06/10/2023
#እርጉዝ ለመሆን ምን ያህል ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አለብዎት?
ምናልባት እድለኛ ከሆኑ በመጀመሪያ ሙከራዎ ሊያረግዙ ይችላሉ። ነገር ግን ለአንዳንድ ጥንዶች ተጨማሪ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል። ታዲያ በሚያስገርም ሁኔታ ሳይንስ ጥንዶች በተደጋጋሚ ወሲብ ቢፈፅሙ የማርገዝ እድላቸውን ማስፋት ይችላሉ ይለናል።
ለመፀነስ እየሞከሩ ነው? እንግዲያውስ እርጉዝ የመሆን እድልን ሊጨምሩ ወይም ሊቀንሱ የሚችሉ አንዳንድ ምክንያቶች አሉ። ቶሎ ማርገዝ ከፈለጉ፤ መቼ እና ምን ያህል ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ እንዳለብዎ ማወቅ አስፈላጊ ነው ይላሉ ባለሙያዎች።
ጥናቱ እንደሚለው ከሆነ ሰውነትዎ ለመፀነስ ዝግጁ በሆነበት ጊዜ ተደጋጋሚ ወሲቦችን መፈፀም የማርገዝ እድልን ይጨምራል። ጥናቱ እንዳመለከተው ባለትዳሮች በመጨረሻ ውጤቱን ከማግኘታቸው በፊት በአማካይ 78 ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይፈጽማሉ።
ይሄ ቁጥር ከ158 ቀናት አልያም 6 ወራት ድረስ ይችላል። ባለሙያዎች በጥናት አገኘነው ያሉት መረጃ አብዛኞቹ ባለትዳሮች ለመፀነስ ሲሞክሩ በወር 13 ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንደፈፀሙ ያሳያል።
ሆኖም ግን ይላሉ ባለሙያዎቹ፤ ሆኖም ግን በዙ ጊዜ የግብረስጋ ማድረግ እንደሚታሰበው ያክል አስደሳች አይደለም ይልቁንስ አንዳንድ ባለትዳሮች ለማርገዝ ተብለው የሚደረጉ የግብረስጋ ግንኙነትን እንደስራ እንደሚቆጥሯቸው አምነዋል።
ይባስ ብሎ አንዳንድ ባለትዳሮች መፀነስ እንደማይችሉ በመፍራት እንደ ግፊት ይወስዱታል። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ባለሙያዎቹ ምንም እንኳን ልጅ ለማግኘት እየሞከራችሁ ቢሆንም አንዳችሁ ስለአንዳችሁ ግን ማሰብ ማቆም የለባችሁም በማለት የሚመክሩት።
☑️ ወሲብ ለመፈፀም የወሩ ተመራጭ ጊዜ
የማርገዣ ወቅት ማለት ሴቶች ፅንስ ለመያዝ ዝግጁ የሚሆኑበት ወቅት ሲሆን በዚህ ጊዜ የሚደረግ ወሲብም እርግዝናን የመፍጠር እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ይህ የመዳበር ወቅት እንቁላል ከሚፈጠርባቸው አምስት ቀናት ቀደም ብሎ አልያም የእንቁላል መፈጠሪያ ቀንን ያጠቃልላል።
ከእንቁላል ማምረት ቀን ሁለት አልያም 3 ቀናት ቀደም ብሎ ወይንም በአንቁላል መመረቻ ቀን ወሲብ መፈፀም እርግዝና የመፈጠር እድሉን ከፍተኛ ያደርገዋል። እንቁላል ከኦቫሪ ከተለቀቀ በኋላ እንቁላሉ ከ12 እስከ 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ነው ማዳበር የሚችለው።
በሌላ በኩል የወንዱ ዘር በሴት የመራቢያ ሥርዓት ውስጥ እስከ አምስት ቀናት ሊቆይ ይችላል። እርጉዝ ለመሆን በሚሞክሩበት ጊዜ ሳይሆን ከዚያም በፊት ባለሙያዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አለብዎት የሚሉበት ምክንያትም ይህ ነው።
☑️ ግብረ-ሥጋ የመፈፀሚያ መንገድ
ጥቂት ሰዎች ወሲብ የሚፈፀምበት መንገድ በራሱ እርጉዝ የመሆን እድልን ሊወስን ይችላል ብለው ያምናሉ። በበርካታ ጥንዶች የሚታወቁት ወሲብ የመፈፀሚያ መንገዶች መካከል ወንድ ከሴቷ ላይ አልያም ከኋላ ሆኖ የሚፈፅምባቸው ዘዴዎች እጅግ ይታወቃሉ።
ጥንዶችም እንደሚሉት ከሆነ እነዚህ ወሲብ የመፈፀሚያ መንገዶች የወንድ ዘር በሴቷ የመራቢያ አካል ውስጥ ተጉዘው የዳበሩ እንቁላሎችን እንዲያገኙ በማስቻል ደረጃ የሚወዳደራቸው የለም። ነገር ግን እነዚህ ወሲብ የመፈፀሚያ መንገዶች በሳይንስ የተረጋገጠ አለመሆናቸውን ልብ ይሏል።
በነገራችን ላይ እስካሁን ካስነበብናች በሚፃረር መልኩ አንዳንድ ባለሙያዎች በቀን ከአንድ በላይ ወሲብ መፈፀም የወንድ ዘር ወሲብ የመፈፀም አቅሙን ያዳክመዋል ብለው ያስባሉ።
ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ከሆነ ማርገዝ የፈለጉ ጥንዶች በሳምን ቢያንስ 3 አልያም 4 ጊዜ ወሲብ ለመፈፀም ቢያልሙ አወንታዊ ለውጥ ሊያዩ ይችላሉ፡፡ በበርካታ ጥናቶች መሠረት በየሁለት ቀኑ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ጥንዶች ከፍተኛ የመፀነስ እድል አላቸው።