MedInfo Ethiopia

MedInfo Ethiopia Provides drug and medical information for patients, caregivers and healthcare professionals.

በ ዚህ ገፅ ላይ በ አማርኛ እና በእንግሊዘኛ የሚዘጋጁ፡ ወቅታዊ እና ታማኝ የመድሃኒት እና የጤና መረጃዎች፤ ክሊኒካል ፋርማሲ ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች፣ ትምህርቶች እና ውይይቶችን፤ ፋርማሲነክ ቀልዶችንም ያገኛሉ፡፡ በመድሃኒት ዙሪያ ላይ የሚነሱ ማንኛውንም ዓይነት ሃሳቦች እና ጥያቄዎችን እንቀበላለን፤ ፈጣንም መልስ እንሰጣለን፡

አፅድቶ መልሶ ለመጠቀም
02/04/2020

አፅድቶ መልሶ ለመጠቀም

13/03/2020

"የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ዘዴዎች"

● ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ

● እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ

● ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣

● እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣

● ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣

● በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም
ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው
ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣

● በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣

● መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና
ፍርሀት ይከላከሉ!

የበለጠ መረጃ ሲያስፈልግ ነጻ በሆነው 8335 የስልክ መስመር ላይ መደወል ይቻላል፡፡

***

ለጥንቃቄ

ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ!

የምትችሉ ሁሉ የፀሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡

በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡

በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ፀሐይ ላይ ብታሰጧቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡

From different sources

18/02/2020

ስኳር በሽታ
የህመም ምልክቶች፥
– በተደጋጋሚ መሽናት
– ክፉኛ የሆነ የውሃ ጥማት
– የሽንት ቱቦዎች መመረዝ
– ድካም
– የቁስል በደንብ አለመዳን

አንዳንድ መንስኤዎች፥
– በምግብዎ ውስጥ ብዙ ስኳር መኖር
– በዘር

በሚገባ ተደርጎ እንክብካቤ ካልተደረገለት፣ ሊታዩ የሚችሉ የረጅም ግዜ ውጤቶች፥
– የዓይን መታወር
– የእግር የደም ዝውውር መቀነስ፣ ብሎም ለእግር መቆረጥ መዳረግ
– ከሚገባ በላይ ክብደት መጨመር
– ራስን የመሳት ስሜቶች
– ግር ማለት፣ ብስጭት፣ ቆጣ ማለት

21/06/2019

Post-pill ፡ key facts and warning

መጠቀም የሚያሰፈልግባቸው ሁኔታወች (when to use post-pill )

1. ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ሲፈጸም(unprotected s*x)
2. ያልተፈለገ እርግዝና ለመከላከል(unwanted pregnancy )
3. በኮንዶም ወሲብ ሲፈጸም ኮንዶም ከተቀደደ(condom broke during s*x)
4. ወሲባዊ ጥቃቶች ሲፈጸሙ(s*xually assaulted)

አወሳሰድ (how to take the pill)
1. ጾታዊ ግንኙነት በተደርገ በ 72 ሰዓት ውስጥ መድሃኒቱን መውሰድ (Take the pill within 72 hours of having s*x)
2. በቶሎ ሲወስዱት የመሥራት እድሉ የተሻለ ነው(The sooner you take it, the better the chance of it working)

 የጎንዮሽ ጉዳት (Side effect)
 ማቅለሽለሽ (Nausea )
 ጡት ህመም (Sore breast)
 የራስ ምታት (Headache)
 የሆድ ህመም (Abdominal pain)

መስጠንቀቂያ (Warning)

 Post-pill ለድንገተኛ ጊዜ የወሊድ መከላከያ ብቻ የሚጠቀም ሲሆን በጾታ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን አይከላከለም(The morning after pill is for emergency contraception only. It doesn't protect against s*xually transmitted disease).
 በተደጋጋሚ መጠቀም አይመከርም (frequent use of post-pill is not advisable)

NB: Every information we provide through online will not replace the doctor/healthcare provider instead it is an information. Contact your healthcare provider for further information

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MedInfo Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to MedInfo Ethiopia:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram