ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium clinic

ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium clinic, Doctor, Addis Ababa.

የቦዲቲ ዲሲ መካከለኛ ክሊንክ የላቦራቶሪ ባለሙያ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል::  እድላችሁን ሞክሩ ÷ተወዳደሩ! መልካም ዕድል!  ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium...
27/01/2025

የቦዲቲ ዲሲ መካከለኛ ክሊንክ የላቦራቶሪ ባለሙያ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል:: እድላችሁን ሞክሩ ÷ተወዳደሩ!

መልካም ዕድል! ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium clinic ቦዲቲ ከተማ እግር ኳስ ክለብ Wolaita Culture & Tourism Ŵįnŋęŕ Šïmøñ Ŵiĥa Yemisha Simon ቦዲቲ/Boditti Isaac Simon Ferenj ቦዲቲ Meme @

22/12/2024
17/11/2024

ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium clinic

Health professionals association Eating healthy is the way defending our body from foreign enemies & empowering our immu...
17/11/2024

Health professionals association

Eating healthy is the way defending our body from foreign enemies & empowering our immunity
ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium clinic Matusawl Simon ቦዲቲ/Boditti @

ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ እና ለደምበኞቻችን::      በቦዲቲ ከተማ የዲሲ መካከለኛ ኪሊንክ በሕግወጥ መንገድ የመዘጋት ሙከራ ተደርጎ በታካሚዎቻችንና በሠራተኞች ቆራጥነት ተከለከለ:: ደስታች...
26/10/2024

ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ እና ለደምበኞቻችን::

በቦዲቲ ከተማ የዲሲ መካከለኛ ኪሊንክ በሕግወጥ መንገድ የመዘጋት ሙከራ ተደርጎ በታካሚዎቻችንና በሠራተኞች ቆራጥነት ተከለከለ:: ደስታችን ሕዝብን በማገልገል ፈጣሪን ማስደሰት ብሆንም መብታችንን የማስጠበቅ ባሕል በዎላይታ ውስጥ የተለመደ አለመሆኑ ባለስልጣናት ስልጣኑን አለአግባብ እንድጠቀሙ አደረገብን::
የድራማው መሪ አቶ ዋለልኝ መሆኑን አጣርተናል:: ከትላንት ወድያ ስለ ሽጉጥ አውርቼ ነበር:: ዛሬ አንድ የጤና መምሪያ ሀላፊ በሰላም ምድር : ያለ ሕግ አግባብ ከመንገድ የሆነ ፖልስ ሽጉጥ አሸክሞ መጣና በሽተኞቻችንንና ሠራተኞችን አወናበደ:: እንፋረዳለን:: ብቻ ሕዝብ ይስማ!

እኔ ከአገር ከወጣሁት 14 ዓመት ሆኖኛል::ከዛሬ 15 ዓመት በፍት በተወለድኩበት ወረዳ ሁለት ኪሊንክ[ በጃጌ እና በቦዲቲ] ከተማ ከፈትኩኝ:: ገና በአንድ ዓመት አገልግሎታችን: የከተማና የወረዳ የጤና ጥበቃ አመራር ጉቦና የሙስና ሰንሰለታቸው ከአቅመ በላይ ሆኖ ነበር::
.. ነገር ግን ከእነዝህ አመራሮች እየተቀያየሩ :እኔ በለሌሁበትም ጭምር: ወደ ኪሊንካችን: እየመጡ ምክንያት እየፈለጉ ያስፈራሩናል:: በቃ ለእነሱ ኪሊንኩን መዝጋት ማለት ከሉካንዳ ቤት ቀላል ነው:: ከሚዘጉብን ብለን የሚጠይቁትን ሁሉ እንሰጣለን:: ሆኖም ከአቅም በላይ ስሆን ቢያንስ እኔ በለሌሁበት ምንም እንዳይሰጣቸው: ከለከልን:: ከእነዝህ አንዱ የተበሳጨው የወረዳው ጤና ብሮ አመራር በራሱ ስልጣን የጃጌ ከተማ ኪሊንኩን አሸገ:: አሁን ሶዶ ነው የሚኖረውና ጡረታ ወጣ:: በአመራር የማይገናኙ: የቦዲቲ ከተማ ጤና መምሪያ ጌቶች ተከታትሎ ያለምንም መረጃ እርስበርስ ተነጋግረው በእልኽ ዘጉብኝ::

በአቃቤ ሕግ በቦዲቲ ፍርድ ቤት ከሰሱኝ:: ለ4 ወር ሥራችን ተዘግቶ ባለሙያዎች ወደ ቤታቸው ገቡ:: የፍርድ ቤት ውሳኔ እየተጠበቀ በ4 ወራት ውስጥ በዳውሮ ዞን: በማላውቅበት አንገላ በሚባል አከባቢ በትንሽ ከተማ : አድስ ኪሊንክ ወድያው ከፈትኩኝ:: እዛው አከባቢ በጣም ደስተኛ ነበርኩኝ::
በስተመጨረሻ የቦዲቲ ከተማ ጓዶች÷ የተወለድኩበት አከባቢ ደንበኞቻችን እና ቤተሰቦቻችን ጠልቃ ገብተው ስለነበረ ፍርድ ቤቱ እውነታውን ፈረደ÷ ዳኛዋ ሴት ነበረችና ሂዱና ሥራችሁን ሥሩ አለችንና ሥራ ከቀጠልኩኝ ዓመት ሳይሞላ የቦዲቲውን ራሴ ዘግቼ : ከአገር ወጣሁት:: ዛሬ ላይ ከክርስቲያን ሆስፒታል ባልተናነሰ የ9 ቀበሌ አርሶአደሮችን በጥራት: እያገለገለ : የጃጌ ከተማ ክሊንክ በወንድሜ ስም ተቀይሮ 16 ዓመታትን አገለገለ::

የክሊንኮቻችን ተጠቃሚው ሕዝብ : በብዛት ከተወልድኩበት አከባቢ ስለሆነ በመለስተኛ ወጪ የበጎ አድራጎት ሕክምና ሥራ እንሠራለን:: ያለምንም ሕጋዊ ማስረጃ ሳይጠየቅ: ለድሆች በብድር ሕክምና እየሰጠን የነፍስ ማዳን ሥራ እየሠራን ÷ አቅም የለሌውንና የስኳር ታካሚዎችን በሌልት በባጃጆች ከቤቱ እናስመጣለን:: ከፈጣሪ የሚከፈለው ደስታችንና የሕዝቡ ፍቅር እያጣጣምን ነው::
# # # # # # # # # # # # # # # # # # #
በነገራችን ላይ ፍርድ ቤቱ እውነታውን ለመፍረድ በራሱ የሕዝብ ጠልቃ ገብነት ወሳኝ ስለሆነ ነው ዛሬ ይኸን የለጠፍኩት ::

#በቦዲቲ ከተማ የዲሲ መካከለኛ ኪሊንክ ከተከፈተ 2 ዓመት ከ8 ወር ሆኖታል :: #ከ16 ሠራተኞች ዘንድሮ 3ቱ በሌላ ቦታ ሥራ አግኝቶ : 13 ሠራተኛ ደስተኛ ሆኖ እንድሠራ ዕድል ፈጥረናል:; በተጨማሪ በሠራተኛ ጀርባ ለሰፊ ቤተሰብ መተዳደሪያ ሆኗል:: በአጠቃላይ ዶክተሮች ÷ ነርሶች ÷ ጤና ሞኮንኖች ÷ ላቦራቶሪ ባለሙያዎች ÷ ጥበቃዎች ÷ የፅዳት ሠራተኞች ÷ የገንዘብ እና የአስተዳደር ክፍል አለ::
#ከሁሉም በላይ ለሰፊው ሕዝብ አማራጭ የሕክምና መንገድ በመፍጠር : ልምድ ባለው ባለሙያ ለ24 ሰዓት ከነሙሉ ላቦራቶሪ ክፍት አድርገናል:: ሌልት አንድ ታካሚ የሚከፍለው ክፍያ ለባለሙያ እንኳን ወጪ አይሸፍንም::

#ከዓምና ጀምሮ ከወረዳ እስከ ዞን ጤና መምሪያ የተወሰኑ ግለሰቦች አንዳንድ ዕብዶችን እየቀሰቀሱብን ይገኛሉ:: በተለያዬ ግዜ ገንዘብ እየጠየቁን ነው:: በአንድ ዓመት ውስጥ #ሶስት የተለያዬ ክስ እና ከሳሽ ቀስቅሰውብናል::
#ከ3ቱ ክሶች :በዲሲ መካከለኛ ኪሊንክ አመራር እና በእኔ ላይ የተከፈቱትን ሁለቱን አሸንፈናል:: የጤና መምሪያው #ፍርድ ቤት የሰጠውን ማዘዣ ላለመቀበል በእልኽ መጡብን::

ከ4 ወር በፍት #በጤና መምሪያ ሽርክና ኪሊንኩ ለ4 ቀን ተዘግቶ በተመላላሽ ታካሚዎቻችን ላይ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ድርግት ተፈፀመ:: የሆነ ሆኖም ብዙ ዋጋ ከተከፈለ በሗላ: ፍርድ ቤቱ ፈረደልን:: ከሳሹ ተቀጣ::በዝምታ አልፈን :ሥራችንን እስከዛሬ ቀጠልን::

ተመልሰው በድጋሚ በሌላ መንገድ መጡብንና የቤቱን አከራይ ቀሰቀሱት :: አከራዪ ላለፉት 6 ወራት ጀምሮ በድንገት 100% ዋጋ ጨመረና ያንንም ተስማምተን: በአከባቢ ሽማግሌ ተወሰነ:: ገንዘቡን ለመስጠት ሲደወልለት: ከአንድ ወር በሗላ አይ ልቀቁት እያለ መጣና ሌላ ተከራይ ግለሰብ አዘጋጅቶ ግለሰቡ እስከ ኪሊንኩ መጥቶ ጎበኘ::
እኛም አይ እንግድህ ሕግ ይከበር÷ አንወጣም አለን:: ቢያንስ የተዋዋልንበት የውል ግዜ ገደብ ማለቅ አለበት እየተባለ: በፍርድ ቤት ተከሰስን ::

አሁን የክስ ሂደቱ በዎላይታ ሶዶ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ ገና ሳይወሰን ከሶዶ ጤና መምሪያ ምንም ያለ ሕጋዊ መሠረት : ክሊንኩን ለመዝጋት ፖልስ ይዘው መጡ:: ተኝቶ የሚታከሙ በሽተኞች ባሉበት ÷ ተመላላሽ ታካሚ እና 13 ሕጋዊ ሠራተኛ ባለቤት ቦታ ላይ የተሰጠውን ስልጣን አለአግባብ በመጠቀም ኪሊንኩን ለመዝጋት ቢሞከርም ታካሚውና ሠራተኞች በከፍተኛ ፍልሚያ እንዳይዘጋ አድርገዋል::

መብትና ግደታ የሚያውቅ ጀግና እንደዝህ ይፈጠራልና ክሊንኩ ለዛሬ ከመታሸግ ተረፈ:: ዛሬ በሰላማዊ ኪሊንክ ላይ ፖሊስ አስከትሎ ለማስፈራራት የመጣው አቶ ዋለልኝ የተባለው ሀላፊ ነው:: ፍቃዱን ለማሳደስ ግዜው ደርሶ ባለሙያውን በየቀኑ ወደ ብሮ ያመላልሳል:: ግን ምን ፈልጎ ነው?

ይሄን ሁሉ ድራማ ከአከራዪና ከሌሎች ጋር በመመሳጠር የጤና ስነምግባር የጎደለበትና ሕግወጥ ተግባር የፈጸመው የጤና መምሪያ ቁጥጥርና ክትትል ክፍል ሀላፊዎች እንድጠየቁ እናደርጋለን :: ሲለዝህ የቦዲቲ ከተማ ነዋሪዎች እና መላው የወረዳ ነዋሪዎች ድጋፍ እንድያደርግ እንጠይቃለን::

በነገራችን ላይ ትልቁ ራዕያችንና ዓላማችን በወረዳ ውስጥ በተለያዪ አከባቢ: የሚሠሩ ሕግወጥ ሕክምና÷ በየጤና ጣብያ በታካሚዎች ላይ የሚደረገውን ኢሰብአዊ ድርግትን ለመከላከያ: መነሻ እንድሆነን እንጅ ለትርፍ ሸቀጥ አንሠራም::
የዲሲ መካከለኛ ኪሊንክ ወደ መጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ከፍ ለማድረግ ከዓምና ጀምሮ ፕሮጄክቱ በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ብሮ ከገባበት በየግዜው የሚደረገው የአመራር ለውጥ ጉዳዪ እንዳይፈጥን እንቅፋት ሆኖብናል:: ያም ሆነ ይህ: በየወረዳ ሕዝባችንን ዋጋ እያስከፈለ የሚገኘውን የጤና ሽፋንን ከመጨመር ይልቅ በሶዶ ከተማ ብቻ የሚዘወር የጤና መምሪያ አሠራር : ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ነው::

Wolaita Ethiopia 🇪🇹 Wolaita Nati (የወላይታ ልጆች )

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዲሲ ክሊኒክ በወላይታ ቦዲቲ Doctors center medium clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category