የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት LEMI KURA sub city health office

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት LEMI KURA sub city health office

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና  ጽ/ቤት  LEMI KURA sub city health office የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ መሆ?

16/04/2022
07/04/2022

የጤና ባለሙያዎችና እንክብካቤ ሠራተኞች ሳምንትን አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ያስተላለፉት መልዕክት
----------------

በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ባለሙያዎችና እንክብካቤ ሠራተኞች ሳምንት በየዓመቱ በመጋቢት ወር መጨረሻ ሳምንት ላይ ይከበራል፡፡

በዚህ ዓመት በዓለም ቀፍ ደረጃ ከ አፕሪል 4-8 2022 መሪ ቃሉን “የጤና ሰራተኞቻችን በተሻለ እንገንባ” “Build the Health Workforce Back Better" በሚል ይከበራል::

በሀገራችን በኢትጵያም የጤና ባለሙያዎችና እንክብካቤ ሠራተኞች ሳምንት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየዓመቱ ባለሙያዎቻችን የዜጎችን ጤንነት በመጠበቅ፣ በማከም፣ እና ህይዎትን በመታደግ እያደረጉት ላለው ጉልህ አስተዋጽኦ እውቅና እና ምስጋና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በጤናው ዘርፍ ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና እንክብካቤ ሠራተኞች የዜጎችን ጤንነት በመጠበቅ፣ በማከም፣ እና ህይዎትን በመታደግ እያደረጋችሁት ላለው ጉልህ እና የማይተካ አስተዋጽኦ የተለየ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል፡፡

በጤናው ዘርፍ ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና እንክብካቤ ሠራተኞች አስተዋጽኦዎች ከብዙ በጥቂቱ፡- በኮሮና ወረርሽኝ የራሳቸውን ህይዎት አሳልፈው ሰጥተው የዜጎችን ህይዎት በመታደግ፣ በወቅታዊ ድንገተኛ ምላሽ አገልግሎት በተመሳሳይ ህይወታቸውን አሳልፈው እየሰጡ የዜጎችን ህይዎት ታድገዋል::

በአጠቃላይ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ጠብቃችሁ የጤና ስርዓቱ የተሻለ እንዲሆን በተሰማራችሁበት የሙያ ዘርፍ የድርሻችሁን እየተወጣችሁ ስለሆነ በተለይም፤ የጤና ስርዓቱን በመደገፍ፣ ተላላፊ የሆኑ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል እና በማከም፣ የዜጎችን ጤና በመጠበቅ፣ የታመሙ ዜጎችን በማከም፣ የጤና ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ በማቋቋም እና የተሰጣችሁን ሙያዊ ሃላፊነት በግንባር ቀደምነት በብቃት በመወጣት እያደረጋችሁት ላለው ጉልህ ሙያዊ አስተዋጽዖ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል፡፡

መንግስት፣ ሕብረተሰቡ፣ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ በጤናው ዘርፍ ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና እንክብካቤ ሠራተኞች እያበረከቱት ስላለው ከፍተኛ የማይተካ ሚና ግንዛቤ ተወስዶ የሚገባቸውን አክብሮት እና ምስጋና እንዲያቀርቡላቸው እየጠየቅሁ እንዲሁም ህይዎታቸውን እየገበሩ ህይወታችንን ለሚታደጉን የጤና ባለሙያዎች እና እንክብካቤ ሠራተኞች ከጎናቸው በመሆን ያሉባቸውን ጉድለቶች ለመሙላት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር

Address

Ayat Adebabay
Addis Ababa

Telephone

+251900000000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት LEMI KURA sub city health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት LEMI KURA sub city health office:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram