St. Peter General Specialized Hospital - ቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • St. Peter General Specialized Hospital - ቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

St. Peter General Specialized Hospital - ቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from St. Peter General Specialized Hospital - ቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል, Hospital, Addis Ababa.

“We are a selfless patriot of health, every day running in the battle field, we live and die on duty, because the only reason is our desire for your Compassionate Care, our existence is you, everything is for you"

04/10/2023
የልብ ህመም✔️✔️✔️✔️የልብ ሕመም በልብ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ ሁኔታዎችን ያጠቃልላል። የልብ በሽታዎች የሚባሉት🔴እንደ የደም ቧንቧ በሽታ🔴መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት (Arrhyth...
01/10/2023

የልብ ህመም
✔️✔️✔️✔️
የልብ ሕመም በልብ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ ሁኔታዎችን ያጠቃልላል። የልብ በሽታዎች የሚባሉት
🔴እንደ የደም ቧንቧ በሽታ
🔴መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት (Arrhythmias)
🔴የተወለዱበት የልብ ችግሮች (Congenital Heart Defects)
🔴የልብ ጡንቻ በሽታ (Cardiomyopathy,Myocardial disease)

🔴የልብ ቫልቭ በሽታ(Rheumatic Valvular Heart disease) ናቸው።

ዋና ዋና የልብ በሽታ ምልክቶች
▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️
🔵 የደረት ህመም
🔵 ራስን መሳት (syncope)
🔵 ድካም
🔵 መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት
🔵 የትንፋሽ እጥረት
🔵 የእግሮች ወይም የቁርጭምጭሚቶች እብጠት

መከላከያ መንገዶች
▫️▫️▫️▫️▫️▫️

የልብ በሽታን ለመቆጣጠር የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች በሽታውን ለመከላከል ሊረዱ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል፦

☑️አለማጨስ
☑️ዝቅተኛ የጨው እና የሳቹሬትድ ስብ ያለ አመጋገብ መመገብ
☑️በአብዛኛዎቹ የሳምንቱ ቀናት በቀን ቢያንስ 30 ደቂቃ 🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🚶‍♀️🚶‍♂️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
☑️ጤናማ ክብደትን መጠበቅ
☑️ጭንቀትን መቀነስ እና መቆጣጠር
☑️ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል እና የስኳር በሽታ መቆጣጠር
☑️ጥሩ እንቅልፍ መተኛት (ለአዋቂዎች በየቀኑ ከ 7 እስከ 9 ሰአታት ይመከራል)

በዶ/ር አይሸሽም ገረመው
ካርድዮቫስኩላር ፕራክቲሽናል ስፔሻሊስት

ልብዎን ይንከባከቡ!

ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
መኖራችን ለእርሶ ነው!

ዜና እረፍት **የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ ትዕግስት በለጠ ወልደማርያም ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓ...
28/09/2023

ዜና እረፍት
**

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ ትዕግስት በለጠ ወልደማርያም ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ለስምንት ዓመታት በሆስፒታሉ ውስጥ በሙያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

መላው የሆስፒታሉ አመራሮችና ሰራተኞች በስራ ባልደረባችን ወ/ሮ ትዕግስት ህልፈተ-ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ጓደኞቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር!

ሆስፒታሉ የአርትሮስኮፒ ቀዶ ህክምና አገልግሎት  መስጠት ጀመረ*********** የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ንዑስ ዘርፍ የሆነውን የአርትሮስኮፒ ቀዶ ህክምና አገል...
21/09/2023

ሆስፒታሉ የአርትሮስኮፒ ቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ
***********

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ንዑስ ዘርፍ የሆነውን የአርትሮስኮፒ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ለታካሚዎች መስጠት ጀምሯል።

የአርትሮስኮፒ ህክምና በማንኛውም ሰው ላይ የመገጣጠሚያ ህመም በሚኖርበት ጊዜ ሰውነትን ሙሉ በሙሉ መክፈት ሳያስፈልግ በትንሽ ቀዳዳ ረቂቅ ካሜራዎች ወደ ውስጥ በማስገባት የተጎዳውን አካል ሙሉ በሙሉ በመመልከት የሚከናወን የቀዶ ህክምና አይነት ነው።

የአርትሮስኮፒ እና ጆይንት ሪፕለስመንት ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር መሀመድ ኢሳ የአርትሮስኮፒ ዘመናዊ ቀዶ ህክምና የተጎዳን የመገጣጠሚያ ክፍል በቀላሉ በካሜራ በመመልከት ህክምናውን በፍጥነት ለመስጠት ስለሚያስችል ታካሚዎች ረጅም ሰዓት ማደንዘዣ ላይ እንዳይቆዩ እና ህክምናው ከተጠናቀቀ በኋላ በቀላሉ አገግመው ወደ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም ህክምናው በሆስፒታሉ ውስጥ መሠጠት መጀመሩ ከዚህ ቀደም ይህን ህክምና ለማግኘት ወደ ውጪ ሀገር መሄድ ግዴታ የነበረውን ሁኔታ እንደሚያስቀር እና ህክምናውን ቀደም ብለው መስጠት በጀመሩ ሌሎች ሆስፒታሎች ላይ ያለውን ወረፋ የመጠበቅ ሂደት በተወሰነ መልኩ ለማሳጠር እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

በተጨማሪም በሆስፒታሉ ህክምናው እንዲጀመር የማሽን እርዳታ ላደረጉት ለ"አውስትራሊያን ዶክተርስ ፎር አፍሪካ" ድርጅት እና ለ"አድፋ" ድርጅት ሀላፊ ዶ/ር ግርሀም ፎርዋርድ እንዲሁም ለሆስፒታሉ አመራሮች ላቅ ያለ ምስጋናቸውን ለማቅረብ እንደሚወዱ ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሆስፒታሉ በድምቀት ተከበረ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮች በሆስፒታሉ በህክምና...
12/09/2023

የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሆስፒታሉ በድምቀት ተከበረ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮች በሆስፒታሉ በህክምና ላይ ከሚገኙ ህሙማንና ሰራተኞች ጋር በደስታ አክብረው ውለዋል።

በተለያዩ የህክምና ክፍሎች ለሚገኙ ህሙማን የእንኳን አደረሳችሁ ፖስት ካርድና አበባ በመስጠትና 2016 ዓ.ም ጤናቸው ተመልሶ መልካም ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት አብሮነታቸውን አሳይተዋል። እንዲሁም በሆስፒታሉ በዛሬው ዕለት ለወለዱና ህክምናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ ወላድ እናቶችም የዳይፐርና ሞዴስ ስጦታ በመስጠት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በስራ ላይ እያሳለፉ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጋር በጋራ ማዕድ በመካፈል በዓሉን በደስታ አሳልፈዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር መታሰቢያ መስፍን በዓላትን በአብሮነት ማሳለፍ በሰራተኛው መካከል የእርስ በእርስ ቅርርብን እንደሚያጠናክር ገልጸው በ2016 ዓ.ም ሆስፒታሉን የበለጠ ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ መላው ሰራተኞች ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲጥሩ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ 2016 ዓ.ም መልካም የስራና የስኬት ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

መልካም አዲስ ዓመት!
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

11/09/2023

እንኳን አደረሳችሁ!
*****

መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2016 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር ፣ የብልፅግና እና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

መልካም በዓል!🙏

- የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎች ሆስፒታሉን ጎበኙ_____________________________________ የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት ዩኤስ ኤይድ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አቱል ጋዋን...
08/09/2023

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎች ሆስፒታሉን ጎበኙ
_____________________________________

የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት ዩኤስ ኤይድ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አቱል ጋዋንዴና የድርጅቱ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኃላፊዎች የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ በዋናነት መድሀኒቱን በተላመደ ቲቢና ቲቢ ህክምና አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ምክትል ኃላፊው በሆስፒታሉ ህክምና እየተደረገላቸው የሚገኙ የኤምዲአር ቲቢ ታካሚዎችንና የላቦራቶሪ ክፍልን ጎብኝተዋል።

ምክትል ኃላፊው የቲቢ ህሙማንን በመጎብኘታቸው እንደተደነቁ ተናግረዋል።

መድሀኒቱን የተላመደ ቲቢ በሽታ ሀምሳ ፐርሰንት የሚሆኑትን ሰዎች የሚገድል በሽታ ነው ያሉት ዶ/ር አቱል አሁን ሕክምናውን ወደ ስድስት ወር በማሳጠር እየተሻሻለ መሆኑን ገልጸው ሆስፒታሉ እየሰራው ያለው ስራና እንክብካቤ ለህክምናው መሰረታዊ ነው ብለዋል። የጤና ሚኒስቴርንና ሆስፒታሉን ስለ አጋርነታቸውም አመስግነዋል።

የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በበኩላቸው ያለ ዩኤስ ኤይድ ድጋፍ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን እንዲሁም የእናቶችንና ህጻናትን ጤና የመቆጣጠርና የማከም ስራ ሊሳካ አይችልም በማለት በጤናው ዘርፍ የአሜሪካ መንግስት እያበረከተ ስላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዩኤስ አይድ በሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ የተለያዩ ስትራቴጂዎችንና ዕቅዶችን በመንደፍ እንዲሁም አዳዲስ ፈጠራዊ ሀሳቦችንና መላዎችን በማቅረብ በኢትዮጵያ ብዙ ድጋፍ በማድረግ በኢትዮጵያ ያለውን የቲቢ ስርጭት ጫናን በመቀነስ በኩል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በቲቢ በሽታ የሚከሰት ሞት እየቀነሰ መምጣቱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

እ.አ.አ በ2035 ቲቢንና ኤምዲ አር ቲቢን ለማጥፋት የኢትዮጵያ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሆነ ዶ/ር ደረጄ ያስታወቁ ሲሆን በቲቢ በሽታ ቁጥጥር ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮም ዶክተሩ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ በ2035 ቲቢን የማጥፋት ግብን ከዩኤስ አይድና ከሌሎች አጋር አካላት በጋራ በመስራት ታሳካለችም ብለዋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በሀገሪቱ የቲቢና የኤምዲ አር ቲቢ የልህቀት ማዕከል በመሆን የቲቢን ህመም ለማጥፋት እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።

እንኳን ደስ አላችሁ! *******አዲስአበባ ፣ ጳጉሜ 1 ፤ 2015 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ) በሆስፒታላችን ከ38 ዓመታት በላይ በማገልገል ላይ የሚገኙ አንጋፋ ሰራተኞቻችን  በዛሬው እለት እየተከበረ ...
06/09/2023

እንኳን ደስ አላችሁ!
*******

አዲስአበባ ፣ ጳጉሜ 1 ፤ 2015 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)

በሆስፒታላችን ከ38 ዓመታት በላይ በማገልገል ላይ የሚገኙ አንጋፋ ሰራተኞቻችን በዛሬው እለት እየተከበረ የሚገኘውን 'የአገልጋይነት ቀን' አስመልክቶ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተካሄደ ዝግጅት ላይ በኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ የእውቅና ምስክር ወረቀት እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በመሆኑም ከ38 አመታት በላይ ህዝባችንን በታማኝነት፣በቅንነት እና በትህትና ስታገለግሉ የቆያችሁ የዛሬ ተሸላሚ አንጋፋ የስራ ባልደረቦቻችን በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በሆስፒታሉ አመራሮች፣ ሰራተኞች እንዲሁም ታካሚዎቻችን ስም የከበረ ምስጋናችንን እናቀርብላችኋለን።

አንጋፋ የስራ ባልደረቦቻችን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እውቅና በማግኘታችሁ እና ሆስፒታሉን በሃገርዓቀፍ ደረጃ እንዲጠራ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ስላደረጋችሁ ታላቅ ኩራት ተሰምቶናል።

መልካም አዲስ ዓመት እና መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላችሁም ከወዲሁ እንመኛለን!🙏

"ሀገር ከማገልገል በላይ ጀግንነት የለም!"

"አንጋፋዎች ለተተኪው ትውልድም አርአያዎች ናቸው!"

 #ጷጉሜ፩ #የአገልጋይነት ቀን ምክንያት በማድረግ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን፣ የቆዳና የጥርስ  የነጻ ህክምና አገልግሎት ለተገልጋይ ደንበኞቹ እየሰጠ ይገኛል። እንዲሁም በ...
06/09/2023

#ጷጉሜ፩

#የአገልጋይነት ቀን ምክንያት በማድረግ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን፣ የቆዳና የጥርስ የነጻ ህክምና አገልግሎት ለተገልጋይ ደንበኞቹ እየሰጠ ይገኛል። እንዲሁም በዛሬው ዕለት ወደ ሆስፒታሉ ለሚመጡ ለሁሉም ታካሚዎችና ጠያቂዎች የትሪያጅ አገልግሎት ነጻ ምርመራ እየሰጠ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም በከተማ ደረጃ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ በሚገኘው የጤና ሚኒስቴር የነጻ ህክምና አገልግሎት ላይ የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።

መኖራችን ለእርሶ ነው!

ዓመታዊ የሰራተኞች ውይይት ተካሄደ____________________________ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዓመታዊ የሰራተኞች ስብሰባ በዛሬው ዕለት በኃይሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካ...
02/09/2023

ዓመታዊ የሰራተኞች ውይይት ተካሄደ
____________________________

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዓመታዊ የሰራተኞች ስብሰባ በዛሬው ዕለት በኃይሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ ከሆስፒታሉ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙያዎችና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን የሆስፒታሉ የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸምና የ2016 ዓ.ም የስራ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በቀረበው ሪፖርትና ዕቅድ በመነሳት በሆስፒታሉ የኦክስጅን ማምረቻ ግንባታ አለመጀመር፣ የሪሰርች ስራዎች በተመለከተ፣ ሆስፒታሉ የቲቺንግ ሆስፒታል ለመሆን የደረሰበት ደረጃ እንዲሁም የፐብሊክና ፕራይቬት ፓርትነርሺፕ ጨምሮ ሌሎች ሃሳቦችና ጥያቄዎች ከሰራተኛው የተነሱ ሲሆን የሆስፒታሉ አመራሮች ምላሽ ሰጥተውባቸዋል።

የሀገሪቱ አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴ ለመምራት የሚያስችለው የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ የሶስት ዓመት የስራ አፈጻጸምና የጤና ዘርፍ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ የሶስት ዓመት የስራ አፈጻጸም በሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር መታሰቢያ መስፍን ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ጉዳዮችም ላይ ከሰራተኛው ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም የሆስፒታሉ የሰራተኞች ክበብ ንግድ ስራ ዕቅድ በኮሚቴው ቀርቦ ውይይት ተደርጎ ስብሰባው ተጠናቋል።

ሀገር ዓቀፍ የክረምት ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ__________________________________ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው በጎነት ለጤናችን በ...
21/07/2023

ሀገር ዓቀፍ የክረምት ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
__________________________________

ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው በጎነት ለጤናችን በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የክረምት የጤና ዘርፍ የበጎ አድራጎት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተካሂዷል።

መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ እንደገለጹት
የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ውጤት ያመጣ መሆኑን ገልጸው የጤና ዘርፍ በመደበኛ የጤና አገልግሎት ስርዓት አገልግሎት ማግኘት የማይችሉ በርካታ የማኅበረሰባችን ክፍሎች የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ በህጻናት ማደጎ የሚገኙ ህጻናት፣ አረጋውያንና ወደ ጤና ተቋም መጥተው ለመታከም ገንዘብ የሚያጥራቸው ዜጎች ያለምንም ክፍያ ነጻ የጤና ምክር፣ ምርመራ፣ ህክምና እና መድኃኒቶች የሚያገኙበት ነው ብለዋል።

እነዚህ ዜጎች የቆዳህክምና፣ የአይን ህክምና፣ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣ የልብ ፣የኩላሊት ፣የጆሮና የጥርስ ህክምናዎች እንዲሁም የአልትራሳውንድና የኢሲጂ የምርመራ አገልግሎቶችን በሁሉም የግልና የመንግስት ጤና ተቋማት እንደሚያገኙ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል።

አምና በተካሄደው የጤና በጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሲሆኑ በዘንድሮ ደግሞ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የክረምት የጤና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጤና ተቋማትና ህብረተሰቡ የበለጠ የሚያቀራርብና የተረሱ ዜጎች የሚታወሱበት እንዲሁም ለጤና ሁሉም የሚረባረብበት እንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከሐምሌ 14 እስከ ነሀሴ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when St. Peter General Specialized Hospital - ቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category