Hamudi Hamudi

Hamudi Hamudi I Hamudi Hamudi am a Professional Psychologist and Social Worker. and also a Muslim Preacher. The Ai

ዛዉያ ቲቪ በአዲስ መልኩና በከፍተኛ ጥራት የረመዷን ስርጭቱን ጀምሯል።
26/03/2023

ዛዉያ ቲቪ በአዲስ መልኩና በከፍተኛ ጥራት የረመዷን ስርጭቱን ጀምሯል።

የታላቁ የረመዳን ወር ዝግጅቻችን በዛውያ ቲቪ ይጠብቁፈሪክዌንሲ 11636ሴምቦልራት 27500ፖለራይዜሸን 5/6ዛውያ ቲቪ ተግባራዊ ዳዕዋ!

😊ከጸኃፊዉ በላይ ሲገባህ👌🏽
29/01/2023

😊ከጸኃፊዉ በላይ ሲገባህ👌🏽

ስነ-ምግባርና ዉጫዊ ገጽታችን   እና   ተቀራራቢ እይታ:(ክፍል1: በኒቼ አመለካከት ምሳሌ)ምንም እንኳን የላቀ/ጥሩ መስህብ ከብዙ አወንታዊ ባህሪያት ጋር የተቆራኘ ቢሆንም ወጥነት ግን የለዉ...
24/01/2023

ስነ-ምግባርና ዉጫዊ ገጽታችን እና ተቀራራቢ እይታ:
(ክፍል1: በኒቼ አመለካከት ምሳሌ)

ምንም እንኳን የላቀ/ጥሩ መስህብ ከብዙ አወንታዊ ባህሪያት ጋር የተቆራኘ ቢሆንም ወጥነት ግን የለዉም። ከላይ አምሮ የታየ ሁሉ ዉስጡ ጣፋጭ ወይም መጥፎ ሊሆን የሚችልበት እድል ሰፊ ነዉ። "ሲያዩት ያላማረ.." የሚለዉ የሀገራችን ብሂል ከስነ-ምግባር አንጻር ያለዉ ቦታ ሀምሳ ሀምሳ ነዉ። እንዲያዉም በMeta Analysis ውበት በሥነ ምግባር ብይን ላይ ያለው አጠቃላይ ውጤት ለዜሮ የቀረበ ነው።

ፍሬድሪክ ዊልሄልም ኒቼ ጀርመናዊ ፈላስፋ፣ ገጣሚ፣ የባህል ሃያሲ፣ክላሲካል ፊሎሎጂስት እና አቀናባሪ ሲሆን ስራው በዘመኑ ፍልስፍና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ግለሰብ ነዉ።

እንደ ፍሬድሪክ ኒቼ እሳቤ የብዙ ሰዎች ሥነ ምግባር በውበት ተጽዕኖ ስር የወደቀ ነዉ። በአይነ ስጋ የሚታይ ዉበት ምግባራችንን በመወሰኑ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለዉ ያምናል። ይህ የብዙሀኑን ሰዉ የተዛነፈ ግንዛቤ ማሳያ ነዉ። ለምሳሌ ይላል ኒቼ፡- "አብዛኛው ሰው መኪና በረሮን ሲደፈጥጣት ሲያይ ምንም አይመስለዉም። ለበረሮዉም አይራራም። ነገር ግን በቀለማት ያሸበረቀች ወፍ ወይም ድመትን መኪና ቢገጫቸዉ ግን እዝነ-ልቦናቸዉ ይራራል። እንዲሁም ከሰው ልጅ የስነ ልቦና እንግዳ ነገሮች አንዱ ለተራበ ውሻ ልቧ የሚያዝን ለስላሳ ሴት ከሌላ ሙት እንስሳ አካል ቁራጭ ስጋ ስትመግበዉ ትመለከታለህ። ከሙት አካሉ ላይ ስጋዉን ለቦጨቀችዉ ስለተገደለዉ እንስሳ ግን ደንታ የላትም።" ከዚህ በመነሳት "የሰው ልጅ ስነ ልቦና በጣም የተወሳሰበ ነው። እሱን ለመረዳት መሞከርም መላውን አጽናፈ ሰማይን የመረዳት ያህል ከባድ ሊሆን ይችላል" ሲል ይደመድማል ኒቼ።

ይህ የፍሬድሪክ ኒቼ ምሳሌና ሀሳብ የሚያሳየን #አንድም: የሰዉ ልጅ በዓይን በሚያየዉ ነገር የመማረክ ስጋዊ ፍላጎቱ ዉስጣዊ ስሜቱና Moral Discription/ግብረገብነትን አዎንታዊ ወይም አሉታዊ በሚል ብይን የመስጠት ዝንባሌዉ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረዉ ሲሆን.. #በሁለተኛ ደረጃ: የዉጫዊ ገጽታ ማማር ከዉስጥ ዉበት እንደሚመነጭና በተቃራኒዉ ዉጫዊ ገጽታን ማስተካከል (ንጽህናን መጠበቅ፣ አምሮ መታየት፣ መልካም መዓዛ የመሳሰሉት ነገሮች) ዉስጣዊ ማንነታችንን ለማነጽ የራሱ አዎንታዊ ሚና እንዳለዉ ይጠቁማል።

ይህን ሀሳብ የሚያጠናክርልን የኢማም-አልገዛሊን ሀሳብ በክፍል2 አቀርባለሁ።

Hamudi Hamudi

ወርቃማው የህይወት ህግ:"በራስ መተማመንህ ዝቅ በማለቱ ምክንያት በራስህ ላይ እምነት ስለሌለህ፣ በንግግርም ሆነ በጽሁፍ ራስህን በመግለጽ ስለምታፍር ወይም ስለምትፈራ: አንተን ወክሎ ሊናገር ...
22/01/2023

ወርቃማው የህይወት ህግ:

"በራስ መተማመንህ ዝቅ በማለቱ ምክንያት በራስህ ላይ እምነት ስለሌለህ፣ በንግግርም ሆነ በጽሁፍ ራስህን በመግለጽ ስለምታፍር ወይም ስለምትፈራ: አንተን ወክሎ ሊናገር የሚችል ትክክለኛውን ሰው በመፈለግ ራስህን አታድክም። ይልቁንስ ሃሳብህን ለመግለፅ የምትጠቀምበትን ትክክለኛ መንገድ በማሰብ የተቻለህን ሁሉ አድርግ!። ማንም ሰዉ አንተ የፈለግከዉን ሊገልጽልህ አይችልምና ሰዎች እንዲረዱህ ስለራስህ ማንንም አማላጅ አትላክ!። ስሜትህን ባንተ ልክ የሚተነፍስልህም ባለመኖሩ ሀሳብህን የሚያሻግርልህ ድልድይ አትፈልግ!። ስላንተ ጥበብ ብቸኛዉ መንገድህ ነዉና ራስህን ለመግለጥና የዉስጥህን ለመግለጽ ጥበብን ብቻ ፈልግ!"🌾🍃

Hamudi Hamudi

አስቀያሚዉ የአስተምህሮ መልክ!አብዛኞቻችን ጆሴፍ ስታሊንን እንደምናዉቀዉ ተስፋ አደርጋለሁ። ጆሴፍ ቪሳሪዮኖቪች ስታሊን የጆርጂያ ተወላጅ የሶቪየት አብዮተኛ እና የፖለቲካ መሪ ነበር።  ከ192...
22/01/2023

አስቀያሚዉ የአስተምህሮ መልክ!

አብዛኞቻችን ጆሴፍ ስታሊንን እንደምናዉቀዉ ተስፋ አደርጋለሁ። ጆሴፍ ቪሳሪዮኖቪች ስታሊን የጆርጂያ ተወላጅ የሶቪየት አብዮተኛ እና የፖለቲካ መሪ ነበር። ከ1924 እስከ እለተ ሞቱ 1953Gc. ሶቭየት ህብረትን ሲመራ የሶቭየት ህብረት ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሀፊ እና የሶቪየት ህብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን በስልጣን ቆይቷል።

እናም በአንድ አጋጣሚ በስሩ ያሉ የፓርቲ አመራሮቹን በተለየ መልኩ አቋሙን ለማሳወቅና ለማስተማር በሚል ዶሮ እንዲመጣለት ያዛል። ዶሮዋንም በአንድ እጁ በሓይል አንቆ በመያዝ በሌላኛዉ እጁ ላባዋን መንጨት ጀመረ። ዶሮዋ ራሷን ነጻ ነማዉጣት ብትንፈራገጥም ከጭብጡ ማምለጥ አልቻለችም። ከላይዋ ላይ ያለዉ ላባዋ ሙሉበሙሉ እስኪያልቅ ከነቀለ በኋላ ወደ ጓዶቹ እየተመለከተ "አሁን ምን እንደሚፈጠር ተመልኩቱ!" በማለት ዶሮዋን መሬት አስቀምጧት ወደኋላ ራቅ አለ። በመቀጠል በእጁ እፍኝ ስንዴ ይዞ ቆመ። በዚህ ጊዜ ሁሉም ጓዶቹ ያስደነቃቸዉን ክስተት ተመለከቱ!። ዶሮዋ ወደ ስታሊን እየተጠጋች ኮቱን ጫማዉ ላይ እንደመዉጣት እየሞከረች ጥሬዉን ለማግኘት ትጥራለች። በእጁ ካለዉ የስንዴ ጥሬ ጥቂት በተን እያደረገላት በግቢዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ ዶሮዋም የሚጣልላትን ጥሬ ፍለጋ በሄደበት ትከተለዋለች።

በዚህ ጊዜ ስታሊን ሁኔታዉን በአግራሞት ሲከታተሉ ወደነበሩ ጓዶቹ በመመልከት በእርጋታ የሚከተለዉን መልዕክት አስተላለፈ።
"ልክ በዚህ መልኩ ሰዎችን መግዛት ይቻላችኋል!። ይህች ዶሮ ያደረስኩባትን ስቃይ ከቁብ ሳትቆጥር የምወረዉርላትን ጥሬ ፍለጋ እንዴት እንደተከተለችኝ አያችሁ? እንዲህ እንደ ዚህች ዶሮ አይነት ሰዎች አሉ። ምን ያህል በደልና ግፍ ቢያደርሱባቸዉ ለፍርፋሪ ሲሉ ከገዢዎቻቸዉ ኋላ እየተከተሉ የሚያነፈንፉ!"

(በእኔ በኩል በራሱ በስታሊን ሀሳብ ብቋጭና ከታሪኩ የምንማረዉ ብዙ ቁምነገር ስላለ የታያችሁን አስተያየት እንድታክሉበት ጋበዝኳችሁ)

Hamudi Hamudi

አዕምሯችንን የምንጠብቅባቸዉ11 መንገዶች:እንደሚታወቀዉ አንጎል አስተሳሰብን፣ ትውስታን፣ ስሜትን፣ ንክኪን፣ የሞተርን ችሎታን፣ እይታን፣ መተንፈስን፣ ሙቀትን፣ ረሃብን እና አጠቃላይ የሰውነታች...
21/01/2023

አዕምሯችንን የምንጠብቅባቸዉ11 መንገዶች:

እንደሚታወቀዉ አንጎል አስተሳሰብን፣ ትውስታን፣ ስሜትን፣ ንክኪን፣ የሞተርን ችሎታን፣ እይታን፣ መተንፈስን፣ ሙቀትን፣ ረሃብን እና አጠቃላይ የሰውነታችን ሁኔታ የሚመጠንበት ሂደትን የሚቆጣጠር ውስብስብ አካል ነው። ከውስጡ የሚዘረጋው አንጎል እና የአከርካሪ ገመድ አንድ ላይ ማዕከላዊውን የነርቭ ሥርዓትን ወይም CNSን ይሠራሉ።

ከዚህ አንጻር አዕምሯችንን መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ እናገኘዋለን። ለዚህ የሚረዱን ብዙ መንገዶች ቢኖሩም ለዛሬ ወሳኝ ያልኳቸዉን 11ዱን መንገዶች እነሆ!

1. መደበኛም ሆነ ተንቀሳቃሽ ስልክ ለንግግር በመጠቀም ወቅት ግራ ጆሮን መጠቀም
2. ቡናም ሆነ አነቃቂ ነገሮችን በቀን ከአንድ ጊዜ በላይ አለመጠቀም
3. በአፍ የሚወሰድ የመድሓኒት እንክብልን በቀዝቃዛ ዉሃ አለመዉሰድ
4. ከ11 ሰዓት በኋላ ከባድ ምግብን አለመመገብ
5. ቅባታማና ስብ የበዛባቸዉ ምግቦችን መቀነስ
6. በጠዋት(በተለይም በባዶ ሆድ) ብዙ ዉሃ መጠጣትና ከሰዓት በኋላ መቀነስ
7. ሞባይል ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ስልክን ከአጠገባችን ማራቅ
8. የጆሮ ማዳመጫ ኤርፎን/ሄድፎን ለረዥም ሰዓት አለመጠቀም
9. ከምሽት 5ሰዓት እስከ ንጋቱ 12ሰዓት ያለዉን ጊዜ ለእንቅልፍ ተመራጭ ማድረግ
(ይህን ጽሁፍ ያሰናዳሁበት ጥናት ይህን ቢልም በሌሎች ጥናቶች እንደተረጋገጠዉና በእኔ በኩልም ከማታ 3-4ሰዓት እስከ ለሊት 11ሰዓት ያለዉ የተሻለ ነዉ ብዬ አምናለሁ)
10. ከእንቅልፍ በፊት መድሓኒት ወስዶ ወዲያዉ አለመተኛት
11. የሞባይል ባትሪ ቀንሶ ለማለቅ/ለመዝጋት በሚቃረብበት ወቅት ስልክን ፈጽሞ አለመጠቀም። ይህም የጨረሩ መጠን በ1000 እጥፍ የመጨመር እድል ስላለዉ በአዕምሯችን ላይ የሚያስከትለዉ ጉዳት ከፍ ስለሚል።
መልካም ጊዜ!💝

Hamudi Hamudi

ስምና ክብርህ ከዕድሜህ በላይ ይኖራል!በጉድጓድ ዉሃ ይገባኛል የተጨቃጨቁ ቁራና ጉጉት በመሀላቸዉ የተፈጠረዉን ወደግጭ ሊያመራ የቀረበ አለመግባባት በሰላምና በመነጋገር መፍታት ባለመቻላቸዉ ገለ...
21/01/2023

ስምና ክብርህ ከዕድሜህ በላይ ይኖራል!

በጉድጓድ ዉሃ ይገባኛል የተጨቃጨቁ ቁራና ጉጉት በመሀላቸዉ የተፈጠረዉን ወደግጭ ሊያመራ የቀረበ አለመግባባት በሰላምና በመነጋገር መፍታት ባለመቻላቸዉ ገለልተኛ ፍርድ እናገኝበታለን ብለዉ ወዳመኑበት የአዕዋፋት ዳኛ ይሄዳሉ። ዳኛዉም ሁለቱንም የወፍ ዝርያዎች አለኝ የሚሉትን የባለቤትነት መረጃ እንዲያቀርቡ ጠየቀ። ሁለቱም ወፎች እርስበርስ እየተያዩ ረዥም ዝምታ በመሀላቸዉ ሰፈነ። ዳኛዉ ከሁለቱም ዝምታ በመነሳት አንዳቸዉም በሌላኛዉ ላይ የሚረታበት በቂ መረጃ የሌለዉ መሆኑን ተረዳ። በዚህ ጊዜ ድንገተኛና እንግዳ ዉሳኔዉን አሳለፈ። "የዉሃዉ ጉድጓድ ባለቤትነት ለጉጉት ይገባዋል!" ሲል ፈረደ።

ጉጉትም ባልተጠበቀዉ ፍርድ በመገረሙ "ክቡር ዳኛ ሆይ! ሁለታችንም በቂ መረጃ ያላቀረብን ሆነን ሳለ እንዴት በደፈናዉ ለእኔ ሊፈረድልኝ ቻለ?" ሲል ጠየቀ።

ዳኛዉም: "እርግጥ ነዉ ሁለታችሁም መረጃ የላችሁም። ይሁን እንጅ አንድ ሐቅ አለ። አንተ እዉነተኛና ታማኝ መሆንህ በመላዉ አዕፋት ዘንድ ይታወቃል!። ሁሉም ለዚህ ዳኝነት ዕድሉ ቢሰጣቸዉ ያለጥርጥርና ያለምንም ልዩነት ሳያቅማሙ ላንተ እንደሚፈርዱ እርግጠኛ ነኝ!። እንዲያም ስለታማኝነት በተነሳ ቁጥር: 'ለእዉነተኝነትማ ማን እንደ ጉጉት!' ይባል የለ?" አለዉ።

ይህን የመሰለን መልስ ከዳኛዉ የሰማዉ ጉጉትም ጥቂት በዝምታ ተዉጦ ሲያብሰለስል ከቆየ በኋላ..: "ነገሩ እንዲያ ከሆነማ: በእዉነተኝነትና ታማኝነት ታዉቆ ከዚያ ተቃራኒዉን የሚፈጽም ሞራል የለኝም!። በመሆኑም የዉሃዉ ጉድጓድ ለቁራዉ ይገባዋል። በጌታዬ ይሁንብኝ በመላዉ አዕፋት ዘንድ የምታወቅበት የእዉነተኝነትና ታማኝነት ማንነቴ ከእኔ ጋር ቢቆይልኝ ከአንድ ሺህ ጉድጓድ ይበልጣል!" በማለት ጥቅሙን አሳልፎ ክብሩን ለማስጠበቅ በቃ።

ቁም ነገሩ:
መልካም ስምህን ጠብቅ ነዉ!። ክብርህ ራስማልህ ነዉ። ስምና ክብርህ ከአንተ ዕድሜ ይበልጣል!። አንተ ብትሞት እንኳን ስምህ አይሞትም። ክፉም ሆንክ ደግ ትታወስበታለህ። ዝክርህን ጠብቅ። ስላንተ ደግነት ኑረህም ሆነ አልፈህ ስምህ ያወራልህ ዘንድ በመልካምነትህ ጽና!።

ታላቁ ሊቅ ኢማም አሻፊዒ የሚከተለዉን ቃል ሰክከዋል!
አንዳንድ ሰዎች አሉ አልፈዉ ሚዘከሩ
አንዳንድ ሰዎች አሉ ኖረዉም ያልኖሩ
Hamudi Hamudi

ነጻነትና ደስታ የተሳሰሩ ናቸዉ!ይህ ክስተት በካርናታካ ከኮምባሩ ደን አጠገብ ካለ የውሃ ማጠራቀሚያ ማዕከል ዉስጥ የተፈጠረ  ነዉ። አቦሸማኔዉ ውሻውን እያሳደደው ነበር። ውሻው በመስኮቱ በኩል...
18/01/2023

ነጻነትና ደስታ የተሳሰሩ ናቸዉ!

ይህ ክስተት በካርናታካ ከኮምባሩ ደን አጠገብ ካለ የውሃ ማጠራቀሚያ ማዕከል ዉስጥ የተፈጠረ ነዉ።

አቦሸማኔዉ ውሻውን እያሳደደው ነበር። ውሻው በመስኮቱ በኩል ወደ መጸዳጃ ቤት ገባ። አቦሸማኔዉም ከውሻው በኋላ ተከትሎት ገባ። ወዲያዉም የመጸዳጃዉ በር ተዘጋ። እናም ሁለቱም ሽንት ቤት ውስጥ ተጣበቁ። ውሻው አቦሸማኔዉን ሲያይ በጣም ስለደነገጠ በፀጥታ በአንዱ ጥግ ተቀመጠ። ለመጮህ እንኳን አልደፈረም። ይሁን እንጂ አቦሸማኔዉ እንደዚያ ተርቦ ውሻውን ቢያሳድደውም በጠባቧ መጸዳጃ ቤት ዉስጥ በዝግ ሲያገኘዉ ግን ውሻውን ሊበላዉ አልደፈረም። ውሻውን በአንዴ ቦጭቆ ሆድ እቃዉን ዘርግፎ ሊበላዉ ይችል የነበረ ቢሆንም እንደዛ ሊያደርግ አልተቻለዉም። ሊበላዉ ቢሞክርም ዉሻዉ ድምጹን ሳያሰማና ሳይንቀሳቀስ ከቦታዉ ንቅንቅ ባለባለማለቱ አጠገቡ እየደረሰ ወደኋላ ከመሸሽ በስተቀር ምንም ማድረግ አልቻለም። በዚህ ሁኔታ ሁለቱ እንስሳት ለአሥራ ሁለት ሰዓታት ያህል በተለያዩ ማዕዘኖች ውስጥ አብረው ነበሩ። አቦሸማኔዉም በእነዚህ አስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ተረጋግቶ ተቀምጦ ቆዬ።

ከአስራ ሁለት ሰዓታት በኋላ በደኑ የአንድ ​​ዲፓርትመንት ክፍል ሰራተኞች ወደ ዉስጥ ሲዘልቁና መጸዳጃ ቤቱን ለመክፈት ሲሞክሩ አቦሸማኔዉን በመመልከታቸዉ በለመዱት የማጥመድ ስልት በቁጥጥራቸዉ አስገቡት።

አሁን ጥያቄው የተራበው አቦሸማኔ በቀላሉ ሊበላዉ በሚችልበት ጊዜ ውሻውን ለምን አልበላዉም? የሚለዉ ነዉ።

የዱር አራዊት ተመራማሪዎች ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። እንደነሱ አባባል: የአቦሸማኔዉ ኩምሽሽ ማለት ከለመደዉ የዱር ሜዳ አንዲት ጠባብና ጨለማ ያዘለች መጸዳጃ ዉስጥ መከሰቱ ነጻነቱን ስለነጠቀዉ ነዉ። "የዱር እንስሳት ለነፃነታቸው በጣም ስሜታዊ ናቸው። ነፃነታቸው እንደተነጠቀ ከተገነዘቡ በኋላ ረሃባቸውን እየረሱ ጥልቅ ሀዘን ሊሰማቸው ይችላል። ሆዳቸውን ለመመገብ ተፈጥሯዊ ፍላጎታቸው እየቀነሰ ይሄዳል" ይላሉ ባለሙያዎቹ።

መልዕክቱ:
happiness will be greater the more freedom a person has in her/his life decisions.
የሰዉ ልጅ ደስተኛ የመሆን እድሉ በሕይወቱ በሚኖረዉ ነጻነት ልክ ይወሰናል። ነጻነቱ በሰፋ ቁጥር ደስታዉ ይበዛል። ነፃነት እና ደስታ የተሳሰሩ ናቸው። እንደፈለግነው የማሰብና የመተግበር አቅማችን ባለን የሕይወት ነፃነት ይወሰናል። ነጻነታችንን ስንነጠቅ የተለየ ነገር ማሰብም ይሳነናል።
Hamudi Hamudi

ከክስተቱ የተረዳነዉን ሀሳብ በተሻለ መልኩ መግለጽና ማዳበር ይቻላል!።

"ጉቱ" ይባላል። የ146 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነዉ። "ማጨስ እንዳቆም የመከሩኝ ዶክተሮች ሁሉ ሞተዋል!" ይላል። 🙃🙂NB: እርግጥ ይህ ምስል ማንም ሰዉ ቀኑ ካልደረሰ እንደማይሞት ከ100/1...
15/01/2023

"ጉቱ" ይባላል። የ146 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነዉ።
"ማጨስ እንዳቆም የመከሩኝ ዶክተሮች ሁሉ ሞተዋል!" ይላል።
🙃🙂

NB: እርግጥ ይህ ምስል ማንም ሰዉ ቀኑ ካልደረሰ እንደማይሞት ከ100/1 ማሳያ ሊሆን ይችላል እንጂ የትንባሆን ጎጂነት ጥያቄ ዉስጥ አያስገባዉም!።

Hamudi Hamudiን follow, Like& Share ያድርጉ
አመሰግናለሁ!

የስሎቫኪያዉ የቃልኪዳን ሀዉልት!🥰ይህ ሃውልት በስሎቫኪያ ዋና ከተማ ብራቲስላቫ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ወጣት የጽዳት ሰራተኛን ለማስተዎስ የቆመለት ምስሉ  ነዉ። ወጣቱ አንዲት ሴት ልጅ ወድዶ ...
14/01/2023

የስሎቫኪያዉ የቃልኪዳን ሀዉልት!🥰

ይህ ሃውልት በስሎቫኪያ ዋና ከተማ ብራቲስላቫ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ወጣት የጽዳት ሰራተኛን ለማስተዎስ የቆመለት ምስሉ ነዉ።

ወጣቱ አንዲት ሴት ልጅ ወድዶ በፍቅሯ ከንፎ ነበር። ይህን የተረዳችዉ ጉብል እሷም ተመሳሳይ የፍቅር ስሜት ይሰማት ነበርና ፊት አልነሳችዉም። ወጣቱም እንደምንም ብሎ ፍቅሩን ይገልጽላታል። ስለሚሰራዉ የስራ ዓይነት ጠይቃዉ ራሱንም በእዉነተኛ ማንነቱ ማሳወቅ እንዳለበት በማመን እዉነቱን ይነግራታል። (የጽዳት ሰራተኛ መሆኑን!)።

በዚህ ጊዜ ልጅቱ በጣም ይቀፋታል። ሆኖም ስሜቷ እንዳይታወቅባት በዉስጧ አምቃ ጥሩ ሙድ ላይ እንዳለች መስላ ታወራዋለች። ተገናኝተዉ ሻይቡና እያሉ ቢጨዋወቱ ደስ እንደሚለዉ ሲነግራት በሰዓቱ እርሱን ላለማስቀየም በሚል ምክንያት ይሁንታዋን ቸረችዉ። በቀጠራት ሰዓትና ቦታም እንደምትገኝ ቃል ገባችለት።

የቀጠሮዉ ቀን ሲደርስ በሰዓቱ ወደ ተቀጣጠሩበት ቦታ ይሄዳል። ረዘም ላለ ሰዓት ቢጠብቃትም አልመጣችም። የገባችውን ቃል አፍርሳለች!። እርሱ ግን ከዚያን ዕለት ወዲህም በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይጠብቃታል።

የወጣቱ የቅርብ ጓደኞች ወዳጃቸዉን በዚህ ሁኔታ ሲመለከቱት አላስችላቸዉ ብሎ በየተራ እየሄዱ ሻይ እያጣጡ ያጽናኑት ነበር።

ፍቅሩን ትመጣለች ብሎ በተስፋ የሚጠብቀዉ ወጣት ለዓመታት በዚህ ሁኔታ ቆይቶ ይሞታል!።
ታሪኩን ያየና የሰማዉ የከተማዉ ማሕበረሰብም በሁኔታዉ እጅጉን በማዘኑ ይህን የፍቅር ሰዉ ለማስታወስ አንድ ነገር ሊደረግ ይገባል በማለት በስሙ ሀዉልት ተቀረጹለት። ከሀዉልቱም ጎንም በስሙ ካፌ ተሠራለት። ሰዎች እዚህ ካፌ እየመጡ በዉስጣቸዉ አብረውት ቡና እየጠጡ እንደሆነ በማሰብ ለእርሱ ያላቸውን ፍቅርና ርኅራኄ ይገልጹለታል። ወጣቱ ለሰራዉ ስራ ዋጋ ይሰጣሉ። መስዕትነቱን ይዘክራሉ። ሌሎች የጽዳትም ሆነ ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ የማሕበረሰብ ክፍሎችንም ክበር መስጠት እንዳለባቸዉ በዚህ ቦታ ይገነዘባሉ!። የሥራን ክቡርነት በዚህ ቦታ ያስታዉሳሉ። በተለይም ብራቲስላቫ ንፁህ እንድትሆን ይተጋሉ። ስለፍቅርም ታማኝነታቸዉን ከቃል በላይ ሊያሳዩ ቃል ይገባሉ።

(በምስሉ እንደሚታየዉ ከሐዉልቱ አናት/ጭንቅላቱ ላይ የተቀመጠዉ ባርኔጣ ለስላሳ ነዉ። ይህም የሆነዉ ሰዎች ሰላምታቸዉንና ክብራቸዉን በእጃቸዉ እየዳበሱ በመሆኑ ተደጋጋሚ እጅ ያረፈበት ከመሆኑ የተነሳ ነዉ)።

Hamudi Hamudi

😀
13/01/2023

😀

"ደስታቸዉን በሌሎች ላይ ያንጠለጠሉ ሁሉ በብቸኝነት አረር ተገርፈዉ ሞተዋል!" #ዴስቶቭስኪ
13/01/2023

"ደስታቸዉን በሌሎች ላይ ያንጠለጠሉ ሁሉ በብቸኝነት አረር ተገርፈዉ ሞተዋል!"
#ዴስቶቭስኪ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251980479303

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hamudi Hamudi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Hamudi Hamudi:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category