Rida Mental Health Consultancy

Rida Mental Health Consultancy To Inspire people for a better tomorrow, reach to our people to make a difference in their lives by

World Mental Health DayWorld Mental Health Day 2021 - Mental health care for all: let’s make it a reality10 October 2021
10/10/2021

World Mental Health Day

World Mental Health Day 2021 - Mental health care for all: let’s make it a reality

10 October 2021

የፓኒክ ህመም / Panic Disorder/ይህ የአእምሮ ህመም እስከ 1980 እ.ኤ.አ ድረስ የበሽታ አይነት ሆኖ አልታመዘገበም ነበር። አሁንም ቢሆን በፓኒክ ህመም /Panic Disorder/ ...
19/06/2021

የፓኒክ ህመም / Panic Disorder/

ይህ የአእምሮ ህመም እስከ 1980 እ.ኤ.አ ድረስ የበሽታ አይነት ሆኖ አልታመዘገበም ነበር። አሁንም ቢሆን በፓኒክ ህመም /Panic Disorder/ የሚሰቃዩ በርካታ ሰዎች የልብ ሃኪም ጋር ክትትል አላቸው፤ ምልክቱ ከልብ እና ሳንባ በሽታ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው። ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት በኋላ የፓኒክ በሽታ የጭንቀት አይነት ሆኖ ሊታይ ችሏል።

 ምልክቶቹ

• ድንገተኛ እና ከፍተኛ የፍርሃት/ጭንቀት/ ስሜት መኖር ሲሆን
o ይህ ስሜት ብዙዉን ጊዜ ቀስቃሽ የለዉም፤ እንደዉም በእንቅልፍ ለይ እያሉ አልያም ዘና እያሉ ሊነሳ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ግን ትንንሽ ዉጥረቶች ሊቀሳቅሱት ይችላል።
o የምልክቱ ጥቃት/ Attack/ ከደቂቃዎች እስከ 1 ሰዓት ሊወስድ ይችላል።

• አካላዊ ምልክቶች
o ፈጣን የልብ ምት
o የመታነቅ አልያም የመታፈን ስሜት
o የደረት ህመም
o ማላብ
o ማንቀጥቀጥ
o ብርድ ብርድ ማለት ወይም ሙቀት ስሜት መሰማት
o የራስ ማዞር ስሜት
o ከቁጥጥር ዉጭ የመሆን ወይም “አእምሮን የመሳት” ስሜት
o ማቅለሽለሽ/ ሆድ መጎርበጥ/
o ሰመመን ዉስጥ የመሆን/ የመቃዠት/ ስሜት
o የመደንዘዝ ስሜት

• ከእነዚህ ዉስጥ 4 እና ከዛ በላይ ካለ እንዲሁም

• ከምልክት ጥቃቱ ቀጥሎ ከ 1 ወር እና ከዛ በላይ የሚቆይ ከሚከተሉት ስጋቶች 1 ወይም ከዛ በላይ ሲቆይ
o በድጋሚ ምልክቶቹ ይመጣሉ የሚል ስጋት
o ምልክቱ ጤናዬ ለይ ጉዳት ያደርሳል የሚል ስጋት
o በፓኒክ ህመሙ ምክንያት የባህሪን ለዉጥ ስጋት

 ተጋላጭነት
• በሽታው የሚነሳው አማካኝ እድሜ 24 አመት ነው።
• ሴቶች ከወንዶች በበለጠ በ2 እጥፍ ይጠቃሉ።
• ስነ-ህይወታዊ / በዘረ-መል/ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።
• በፓኒክ በሽታ የሚሰቃዩ ሰዎች ለድብርት ህመም /60%/ እንዲሁም ራስን ለማጥፋት

 ህክምና
• በአጠቃለይ 2 አይነት ህክምና ለፓኒክ ህመም ይሰጣል። እንዚህም

1. የመድሃኒት ህክምና
 የመድሃኒት ህክምና ከስነ ልቦና ህክምና በፈጠነ ለዉጥ ያመጣል
 የተለያዩ የመድሃኒት አይነቶች በመሞከር እንደታማሚው የሚስማማዉን መምረጥ ይቻላል

2. የስነ ልቦና ህክምና
 በሙያው የሰለጠነ ሰው ማግኘት ያስፈልጋል።
 ለዉጥ ለማማጣት ረዘም ያለ ጊዜ ቢወስድም ከመድሃኒት ህክምናው ጋር አንጻራዊ ዉጤት አለው

መልካም ጊዜ !!!

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ
RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
12 ሰኔ 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

16/05/2021

የአእምሮ ጤና በፋና-የአእምሮ ጤና እና በጎ አድራጎት ድርጅቶች
===========================
ዘውትር እሁድ በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ከ11:00 እስከ 12:00 ሰአት በሚተላለፈው የአእምሮ ጤና ዝግጅታችን የዛሬው ርእሰ ጉዳይ በአእምሮ ጤና ላይ የሚሰሩ በጎ አድራጎት ስራዎች ነው። የጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ከሆነው ዲያቆን መለሰ አየለ ከዶ/ር መሀመድ ጋር ቆይታ ያደርጋል።

~የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር እንዴት ተመሰረተ?
~ምን አይነት አገልግሎት ነው የሚሰጠው?
~አገልግሎቱን የሚያገኙ ሰዎች ምን ያህል ናቸው።
~የገቢ ምንጫቸው ምንድነው? በእነዚህና ተያያዥ ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ይኖረናል።

ለዲያቆን መለሰ ወይም ለኛ ጥያቄ ካላችሁ ላኩልን ምላሽ እንሰጣለን። በዝግጅታችን ላይ ሀሳብና አስተያየታችሁን ላኩልን ለማሻሻል ይጠቅመናል።
የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበርን ለመደገፍ 6860 ላይ ok ብለው ይላኩ።

የአእምሮ ጤና የሁላችንም ጉዳይ ነው።

~~~~~በዓልን ተከትሎ የሚመጣ ጭንቀት~~~~~አመት በዓል የደስታ ጊዜ ነው። ሆኖም ግን ጭንቀትን፣ ብቸኝነትን እንዲሁም ሃዘንን ይዞ ይመጣል። ለአብዛኛው ሰው በዓል ከቤተሰብ፣ ዘማድ አዝማድ፣...
12/05/2021

~~~~~በዓልን ተከትሎ የሚመጣ ጭንቀት~~~~~

አመት በዓል የደስታ ጊዜ ነው። ሆኖም ግን ጭንቀትን፣ ብቸኝነትን እንዲሁም ሃዘንን ይዞ ይመጣል። ለአብዛኛው ሰው በዓል ከቤተሰብ፣ ዘማድ አዝማድ፣ ጓደኛ ጋር ልዩ ጊዜ የሚያሳልፉበት ቢሆንም ለአንዳንድ ሰዎች ግን በተቃርኒው ከባድ ጊዜ ያሳልፋሉ።

በተለይ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንዲሁም የሰላም እጦት ጋር ተያይዞ በዓላት የሃዘን እና የጭንቀትን ወዝ ተቀብተው ብቅ ይላሉ። እነዚህ አሉታዊ ስሜቶች ጊዜያዊ የስሜት መዋዠቅ እንጂ የአእምሮ ህመም አይደሉም። ሆኖም ግን አብዛኛው የአእምሮ ህመሞች የሚቀሰቀሱት በዓላት ከመምጣታቸው ባሉት ጥቂት ሳምንታት እንዲሁም ከበዓል በኋላ ባለው 1 ወር ጊዜ እንደሆነ ይጋመታል።

ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚመጡ ጭንቀቶችን ለመቋቋም የሚከተሉትን ነጥቦች እነሆ

1. የአሁኑ በዓል የተለየ ነው
እንደበፊቱ ባይሆንም ደስታን ላማግኘት የመስኮት ቀዳዳ በቂ ነው። የዘንድሮዉን ለዘንድሮ

2. በዓል ከቤተሰብ፣ ዘማድ አዝማድ እና ጓደኛ ጋር የምንጠያየቅበት/ የምንዘያየርበት/ ጊዜ ነው።
እርግጥ “ሁሉም ሙሉ” ቢሆን ማናችንም ባልጠላን፤ ግን የበዓል አላማው ይህ አይደለም።

3. አመስጋኝ መሆን ይረዳል።
በከፋን በሌለን ጊዜ ሁላ “እንኳን አደረሳችሁ” መባባል ደስታን ይሰጣል። መልካም ላደረገልን ሰውም ምስጋናን መስጠት ደግሞ ድርብ ደስታ ያመጣል

4. ራስህን ከመንከባከብ ወደኋላ አትበል።
በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ አካል ብቃት መቀጠል፣ የግል ንጽህናን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። አልፎም ከትዳር አጋር ጋር ጊዜ ማሳለፍ ጠቃሚ ነው።

5. በጎ አድራጎት ስራ ለይ ማሳተፍ
ከራስ በላይ ለሌሎች መዋል የሚፈጥረው የሞራል እርካታ መለኪያ የለውም። እንደምንችለው እንደአቅማችን በአይነት፣ በገንዘብ እንዲሁም በጉልበት መሳተፍ ጠቃሚ ነው።

6. እርዳታ መጠየቅ ድክመት አይደለም
ቤት ዉስጥ የሚሰሩ ስራዎች፣ ማሟላት ያለብንን ነገር ቢኖር ከሌሎች እርዳታ ብንጠይቅ በዙ ጭንቀትን ይቀርፍልናል፤ ወዳጅነትንም ያስድጋል።

7. ያጣነዉን ሰው ጊዜ ወስደን ማሰብ/ማዘን
ዛሬ ላይ አብረውን የሌሉትን ወዳጆቻችንን ዉስን ጊዜ ሰጥተን ማስብ ቀሪዉን የበዓል ጊዜ በደስታ እንድናሳልፍ ይረዳናል።

!!መልካም በዓል!!

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ

RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
4 ግንቦት 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

እጅግ አዝነናል... የኦቲዝም ልሳን ... ዘሚ ዩኑስ
11/05/2021

እጅግ አዝነናል... የኦቲዝም ልሳን ...
ዘሚ ዩኑስ

~~~ሱስ በቋሚ ተጠቃሚዎች እና በማይጠቀሙ ሰዎች ያለው ልይነት~~~ቋሚ ተጠቃሚ ያልሆኑ• የህይወት ኑሮ መደበኛ/ ኖርማል/ ነው።• በህይወታቸው የሚደርሰዉን ዉጣ ዉረዶችን ከሱስ ዉጭ አማራጭ ይ...
15/04/2021

~~~ሱስ በቋሚ ተጠቃሚዎች እና በማይጠቀሙ ሰዎች ያለው ልይነት~~~

ቋሚ ተጠቃሚ ያልሆኑ

• የህይወት ኑሮ መደበኛ/ ኖርማል/ ነው።
• በህይወታቸው የሚደርሰዉን ዉጣ ዉረዶችን ከሱስ ዉጭ አማራጭ ይይዛሉ። አልፎ አልፎ ዘና ለማለት ወጥተው ይዝናናሉ፤ አብዛኛዉን ጊዜ ሱስ ሲጠቀሙ መጠን አያልፉም። ይህ በሚቀጥለው ቀን የእረፍት/ እርካታ/ ስሜት ይሰማቸዋል።
• አንዳንድ ጊዜ መጠን ያላፈ አጠቃቀም ካላቸው ቀጣዩ ቀን ይከብዳቸዋል፤ ሃንግ ኦቨር /Hang over/፣ ጸጸት ይኖራቸዋል።
• በስተመጨረሻ ኖርማል የህይወት ኑሯቸውን ይቀጥላሉ።

ቋሚ ሱስ ተጠቃሚ ከሆኑ

• “ኑሮ ደባሪ ነው” የሚል እሳቤ ይይዛሉ።
• ሱስ ድብርትን ሲቀርፍ የሚሰጠው ደስታ፣ በርካታ ጥሩ ነገሮችን እጅግ ማራኪ እንዲሆኑ ያደርገዋል/ በተጋነነ መልኩ/፤ ለዚህም ሲባል ሱስ ተመራጭ ይሆናል።
• ችግሩ ሱሱ ከሰዉነት ሲወገድ/ ጊዜው ሲያበቃ/ ከመጀመርያው የገዘፈ “ደባሪ ኑሮ” ወስጥ ይገባሉ። /ማጋነን አይደለም፤ በጣም ይደብራቸዋል።/
• ለዚህም ሲባል ይህን “ደባሪ ኑሮ” ካለ ሱስ መግፋት አይታሰብም።

እንደማጠቃለያ ሰዎች ከሱስ እንዲወጡ ችግራቸውን ለመረዳት ብንሞክር እንዲሁም ወቀሳን ብንቀንስ፤ ሱስን እንደህመም አይተነው ልንረዳቸው እንችላልን። ሁሉም ነገር ከእውቀት ይጀምራል።

!! ረመዳን ሙባረክ !!

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ
RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
7 ሚያዝያ 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

~~~ሀዘን ከሞት በኋላ~~~የሚወድቱን ሰው በሞት ማጣት ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ይከታል። ህይወት ያለ ወዳጅ መምርት እጅግ ፈታኝ ነው። ማዘን ይህንን አዲስ ህይወት እንድንለምድ የሚያደርገን ሂደት...
02/04/2021

~~~ሀዘን ከሞት በኋላ~~~

የሚወድቱን ሰው በሞት ማጣት ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ይከታል። ህይወት ያለ ወዳጅ መምርት እጅግ ፈታኝ ነው። ማዘን ይህንን አዲስ ህይወት እንድንለምድ የሚያደርገን ሂደት ነው። ለቅሶ መቀመጥ (ማዘን) ማለት ያጣነውን ወደጃቻችንን መርሳት ማለትም አይደለም፤ እንደውም ያጣነውን ሰው ትውስታዎች ከፍተኛ ዋጋ የምንሰጥበት እንጂ። ይህ ሲሆን በሞት ያጣናቸውን ወዳጃቻችን በልባችን ውስጥ ይዘን ህይወትን መምራት እንጀምራለን።

በሞት የተለየንን ሰው ስናዝን ያሉ 4 ሂደቶች እነሆ።

1. የወዳጅን ሞት መቀበል፡፡

• የሞት መርዶ ከሰማን በኃላ እንደናገጣለን፤ ለመቀበል ይከብደናል፡፡ በሂደት የወዳጅ ሞትን መቀበላችን አይቀርም፤ስሜትችንን መገንዘብ የምጀምርበት ጊዜ ይሆናል።

2. ሀዘንን ማስታመም ተገቢ ነው፡፡

• ሀዘን በርካት የስሜት ሂደቶች አሉት፡፡ ቁጣ፤ንዴት፣ ክህደት፣ ድብርት ወዘተ…… ።እነዚህ አለመቀበል፡ ማራዘም አለየም መሸሽ ሊሞክር ይቻላል፡፡ ግን በኃላ ላይ መንፀባረቁ አይቀርም፡፡ በጊዜው ማስታመም ተገቢ ነው፡፡ ሰሜቱ ሲመጣ ማስታመም አለብን፡፡

3.ካለ ወዳጅ መኖር ይለመዳል።

• ኑሮ ካለ ወዳጅ አስገዳጅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ከእለት ተእለት ትንሽ ለውጥ እስከ ከፍተኛ የህይወት ለውጥ (ትምህርት ማቆም ፤ከቤት መውጣት፣ ወዘተ...) ይህ ሂደት እጅግ ከባድ ነው፡፡ በዚህ ሂዳት ማለፍ ሟችን የበለጠ ሊያስወታስ ይችላል። ነገር ግን ህይወት መቀጠሉ አይቀርም፡፡

4. ሟች ወዳጅን የምናስታውስበት መንገድ መቅርፅ።

• ህይወትን ካለ ወዳጅ መምረት ማለት ሟችን መርሳት ማለት አይደልም፡፡ በልባችን ትልቅ ቦታ አላቸው፤ የሌሎችንም ቦታ አይጋፉም። ሌላ ወዳጅ ለማፍራት ልባችን ቦታ ሊኖረውም ይገባል፡፡ ትውስታቻው ግን ሁሌም አብሮን ይኖራል፡፡

ከመችወም በላይ እጅግ ፈተኝ የሆነ የበሽታ መቅሰፍት /ኮቪድ 19/ ወዳጆቻችንን እየነጠቀን ባለበልት በዚህ ጊዜ ጥንቃቄ አንዳይለየን አደራ ይያልኩ፣ ሀዘንን ለማቅለል የሚረዱ መረጃዎችን በቅርቡ ይዤ እመለሰላሁ።

ሰላም፣ ፍቅር፣ ጤና ለሁላችን!!!!

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ
RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
24 መጋቢት 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

ዓይናፋሮችን ለመርዳት ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ወዳጅ ምን ያድረግ?• መጀመርያ ማድረግ ያለብን ስለ ዓይናፋርነታቸው መወያየት ነው። በውይይት ጊዜ ስሜታቸው እንዳይጎዳ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላ...
27/03/2021

ዓይናፋሮችን ለመርዳት ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ወዳጅ ምን ያድረግ?

• መጀመርያ ማድረግ ያለብን ስለ ዓይናፋርነታቸው መወያየት ነው። በውይይት ጊዜ ስሜታቸው እንዳይጎዳ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ማናችንም ብንሆን ስለድክመታችን መስማት አሉታዊ ስሜት ዉስጥ ይከተናል፤ ይህ ደግሞ ሽሽት ዉስጥ እንጂ ለውጥ ዉስጥ አይከተንም።
• ስለ ቀን ዉሏቸው እንዲነግሩን ማድረግ /ማበረታታት/ ብሎም ምን እንደተሰማቸው መጠየቅ
• በሰዎች ቅቡልነትን ማግኘት እንዲሁም ማጣትን መወያየት። ትሞክሮን ማጋራት ይጠቅማል።
• ፈረንጆች “Role Play” የሚሉት አልያም የሰዎች ባህርይ በመላበስ ከዓይናፋሮች ጋር መተውን ይረዳቸዋል።
• ማንኛዉም አይነት የህይወት እቅድን በፍላጎት፣ በአቅም እንዲመጥኑ፣ እርዳታ መስጠት።
• ሁሉም ሰው የራሱ አሉታዊ ሃስብ እንዳለው ማስረዳት፣ ችግር የሚሆነው ህይወትን/ ኑሮን/ ሲጎዳ እንደሆነ መግለጽ፣ ከዚህ ሀሳብ ለመውጣት በሚያደርጉት ጉዞ ለማገዝ መተባበር። በተለይ በራስ ለይ ያለን አሉታዊ ሃሳብ በተመለከተ።
• ለዓይናፍርነታቸው አስተዋጾ የሚያደርጉ ነገሮችን መለየት.... ለምሳሌ ተቺዎችን፣ ጭንቀት፣ ሱስ ሊያባብሱት እንደሚችሉ ጥቆማ መስጠጥ።

በመጨረሻም......” በህይወት ዘመናችን ዉስጥ ቢያንስ በኣንድ ነገር ዓይናፋር ሆነን አልፈናል...” ብል መሳሳት ይሁን መልሱን ለናንተ።

ሰላም እና ፍቅር ተመኛሁ

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ
RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
18 መጋቢት 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

**ዓይናፋርነት**                                          ከ APA የተቀነጨበነገሮችን መራቅ አልያም መሸሽ ለዓይናፋሮች ብሎም ለእነሱ ዙርያ ቅርብ ለሆኑ ሰዎች ችግር...
12/03/2021

**ዓይናፋርነት**
ከ APA የተቀነጨበ

ነገሮችን መራቅ አልያም መሸሽ ለዓይናፋሮች ብሎም ለእነሱ ዙርያ ቅርብ ለሆኑ ሰዎች ችግር ይፈጥራል

ነገሮችን መርቅ አልያም መሸሽ ስንል

• ማህበራዊ ዝግጅቶችን በመጨረሻ ሰዐት መሰረዝ
• አዎንታዊ ማህበራዊ መስተጋብር የሚሰጡ ሁኔታዎችን መሸሽ
• ጥቂት ወይም ምንም ጓደኛ አለመኖር
• ቅሬታ አቅራቢ ወይም ነቃፊ መሆን
• በራስ አለመተማመን
• በባህርያቸው የጓደኞቻቸውን፣ የቤተሰብ አባላትን ብሎም አስተማሪዎቻቸውን ትኩረት በአሉታዊ መንገድ ይስባል
• ከሌሎች ጋር ፊት ለፊት ላለመገናኘት ከመጠን ያለፈ የስማርት ስልኮችን ይጠቀማሉ።

ምክንያቶቹ

1. ስነ ህይወታዊ

o የሸሺ ስብእና ያለቸው ሰዎች አብዝተው ስሜታዊ እና ለለመጎዳት የሚርቁ ናቸው። የሚረዳቸው ሰዎች ካለገኙ ይከፋሉ።

2. አስጨናቂ ሁኔታን ያለፉ ሰዎች

o በህይወታቸው አሳፋሪ ነገር የደረሰባቸው ሰዎች፣ በተደጋጋሚ ስራ አልያም ት/ቤት የሚቀይሩ ልጆች እንዲሁም የቤተሰብ አለመረጋጋት ያላቸው ሰውች ካሉ

3. አሉታዊ የቤተሰብ ግንኙነት

o ልጆቹን አብዝቶ የሚተች፣ የሚቆጣጠር፣ በሌሎች የሚያሳፍር ወላጅ ካለ፣ እንዲሆም ያልተፈታ ግጭት ካለ።

4. የስራ/ የትምህርት/ ዉጥረት

o በትንሽ በትልቁ የውድድር መንፈስ ያለበት ት/ቤት/ ወይም መ/ቤት ደካማ አፈጻጸም ያላቸውን ሰዎች ያጋልጣሉ፤ የበላዮች ብቻ ይሸለማሉ፤ ጉልቤዎችም /Bullies/ ይመሰረታሉ ።

ዓይናፋሮችን እንዴት እናግዛቸው????
በሚቀጥለው ጽሁፌ እመለሳለሁ

ሰላም ተመኘሁ

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ
RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
3 መጋቢት 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

ከአስደንጋጭ ገጠመኝ በኋላ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት/ Post-Traumatic Stress Disorder/የህይወት ገጠመኝ የሌለው ሰው ይኖር ይሆን ?  ይብዛም ይነሰም ሁላችንም ዛሬ እስካለን...
26/02/2021

ከአስደንጋጭ ገጠመኝ በኋላ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት/ Post-Traumatic Stress Disorder/

የህይወት ገጠመኝ የሌለው ሰው ይኖር ይሆን ? ይብዛም ይነሰም ሁላችንም ዛሬ እስካለንበት ድረስ ለመልካም ነገር ውይም ደግሞ ለመጥፎ ነገር ተጋልጠናል። ብዙ ሰዎች እጅግ አስደንጋጭ ነገር በራሳቸው አልያም በቤተሰቦቻቸው ለይ ገጥሟቸው ተጨንቀው፣ ተረብሸው ኑሮን በመከራ ይኖራሉ።

በአደጋ /ተሽከርካሪ/፣ በወንጀል/ በድብደባ፣ ስለት መወጋት/፣ በጦርነት፣ ጾታዊ ትንኮሳ፣ ተፈጥሮዊ አደጋ/ ጎርፍ፣ እሳት፣ መሬት መንቀጥቀጥ/ ወዘተ በኋላ የሚፈጠር የአዕምሮ ህመም ደህረ ሰቀቀን ጭንቀት / Post-Traumatic Stress Disorder/ በመባል ይታወቃል።

• ስርጭት

ሴቶች ለይ ይበዛል። 10 በመቶ ለሴቶች /ጾታዊ ጥቃት ስለሚበዛ/ ፣ 4 በመቶ ለወዶች/ ከግጭት ጋር በተያያዘ/
ወታደሮች ለይ 30 በመቶ እንደሚጠጋ ጥናቶች ያሳያሉ። ወጣቶች ለይ ስርጭቱ ከፈተኛ ነው።

• አጋላጮች

ማንም ሰው ከዚህ ችግር የተጠበቀ አይደለም። ነገር ግን ማህበራዊ ተሳትፏቸው አነስተኛ የሆኑ ሰዎች የበለጠ ሊጠቁ ይችላሉ፤ እንደ ምሳሌ ብቸኛ ሰዎች፣ ትዳር የሌላቸው/በሞት አልያም በፍች ሊሆን ይችላል/ ፣ ከፈተኛ ድህነት ዉስጥ ያሉ/ የወንጀል ሰለባ ሰለሚሆኑ/፣ አብዝቶ የሱስ ተጠቃሚዎች፣ አንዳንድ የስብእና ችግር አይነቶች፣ ተያያዥ ጭንቀቶች እንዲሁም ድባቴ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው።

• ምልክቶቹ

1 ለአሰቃቂ ነገር ተጋላጭ ከሆኑ በኋላ የሚፈጠር ነው።

በራሳቸው ለይ የተፈጠረ ገጠመኝ ሲሆን፣ ሌሎች ሰዎች ለይ ሲደርስ መታዛብ፣ በቤተሰብ አባል ለይ መደርሱን ሲያዉቁ፣ እና ተደጋጋሚ አጋላጮች ሲኖሩ/ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች/

2 ተመላላሽ፣ ጣልቃ ገብ የሆነ የሚረብሽ ትውስታ፣ ቅዠት፣ ሰመመን ዉስጥ መግባት።

አደጋው እንደ አዲስ በእዉን የሚፈጠር ይመስላቸውል፣ ሁኒታዉን እንደነበረው ይተገብሩታል፣ ፍንጭ የመሰጡ ነገሮች /ሲሰሙ፣ ሲያዩ/ ይረብሻቸዋል።

3 የጸና ሽሽት ውስጥ ይገባሉ።

ስለሁኔታው ትዉስታ የሚሰጣቸውን ላለመስማት፣ ላለማየት፣ ሰውችንም ላለማግኘት በጽናት ይሻሻሉ። ትውስታውንም ለመርሳት ሱስ ይጠቀማሉ።

4 አሉታዊ አስተሳሰብ እና ስሜት ይኖራቸዋል

“እኔ መጥፎ ነኝ፣ ማንም ሰው አይታመንም፣ አለም ክፉ ናት” የሚሉ አስተሳሰቦች በግለሰቡ ለይ ይነግሳሉ። እራስን መውቅስ ራስን ለማጥፋት ሲገፋፋ፣ ሌሎችን መውቃስ ደግሞ ለከፋ የአዕምሮ ጤና መታወክ፣ ሱሰኝነት ብሎም ክፋት ይዳርጋል። ፍርሃት፣ ቁጭት፣ ቁጣ መገለጫቸው ይሆናል። እነዚህ ስሜቶች ቁጥጥር ከሌለው ሌሎሎች ሰዎችን ሳያውቁት ሊጎዶ ይችላሉ።

5 ድንጉጥ እና ደንታ ቢስ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቶሎ ይቆጣሉ፣ ሁሉንም ነገር በነቂስ ይከታተላሉ፣ ይበረግጋሉ፣ የወራጫሉም። እንቅልፍ ለይ ይሰቃያሉ፣ በህይወታቸውም ደንታ ቢስ ይሆናሉ።

• ህክምናው

የስነልቦና እንዲሁም የመድሃኒት ናቸው።

ጊዜ የሚፈልግ እና ቀስ በቀስ በሂደት የሚስተካከል የህመም አይነት ስለሆነ በጊዜ ከተገኛ ዉጤታማነቱ አመርቂ ይሆናል።

ቸር እንሰንብት

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ
RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
19 የካቲት 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

ከህይወታችን ተሞክሮ ብዙ ነገር እንማራለን!!(ከማርክ ማንሰን የተቀነጨበ)ከልጅነታች አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ስለብዙ ነገር አስበናል፣ ተጨንቀናል፡፡ ይህ ሰዋው ባህርያችን ነው፡፡ በህይ...
20/02/2021

ከህይወታችን ተሞክሮ ብዙ ነገር እንማራለን!!
(ከማርክ ማንሰን የተቀነጨበ)

ከልጅነታች አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ስለብዙ ነገር አስበናል፣ ተጨንቀናል፡፡ ይህ ሰዋው ባህርያችን ነው፡፡ በህይወታችን ለሚያገጥሙን ነገሮች አልያም ተሞክሮዎች ትኩረታችንን መንፈልግ ፈጽሞ አይቻልም፡፡

ለወደድነው ሰው ፍቅር ሰጥተናል፣ ለችግሮቻችን ብዙ መስዋትነትን ከፍለናል፤ ስለወደፊቱ ህይወታችን ብዙ አስበናል፤ እንዳንዶቻችንም ተጨንቀናል፡፡

ነገር ግን እድሜያችን እየገፍ ሲመጣ በተሳካሉን ነገሮች ተደስተን፤ እንዲሁም በወደቅንበት ነገር ደግሞ ተምረንበት ህይወታችንን ትርጉም እንሰጣዋለን። ይህ ሁኔታ ለእኔ በአስተሣሰብ እና በስሜት የመብሰለ ምልክት ይመስለኛል።

እስኪ አንድ ጊዜ ከስር ያሉትን ሃሳቦች ጥቂት ደቂቃ ሰጥተን እንመርምር፤ ይጠቅመን ይሆናል

1) በአንድ ሰው ተገፍተህ ወይም ተንቀህ ካዛ የተሻለ ሰው አግኝተህ ታውቃለህ ?
2) ሰዎች ስለ አንተ ብዙ ሳያውቁ ፈርደዉህ ያውቃል።
3) ባለሰብከው መንገድ ወይም ብዙ ባለፋህበት፣ ባልደከምክበት ነገር /የፈጣሪ ስራ ነው የሚስብልህ/ ውጤታማ ሆነህ ታውቃለህ?
4) የታገልክለት ቁም ነገር ወይም አላማ ለሌላ ሰው ደንታ የማይሰጠው ሆኖ ተረድተህ ታውቃለህ?

የአንተ ማንነት /ስብእና/ ብስለት መለካት የሚችለው አንተው እራስህ ይገበዋል ለምተለው ነገር ትኩረትህን ስትሰጥ፣ ስትሰራ ብቻ እና ብቻ ሲሆን ነው። በዚህ ውስጥ ውድቀት እንዳለ ሁሉ ተዐምር መኖሩንም አትርሳ። ከውድቅትህ ተምረህበት ታላፍለህ እንጂ ህይወትን አያስቆምም። ከአንተ የሚጠበቀው ገመዱን መፍታት ነው።

~~~~ህይወት ይቀጥላል~~~

መልካም ቅዳሜ!!!

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ

RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
13 የካቲት 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

ድብርት /ድባቴ/- ከ 8 ወንድ 1 ይጠቃል- ከ 6 ሴት 1 ትጠቃለች- መካከለኛ እድሜ ክልል ላይ በብዛት ይስተዋላልለምን በሴቶች በዛ1) ከሰውነት ሆርሞን ኡደት ጋር ስለሚያያዝ2) ከእርግዝናና...
06/02/2021

ድብርት /ድባቴ/

- ከ 8 ወንድ 1 ይጠቃል
- ከ 6 ሴት 1 ትጠቃለች
- መካከለኛ እድሜ ክልል ላይ በብዛት ይስተዋላል

ለምን በሴቶች በዛ
1) ከሰውነት ሆርሞን ኡደት ጋር ስለሚያያዝ
2) ከእርግዝናና ወሊድ ጋር ስለሚያያዝ
3) ማህበራዊ ተፅእኖ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የቤተሰብ ጫና ወዘተ ናቸው……….

ምልክት፡- 2ቱ ዋና ምልክቶች፡-

1) የሀዘን ሰሜት (Sad mood)
2) በፊት የሚያስደስት ነገሮችን ፍላጎት ማጣት (Loss of interest in pleasurable activities)

ቀሪ ምልክቶች፡-
 ቁጭት (Guilt)
 የጉልበት መዛል (Loss of energy)
 ትኩረት ማጣት (Concentration problem)
 ምግብ ፍላጉት መቀነስ ፤ወይም መጨመር (Loss or increased Apitite)
 መቁነጥነጥ አልያም መፍዘዝ (agitation or Retardation)
 እንቅልፍ እጦት አልይም መብዛት (insomnia or hypersomnia)

በወጣቶች ለይ - የመነጫነጭ ስሜት የዋና ምልክት ሊሆን ይችላል

ከላይ የተጠቀሱት ምልከቶች
o ጊዜን መሰረት ሊደርጉ ይችላል (with Seasonal pattern)
o ቅዥት ሊኖረው ይችላል (with psychosis)
o ጭንቀት ጋር ሊያያዝ ይችላል (with anxiety)
o ከወለድ እና እርግዝና ጋር ሊዛመድ ይችላል (with peripartum)

ለድብርት አገላጭ መሰረታዊ አስተሣሰቦች 3 ናቸው
1. ስለራስ ያለን ግምት አሳንሶ ማሰብ (worthlesness)
2. ራስን የመርዳት ጨለምተኛ ሃስብ / (helplessness)
3. ተስፋ መቁረጥ ሃሳብ (hoplesness)

ራስን ማጥፍት
• መፍትሄ መስሎ ሊታያቸው ይችላል
• አብዛኛው ራስን ማጥፍያ መንገድ - ገመድን በመጠቀም ነው፡፡

ህክምና - ዉጤታማ ነው
1) የመድህኒት ህክምና
2) የሰነ ልቦና ህክምና

ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ህክምና ያግኙ፡፡

ራስን ማጥፍት መፍትሄ አይደለም፡፡

አገልግሎት ከፈለጉ በ 0966 13 73 69 ይደዉሉ
RIDA ሪዳ የአእምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት።

ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ
29 ጥር 2013

ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ /MD/
ሳይካትሪስት/ Psychiatrist

Address

Lideta, Smart Plaza, 2nd Floor, Office: S03
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 20:00
Tuesday 09:00 - 20:00
Wednesday 09:00 - 20:00
Thursday 09:00 - 20:00
Friday 09:00 - 20:00
Saturday 09:00 - 20:00
Sunday 09:00 - 12:00

Telephone

+251966137369

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rida Mental Health Consultancy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Rida Mental Health Consultancy:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram