ንስር የመነፅር ስራ Nisir optics

ንስር የመነፅር ስራ Nisir optics ንስር

28/05/2024


Market

ግላኮማ በዓለም ላይ ዓይነ ስዉርነት በማምጣት ከዓይን ሞራ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀስ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ከዓይን ሞራና ዓይን ማዝ በመቀጠል በሦስተኛ ደረጃ ይቀመጣል። በዓይ...
17/03/2023

ግላኮማ በዓለም ላይ ዓይነ ስዉርነት በማምጣት ከዓይን ሞራ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀስ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ከዓይን ሞራና ዓይን ማዝ በመቀጠል በሦስተኛ ደረጃ ይቀመጣል። በዓይን ሞራ እንዲሁም በዓይን ማዝ የሚመጣን ዓይነ ስዉርነት በቀዶ ህክምና ሰዎች ችግሩ ከመከሰቱ በፊት ወደነበራቸዉ እይታ ወይም ተቀራራቢ የእይታ መጠን መመለስ ሲቻል በግላኮማ ምክንያት የመጣን የእይታ መቀነስ (ዓይነ ስዉርነት) ግን መመለስ አይቻልም። ለዚህም ነዉ የግላኮማ ችግር አሳሳቢና አስጊ የሚሆነዉ። ሥለዚህ የህክምናዉ ዋና አላማ ህመሙ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስና የጉዳቱ መጠን እየከፋ እንዳይሄድ ማድረግ ነዉ። ይህን እዉነታ ችግሩ ያለባቸዉ ወይም ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በደንብ ሊገነዘቡት ይገባል። በተጨማሪም እንደ ዓይን ሞራ በአንድ ጊዜ ህክምና ሊድን የማይችል በመሆኑ ችግሩ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ በሕይወት ዘመን ሙሉ ክትትል ማድረግን ይጠይቃል።

ረዘም ላለ ጊዜ ማለትም በቀን በአማካይ ከ 2 ሰዓት በላይ ኮምፒውተር ወይም ስማርት ፎን ይጠቀማሉ? ወይም ቴሌቪዥን ይመለከታሉ? ወይስ በበረሃማ ቦታዎች አልያም በክፈተኛ ቦታዎች ይኖራሉ? እን...
28/02/2023

ረዘም ላለ ጊዜ ማለትም በቀን በአማካይ ከ 2 ሰዓት በላይ ኮምፒውተር ወይም ስማርት ፎን ይጠቀማሉ? ወይም ቴሌቪዥን ይመለከታሉ? ወይስ በበረሃማ ቦታዎች አልያም በክፈተኛ ቦታዎች ይኖራሉ? እንገዲያውስ ዓይንዎት አደገኛ ለሆነ ልዕለ ሃምራዊ እና ሰማያዊ ጨረር የተጋለጠ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብዎታል፡፡ ጨረሮቹ ምን ዓይነት ጉዳት እንደሚያስከትሉ እና እንዴት መከላከል እና ማከም እንደሚቻል እንዲሁም ሌሎች ከዓይን ጤና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ክሊኒካችን ጎራ ይበሉ፡፡
0920250000

ንስር ቪዥን ስፔሻሊቲ የዓይን ክሊኒክ https://t.me/+uxyNn1780T0yMWU0በዓይን ስፔሻሊስት ሀኪሞች ዶ/ር ዳንኤል ማርየ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ይግዛው ከበቂ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ...
25/02/2023

ንስር ቪዥን ስፔሻሊቲ የዓይን ክሊኒክ
https://t.me/+uxyNn1780T0yMWU0
በዓይን ስፔሻሊስት ሀኪሞች ዶ/ር ዳንኤል ማርየ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ይግዛው ከበቂ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ የዓይን ቀዶ ህክምና ጨምሮ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል
አድራሻ
ባህር ዳር ቀበሌ 07 ሀን ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት
ስልክ 0920250000 ይደውሉ

As the WHO report more than  2.2 billion people have a vision impairment or blindnessWe are ንስር ቪዥን የዓይን ስፔሻሊቲ ህክምና Nisi...
08/02/2023

As the WHO report more than 2.2 billion people have a vision impairment or blindness

We are ንስር ቪዥን የዓይን ስፔሻሊቲ ህክምና Nisir Vision speciality Eye clinic ready for any of eye related treatment
Call 0989298989 /0920250000

ለመጨረሻ ጊዜ ዓይኖትን የተመረመሩት መቼ ነው?አስፈላጊውንስ ክትትል ለዓይኖት ያደርጋሉ?ይምጡና ሁሉን ባሟላው ክሊኒካችን ይመርመሩ፡፡ምቾቶንና ፍላጎቶን ለማሟላት ተዘጋጅተን እንጠብቆታለን፡፡
07/02/2023

ለመጨረሻ ጊዜ ዓይኖትን የተመረመሩት መቼ ነው?
አስፈላጊውንስ ክትትል ለዓይኖት ያደርጋሉ?
ይምጡና ሁሉን ባሟላው ክሊኒካችን ይመርመሩ፡፡
ምቾቶንና ፍላጎቶን ለማሟላት ተዘጋጅተን እንጠብቆታለን፡፡

የስኳር ህመም ሲያጋጥምዎ ገና በለጋ እድሜዎ የዓይን ሞራ ግርዶሽ የመከሰት እድል በእጥፍ ወይም በሦስት እጥፍ ይጨምራል።በደምዎ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ሲጨምር   የዓይን ሞራ ግርዶሽ እንዲ...
02/02/2023

የስኳር ህመም ሲያጋጥምዎ ገና በለጋ እድሜዎ የዓይን ሞራ ግርዶሽ የመከሰት እድል በእጥፍ ወይም በሦስት እጥፍ ይጨምራል።
በደምዎ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ሲጨምር የዓይን ሞራ ግርዶሽ እንዲፈጠር ያደረጋል ።

የዓይን ሞራ ግርዶሽ እንዳይፈጠር ወይም ለማዘግየት የሚመከረው መንገድ የስኳር መጠኖትን በመድሃኒት እና በአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል አልያም ሃኪሞት ጋር በየጊዜው ክትትል በማድረግ እንዲሁም ዓይኖት ያለበትን ሁኔታ በየጊዜው መታየት ይኖርቦታል
ንስር ቪዥን የዓይን ህክምና እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ልምድ ባለው የዶክተር ቡድን አማካኝነት ምርጡን የዓይን እንክብካቤ ድጋፍ፣ ፈጣን ምርመራ እና የላቀ ህክምና እንሰጣለን
https://t.me/+uxyNn1780T0yMWU0
አገልግሎታችንን ለማግኘት ይደውሉ
+25192025000

20/20/20 ህግ ይጠቀሙ
01/02/2023

20/20/20 ህግ ይጠቀሙ

ለዓይነ ስውርነት አጋላጭ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? ሕክምናቸውስ? አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓይነ ስውርነት የሚዳርጉ በርካታ መንስኤዎች  መኖራቸውን ባለሙያዎች ይናገራ...
23/01/2023

ለዓይነ ስውርነት አጋላጭ መንስኤዎች ምንድን ናቸው? ሕክምናቸውስ?

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓይነ ስውርነት የሚዳርጉ በርካታ መንስኤዎች መኖራቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በዚህ ጽሑፍ ለዓይነ ስውርነት ከሚያጋልጡ በርካታ መንስኤዎች መካከል ሥድስቱን አንስተን ከባለሙያ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

በጽሑፉ ውስጥ ስለ ዓይነ ስውርነት ሲነሳ በተፈጥሮ ዓይነ ስውር የሆኑትን ሳይሆን የዕይታ ብርሃን ኖሯቸው በሂደት ብርሃናቸውን የሚያጡትን መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

በአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ክፍል ኃላፊ እና የዓይን ሐኪም ዶክተር ሰሎሞን ቡሳ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የሞራ ግርዶሽ፣ ግላኮማ፣ ትራኮማ፣ አነጣጥሮ የማየት ችግር (ሪ ፋክቲቭ ኢር)፣ የስኳር ሕመም (ዲያቤቲስ) እና ከመደበኛው የመወለጃ ጊዜ ቀድሞ መወለድ ዓይነ ስውርነትን ከሚያስከትሉ በርካታ መንስኤዎች መካከል ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡

1. የሞራ ግርዶሽ

የሞራ ግርዶሽ በተፈጥሮ ከሚመጡ ለዓይነ ስውርነት አጋላጭ መንስኤዎች አንዱ ሲሆን÷ በኢትዮጵያ ከፍተኛው የዓይነ ስውርነት ምክንያት ሆኖ ይጠቀሳል፡፡

ከ15 ዓመታት በፊት የተካሄደ የጥናት ውጤት እንዳመላከተው÷ በኢትዮጵያ ከሚኖረው ሕዝብ ቁጥር 1 ነጥብ 6 በመቶው የዕይታ ችግር አለበት፡፡ አሁን ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡

በጥናቱ ግኝት መሰረት ካለው የዓይነ ስውርነት ምጣኔ 50 በመቶ የዓይነ ስውርነት ምክንያቱ የሞራ ግርዶሽ መሆኑን ጠቁመው÷ ይህም በተፈጥሮ (አብሮ በመወለድ)፣ በአደጋ (ምት) እና በዕድሜ መግፋት ሊመጣ እንደሚችል የስረዳሉ።

የሞራ ግርዶሽን ቀድሞ መከላከል ባይቻልም ከተከሰተ በኋላ ግን በቀዶ ሕክምና ይስተካከላል ነው ያሚሉት፡፡

2. ግላኮማ

ጤናማ የዓይን ግፊት ከ10 እስከ 21 ድረስ ሲሆን÷ ከ21 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኩሪ በላይ ከሆነ ግፊቱ ከፍ ማለቱ ብቻ ሳይሆን በተጓዳኝ የዓይን ነርቭን (ኦፕቲካል ነርቭ) በመጉዳት ዕይታን ይቀንሳል ይላሉ፡፡

ቶሎ ሕክምና ካልተደረገለትም እስከ ዓይነ ስውርነት እንደሚያደርስ ባለሙያው ገልጸዋል።

ግላኮማ በዘር ይተላለፋል፣ ምክንያታቸው በውል ባልታወቁ ሁኔታዎች ይከሰታል፣ አንዳንዴ የዓይን ውስጥ ሕመሞችም ይህን ሊያመጡት ይችላሉ፡፡

ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ስለሌለው ዕይታ ቀስ በቀስ እየቀነሰ ይሄድና ፊት ለፊት ብቻ እንጂ ወደ ጎን ማየት እስከማይቻልበት ደረጃ ያደርሳል ይላሉ ባለሙያው፡፡

ግፊቱ ከፍ በሚልበት ጊዜ ደግሞ የራስ ምታት ያስከትላል፣ በመብራት ዙሪያ እንደ ቀስተደመና የሚመስሉ ቀለማትን ያሳያል፣ ብዥታዎችንም ይፈጥራል፡፡

እንደዚህ በሚሆንበት ጊዜ ተመርምሮ ሕክምና መጀመር ይገባል፤ ሕክምናው ለዕድሜ ልክ የሚሰጥ ሲሆን መቋረጥ የለበትም ይላሉ ዶክተር ሰሎሞን፡፡

የተጎዳውን ነርቭ መመለስ ስለማይቻል ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ግፊቱን ለማውረድ መድኃኒቱ እንደሚሰጥ አስገንዝበው÷ ያለው ዕይታ ባለበት እንዲቆይ (እንዳይጠፋ) ለማስቻል ይህን በማድረግ ዕይታን ማቆየት እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡

3. ትራኮማ

በኢትዮጵያ ዓይነ ስውርነትን ከሚያስከትሉ መንስኤዎች ትራኮማ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝና በጀርም የሚመጣ ሕመም ነው፡፡

ባብዛኛው የውኃ እጥረት ባለበትና ሞቃታማ አካባቢ፣ ዝንቦች በብዛት በሚፈለፈሉበት፣ ሰዎች ትፍግፍግ ብለው በሚኖሩበትና በሚተኙበት፣ ፎጣና የትራስ ጨርቆችን በጋራ በመጠቀም ይከሰታል፤ ይተላለፋልም።

ይህ ሕመም የዓይንን ቆብ ወደ ውስጥ ቆልምሞ ጸጉሩ የዓይን ብሌንን እየፈገፈገ አቁስሎ ጠባሳ በመፍጠር ብርሃን እንዳይተላለፍ በማድረግ ዓይነ ስውርነትን ያስከትላል፡፡

ስለሆነም የአካባቢ እና የግል ንጽህናን በመጠበቅ ቀድሞ መከላከል እና ሕመሙ ከተከሰተ በኋላም ሕክምና በማድረግ በትራኮማ ምክንያት የሚመጣውን ዓይነ ስውርነት ማስቀረት እንደሚቻል ባለሙያው መክረዋል።

4. አነጣጥሮ የማየት ችግር (ሪ ፋክቲቭ ኢር)

ከአነጣጥሮ የማየት ችግር ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ችግሮች ደረጃቸው የተለያየ ሲሆን በመነጽር የመስተካከል ዕድል እንዳላቸው ይታመናል።

በየትኛውም ሰው ላይ ሕመሙ ቢስተዋልም በይበልጥ ልጆች፣ ወጣቶች፣ ተማሪዎች አነጣጥሮ የማየት ችግሮች በከፍተኛ ደረጃ እንደሚታይባቸው መረጃዎች ያመላክታሉ።

ቢያንስ ወደ 7 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆነው የዕይታ ችግር ከአነጣጥሮ የማየት ችግር የሚመጣ መሆኑን ዶክተር ሰሎሞን ተናግረዋል።

እነዚህ ሰዎች ተመርምረው መነጽር ሊታዘዝላቸው እና ዕይታቸውን ማስተካከል የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባም ይመከራል።

5. የስኳር ሕመም (ዲያቤቲስ)

ሌላኛው የዓይነ ስውርነት መንስኤ በአሁኑ ወቅት ከከተማ እስከ ገጠር እተስፋፋ የሚገኘው የስኳር ሕመም ነው፡፡

በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ሳይስተካከል ሲቀርና ከፍ ብሎ በሚገኝበት ወቅት እንደሚከሰት የሚታመነው የስኳር ሕመም፥ በባህሪው የደም ስሮችን ልፍስፍስ የማድርግ እና በቀላሉ እንዲቀደዱና ደም እንዲረጩ የሚያደርግ ነው ይላሉ ባለሙያው።

በመሆኑም ሕክምና ካልተደረገ በዓይን ውስጥ (ረቲና ላይ) ያሉ ቀጫጭን የደም ስሮች በቀላሉ ደም ሊረጩ ይችላሉ፤ ይህን ተከትሎም ዕይታ ሊጎዳና ሊጠፋ የሚችልበት አጋጣሚ ይከሰታል ነው የሚሉት፡፡

ስለዚህ የስኳር ታማሚዎች ሁልጊዜ የደም ስኳራቸውን እንዲስተካከል ሕክምናቸውን መከታተል ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲህ ሲሆን ዕይታቸው ሳይጎዳ ለረጅም ጊዜ ይቆያል ሲሉ ይመክራሉ፡፡

6. ከመደበኛው የመወለጃ ጊዜ ቀድሞ መወለድ

ከመደበኛው የመወለጃ ጊዜ (ዘጠኝ ወር) ቀድሞ መወለድ ለዓይነ ስውርነት ከሚጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል።

ሕጻናት በማህጸን ውስጥ እያሉ ሙሉ ዕድገቱን ያልጨረሰው ብሌን (ረቲና) በሚወለዱበት ጊዜ፥ ደም መርጨት፣ የብሌን መላቀቅ ችግር ያስከትልና ለዓይነ ስውርነት ሊያደርስ እንደሚችል ባለሙያው አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ያለ ጊዜያቸው የሚወለዱ ሕጻናትን ወደ ሕክምና በመውሰድ ዓይናቸው እንዲመረመርና ተገቢው ክትትል መደረግ ይኖርበታል ነው የሚሉት፡፡

ከ15 ዓመታት በፊት በተካሄደ የጥናት ውጤት እንደተመላከተው÷ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖረው ሕዝብ ቁጥር 1 ነጥብ 6 በመቶው ዓይነ ስውር (የዕይታ ችግር ያለባቸው) ናቸው፡፡ አሁን ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡

ለዓይነ ስውርነት በማጋለጥ ሂደታቸው ቅደም ተከተል መሰረትም÷ የሞራ ግርዶሽ፣ ትራኮማ፣ ግላኮማ፣ አነጣጥሮ የማየት ችግሮች፣ የስኳር ሕመምና የተለያዩ ምክንያቶች፣ የሕጻናት የዓይነ ስውርነት ችግሮች ይጠቀሳሉ፡፡

በአብዛኛው የዓይን ሕመም ሕክምና በሀገር ውስጥ ስለሚሰጥ፥ ህብረተሰቡ በዓይኑ ወይም በዕይታው ላይ ዕክል ሳያጋጥመው ቀድሞ ለመከላከሉ ትኩረት እንዲሰጥና ችግሩ ካጋጠመም ጊዜ ሳያባክኑ ወደ ዐይን ሕክምና ተቋም እንዲሔድ ሲሉ ባለሙያው መክረዋል።

ህብረተሰቡ በልማድ ወደ ሕክምና ተቋም የሚሔደው የዕይታ ችግር ሲደርስበት መሆኑን በመጠቆም፥ አንድ ሰው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ቢመረመር የዓይኑን በጤንነት የመቆየት ጊዜ ማራዘም ይቻላል ነው ያሉት።

ምክንያቱም በዘር ሊተላለፉ የሚችሉ የዓይን ችግሮች ስላሉና ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ሳያሳዩ (ለምሳሌ ግላኮማ) ዓይነ ስውርነትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ስላሉ ነው ብለዋል።

በዮሐንስ ደርበው

እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! Happy Epiphany
19/01/2023

እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! Happy Epiphany

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251989298989

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ንስር የመነፅር ስራ Nisir optics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ንስር የመነፅር ስራ Nisir optics:

Share