
30/08/2024
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም በ12ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም በ12ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል። የታንዛኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ቃሲም ማጃሊዋ የከፈቱት ኮንፈረንስ “በምስራቅ አፍሪካ ክልል ድንበር ተሻጋሪ የህክምና ሪፈራሎችን እና የጤና ክብካቤን ማሳደግ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ነው። የምስራቅ አፍሪካ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን አባል የሆነበት እስከ 50% የሚደርሰውን የጤና አጠባበቅ አገልግሎት የሚሸፍን በተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ የጤና የጤናው ዘርፍ ማህበራትን ያቀፈ ድርጅት ነው። የኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ ከሴፕቴምበር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቀጣዩ የምስራቅ አፍሪካ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን 13ኛው የምስራቅ አፍሪካ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2025 በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ይስተናገዳል።