Apex Medical and Sexual Health Clinic

Apex Medical and Sexual Health Clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Apex Medical and Sexual Health Clinic, Medical and health, Addis Ababa.

13/05/2023

**የወንድ #ብልት ብቃት መጨመሪያ መድሃኒቶች**

የወንድ ብልት ማሳደግያ እና የወሲብ ብቃት ማሻሻያ መድሃኒቶች አብዛኛውን ጊዜ በተጋነነ ማስታወቂያቸው ነው ሚታወቁት ይህም የብልት #ውፍረት መጨመር፣ ማስረዘም ፤ ፍላጎት መጨመር እና ረዥም የወሲብ ጊዜ እንዲያሳልፉ እናደርጋለን ይላሉ
ነገር ግን እንዚህ አብዛኛው የወሲብ ብቃት ማሻሻያ መድሃኒቶች በአሜሪካ የምግብ እና የመድሃኒት ቁጥጥር ተቋም ፍቃድ የሌላቸው ናቸው። ከዝህም አልፎ እነዚህ መድሃኒቶች ያለ ሀኪም ተዕዛዝ ይገዛሉ ለከፍተኛ የጤና ቀውስም ይዳርጋሉ። ከዚህ በተቃራኒ ደሞ ፍቃድ ያላቸው እና በሳይንሱ አለም የተረጋገጡም ይገኛሉ።
#የወሲብ ብቃት መጨመሪያ መድሃኒቶች ምንድን ናቸው?
እነዚህ መድሃኒቶች ወደ ብልት የሚሄደውን የደም ፍሰት በመጨመር ብልት ጥንካሬ እንዲኖረው፣ ለረዥም ሰዐት እንዲቆይ እና የተሻለ የወሲብ እርካታ እንዲኖር እናደርጋለን ይላሉ
#በውስጣቸው ምን ምን ይይዛሉ?
እነዚህ መድሃኒቶች በውስጣቸው #ቫይታሚን፣ ሚኒራል፣አሚኖ አሲድ እና ቅጠላቅጠል ይይዛሉ
የወንድ ብልት ብቃት ማሻሻያዎች ብዙ አይነት ናቸው ከእነዚህም ውስጥ የሚዋጡ ኪኒኖች፣ የሚቀቡ ክሬሞች፣ የሚቀቡ ቅባቶች ወይም ጄል፣ ብልት ላይ የሚገጠሙ ማሽኖች እና የብልት ሰርጀሪ ማድረግ ይገኙበታል።
#የእነዚህ መድሃኒቶች አላማ ምንድን ነው?
የወሲብ ብቃት ማሻሻያ መድሃኒቶች እንሰጣለን ከሚሉት ጥቅም ውስጥ ስንፈተ ወሲብ ለማከም፣ ለግንኙነት ፍላጎት ማነስ፣ ቶሎ በመጨረስ ለሚቸገሩ መፍትሄ አለን ይላሉ።
#ምን አይነት ጉዳት ያመጣሉ?
እነዚህ መድሃኒቶች ለከፍተኛ #የልብ ድካም በማጋለጥ እስከ #ሞት ሊያደርሱ ይችላሉ፤ ሌላኛው ጉዳታቸው ለስትሮክ ሊዳርጉ ይችላሉ ይህም ማለት ወደ አዕምሮ የሚሄደውን የደም ዝውውር በማስቆም ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
በተጨማሪም ከመድሃኒቶች ጋር መጋጨት ከፍተኛ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ ይህም ለምሳሌ የደም ግፍት፣ የልብ ድካም መድሃኒቶችን የሚወሰድ ሰዎች ቢወስድዋቸው ለከፋ የጤና ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ። ከነዚህም ጋር በተያያዘ የመድሃኒቱ ጥገኛ በመሆን (ሱስ) ያለመድሃኒቱ ምንም አይነት ግንኙነት መፈጸም ያለመቻል ሊያጋጥም ይችላል።
#መፍትሄ ምንድነው?
በመጨረሻም እነዚህን መድሃኒቶች ያለ በቂ ምርምራ፣ የጤና ባለሞያ ምክር እና ትዕዛዝ መወሰድ ጉዳቱ ከፍተኛ ሰለሆነ አስፈላጊውን የባለሞያ ድጋፍ በማግኘት እና ፍቃድ ያላቸውን መድሃኒቶች በመጠቀም በጤናማ መንገድ ጤናውን ማግኘት ይችላሉ።
በአካል #ቀጠሮ ለማስያዝ 0948339660

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apex Medical and Sexual Health Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram