09/11/2023
የአእምሮ ህመም የሰው ልጅ ከሚገጥመው የህመም አይነት አንዱ ሲሆን ይህ ህመም የሰውን ባህሪ፣አስተሳሰብ፣ስሜት የሚጎዳ ህመም ነው።ከዚህ የተነሳ የዚህ ህመም ተጠቂ የሆነ ሰው በስራው ፣በቤተሰብና በማህበራዊ ህይወቱ ላይ ችግር ይገጥመዋል።
የአእምሮ ጤና መታወክ ምልክቶች
-የሰውነት ንፅህና አለመጠበቅ
-እንቅልፍ ማጣት ወይም መብዛት
-ከመጠን ያለፈ ክብደት መጨመር ወይም መቀነስ
-የትምህርት ወይም የስራ ብቃት ማነስ
-ያልተለመደ የባህሪ ለውጥ ለምሳሌ ቶሎ መበሳጨት ፣ማዘን ወይንም መጨነቅ
-ስለሞት ማውራት!!!!
-ራስን ለማጥፋት ማሰብ ወይም መሞከር
-ሌላን ሰው ለመጉዳት ማሰብ ወይም መሞከር
-በባልና ሚስት ወይም ፍቅረኛሞች መሀል ሀይል የታከለበት ግጭት ወይም ፀብ
-ከመጠን በላይ መደሰት ወይም ማዘን
-እራስን መጠበቅ ወይም ማስተዳደር አለመቻል እና የመሳሰሉት ለአእምሮ ጤና መታወክ ምልክቶች ናቸው።
የአእምሮ ህመም ከሌላው አካላዊ ህመም የሚለይበት ምክንያት ህመምተኛው ግለሰብ በሚታመምበት ወቅት "እዚህ ቦታ ላይ አሞኛል" ብሎ ከመናገር ይልቅ ለየት ያለ የባህሪ ፣የስብዕና ፣የአስተሳሰብ፣ወይንምየስሜት ለውጥ እያመጣ መሄዱ ነው።
ጤናማ አእምሮ ለጤናማ ኑሮ!!!!
እምነት ታደለ(የአእምሮ ህክምና ባለሙያ)
ይቀጥላል....