፅንሱ እድገት እና መዳበር መገምገም አለበት።
*የመደበኛ መውለጃ ጊዜ ሳይደርስ በፊት እንዲወለድ የሚያስገድዱ ቅድመ ሁኔታዎች የቅድመ ወሊድ የፅንስ ክትትል አንቴፓርተም ምርመራ ውጤት የፅንስ መጎዳትን የሚያመልከት ከሆነ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት መጨመር፣ የኩላሊት አቅም መድከም እና የእይታ አቅም መዳከም ናቸው።
* ለስኳር በሽታ ታማሚ እናቶች የተፈጥሮ የመውለጃ መንገድ የሚመረጥ ሲሆን በሲዛሪያን ወይም በቀዶ ህክምና መውለድ የሚያስፈልገው በአልትራሳውንድ የተገመተው የፅንስ ክብደት ከ4500 ግራም በላይ ከሆነ እና ሌላ የሚያስገድዱ ምክንያቶች ካሉ ብቻ ነው ።
* በምጥ ጊዜ እና በወሊድ ወቅት የእናቶችን የደም ስኳር መጠን ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ለፅንሱ የተሻለ ውጤት ያመጣል።
* በምጥ ጊዜ የደም ስኳር መጠን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ ። እነዚም በምጥ ጊዜ በጉልበት እንቅስቃሴ ወቅት እንደሚሆነው የሀይል ፍላጎት መጨምር እና ከፈሳሽ ውጭ በምጥ ጊዜ ምግብ መከልከል ናቸው።

ይቀጥላል…

🌼🌼🌼 እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በለሳም አደረሳችሁ! 🌼🌼🌼
26/09/2025

🌼🌼🌼 እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በለሳም አደረሳችሁ! 🌼🌼🌼

የስኳር በሽታ በእርግዝና ወቅት* የስኳር በሽታ በእርግዝና ወቅት በሁለት ይከፈላል። የእርግዝና ስኳር በሽታ እና ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ተብለው ይከፈላሉ።  የእርግዝና  ስኳር በሽታ በ...
24/09/2025

የስኳር በሽታ በእርግዝና ወቅት
* የስኳር በሽታ በእርግዝና ወቅት በሁለት ይከፈላል። የእርግዝና ስኳር በሽታ እና ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ተብለው ይከፈላሉ። የእርግዝና ስኳር በሽታ በ7% ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ ሲከሰት ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ 1% የሚሆኑ እርግዝናዎችን ያጠቃል።
* ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ በእርዝና ወቅት በሶስት ይከፈላል። አይነት 1 ፣ አይነት 2 እና ሌሎች ከልዩ ልዩ ጄኔቲካዊ-፣ መድሃኒት-ወይም በኬሚካል ምክንያት የሚከሰት የስኳር በሽታ ተብሎ ይከፈላል ። የእርግዝና ስኳር በሽታ ከዓይነት 2 ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ጋር በአመጣጥ ይመሳሰላል።
* የእርግዝና ስኳር በሽታ በእርግዝና በሚመጣ የሜታቦሊዝም ለውጥ ምክንያት እንደተጋለጠ እንደ አይነት 2 የስኳር በሽታ ሊቆጠር ይችላል። ለሁለቱም ሁኔታዎች የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ተመሳሳይ ሲሆኑ ከልክ በላይ መወፈርን፣ በቤተሰብ የስኳር ህመም መኖር እና በዕድሜ መግፋት ናቸው።
* በሁሉም ሴቶች ላይ እርግዝና እየገፉ በመጣ መጠን ለኢንሱሊን ሆርሞን የሰውነት የመታዘዝ አቅም እየቀነሰ ይሄዳል። አብዛኛውን ጊዜ የእርግዝና ስኳር በሽታ ያለባቸው ታካሚዎች የጾም ላይ ግሉኮስ ወይም የደም ስኳር መጠናቸው አይዛባም። ስለዚህ በሽታውን እርግዝና ላይ ለማወቅ የተለየ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል ። ምርመራው በአብዛኛው የሚከናወነው ከ24 እስከ 28 ሳምንት ባለው የእርግዝና ወቅት ነው ።
* በእርግዝና ወቅት ለስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ለማወቅ በመጀመሪያው የእርግዝና ክትትል ላይ መገምገም አለበት። ከዛም አናሳ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ተጋላጭ ተብሎ ይከፈላል። ከፍተኛ ተጋላጭ የሚባሉት ከፍተኛ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ፣ በቅርብ ቤተሰብ የስኳር በሽታ መኖር እና የበፊት የእርግዝና ስኳር በሽታ መኖር ናቸው።
* ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑት ወዲያውኑ ምርመራ ይደረግላቸዋል። የመጀመሪያው ምርመራ ነፃ ከሆነ የስኳር በሽታ ምልክቶች በሚታዩበት ጊዜ ወይም በ24-26 የእርግዝና ሳምንት ላይ ድጋሚ ምርመራ ይደረጋል። ከከፍተኛ ተጋላጮች ውጭ የተቀሩት ከ24-26 የእርግዝና ሳምንታቸው ላይ የመጀመሪያው ምርመራ ይደረግላቸዋል።
* በእርግዝና ወቅት የስኳር ህመም ብዙ ችግሮችን ያስከትላል። እነዚህ ዘርፈ ብዙ ሲሆኑ ችግሮቹ በእርግዝና ወቅት ከዛም ከእርግዝና በኋላ የሚከሰቱ ናቸው። እነዚህ ችግሮች በእናት ላይ ፣ በፅንስ ላይ ፣ እንዲሁም በተወለደው ጨቅላ ህጻን ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ ።
* በእናት ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ችግሮች መካከል በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት መጨመር ፣ ያለጊዜው ምጥ መምጣት ፣ የፅንስ መቋረጥ እና ከስኳር በሽታ ጋር የተያያዘ ኪቶአሲዶሲስ (diabetic ketoacidosis) በዋናነት ይጠቀሳሉ ።

* በፅንስ ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ችግሮች መካከል አብረዉ የሚወለዱ በተፈጥሮ የሚመጡ በሽታዎች፣ የክብደት መብዛት ፣ የፅንስ መጥፋት፣ የእድገት መቀንጨር እና እንዲሁም የእንሽርት ውሃ ከመጠን በላይ መብዛት ናቸው ።
* ከወሊድ በኋላ በጨቅላ ህጻን ላይ ብዙ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላል ። ከእነዚህ ሊከሰቱ ከሚችሉ ችግሮች ውስጥ የደም ስኳር መጠን ዝቅ ማለት፣ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ዝቅተኛ መሆን፣ የሰውነት ቢጫነት፣ እና የልብ ሕመም ተጠቃሽ ናቸው ።
* እውነተኛ የእርግዝና ስኳር በሽታ ያለባቸው ሴቶች ቅድመ እርግዝና የስኳር በሽታ ካለባቸው ሴቶች በተቃራኒ አብዛኛውን ጊዜ ከስኳር በሽታ ጋር የተያያዘ ደም ቧንቧን ለሚያጠቃ በሽታ የመጋለጥ እና የተፈጥሮ እክል ያለባቸው ሕፃናት የመውለድ አጋጣሚያቸው ከፍ ያለ አይደለም። ምክንያቱም የህመሙ ቆይታ አጭር ጊዜ መሆን እና በሽታው በእርግዝናው ዘግይቶ መጀመሩ ነው።
* አብረዉ የሚወለዱ በተፈጥሮ የሚመጡ በሽታዎች ከ30 በመቶ እስከ 50 በመቶ ለሚሆነው ከስኳር በሽታ ጋር በተያያዘ የፅንስ እና ጨቅላ ህፃናት ሞት መንስኤ ናቸው። እነዚህ አብረው የሚወለዱ በሽታዎች ልብን፣ ማእከላዊ ስርአተ ነርቭን፣ ኩላሊትን፣ ጨጔራና አንጀትን እንዲሁም የጀርባ አጥንትን ሊያጠቁ ይችላሉ።
* እክል ወይም አብረዉ የሚወለዱ በተፈጥሮ የሚመጡ በሽታዎች ያለባቸው ሕፃናት የመውለድ አጋጣሚን ከፍ የሚያደርጉ ነገሮች ከእርግዝና በፊት አጥጋቢ የደም ስኳር ቁጥጥር አለመኖር ፣ ለረጅም ግዜ የቆየ የስኳር በሽታ መኖር እና የደም ቧንቧ በሽታ መኖር ናቸው።
* ሄሞግሎቢንኤዋንሲ ወይንም በደም ውስጥ ስኳር መጠን ከልክ በላይ መብዛት ምክንያት የቀይ የደም ሕብረ ህዋስ ላይ ያላግባብ ተጣብቆ ያለውን ስኳር መጠን በመጀመሪያው የእርግዝና ሦስት ወራት ውስጥ ሲለካ አብረዉ የሚወለዱ በተፈጥሮ የሚመጡ በሽታዎች የመከሰት አጋጣሚን ሊተነብይ ይችላል ።
* ከልክ ያለፈ የፅንስ እድገት ሌላው ሊፈጠር የሚችል ችግር ሲሆን በስኳር በሽታ ምክንያት ሲሆን ከሌሎች ምክንያቶች በተለየ በፅንሱ ላይ ትልቅ የሆድ ዕቃ እንዲከሰት ያደርጋሉ። ይህም በወሊድ ጊዜ ሾልደር ዲስቶሺያ የሚባል ጣረምጥ እንዲሁም በፅንሱ ላይ የወሊድ ጊዜ አደጋ ሊያስክትል ይችላል።
ይቀጥላል…

… ካለፈው ሳምንት የቀጠለበጤና ባለሙያ የሚደረግ አካላዊ ምርመራ • አንዲት ነፍሰጡር ሴት ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች አይታ ከመጣች በጤና ባለሙያው እነዚህ አካላዊ ምርመራዎች ይደረጋሉ። • ...
16/09/2025

… ካለፈው ሳምንት የቀጠለ

በጤና ባለሙያ የሚደረግ አካላዊ ምርመራ
• አንዲት ነፍሰጡር ሴት ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች አይታ ከመጣች በጤና ባለሙያው እነዚህ አካላዊ ምርመራዎች ይደረጋሉ።
• የደም ግፊታቸው ፣ የልብ ምታቸው፣ የሙቀት መጠናቸው፣ የኦክስጅን መጠናቸው እና አተነፋፈሳቸው ይለካል።

የማህፀን ምርመራ
በምጥ ወቅት የማህፀን ጫፍ ቀስ በቀስ እየከፈተ ይሄዳል። ያለ ጊዜ በሚመጣ ምጥ ወቅት ማህፀን ጫፍ መክፈቱን ለማየት የማህፀን ምርመራ ይደረጋል።ከዚህም በተጨማሪ በየተወሰነ ጊዜ የሚመጣውን የማህፀንን መኮማተር በመቁጠር እንዲሁም ጥንካሬውን በማየት ምጥ መጀመሩን መናገር ይቻላል።

የአልትራሳውንድ ምርመራ
ይሄም የፅንሱን ደህንነት፣ አቀማመጥ እና ክብደት ለማየት፣ የእንሽርት ውሀ መጠን ለመለካት ይጠቅማል። ከዚህ በተጨማሪ የማህፀን ጫፍ ለመለካት እና የእንግዴ ልጅ አቀማመጥ እና ቦታ ለማወቅ ይጠቅማል። ይህም የህክምና ውሳኔዎችን ለመወሰን ይረዳል።

የላብራቶሪ ምርመራዎች
- ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የደም እና የሽንት ምርመራዎች ሊደረጉ ይችላሉ። ይህም በደም እና በሽንት ውስጥ ኢንፌክሽን ካለ ለማየት ይጠቅማል።

ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥና ቅድመ ወሊድ የሚያስከትሉት ችግሮች፦
ያለ ጊዜ መወለድ ለተለያዩ ችግሮች ሊዳርግ ይችላል። ይህም ልጁ ምን ያህል ቀደም ብሎ ተወልዷል በሚለው ይወሰናል። ከመወለጃ ጊዜያቸው የበለጠ አስቀድመው የተወለዱ ህፃናት ለችግሮቹ የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።
• ያለ ጊዜ የሚወለዱት ህፃናት ሳንባቸው ያልዳበረ ስለሆነ የትንፋሽ እጥረት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማቸዋል። ይሄም ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው እንዲታከሙ ያስገድዳል። ይሄ ደሞ ለኢንፌክሽን የበለጠ ተጋላጭ ያረጋቸዋል።
• በተጨማሪ በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም ይቻላል። ይሄም ለረጅም ጊዜ የነርቭ ጉዳት ያስከትላል። እነዚህ ችግሮች በልጅ አእምሮና በማሰብ ችሎታ እድገት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፤ ይህም ወሳኝ ክንውኖች ላይ ለመድረስ መዘግየት ያስከትላል።
• የአንጀት ቁስለት፣ እብጠት እና የባክቴሪያ ኢንፌክሽን የሚያስከትል ከባድ የአንጀት በሽታ ሊያጋጥማቸው ይችላል።
• ያለ ጊዜ የተወለዱ ህፃናት ለአንደንድ የልብ ህመም የተጋለጡ ናቸው።
• ያለ ጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት ያልዳበረ በሽታ የመቋቋም ስርዓት ስላላቸው ለኢንፌክሽን እና ለተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣሉ።ይህም ለከፍተኛ ህመም እና ሞት ይዳርጋቸዋል።
• ያለ ጊዜያቸው የተወለዱ ህፃናት ወደፊት ለምሳሌ ሴረብራል ፖልሲ፣ የማየት እና የመስማት ችግር እንዲሁም የእድገት መዘግየት፣ እንደ ከፍተኛ የደም ግፊትና የስኳር በሽታ ያሉ ሥር የሰደዱ የጤና እክሎችን ሊያስከትል ይችላል።
• ከዚህ በተጨማሪ እናትየው ለረጅም ጊዜ ሆስፒታል ልትተኛ ትችላለች ይሄም ለኢንፌክሽን የመጋለጥ ዕድሏ ከፍ ሊል ይችላል። በአጠቃላይ ያለ ዕድሜ መወለድ በልጅ አጠቃላይ ጤንነትና ደህንነት ላይ ዘላቂ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥን እንዴት መከላከል ይቻላል?
መደበኛ የቅድመ ወሊድ ክትትል ያለግዜው የሚመጣ ምጥን ለመከላከል ጠቃሚ ነው። በቅድመ ወሊድ ምርመራ ጊዜ ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ እና ለመከላከል ይቻላል።
• በእርግዝ ወቅት አንዳንድ የአኗኗር ለውጦችን ማድረግ ለምሳሌ ሲጋራ ማጨስን ማቆም፣ አልኮል እና አደንዛዥ እጾችን ማስወገድ እና የተመጣጠነ ምግብን መመገብ ይረዳል።
• የጤና ተቋማት ያለ ጊዜ የሚወለዱ ህፃናት ቁጥር እንዲቀንስ ለማድረግ የግል እቅድ ማውጣት ይችላሉ። በተጨማሪም በየጊዜው በሚደረግ ምርመራ ኢንፌክሽኖችን ቀደም ብሎ ለማወቅና ለማከም ያስችላል።
• ምጥ ከጀመረ በኋላ ምን ማድረግ እንችላለን?
ምጥ ከተፈጠረ በኋላ የተለያዩ የህክምና እርዳታዎች በጤና ባለሙያዎች ይሠጣሉ።
ከነዚህም መካከል:
• ቶኮሊቲክስ በመስጠት ይህም ምጥን ለመግታት እና ለማዘግየት የሚሠጡ መድሃኒቶች ናቸው።
• ስቴሮይድ: ይህም የፅንሱን ሳንባ ብስለት በማፋጠን ከወሊድ ጋር ተያይዞ የሚመጡ የአተነፋፈስ ችግሮችን ይቀንሳሉ።

• ማግኒዥየም ሰልፌት: ይህም የሕፃኑን አእምሮ ይጠብቃል እናም ሴሬብራል ፓልሲ የመያዝ እድልን ይቀንሳል።
• አንቲባዮቲክስ: ይሄ ደግሞ በይበልጥ የእንሽርት ውሀ ከፈሰሰ በኋላ ማህፀን ለኢንፌክሽን ተጋላጭ እንዳይሆን ለመከላከል ይጠቅማል።

ያለጊዜ ምጥ መጣ ማለት ያለጊዜ ልጅ ይወለዳል ማለት ነው?
ሁልጊዜ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ምጥ ከጀመረ በኋላም እንኳን የተለያዩ የጤና እርዳታ የተደረገላቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ምጣቸውን ማዘግየት ተችሏል።
• ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ የሚያሳየውን ምልክቶች መረዳት እና ማወቅ አንዲሁም ምልክቶቹን ሲያዩ አቅራቢያ ወዳለው የጤና ተቋም በፍጥነት በመሄድ በወሊድ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን መቀነስ ይቻላል።
• ያለ ጊዜያቸው የተወለዱ ህፃናት የተለየ የጤና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በመሆኑም አንዲት ነፍሰጡር እናት ያለ ጊዜዋ የምጥ ምልክቶችን ካየች በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርባታል።
• ያለጊዜ የተወለደ ህፃን እንደተወለደ በጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ የጤና እርዳት ስለሚያስፈልገው ወደ ጨቅላ ህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ገብቶ አስፈላጊ እንክብካቤ እና የጤና እርዳታ ሊደረግለት ይገባል።

ልጅዎ ወደ ጨቅላ ህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ሲገባ ምን ሊጠብቁ ይገባል?
• የመጀመሪያው ከፍተኛ እንክብካቤ ላይ ያተኮረ ልዩ አካባቢ ይጠብቁ። የላቁ የህክምና መሳሪያዎችን በመጠቀም ልጅዎ በጤና ባለሙያዎች ቡድን ክትትል ይደረግለታል። የጨቅላ ህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል በሚኖሮት ቆይታ ውስብስብ የሕክምና ቃላትን፣ ሂደቶች፣የተለያዩ ቱቦዎች እና ተቆጣጣሪዎች ስለሚኖሩ የስነልቦና ዝግጁነት ያስፈልጋል። በዚህን ወቅት ከልጅዎ ጋር መደበኛ ጉብኝት እና የግንኙነት ጊዜ ይበረታታሉ። የልጅዎን እድገት እና እንክብካቤ እቅድ ለመረዳት እዚያ ካሉ የጤና ባለሞያዎች ጋር መግባባት ቁልፍ ነው።

ያለጊዜ ለተወለደ ጨቅላ ህፃን ደህንነት ለመጠበቅ ወላጆች ቤት ውስጥ ማድረግ ያለባቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?
• ከፍተኛ ስጋት ላለው ህጻንዎ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን ማረጋገጥ ብዙ ቁልፍ እርምጃዎችን ያካትታል። ከነዚህ መካከል ህፃኑ ከመጠን በላይ ማሞቅ ወይም ማቀዝቀዝን ለመከላከል የሕፃኑን ክፍል የሙቀት መጠን 20-22°c ያቆዩት።
• የኢንፌክሽን አደጋዎችን ለመቀነስ ንፅህና ያስፈልጋል። ለጀርሞች ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚመጣውን የሰው ብዛት መገደብ እና ለመጠየቅ የሚመጡ ማንኛውም ሰው ጤናማ መሆኑን ማረጋግጥ። የልጅዎን ሳንባ ለመጠበቅ ማንም ሰው በቤት ውስጥ እንደማያጨስ ማረጋገጥ።

ከቅድመ ወሊድ በኋላ ፍርሃትን እና ጭንቀትን ማሸነፍ፡
አንዲት ነፍሰጡር ያለጊዜ በሚጀምር ምጥ እና ከቅድመ ወሊድ በኋላ፣ ፍርሃት እና ጭንቀት ሊሰማት ይችላል። ይሄ ደሞ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን እነዚን ስሜቶች የመቋቋሚያ ዘዴዎች መጠቀም ሊረዱ ይችላሉ።
• ስለልጅዎ ሁኔታ እራስዎን ያስተምሩ። ይህን በማድረግ ውስጥ በራስ የመተማመን ልምድን ያዳብራሉ። ልምድ እና ምክር ለመጋራት ከሌሎች ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ካለፉ ወላጆች ጋር መገናኘት ይጠቅማል።

• ጭንቀትን ለመቆጣጠር የተለያዩ የመዝናኛ ዘዴዎችን ይለማመዱ። ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች እና የምክር አገልግሎቶች ድጋፍ ይፈልጉ። እርስዎ እና ልጅዎ አንድ ላይ በሂደቱ ውስጥ ሲያድጉ በትናንሽ፣ አወንታዊ ክንውኖች ላይ ማተኩር እና ትንንሽ ድሎችን ማክበርም ይረዳል።

ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ያለጊዜ የሚጀምር ምጥ እና ቅድመ ወሊድ ልዩ የሆነ የሕክምና እርዳታና እንክብካቤ እንዲሁም ስሜታዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ችግሮች ናቸው። አደጋዎችን እና ምልክቶችን መረዳቱ ወቅታዊ የህክምና ጣልቃገብነት እንዲኖሩ ያደርጋል። ይህም ለእናቲቱም ሆነ ለህፃኑ ጥሩ የሆነ ውጤት ይኖረዋል።
• የጨቅላ ህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ወሳኝ የጤና እርዳታ እና እንክብካቤን ይሰጣል። ወላጆች በመረጃ በተደገፈ ጥብቅና እና ተከታታይ ተሳትፎ ለልጃቸው ማገገም ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
• ፍርሃትን እና ጭንቀቶችን በትምህርት እና እርስ በራስ በመደጋገፍ የራስ መተማመንን ለመፍጠር አስፈላጊ ነው። በተጠናከረ እንክብካቤ እና ድጋፍ፣ ቤተሰቦች ያለጊዜ የሚጀምር ምጥን እና የቅድመ ወሊድ ውስብስብ ሁኔታዎች መረዳት እና ለልጃቸው ጤናማ የወደፊት ህይወት መስራት ይችላሉ።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🤰 ውድ የለእናት ቤተሰቦችእንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ 🌼🌼            🌼 2018 🌼 🌼መልካም አዲስ ዓመት።🌼
11/09/2025

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🤰 ውድ የለእናት ቤተሰቦች

እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ 🌼🌼

🌼 2018 🌼

🌼መልካም አዲስ ዓመት።🌼

… ካለፈው ሳምንት የቀጠለያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ ምን ማለት ነው? • ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ ማለት አንዲት ነፍሰጡር ከ37 የእርግዝና ሳምንታት በፊት ምጥ ሲጅምራት ማለት ነዉ። • ያለ ጊዜ ...
08/09/2025

… ካለፈው ሳምንት የቀጠለ

ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ ምን ማለት ነው?

• ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ ማለት አንዲት ነፍሰጡር ከ37 የእርግዝና ሳምንታት በፊት ምጥ ሲጅምራት ማለት ነዉ።
• ያለ ጊዜ ምጥ መምጣት ያለ ጊዜያቸው ልጆች እንዲወለዱ ያደርጋል። ያለ ጊዜ የተውለዱ ህፃናት ለተለያዩ የጤና እክሎች የተጋለጡ ናቸው።
• ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ እና ቅድመ ወሊድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ነው። እነዚህም የሚወለዱ ጨቅላ ህፃናትን ለህመም እና ለሞት የሚዳርጉ መንስኤ ናቸው።
• የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እንደገመተው በየዓመቱ ወደ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ያለ ጊዜያቸው ይወለዳሉ፣ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚወለዱ ሕፃናት መካከል ከአስር
ህፃናት አንዱ ነው።
• በኢትዮጵያ በተደረጉ ጥናቶች ያለጊዜ የሚጀምር ምጥ እና ቅድመ ወሊድ የተለያየ መጠን እንዳላቸው ጠቁመዋል። እ.ኤ.አ. በ2020 በተደረገ ስልታዊ ግምገማ እና ሜታ- ትንተና በኢትዮጵያ የቅድመ ወሊድ መስፋፋት 12.18% አካባቢ እንደሆነ ገምቷል።
• ምጥ ያለ ጊዜ እንዲመጣ ሊያደርጉ የሚችሉ አጋላጭ ሁኔታዎችን ማወቅ፣ ምልክቶቹን እና እንዴት ህክምና ማግኘት እንደሚቻል መረዳት ለነፍሰጡር እናቶች እንዲሁም ለሚወለዱ ህፃናት ከፍተኛ አስተዋፆ አለው።

መንስኤ
• አንዲት ነፍሰጡር ሴት ያለጊዜ ምጥ ለምን እንደሚጀምራት ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። ማለትም አብዛኛውን ጊዜ መንስኤው አይታወቅም።
• ነገር ግን ያለ ጊዜ ለሚመጣ ምጥ አጋላጭ የሚያረጉ ሁኔታዎች አሉ።

አጋላጭ ሁኔታዎች
• እድሜ: ይሄ ማለት እድሜያቸው ከ17 በታች ወይም ከ35 አመት በላይ ከሆነ
• ከዚህ በፊት በነበረ እርግዝና ያለ ጊዜ ምጥ አጋጥሟት ከነበረ
• የመሀፀን መለጠጥ ማለትም የእንሽርት ውሀ መብዛት፣ ከአንድ በላይ እርግዝና (መንታ፣ ሶስት ወዘተ..)
• ሌላ ተጓዳኝ በሽታ መኖር ለምሳሌ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ የእንቅርት በሽታ፣ የኩላሊት ህመም
• የሽንት ቱቦ፣ የኩላሊት ኢንፌክሽን እንዲሁም ደሞ ያልታከመ የአባላዘር በሽታ ካለ
• ጭንቀት፣ አደጋ ደርሶ ከነበረ
• በእርግዝና ወቅት ሲጋራ ማጨስ፣ አደንዛዠ እፅ መጠቀም
• ከመሀፀን ደም መፍሰስ
• የነፍሰጡሯ ሴት ዝቅተኛ የክብደት መጠን ወይም በጣም ከፍተኛ ክብደት መጨመር።

ምልክቶች
የሚከተሉትን ምልክቶች ማወቅ እና መረዳት መቼ የጤና ባለሙያ እርዳታ እንደሚያስፈልግ እና በጊዜ ወደ ጤና ህክምና ተቋም በመሄድ የሚያስፈልገውን ምርመራና ህክምና ለማግኘት ይረዳል።

ምልክቶች
• ያለ ጊዜ የሚመጣ ምጥ ከተለመደው የምጥ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ነው።
እነሱም፦
• የማህፀን መኮማትር ወይም የመሀፀን ጭብጥ ዘርጋ ማለት መጀመር (በ1 ሰዓት ውስጥ ከ6 በላይ የመሀፀን ጭብጥ ዘርጋ ማለት)
• የሆድ ቁርጠት ምልክቶች
• የታችኛው ጀርባ ላይ ህመም መሰማት
• ከመሀፀን የሚወጣዉ ፈሳሽ መጨመር ወይም መቀየር ለምሳሌ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ፣ እንደ ውሀ አይነት ፈሳሽ መውጣት
• የእንሽርት ውሀ መፍሰስ

ህክምና ተቋም መሄድ ያለብኝ መቼ ነው?
• ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከታዩ አቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የጤና ህክምና ተቋም በአስቸኳይ መሄድ ይኖሩቦታል።
• በጤና ባለሙያ ሳይታዩ ያለጊዜ ምጥ መምጣቱን ማወቅ አስቸጋሪ ነው። ይህንንም ለማድረግ የጤና ባለሞያዎች የተለያዩ ምርመራዎችን ያደርጋሉ።

በህክምና ተቋም የሚደረጉ ምርመራዎች
• አንዲት ነፍሰጡር ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች አሳይታ ከመጣች የጤና ባለሙያው የሚከተሉትን ምርመራዎች ሊያደርግ ይችላል።
• እነዚህን ምርመራዎች ማድረግ ያለጊዜ ምጥ መምጣቱን ለማወቅ እንዲሁም ተገቢውን የህክምና እርዳታ ለመስጠት ይረዳል። እነዚህም ምርመራዎች የሚጀምሩት የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እና አካላዊ ምርመራ በማድረግ ነው። ይህም አሁን ያለውን ሁኔታ ለመረዳት፣ ከዚህ በፊት እርግዝና ከነበረ በዚያን ወቅት የተፈጠረ ችግር ከነበረ ለማወቅ እንዲሁም ለምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ይረዳል።

በጤና ባለሙያ ሊጠየቁ የሚችሉ ጥያቄዎች:
• ወደ ጤና ባለሙያ የመጡበት ምክንያት፣ ስላዩት ምልክቶች በደንብ ይጠይቃሉ።
• ሌላ ተጓዳኝ በሽታ ካለ እንዲሁም
• ከዚ በፊት እንዲ አይነት ነገር በቀድሞ እርግዝና ተፈጥሮ ከነበረ ይጠይቃሉ።

በጤና ባለሙያ የሚደረግ አካላዊ ምርመራ

ይቀጥላል….

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሠላም አደረሰዎ!
04/09/2025

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሠላም አደረሰዎ!

ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ (Preterm Labor) • ያለ ጊዜ የሚመጣን ምጥ ለመረዳት መደበኛ ምጥ ምን እንደሆነ መረዳት ይጠቅማል። • መደበኛ ምጥ ድንገተኛ ምጥ በመባልም ይታወቃል።  የሕክም...
03/09/2025

ያለ ጊዜ የሚጀምር ምጥ (Preterm Labor)
• ያለ ጊዜ የሚመጣን ምጥ ለመረዳት መደበኛ ምጥ ምን እንደሆነ መረዳት ይጠቅማል።
• መደበኛ ምጥ ድንገተኛ ምጥ በመባልም ይታወቃል። የሕክምና ጣልቃ ገብነት ሳያስፈልግ ልጅ የሚወለድበትን ተፈጥሯዊ ሂደት ያመለክታል።
• መደበኛ ምጥ በእያንዳንዱ ሴት ላይ የሚለያይ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። የምጥ ደረጃዎቹን እና ምልክቶቹን መረዳት ነፍሰጡር እናቶች ጥሩ እና በራስ የመተማመን ስሜት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል። አንድ የተለመደ እርግዝና በአብዛኛው የመጨረሻ የወር አበባ ከታየበት ጊዜ ጀምሮ ከ37 እስከ 42 ሳምንት ይቆያል ተብሎ ይታሰባል። መደበኛ ምጥም የሚጀምረው በዚህ ጊዜያት ውስጥ ነው።
• የመደበኛ የቅድመ ወሊድ ክትትል መኖር፣ ከቤተሰብ እና ጓደኛ ጥሩ ድጋፍ መኖር ለጤናማ እርግዝና፣ ለምጥ እንዲሁም ለወሊድ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው።

የምጥ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
• ማህፀን መኮማተር ይጀምራል። ይህም የበለጠ መደበኛ፣ ጠንካራ እና የተቀራረበ እየሆነ ይሄዳል።
• የእንሽርት ውሀ መፍሰስ፦ ምጥ ጀምሮ ካልነበረ ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው የእንሽርት ውሀ ከፈሰሰ በኋላ ነው።
• በመደበኛ ምጥ የማህፀን ጫፍ ቀስ በቀስ እየከፈተ ይሄዳል። ይህም በጤና ባለሞያዎች ክትትል ይደረጋል።
• የጀርባ ህመም፣ የማያቋርጥ የታችኛው ጀርባ ህመም።
• ሌሎች የምጥ ምልክቶች፡ ወደ ታች የመግፋት ስሜት፣ የሆድ ቁርጠት፣ ተቅማጥ፣ የማህፀን ፈሳሽ ደም ቀላቅሎ መፍሰስ፣ የማህፀን ፈሳሽ መጠን መጨመር የሚጠቀሱ ናቸው።

የምጥ ደረጃ በሦስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል።
•የመጀመሪያ ደረጃ ምጥ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ የምጥ ደረጃ በመባል ይታወቃል።
• እነዚህን የምጥ ደረጃዎች ማወቅ ነፍሰ ጡር እናቶች መደበኛ ምጥ ላይ ምን መጠበቅ እንዳለባቸው ለመረዳት ይጠቅማል።
• የመጀመሪያ ደረጃ ምጥ ከብዙ ሰዓታት እስከ ቀናት ሊቆይ ይችላል። የማህፀን መኮማተር በቀስታ ይጀምራል፣ ቀስ በቀስም መደበኛ እና ጠንካራ እየሆነ ይሄዳል።
• ከዚህ በተጨማሪ የማኅጸን ጫፍ መክፈት ይጀምራል። በዚ ጊዜ ንፋጭ የሚመስል ፈሳሽ ከማህፀን ይወጣል ይሄም የማህፀን በር ጫፍ እየሰፋ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው።
• የመጀመሪያ ደረጃ ምጥ የሚያበቃው ጠንካራና መደበኛ ምጥ ሲኖር እና ማህፀን ሙሉ ለሙሉ ሲከፍት ነው።
•ሁለተኛ ደረጃ ምጥ፦ አንዲት ነፍሰጡር ሁለተኛ ደረጃ ምጥ ውስጥ ገብታለች የምንለው የማኅጸን ጫፍ ሙሉ በሙሉ ሲከፍት እንዲሁም የማህፀን መኮማተሩ ጠንካራ እየሆነ ሲሄድ ሲሆን የሚጠናቀቀውም ልጅ በመውለድ ነው።
• እንደ እናትየው ጤና ፣ የሕፃኑ አቀማመጥ እና የእናቲቱ የመጀመሪያ እርግዝና መሆን አለመሆን እንዲሁም በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ከጥቂት ደቂቃዎች እስከ ብዙ ሰዓታት ሊቆይ ይችላል።
•ሶስተኛው ደረጃ፡- ይህ ደረጃ የእንግዴ ልጅ መውለድን ያካትታል። ብዙውን ጊዜ ህፃኑ ከተወለደ በ30 ደቂቃ ውስጥ ይከሰታል፡ ምልክቶቹም መጠነኛ የማህፀን መኮማተር እና የእንግዴ ልጅ ከማህፀን ግድግዳ ላይ ተነቅሎ መውጣትን ያካታትታል።
ይቀጥላል....

በቅድመ ወሊድ ጊዜያት እንዴት የእናቶችን እና የልጆቻቸውን ግንኙነት ማጠናከር እንችላለን?የቅድመ ወሊድ ጊዜ ከመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ጊዜያት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የእርግዝና ጊዜያት እንዲሁም...
25/08/2025

በቅድመ ወሊድ ጊዜያት እንዴት የእናቶችን እና የልጆቻቸውን ግንኙነት ማጠናከር እንችላለን?
የቅድመ ወሊድ ጊዜ ከመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ጊዜያት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የእርግዝና ጊዜያት እንዲሁም ከህፃኑ የዉልደት ጊዜያት በፊት ያለው ይሆናል ። ይህም አንድ ብለን ከምንቆጥረዉ ሳምንት እስከ 38ተኛ ሳምንት ነዉ።
ታድያ እነዚህ ወሳኝ ጊዜያት የተሳኩ መሆናቸው የወሊድ ወቅትን እና ከዛም በኃላ ያሉትን ጊዜያት የተሳኩ ያደርጉልናል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የእናቶች አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጤንነት ዋነኛዉ ጉዳይ ነዉ። ስለ ስነልቦና ዝግጁነት እና ጤንነት ስናነሳ የእናቶች እና ልጆቻቸው ጠንካራ ግንኙነት ማንሳት እንችላለን። ይህን ግንኙነት ለማጠናከር ይረዳን ዘንድ ጥቂት ዘዴዎችን እንመልከት።
1. የድምፆች ሀይል በቅድመ ወሊድ:- በተረጋገጠው ሳይንሳዊ ጥናት በማህጸን ውስጥ ያለው ፅንስ ከ18ተኛው ሳምንት ጀምሮ ድምፆችን መለየት እንደሚችል ያስረዳል። ከዚህም ቀዳሚውን ድርሻ የሚወስደው ከእናታቸው የሚወጣውን ድምፆች ይሆናል።
- ንግግር መጀመር እና በድግግሞሽ ንግግር ማድረግ:- ይህ እጅግ አስፈላጊ እና አስደናቂ ተግባር በማህጸን ውስጥ ላለው ፅንስ አስፈላጊ ነው። ይህም ፅንሱ የእናቱን ድምፅ እንዲለይ እና እንዲያውቅ ብሎም የተላመደውን የእናቱን ድምፅ በተደጋጋሚ በሚሰማበት ወቅት ደስታ እንዲሰማው ይረዳል።
2.በእጆቻችን መዳሰስ
በእጆቻችን መዳሰስ ሌላኛዉ እናቶችን ከልጆቻቸዉ ጋር ያላቸዉን ቅርበት እና ግንኙነት የሚያዳብር ሁኔታ ነው። በማህፀን ያሉ ልጆች በሚዳበሱበት ግዜ ለተሰጣቸዉ ንክኪ እና መዳበስ ምላሽን ይሰጣሉ። ይህም በተደጋጋሚ ጊዜ ስሜቱን በመላመድ ደስተኛ ከመሆንም ባለፈ ከእናቶቻቸው ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠነክራል።
3.ለልጆቻቸው ማዉራት እና ዜማን ማሰማት
ልጆች ከእናታቸው ማህፀን ዉጫዊ ክፍል የሚመጣላቸውን ድምፅ ከመለየት ባለፈ በጥሩ መንፈስ እና ስነልቦናዊ መረጋጋት ላይ ሁነዉ በሚሰሟቸው ድምፆች እርጋታ እና ደስታ ማግኘት ይችላሉ። በዚህም ከእናታቸዉ የሚመጣዉን ዜማ ወይም ንግግር ያስተውላሉ ደስታንም መረዳት ይችላሉ።
4.ድምፅን ከፍ አድርጎ ማንበብ
ይህ አይነት ተግባር እጅግ አስደሳች ነው። ልጆች ይህን ተግባር በድግግሞሽ ማድረግ የድምፅን ምት እና ሀረግ መለየት ያስችላቸዋል።
በአጠቃላይ ይህ አይነቱ ግንኙነት በጣም መሠረታዊና ዘላቂ ፍቅርን የሚያፀና ሁኔታ ነው።ይህም በእርግዝና ወራት እንዲሁም ከወሊድ በኃሏ ባሉት ወራት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በዘላቂነት ላሉት የእድገት ጊዜያት እና ስሜታዊ ቁርኝት ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና አላቸው።

Address

Adwa Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lenat-MOM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Lenat-MOM:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram