18/04/2026
"Surname" ወይም "Last Name" ወይም "Family Name" ሲባል የአባት ስም ወይስ የአያት ስም?
እንደሚታወሰው ትናንት በገጼ ላይ ባደረግኩት የሕዝብ አስተያየት (Poll) ጥናት መሰረት ፣ ብዙዎቻችን ዓለም አቀፍ ፎርሞችን ስንሞላ የምንሳሳትበት አንድ ትልቅ ነጥብ እንዳለ ተረድቻለሁ። በፖሉ ላይ ከተሳተፉት 122 ሰዎች መካከል 76ቱ (62.3%) ትክክለኛውን መልስ ሲመልሱ፣ የተቀሩት 46ቱ (37.7%) ግን አሁንም "Surname", "Last Name", "Family name" ማለት "የአባት ስም" እንደሆነ ያስባሉ። ይህ ማለት ከሦስት ሰው አንዱ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዥታ አለበት ማለት ነው።
የስሞች አመዳደብ በዓለም አቀፍ ደረጃ
በምዕራባውያን እና በዓለም አቀፍ አሰራር "Surname" ወይም "Last Name" ማለት የቤተሰብ ስም (Family Name) ማለት ነው። በእኛ ሀገር ደግሞ የቤተሰብ ስም የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ በቋሚነት ስለሌለ፣ በዓለም አቀፍ ስምምነት መሰረት የአያት ስም እንደ "Last Name" ተቆጥሮ ይወሰዳል። በአንፃሩ የእኛ የግል ስም "First Name" ወይም "Given name" ፣ የአባታችን ስም ደግሞ "Middle Name" ተብሎ ይጠራል።
ምናልባትም ምዕራባውያንን ጨምሮ ብዙ አገሮች ጋር በ First name ተመሳሳይ ነን ለእኛ የተሰጠ ስም ስለሆነ። Middle and Last name አጠራር ላይ ግን ከላይ እንደገለጽኩት በፍጹም ፍጹም የተለያየን ነን።
ፈረንጆች ደስ የሚላቸውን የሚወዱትን whatever የፈለጉትን ሰው አክብሮታቸውንና መውደዳቸውን ለመግለጽ ሊጠቀሙ ይችላሉ። ብዙ ጊዜ Middle name ላይ የሚጽፉት አንድ ፊደል ብቻ ነው። ለምሳሌ :- Barack H. Obama
ባራክ የሚለው ቤተሰቦቹ ያወጡለት የራሱ መጠሪያ ስም ወይም First name or Given name ማለት ነው። ዘ. ወይም ዘussen የሚለው Middle name ይባላል። እኛ ጋር ብዙ ጊዜ በስምምነት የአባት ስም እንሞላበታለን ምክንያቱም Middle name የሚባል ስለሌለን ፤ ይሄ ግን ከነሱ ጋር ፈጽሞ አይገናኝም እነሱ የሚጠቀሙት የፈለጉትን ማክበር የሚፈልጉትን ሰው የሚጨምሩበት እና የሚጠሩበት ነው።
ኦባማ የሚለው ግን Last name ሲሆን የቤተሰብ ስም ማለት ነው ፤ አጠቃላይ ቤተሰቡን አንድ አድርጎ አስተሳስሮ የሚጠራ ስም ፤ ይህ ማለት እናቱ ሚስቱ ልጁ ወዘተ ቤተሰቡ በአንድ የሚጠሩበት ማለት ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው የኦባማ ሚስትንም ሆነ ልጆቹ በዚህ ስም ይጠራሉ እኛም ኦባማ እያልን ነው የምንጠራው። ስለዚህ የምዕራባውያን የስም አጠራር ከኛ አጠራር ጋር ፍጹም የተለየ መሆኑን የተረዳን ይመስለኛል።
ሁለቱ ስሞች ላይ ቋሚ ህግ የለም እኛ ከነሱ ጋር ለመሳሰል እና የተለያዩ የትምህርት ፣ የህክምና ፣ እንደዚሁም የስራ እንቅስቃሴ ስናደርግ ከነሱ ለመመሳሰል የቤተሰብ ስም የሚለው ላይ የአያት ስም እሚጠቀማለን ፣ የአባት ስም የቤተሰብ ስም ቦታ ላይ ፈጽሞ መጠቀስ የለበትም።
በርካታ ኢትዮጵያውያን Last Name ተብለው ሲጠየቁ የአባቴን ነው ወይስ የአያቴን የምነግርህ የሚል መደናገር ይታይባቸዋል ይህ አንዳንድ በውጭ ሀገር የሚኖሩትንም ይጨምራል። አንድ ሰው Last Name ተብሎ ሲጠየቅ በድፍረት የአያቱን ስም ነው መናገር ያለበት።
ትክክለኛው የስም አሞላል ዘዴ የቱ ነው?
ብዙ ጊዜ በምንሞላቸው ፎርሞች ላይ "Middle Name" የሚል ሳጥን ላይኖር ይችላል። በዚህ ጊዜ የአባታችንን ስም ከግል ስማችን ጋር አያይዘን "First Name" በሚለው ሳጥን ውስጥ መጻፍ ይኖርብናል።
ለምሳሌ፦ ስምዎ መሐመድ፣ የአባትዎ ስም ሰይድ፣ የአያትዎ ስም አህመድ ቢሆን፤
First Name: Mohammed Seid
Last Name / Surname: Ahmed
ተብሎ መሞላት አለበት። ይህን ዘዴ ካልተከተልን ፣ ስማችን በፓስፖርታችን ወይም በሌሎች ኦፊሴላዊ ሰነዶቻችን ላይ ካለው ጋር የማይገጥም (Mismatch) ሊሆን ይችላል።
በዚህ አጋጣሚ ምዕራባዊያን ከዚህ ፎርም በኋላ በምታደርጉት ማንኛውም አይነት ግንኙነት አህመድ ብለው ነው የሚጠሯችሁ ማለት ነው።
ለምን ጥንቃቄ ያስፈልገናል?
ዲጂታል ክህሎት (Digital skills) ማለት አፕሊኬሽኖችን መጠቀም ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፍ የአሰራር ደንቦችን መረዳትም ጭምር ነው። በስም አሞላል ላይ የምንሰራው ትንሽ ስህተት የትምህርት ማስረጃዎቻችን ተቀባይነት እንዲያጡ፣ የባንክ ዝውውሮች እንዲዘገዩ ወይም የቪዛ ጥያቄዎቻችን ውድቅ እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ ማንኛውንም ፎርም ከመሙላታችን በፊት የቃላቱን ትርጉም በደንብ መረዳት ይኖርብናል።
ብዙ ጊዜ የተለያዩ ሳይቶች ላይ አካውንት ከከፈትን በኋላ የስነድ የስነድ ማረጋገጫ ስንጠየቅ ፓስፖርት እናስገባለን ፤ ከምርመራ በኋላ ጥያቄያችን ውድቅ የሚደረግበት ምክንያት አንዱ ኮፓስፖርታችን ጋር አለመመሳለሉ ነው።
ለበለጠ ፓስፖርት ያላችሁ ፓስፖርታችሁን ማየትና ማረጋገጥ ትችላላቸሁ። እዚህ ገጽ ውስጥ በርካታ ምሁራን ስላላችሁ ተጨማሪ ሀሳብ መጨመር ትችላላችሁ።
እናንተስ ከዚህ በፊት ባላችሁ ልምድ "Surname" የሚለውን ሳጥን እንዴት ነበር የምትሞሉት? በስም አሞላል ስህተት የገጠማችሁ ችግር ነበር? ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን።👇