yadah home care ያዳህ የ ቤት ለቤት የ 24 ሰአት ነርስ አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • yadah home care ያዳህ የ ቤት ለቤት የ 24 ሰአት ነርስ አገልግሎት

yadah home care ያዳህ የ ቤት ለቤት የ  24 ሰአት ነርስ አገልግሎት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from yadah home care ያዳህ የ ቤት ለቤት የ 24 ሰአት ነርስ አገልግሎት, Medical and health, Addis abeba, Addis Ababa.

09/08/2023

ያዳህ የቤት ለቤት የናርሲንግ አገልግሎት
* የደም ፣ የስኳር እንዲሁም ፊዚዮቴራፒ አገልግሎት(ማሳጅ አገልግሎት) ባሉበት
* ሙሉ የህክምና እንክብካቤ
* በሀኪም የታዘዙ መዳኒቶችን መስጠት ና መከታተል ........

# 0941912501

ሁሌም እርሰወን ይጠብቃል!

06/08/2023

Yadah home care

  (Gout Arthritis)ምንነት> ሪህ ዩሪክ አሲድ የተባለ የሰውነታችን ኬሚካል በመገጣጠሚያዎቻችን ሲጠራቀም የሚፈጠር በሽታ ነው።> በብዛት በእግራችን የአውራ ጣት(podagra)፣ ቁርጭም...
06/08/2023

(Gout Arthritis)
ምንነት
> ሪህ ዩሪክ አሲድ የተባለ የሰውነታችን ኬሚካል በመገጣጠሚያዎቻችን ሲጠራቀም የሚፈጠር በሽታ ነው።
> በብዛት በእግራችን የአውራ ጣት(podagra)፣ ቁርጭምጭሚት(ankle)፣ ጉልበት(knee) እንዲሁም በእጃችን የክንድ(elbow) እና የእጅ(wrist) መገጣጠሚያዎች ላይ ይከሰታል።
አጋላጭ ምክንያት(risk factor)
> አልኮል መጠጣት
> ፕሮቲን የበዛባቸው የምግብ አይነቶች መመገብ(ምሳሌ ስጋ፣ ሽሮ፣ እንቁላል፣ አሳ...)
> ከመጠን ያለፈ ውፍረት
> የኩላሊት በሽታ መኖር
> ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት
> ስኳር በሽታ
> ጭንቀት፣ ድካም
> የተለያዩ መድኃኒቶች(ምሳሌ የሚያሸና መድኃኒት፣ አስፕሪን...)
ምልክቶች(clinical features)
> ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚኖር ኃይለኛ ህመም
> የመገጣጠሚያ ማበጥ፣ መቅላትና የሙቀት መጠን መጨመር
> ትኩሳት
> ብርድ ብርድ ማለት
ጠንቅ(complications)
> የመገጣጠሚያ መበላሸት(degenerative arthritis)
> የኩላሊት በሽታ(uric acid/urate nephropathy)
> የኩላሊት ጠጠር
> የመገጣጠሚያ ልክፍት(secondary infection)
> ስብራት
ምርመራ
> የደም ምርመራ
> የዩሪክ አሲድ መጠን ምርመራ(serum uric acid)
> የመገጣጠሚያ ፈሳሽ ምርመራ(synovial fluid analysis)
> አልትራሳውንድ፣ ኤክስ ሬይ
> CT scan, MRI
ህክምና
> የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች፦ NSAIDs, steroid
> የዩሪክ አሲድ መጠን የሚቀንሱ መድኃኒቶች፦ allopurinol, febuxostat
> ከላይ የተጠቀሱትን አጋላጭ ነገሮች(risk factors) ማስወገድ
ምን እናድርግ?
× ፕሮቲን ያላቸው ምግቦችን መቀነስ ወይም ለጊዜው መተው
× ውሃ በብዛት መጠጣት(በቀን ከ8 ብርጭቆ በላይ)
× አልኮል መጠጥ መተው
× የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
× ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ጤና ተቋም መሄድ

Source:- Info Health Center

06/08/2023


• የጀርባ ህመም በአለማችን ከ5 ሰዎች 3 ሰዎችን ያጠቃል። ብዙ ሰዎችን ከስራቸው ሳይቀር የሚያስተጐጉልና ወደ ህክምና ቦታ እንድመላለሱ የሚያደርግ ከባድ ችግር ነው።
• በተለያየ አደጋ፡ አግባብ ባልሆነ የአካል እንቅስቃሴ፡ በተዛባ አቀማመጥና አተኛኘትና በተለያዩ ህመሞች ችግሩ ይፈጠራል።
• የጀርባ ህመም በማንኛውም የእድሜ ክልል ቢፈጠርም በእድሜ የገፉ፡ እርጉዞችና የነርቭ ኢንፌክሽን ያለባቸው ላይ ጎላ ያለ ነው።
• ቀድሞ ይሰሩት የነበረ ከባድ ስራ፡ የድስክ መንሸራተትና የጀርባ ላይ አደጋ እድሜ ሲጨምር የጀርባ ህመም እንድባባስ ያደርጋሉ።
• ጀርባ ከአጥንት፡ ከጅማት፡ ከጡንቻ፡ ከነርቭ፡ ከደም ቱቦና ከሌሎችም የተዋቀረ ነው።

• የድስክ መንሸራተት
• የተዛባ የሰውነት ቁመና
• አደጋ ወይም ምት
• የጀርባ ውልቃትና ወለምታ
• የጅማት መጨማደድናመለጠጥ
• የድስክ ጉዳት
• ስብራት
• መውደቅ
• ከባድ ነገሮች በዘፈቀደ ማንሳት፡ ማውጣት፡ ማውረድና ማንቀሳቀስ
• የድስክ መጉበጥና ማበጥ
• የነርቭ መጐዳት
• የጅማት ኢንፌክሽን
• የአጥንት መሳሳት
• የኩላሊት ችግር
• ለብዙ ሰአት መቀመጥና መቆም
• ብዙ ሰአት ኮምፒውተር ላይ ማታኮር
• ብዙ ሰአት በጀርባና በደረት መተኛት
• የጀርባ ካንሰር
• የዳሌ አጥንት ዙሪያ ኢንፌክሽን
• የነርቭ ኢንፌክሽን

• የስራ አይነት
• እርግዝና
• እርጅና
• ዘር
• ማጤስ
• ውፍረት
• የአጥንት መሳሳት
• የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ

• የደርባ ቁርጥማትና ህመም
• ክብደት መቀነስ
• ትኩሳት
• እብጠት
• የእግር ህመምና እብጠት
• የጉልበት ህመም
• ለመሽናት መቸገር
• መደንዘዝ
• ሽንትና ሰገራን መልቀቅ
• መጥፎ የጀርባ ስሜት
• መልፈስፈስ

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
1978

Telephone

+251941912501

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when yadah home care ያዳህ የ ቤት ለቤት የ 24 ሰአት ነርስ አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to yadah home care ያዳህ የ ቤት ለቤት የ 24 ሰአት ነርስ አገልግሎት:

Share