Ethiopian Medical Association

Ethiopian Medical Association The Ethiopian Medical Association (EMA) is a membership organization representing Medical Doctors registered to practice in Ethiopia.

ዛሬ የአለም የስትሮክ ቀን ነው ስለስትሮክ ጥሩ ግንዛቤ ለማግኘት እንዲችሉ ከዚህ በታች ያለውን በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ALERT Comprehensive Specialized...
29/10/2025

ዛሬ የአለም የስትሮክ ቀን ነው

ስለስትሮክ ጥሩ ግንዛቤ ለማግኘት እንዲችሉ ከዚህ በታች ያለውን በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ALERT Comprehensive Specialized Hospital የተዘጋጀውን ቪዲዮ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል፡፡ በዚህ ቪድዮ ዶ/ር ክብርተ ጸጋዬ በ አለርት ሆስፒታል የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት ስለ ስትሮክ በሽታ መንስኤ ፣ ህክምና እና ምልክቶች ያስረዱናል።

እንዲሁም ከዚህ በታች የተቀመጡትን ዝርዝር ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ፡፡

- ለስትሮክ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድናቸው?
- እንዴትስ መከላከል እንችላለን ?
- የስትሮክ ምልከቶች ምንድን ናቸው ?
- ቀድሞ ስትሮክ ያጋጠመው ሰው ተመልሶ ጤናማ ህይወትን መምራት ይችላል?
- የመዳን ሂደቱን የሚወስኑ ነገሮችስ ምንድናቸው የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችም ተካተዋል፡፡

የራስዎንና የቤተሰቦን ጤና ይጠብቁ፡፡

የስትሮክ በሽታ መንስኤ ህክምና እና ምልክቶች /ዶ/ር ክብርተ ጸጋዬ የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት/አለርት ሆስፒታል

ሄፓቶሴሉላር ካርሲኖማ (HCC)፡ የዝምተኛው ገዳይ ማንነትሄፓቶሴሉላር ካርሲኖማ (HCC)፣ በተለምዶ የጉበት ካንሰር በመባል የሚታወቀው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ትልቅ የጤና ችግሮች መካከል አ...
27/10/2025

ሄፓቶሴሉላር ካርሲኖማ (HCC)፡ የዝምተኛው ገዳይ ማንነት

ሄፓቶሴሉላር ካርሲኖማ (HCC)፣ በተለምዶ የጉበት ካንሰር በመባል የሚታወቀው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ትልቅ የጤና ችግሮች መካከል አንዱ ነው። ይህ ችግር በአገራችን ካለው የሄፓታይተስ ቫይረስ (በተለይ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ) ከፍተኛ ስርጭት ጋር የሚዛመድ ነው።
ከሄፓታይቲስ ጋር ያለው ግንኙነት፡- በሄፓታይተስ ቫይረስ ከተጠቁ ታካሚዎች በየዓመቱ 20% የሚሆኑት ችግራቸው ወደ HCC (የጉበት ካንሰር) የመሸጋገር አደጋ አለው።
ዋናው ፈተና የካንሰሩ ባሕርይ ነው፡- HCC ገና በመጀመርያ እና ሊድን በሚችልበት ደረጃ ላይ እያለ ብዙ ጊዜ ምንም ምልክት አያሳይም። በአገራችን ውስጥ የተደራጀ የቅድመ ካንሰር (screening) ፕሮግራም አለመኖር ሲታከልበት፣ በሽታው ወደ ከፍተኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ሳይታወቅ ይቆያል። ለዚህም ነው HCC (የጉበት ካንሰር) "ዝምተኛው ገዳይ" ተብሎ የሚጠራው።
ዋናው መልዕክት እና መፍትሔው:

ቅድመ ምርመራ ሕይወት አድን ነው: HCC በጊዜ ከታወቀ 'ሊቆረጥ' (በቀዶ ህክምና ሊወገድ) እንደሚችል ከተረጋገጠ፣ የቀዶ ጥገና ሕክምና ለታካሚው ተመራጭ እና ሙሉ በሙሉ የመዳን ዕድል የሚሰጥ ሕክምና ነው።
ከሚያስፈልጉ ርምጃዎች ውስጥ፡ ወደ ካንሰር የሚወስደውን ሂደት ለመከላከል የሄፓታይተስ ቫይረስን በተመለከተ ግንዛቤ መፍጠር፣ የቅድመ ካንሰር ምርመራ በየጊዜው ማድረግ እና ካንሰር ሲከሰት ተገቢውን ሕክምና በጊዜው ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

Hepatocellular Carcinoma (HCC): Unmasking Ethiopia's Silent Killer

Hepatocellular Carcinoma (HCC), the most common form of liver cancer, is a critical public health challenge in Ethiopia. This is not just a medical statistic—it is a reflection of the high prevalence of chronic viral hepatitis (Hepatitis B and C) that our country faces.
The link is stark: Approximately 20% of patients living with chronic viral hepatitis are at risk of developing HCC annually.
The major hurdle is its nature: HCC is often asymptomatic in its early, curable stages. Coupled with the absence of a structured national screening program in Ethiopia, this means the disease frequently goes undetected until it has progressed significantly. This is precisely why HCC is tragically nicknamed as "silent killer."
The Critical Takeaway:

Early Detection is Life-Saving: When HCC is caught early and remains resectable (meaning it can be surgically removed), surgical management offers the best chance for a curative outcome.
The Need for Action: We must prioritize efforts to increase awareness, screening, and effective management of chronic viral hepatitis to prevent this progression to cancer and managing HCC timely are vital.



Dr. Wuletaw Chane Zewude

ዶ/ር ፈቀደ አግዋርልዩ ተሸላሚ************በአዲስ አበባ ከተማ መሳለሚያ፤ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ነው የተወለዱት፡፡ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሰላም በር አንደኛና መለ...
25/10/2025

ዶ/ር ፈቀደ አግዋር
ልዩ ተሸላሚ
************
በአዲስ አበባ ከተማ መሳለሚያ፤ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ነው የተወለዱት፡፡ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሰላም በር አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና በአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡
የመጀመሪያ የህክምና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን የጎንደር ህክምና ሣይንስ ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን የአጠቃላይ ቀዶ ጥገና ትምህርታቸውን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተከታትለዋል፡፡ የልብ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ደግሞ በህንድ አገር ተምረዋል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በፊዚዮሎጂ መምህርነት እና በቀዶ ጥገና ረዳት ፕሮፌሰርነት አገልግለዋል፡፡ በደምቢ ዶሎ ሆስፒታል የአጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም በመሆን ያገለገሉ ሲሆን አሁን ድረስ በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል የአዋቂዎች እና የህፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪም ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡
በሀገራችን የመጀመርያውን ልብና ሳንባን ተክቶ የሚሰራ ማሽንን በመጠቀም (Heart Lung Machine) የልብ ቀዶ ጥገናን አስጀምረዋል፡፡ ዛሬ ላይ ከ1000 የሚበልጡ ጨቅላ ህፃናትና አዛውንቶችን የተሳካ የልብ ቀዶ ጥገናዎችን ሰርተዋል።
በሚሰሯቸው ቀዶ ጥገናዎች ላይ በማተኮርም ከ15 ያላነሱ ሳይንሳዊ የምርምር ፁሑፎችን በመጻፍ በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል። “የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ” በሚል ርዕስም በአማርኛና በእንግሊዘኛ መጽሐፍ ጽፈው አበርክተዋል።
በሀገራችን የተንሰራፋውን የRheumatic የልብ በሽታ ጫና ለመቀነስ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የሚል ግብረ ሰናይ ድርጅት አቋቁመው ከፍለው መታከም የማይችሉ ታዳጊ ህመምተኞችን ቀዶ ጥገና እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ አሁን ላይም ለ40 ታዳጊዎች የነፃ የልብ በር ቀዶ ጥገና አድርገዋል።
ዶ/ር ፈቀደ አግዋር፤ በጤና ሙያ መስክ ላበረከቱት የላቀ ልዩ ስራና የሙያ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ልዩ ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎበተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት*************በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሜጋ ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ድሬ ወረዳ ሜ...
25/10/2025

ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ
በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት
*************
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሜጋ ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ድሬ ወረዳ ሜጋ ከተማ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞያሌ፣ ነገሌ ቦረና ተከታትለዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጤና ሳይንሰ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ በህክምና ዶክትሬት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን ከአዳማ ህክምና ኮሌጅ፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዓለም አቀፍ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር (Global Health Supply Chain Management) ከኪንቲ ስቴት እና ኢንፓዎር ስኩል ኦፍ ኸልዝ ከሱዊዘርላንድ እንዲሁም በዓለም አቀፍየህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ከፍተኛ ሰርተፊኬት ከዋሽንግተንዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል።
ሙያዊ ጉዟቸውን የጀመሩት በቦረና አርብቶ አደር አካባቢ ሲሆን በቂ መሠረተ ልማት በሌላቸው አከባቢዎች በበጎ ፍቃደኝነት ለማገልገል ራሳቸውን በፈላጎት አሬሮ ወረዳ መደብ። የአሬሮ ወረዳ በሙያቸው፣ በጤና ጣቢያ ኃላፊ፣ የድሬ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት እና የቦረና ዞን ጤና መምሪያን ጨምሮ በባለሙያነትና በኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመምህርነት፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በመሆንም ሰርተዋል። በክልሉም የተለያዩ አሰራሮችን በኪልንካል እና በጥራት የሰሩ።
በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት አዳዲስ ሃሳቦች በማመንጨትና በመተግበር አርአያ መሆን የቻሉ ናቸው፡፡ ከ5 የሚበልጡ ጥናታዊ ጽሁፎችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል። ቀጥተኛ የጤና ተቋማትን የመድኃኒት አቅርቦት ከ30 በመቶ ወደ 69 በመቶ በማስፋት፣ ለአመታዊ ቆጠራ እስከ 45 ቀናት መጋዘኖች ተዘግተው ተገልጋዮች ይጉላሉበት የነበረውን አሰራር በመቀየር በአማካኝ ከ5 ቀናት በታች እንዲሆን የሰሩ።
ተቋሙ ከሀገር ውስጥ አልፎ በአካባቢያችን ካሉ አቻ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል በተበጣጠሰ መልኩ ሲተገበር የነበሩ የቴክኖሎጂ ስርዓትን በማዘመን እና የተናበበ እንዲሆን ለማስቻል ዓለም የደረሰበት የመጨረሻውን የቴክኖሎጂ መፍትሄ ERP-SAP የተባለውን አሰራር ዘርፈ ብዙ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር እና በማቀናጀት ሥራ ላይ እንዲውል ሌት ተቀን የተጉ፣ በፖሊሲ ማሻሻያና ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የአቅራቢዎች ኮንፈረንስ የአገር ውስጥ አምራቾችን ሚና እንዲጠናከር አድርገዋል።
ለኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል አገልግሎት አለም አቀፍ እውቅናን አምጥቷል። የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ISO የጥራት ሰርተፍኬት እንዲያገኝ አድርገዋል፡፡በደረጃ ቀይ የነበረውን የከሰታም ኮምሸን ደረጃ በማሻሻለ‍እ ለሶስት ተከታታይ አመታት የፕላቲኒየም ታማኝ ታክስ ከፋይነት ደረጃን በማግኘት እና እ.ኤ.አ በ2024 የአለም ጤና አቅርቦት ሰንሰለት ጉባኤ ላይ ከ39 ሀገራት ጋር በመወዳደር የታላቁን (Grand Prize) ሽልማት አሸንፈዋል።
እ.ኤ.አ. ከ2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እያገለገሉ የሚገኝ ሲሆን በርካታ የአስተዳደር ቦርዶች እና የብሔራዊ ፖሊሲ ቡድኖች አባል በመሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በጤናው ዘርፍ በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዎ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

ዶ/ር መረርቱ ተመስገን በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት ተሸላሚ************* የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር  የቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር መረርቱ ተመስገን በኦሮሚያ ክልል በነ...
25/10/2025

ዶ/ር መረርቱ ተመስገን
በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት ተሸላሚ
*************
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር መረርቱ ተመስገን በኦሮሚያ ክልል በነቀምት ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በኪዳነ ምሕረት ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአ/አ ከተማ ቤተል መካነ ኢየሱስ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡
የመጀመሪያ የሕክምና ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርስቲ፣ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊቲ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡ እንዲሁም በህፃናት ድንገተኛና ፅኑ ህሙማን ህክምና ሰብ ስፔሻሊቲን በአሜሪካና በህንድ ሀገራት አጠናቀዋል፡፡
በአምቦ ሆስፒታል በጠቅላላ ሀኪምነት፣ በየካቲት 12 ሆስፒታል የሕፃናት ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊና ምክትል ፕሮቮስት በመሆን አገልግለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ቦርድ አባል እንዲሁም የምስራቅ፣ የመካከለኛው እና የደቡብ አፍሪካ የህፃናት ህክምና እና የህፃናት ጤና ኮሌጅ የመስራቾች አባል ናቸው፡፡ በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተባባሪ ኘሮፌሰር ማዕረግ በሕፃናት ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስትነት እንዲሁም በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
ካበረከቷቸው አስተዋፅኦዎች መካከልም የጤና ስርአት ተኮር የስፔሻሊቲ ትምህርት ማስፋፋትና ማጠናከር፣ የተለያዩ መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ የሕፃናት የሕክምና አገልግሎት የማሻሻያ ሥራዎች፣ በሕፃናት የቃጠሎ ሕክምና ሂደት፤ በህፃናት የላንቃ መሰንጠቅ የሕክምና አልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል የሰሯቸው ስራዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በርካታ አጫጭር ስልጠናዎችን የተከታተሉ ሲሆን የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችንም ሰርተዋል፡፡
በአቢሲኒያ የሊደር ሺፕ አዋርድ የተሰጣቸው እውቅናን ጨምሮ በርካታ እውቅናዎች ተበርክቶላቸዋል፡፡
ዶ/ር መረርቱ ተመስገን፤ በጤናው ዘርፍ በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዎ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

ዶ/ር አህመድ መሐመድበህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት**************በሐረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሐረር ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር ከተማ...
24/10/2025

ዶ/ር አህመድ መሐመድ
በህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት
**************
በሐረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሐረር ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር ከተማ ቤተልሄም ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወንጂ ቁጥር 2፣ በአዳማ አፄ ገልውዲዎስ እና በሐረር ተከታትለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ እና የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊቲ ትምህታቸውን ተከታትለዋል፡፡
ለ35 አመታት በዋርዴር ጤና ጣቢያ፣ በቀብሪ ደሀር ሆስፒታል፣ በጎዴ ሆስፒታል በባለሙያነትና በሃላፊነት እንዲሁም በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ ቁጥጥር እና የመከላከል ክፍል እንዲሁም በካራማራ ሆስፒታል በሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስትነት ሰርተዋል፡፡ አሁን በጂጂጋ ዩኒቨርሲቲ ሼኽ ሀሰን የቤሬ ቲቺንግ ሆስፒታል በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
ዶ/ር አህመድ መሐመድ፤ በህይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

ዶ/ር ፈቃደ የራክሊየህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት************በአዲስ አበባ ከተማ ሽሮሜዳ አካባቢ ነው ተወለዱ፡፡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአምሃ ደስታ እና በመነን...
24/10/2025

ዶ/ር ፈቃደ የራክሊ
የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት
************
በአዲስ አበባ ከተማ ሽሮሜዳ አካባቢ ነው ተወለዱ፡፡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአምሃ ደስታ እና በመነን ትምህርት ቤቶች ተምረዋል፡፡
የህክምና ትምህርታቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና ዶክትሬት ተመርቀዋል፡፡ የስፔሻላይዜሽን ትምርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በስነ-ደዌ ተከታትለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይርጋ ጨፌ ጤና ጣቢያ፣ በዲላ ሆስፒታል፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና እና በመምህርነት ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት አገልግለዋል።
በስራ ቆይታቸውም 20 የህክምና ተማሪ ባቾችን አስተምረው በማስመረቅ፣ በቀድሞ በደቡብ ክልል የመጀመሪያውን የፓቶሎጂ ላቦራቶሪና የስፔሻላይዜሽን ፕሮግራም ስራ እንዲጀመር አስተዋጽኦ አድርገዋል፣ የሂስቶፓቶሎጂ አገልግሎት፣ የስነ-ህዋስ ምርመራና የደም ናሙና ምርመራ እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ በተጨማሪ የፓቶሎጂ እና የፕሪ ክሊኒካል የትምህርት ክፍል ኃላፊም ሆነው አገልግለዋል፡፡
ዶ/ር ፈቃደ የራክሊ፤ በህይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ የሙያ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

ዶ/ር ኮከብ መሐመድየህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ*************በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ በደደር ወረዳ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማና...
24/10/2025

ዶ/ር ኮከብ መሐመድ
የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ
*************
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ በደደር ወረዳ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማና በአዲስ አበባ ተምረዋል፡፡ የህክምና ዲግሪያቸውን ከጎንደር ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ የማህፀንና ፅንስ ህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
ከ38 ዓመት በላይ በተሻገረው የስራ ልምዳቸው በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር፤ በህይወት ፋና ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ህክምና ክፍል ኃላፊ፤ በደደር ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር፣ በሐረር ጀጎል ሆስፒታል፤ በፖሊስ ሆስፒታልና በሐረር ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በባለሙያነት እና በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን በተለያዩ ሆስፒታሎችና የህክምና ኮሌጆች ሃላፊና የቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በሀገር ውስጥና በውጭ ሃገራት በርካታ ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ሰርተዋል፡፡
በምስራቅ ኢትዮጵያ የመካንነት ችግርን ለመቅረፍ እና የእናቶችን የመውለድ ጥያቄ ለመመለስ የበኩላቸውን አስተዋፅዎ አድርገዋል፡፡ በዚህም ከ15,880 በላይ እናቶች ልጅ ወልደው እንዲስሙ ሙያዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፡፡
ዶ/ር ኮከብ መሐመድ፤ በጤናው ዘርፍ በህይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ የሙያ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ለምን አታደርጊም? ምንም ገንዘብ ሳታወጪ- ለአንቺ ብሎ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ባዘጋጀው ነጻ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ ትችያለ...
22/10/2025

የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ለምን አታደርጊም?

ምንም ገንዘብ ሳታወጪ- ለአንቺ ብሎ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ባዘጋጀው ነጻ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ ትችያለሽ፡፡

🌸 Free Breast Health Screening! 🌸

Ladies, your health matters!

Join SPHMMC for a free breast screening and learn about early detection and prevention. Don’t miss this opportunity to take care of yourself!

📅 Date:Oct 25 –Nov 01 (ጥቅምት 15 - 22)
📍 Location: St. Paul's Hospital Millennium Medical College-SPHMMC
⏰ Time: 03:00- 10:00 Local time

📢 Join Our Upcoming EMA Webinar!✨ Topic: From Preparation to Success: A practical Roadmap to Program Accreditation🗓Date:...
22/10/2025

📢 Join Our Upcoming EMA Webinar!

✨ Topic: From Preparation to Success: A practical Roadmap to Program Accreditation

🗓Date: October 24, 2025

🕑 Time: 3:00PM (9:00 - 10:00 Local time)

🗞 CEU: 1.5

👨🏽Presenter:

Aboneh Tesfaye
Accreditation Expert, Acting Desk for Program Accreditation Education & Training Authority (ETA)

👨🏽Moderator :

Dr.Natnael Abebe
Assistant Professor of Obstetrics and Gynecology at Bahir Dar University, College of Medicine and Health Sciences, External Assessor of Program Accreditation

👉 Register Now: https://forms.gle/7W52yH7useWc5UZJ8

አሳዛኝ ታሪክ ከአማኑኤል ሆስፒታል ዶ/ር ዮናስ ላቀው እንደጻፈው =================================='ራውንድ' እያደረግን ነው። አዲስ የገቡ ሶስት ታካሚዎች አሉ። ሁለቱን ...
20/10/2025

አሳዛኝ ታሪክ ከአማኑኤል ሆስፒታል
ዶ/ር ዮናስ ላቀው እንደጻፈው
==================================
'ራውንድ' እያደረግን ነው። አዲስ የገቡ ሶስት ታካሚዎች አሉ። ሁለቱን ካናገርኩ በኃላ የሶስተኛው ተራ ሲደርስ ሲስተር 'መምጣት አይችልም' አለችኝ። ያለበት ላየው ሄድኩኝ። ጉልበቶቹ ታጥፈው ይንፏቀቃል፤ መራመድ አይችልም። እግሮቹ ሰልለዋል። ስለህመሙና ስለህክምናው ተነጋገርን። ለምን መራመድ እንደማይችል ግን ሊነግረኝ አልፈለገም። ለተጨማሪ መረጃ እናቱን ማናገር ጀመርኩኝ።

ሁለት ወንድ ልጆች እንደነበሯቸውና አንደኛው ልጃቸውና ባለቤታቸው ከብዙ ጊዜ በፊት እንዳረፉ ነገሩኝ። ብቸኛ ልጃቸው ህመም የጀመረው ከአምስት አመት በፊት እንደነበረና የተለያዩ የባህል ህክምና እንደሞከሩለት ነገሩኝ። ነገር ግን ብዙ ለውጥ እንዳልነበረውና ህመም መሆኑን ባለማወቃቸው ወደ ህክምና እንዳልወሰዱት ነገሩኝ። ይጠፋብኛል ብለው ሰግተው ቤት ውስጥ ለአራት አመታት አስረው እንዳስቀመጡትና በዚያ ምክኒያት መራመድ እንደማይችል ሲናገሩ አይናቸው እንባ አቀረረ። ከአንድ አመት በፊት ሰዎች 'ለምን ህክምና አትወስጂውም?' ብለውኝ ነበር። እኔም ለመውሰድ አስቤ ነበር። ነገር ግን በአቅራቢያችን የአእምሮ ህክምና የለም። እዚህ ለመምጣት ደግሞ አቅም የለኝም። አሁን ራሱ የመጣነው ጎረቤት ገንዘብ ሰብስቦልን ነው። አሉ።
'የሚታከም መሆኑን ባውቅ ኖሮ ልጄን እንዲህ አላደርግውም ነበር።' አሉ። እንባቸው መውረድ ጀመረ። በእናት አንጀት የሚሰማቸውን ሀዘንና ፀፀት ሳስበው ውስጤ ተረበሸ። ሶፍት ከኪሴ አውጥቼ አቀበልኳቸው።

ያን ቀን ከስራ ሰወጣ የአእምሮ ህመም ግንዛቤ የተስፋፋ ቢሆን፣ ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ቢኖር የልጃቸው ሁኔታ እንዴት የተለየ ሊሆን እንደሚችል እያሰብኩ ነበር።
የአእምሮ ህክምና ግንዛቤን መፍጠር የሁላችንም ሀላፊነት ነው። መንግስት ደግሞ የአእምሮ ህክምና ተደራሽ እንዲሆን የማድረግ ሀላፊነት አለበት።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም

A Farewell to the Dearest Son of Hawassa and Giant of the ORIn Loving Memory of Professor Amezene TadesseDear Members of...
16/10/2025

A Farewell to the Dearest Son of Hawassa and Giant of the OR
In Loving Memory of Professor Amezene Tadesse

Dear Members of the Ethiopian Medical Association – Hawassa Chapter, and the wider medical community,

As many of you are already aware, our beloved colleague and mentor, Professor Amezene Tadesse, has passed away. We would now like to share the details of his upcoming funeral ceremony.

Professor Amezene was a deeply respected pediatric surgeon and teacher whose contributions to medicine in Ethiopia have left a lasting legacy. He will be remembered not only for his clinical excellence but also for his humility, dedication, and the many lives he helped shape.

We invite all colleagues, students, healthcare professionals, and friends to join us in honoring his life and work.

The funeral ceremony will take place on Friday, October 17, 2025, at 3:00 PM at Hawassa St. Gabriel Monastery.

Let us gather to pay our final respects to a remarkable physician, educator, and true son of Hawassa.

With sympathy and respect,
Dr. Kindie Woubshet
President, EMA – Hawassa Chapter

Address

Kirkos Sub-City Rosvelt Street, Infront Of Africa Union Main Gate
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:30
Tuesday 09:00 - 17:30
Wednesday 09:00 - 17:30
Thursday 09:00 - 17:30
Friday 09:00 - 17:30

Telephone

+251115521776

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Medical Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethiopian Medical Association:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram