Medical Information

Medical Information በዚህ ገጽ ጤናን የተመለከቱ የሥራ ማስታወቂያዎች፤ ሕይወታዊ ቁም-ነገሮችና አጠቃላይ መረጃዎችን እንለዋወጥበታለን! Medical Media

14/05/2025

የጤና ባለሙያዎች መንግስትን መፍራት ያቆሙት፣ ኑሯቸው ከመንግስት በላይ ስለሚያስፈራ ነው።
Abel Asrat

14/05/2025

የህክምና ባለሙያዎች ጥያቄ የመኖር እንጂ የስልጣን ጥያቄ አይደለም።

ቆይ እኔ የምለው፣ የሆነ የማትወዱት ፖለቲከኛ ሀሳቡን ስለደገፈው ብቻ ጥያቄው ልክ አይደለም ማለት ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ትክክል የሚባለው የናንተ ሰው ሲናገረው ብቻ ነው? እውነትና ፍትህ ያለማንም የቃል-ባላ በራሳቸው መቆም ይችላሉ። በቃ፣ ለዳቦ ጥያቄ መልሱ "ዳቦ" ነው።

"እዚህ አሜሪካን" እያልኩ ላዝግህ ባልፈልግም "እዚህ አሜሪካን" ከፍተኛ ክፍያ የሚከፈላቸው አስር ስራዎች ብለህ ብትጎግል የምታገኘው መልስ Neurosurgeons ($239,200+), Chief Executive Officers (CEOs) ($350,000–$1,500,000), Pediatric Surgeons ($239,200+), Cardiologists ($423,250), Anesthesiologists ($239,200+), Orthopedic Surgeons (Except Pediatric) ($239,200+), Dermatologists ($342,860), Radiologists ($239,200+), Surgeons, All Other ($239,200+), Oral and Maxillofacial Surgeons ($239,200+).... ወደ ብር ልቀይረው?

አየህ ከአስሩ ዘጠኙ የህክምና ባለሙያዎች የሆኑበት ምክንያት አለው። ጎረቤት ኬንያ (ያውም አነሰ፤ ሰልፍ እንወጣለን እያሉ) ለአንድ ዶክተር በዓመት ከ34,000 ዶላር በላይ ደሞዝና ጥቅማጥቅም ስትከፍል ምክንያት አላት። ተወው አሜሪካን፣ ተወው ኬንያንም፣ ከዛሬ ነገ ፈረሰች አልፈረሰች የምንላት ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ መንግስት ስድስት እጥፍ ለሃኪሞቿ ትከፍላለች። የኛ ሀገር ከአለም ለየት ለማለት ነው ሀኪሞቿን በችጋር የምታሰቃየው? ይኸውልህ ይሄ ሙያ እንደሌላው አይደለም። ለአንድ ቀን ቢስተጓጎል ወይ አንተ፣ ወይ ያንተ ከሆኑት አንዱ እስከወዲያኛው ይስተጓጎላሉ።

እና ለምንድነው ቀኑን ሙሉ ከስንት ታካሚ ጋር፣ ምኑም ባልተሟላ፣ በስም ካልሆነ በስተቀር በግብር "የጤና ተቋም" ለማለት በሚከብድ ተቋም ውስጥ ዓመታትን ፈግቶ ሲያበቃ፣ ዛሬም ልጆቹን የሚያበላው፣ የሚያለብሰውና የሚያስተምርበት በማጣት ሲጨንቀው "ደሞዜን አሻሽሉልኝ" ማለቱን እንደ "ጥጋብ" የምታይበት? "ግዴለም እርካታ እየበላህ ኑር" የምትለው አንተ ጠዋት ቁርስህን እርካታ በልተህ ነው የወጣኸው? በባዶ ቤት መኖሩ አንሶ በባዶ ሆዱ ሲያክምህ ነው የሚሻልህ?

አሁን አሁን የሚያሳዝነኝ ምን እንደሆን ታውቃላችሁ? ደህና ቦታ እንዳይደርሱ፣ ደህና ደህና ጭንቅላት ያላቸውን በሙሉ ነጥቀን ነው ህክምና ት/ት ቤት የከተትናቸው። ሰው እንደተረፈው ሰው ከዚያ አውጥተን ደግሞ እናሰቃያቸዋለን።

የነዚህ ሰዎች ጥያቄ ፍትሃዊ ነው። መንግስትም ጥያቄውን ሌሎች ለፖለቲካ ፍጆታ እንዳይጠቀሙበት ከፈራ መፍትሄው ጥያቄውን ማፈን ሳይሆን በጊዜ መፍትሄ መስጠት ነው። እነሱም መንግስትን ጊዜ ሰጥተው "በኛ ጉዳይ ተነጋገሩበት፣ አንድ መድትሄ ፍጠሩልን" አሉ እንጂ ዛሬም ስራቸውን እየሰሩ ነው። ሌላ ሃገር ቢሆን ይሄኔ ማጣፊያው አጥሮ ነበር። ጠያቂዎችን ወስዶ እስር ቤት ማጎር፣ የፖለቲካ ታፔላ እየለጠፉ ማሸማቀቅ፣ ማንገላታትና ማባረር ነገ መውደቂያን ይወልዳል። የገረመኝ ከማንጓጠጥና ከማጠልሸት ውጪ በአክብሮት መልስ ለመስጠት የሚሞክር እንዴት አንድ ሹመኛ ይጠፋል? እኛ ሀገር የሆነ ሰው ካልሞተና ህዝብ ካልተቆጣ በስተቀር መፍትሄ አለመስጠት ... ቢያንስ በዚህ ዙር ቢቀር ጥሩ አይመስላችሁም?
Mitiku K. Kayamo

ይህ ትግል የግለሰቦች የግል ጉዳይ አይደለም። እኔ በበኩሌ ዶ/ር ደረጄ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆነ አውቃለሁ፣ በማእረግ የተመረቀ ጎበዝ ሀኪምም እንደሆነ አውቃለሁ። በጣም የምወደው ለቦታው የሚመ...
14/05/2025

ይህ ትግል የግለሰቦች የግል ጉዳይ አይደለም። እኔ በበኩሌ ዶ/ር ደረጄ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆነ አውቃለሁ፣ በማእረግ የተመረቀ ጎበዝ ሀኪምም እንደሆነ አውቃለሁ። በጣም የምወደው ለቦታው የሚመጥን የበፊት አለቃዬም ነው።ዶ/ር ደረጄ ብቻውን ሊፈታው የሚችለው ነገር እንደሌለም እንረዳለን። እኛ ስንታገል ግን ግለሰቦችን ወይንም ደግሞ የሆነ የፖለቲካ ፖርቲን አይደለም የምንታገለው። የምንታገለው የጤና ባለሞያን፣ ሀኪምንና ህክምናን ያዋረደን የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት እንዲሁም የበጀት ድልድልን ነው።

እዚህ ጥያቄ ውስጥ ተሸናፊና አሸናፊ የለም። ህክምና ሲቆም እንደሀገር ሁላችንም ተሸናፊዎች ነን። ደሀ ሲሰቃይ እና ሲታረዝ ሁላችንም ተሸናፊዎች ነን። ለዚህም ነው ባለሞያው አስቀድሞ ለሀይማኖት ተቋማት የንስሀ ደብዳቤ ያስገባው። ለባለሞያው የተሰጠው ብቸኛው አማራጭ ግን ሁሉንም ተሸናፊ የሚያደርግ ስራ ማቆምን እንዲመርጥ አድርጎታል። ባለሞያው የስራ ማቆምን ጉዳት ስለሚያውቅ ይህ እንዳይሆን ለአመታት እየሰራ ታግሏል። ጥያቄውን ግን የሚመለከተው ጠፋ።

ባለሞያው ሀላፊነት ተሰምቶት ስራውን እየሰራ በጠየቀ ጊዜ ማን መልስ ሰጠው? አሁንም ቢሆን ባለሞያው ስራ ማቆሙ እንዲቀጥል አይፈልግም። የሚፈልገው ሁላችንም ከምንሸነፍበት ወጥተን ሁላችንም ወደምናሸንፍበት መንገድ መውጣትን ነው። ለዚህ መፍትሄው ደግሞ ባለሞያውን እያሰሩና እያስፈራሩ ለበለጠ አመፅና ጥላቻ መጋበዝ ሳይሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደራድሮ ጥያቄውን መመለስ ነው።

እኔ ከበላሁ ሰርዶ አይብቀል የሚሉ፣ የግል ሁኔታቸው የተመቻቸላቸው ሲኒየር ሀኪሞች ለኛ ዘመን ጥያቄ አለመመለስ እና የጥያቄው መታፈን ምክንያት ነበሩ። መቼም ከግል ሁኔታ ወጥተው ለሞያ ክብርና ለቀጣይ የሀኪም ትውልድ አይጨነቁም፣ አብረው መታገል ሲገባቸው ሬዝደንትና ኢንተርንን በማስፈራራት ጥያቄውን ያሳፍናሉ። እኔ በበኩሌ የተመቻቸ ነገር ላይ ነው ያለሁት፤ ነገር ግን የልጅነት ልፋቴንና ሀገሬ ላይ ተስፋ እንድቆርጥ ያረገኝን ነገር አረሳውም። እነዚህን በአንድነት ቆሞ መታገል ያስፈልጋል። የሞያ ጓደኞቼ እና ታናናሾቼ በሞያቸው ኮርተውና ተከብረው ሀገራቸው እንዲኖሩ እመኛለሁ። ለዚያም አብሬ እቆማለሁ።

ህብረተሰቡም ሆነ መንግስት የሀኪምን ድካም፣ ጥረትና ዋጋ ሚተምነው ፈልጎ ያጣው ቀን ነው። በጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ ሞያህንና ልፋትህን በረከሰ ዋጋ እንዲበዘብዙ አትፍቀድላቸው።

ሰባት አመትና ከዛ በላይ ቀን ከሌት አጥንቶና ለፍቶ የከበረውን የህክምና ሞያ የያዘ ሰው ከባጃጅ ሹፌርና ከሊስትሮ በታች እንዲኖር የፈረደ መንግስትም ይሁን ህዝብ ለሚፈጠረው ችግር እራሱን ተጠያቂ ያድርግ። ዛሬ ሀኪሞች ሲታሰሩ እንደድራማ ፀጥ ብለህ ያየህ ህዝብ ነገ ሀኪም ሳታጣ ማንን ልትወቅስ ይሆን? ከዚህ በኋላ ባለሞያው በዓላማና በዓንድነት ከፀና፣ ቀጣይ ጥያቄውም፣ ሰላማዊ ሰልፉም የህዝቡ ነው።

ስለዚህ ለውጥ ከፈለጋችሁ በዓላማ ፅኑ፣ ትግሉን ከግለሰብ ላይ አውርዳችሁ ስርዓቱ ላይ አድርጉ። እስቀመጨረሻው አንድ ከሆንን ምንም አማራጭ ስለሌላቸው ጥያቄችያንን ይመልሳሉ።

ለመንግስት ደግሞ፣ እንደህፃን እልህ ከመግባት ወጥታችሁ ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበትን መንገድ አስቡ። crisis management ክህሎትን ተጠቀሙ እንጂ እንደወጠጤ ጎረምሳ ለችግር ሁሉ መፍትሄ ዱላና ጉልበትን አትጠቀሙ።

ዶ/ር አብርሃም ታሪኩ

🔈   ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በሚገኘው ቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል  ከታሰሩ የጤና ባለሙያዎች መካከል 3ቱ እስካሁን አለመለቀቃቸው የስራ ባልደረቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።ከ3 ቀን በፊት...
14/05/2025

🔈

ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በሚገኘው ቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል ከታሰሩ የጤና ባለሙያዎች መካከል 3ቱ እስካሁን አለመለቀቃቸው የስራ ባልደረቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።

ከ3 ቀን በፊት መፈክሮችን በመያዝ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቅሬታቸውን ለማሰማት ከወጡት ከ10 በላይ የሚሆኑ ጤና ባለሙያዎች በፀጥታ ሀይሎች ተወስደው የነበረ ሲሆን ሌሎቹ ሲለቀቁ 3ቱ ግን እስካሁን አልተለቀቁም ሲሉ የስራ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል።

" የታሰሩት ባለሙያዎች እንደ ማንኛውም ሀኪም ያለውን ቅሬታ በሰላማዊ መንገድ ያቀረቡ እንጂ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው ናቸው " ሲሉ ነው የገለጹት።

" በትላንትናው እለት እነሱን ለማስለቀቅ ሁሉም ሀኪም በስራ ገበታው ላይ ቢውልም ሀኪሞቹ ግን ሊለቀቁ ባለመቻሉ ዛሬ አብዛኛው ሀኪም የስራ ማቆም አድማውን ቀጥሏል " ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሀኪም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፥ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሚገኘው የአብርሃ ጅራ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ብዛት ያለው የፀጥታ ሀይል በመኖሩ እንዲሁም ማስፈራሪያም በመሰጠቱ በፍርሃት በስራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ ተናገረዋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከድንገተኛ ፣ ህፃናት ቀዶ ህክምና እና ተኝተው የሚታከሙ ህመምተኞችን ከሚከታተሉ ሀኪሞች ውጭ ሌሎች በከፊል የስራ ማቆም አድማ ላይ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል።

በተያያዘ መረጃ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎችም ላይ " ለዓመታት የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች አሁንም በዝርዝር ገልጸን ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች የሚመለስ አልተገኘም " በሚል ዛሬም በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የጤና ባለሙያዎች አሉ።

ከዚህ የጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘም ለእስር የተዳረጉ እንዳሉ ለመረዳትም ተችሏል።

ሆስፒታሎችም በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የጤና ባለሙያዎች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ የሚያስጠነቅቁ ማስታወቂያዎችን እያወጡ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

14/05/2025

ሸገር ሬድዮ፣ አምነስቲ፣ ቢቢሲ አማርኛ፣ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ፣ BBC World እንቅስቃሴያችንን ዘግበዋል።

የኩፍኝ መከላከያ ክትባት - ሐረሪምሥል፦ Ministry of Health,Ethiopia
14/05/2025

የኩፍኝ መከላከያ ክትባት - ሐረሪ
ምሥል፦ Ministry of Health,Ethiopia

14/05/2025

የታናሹ ሰቆቃ!

ኑ ራሱን ሸጦ ...ድሃ ቤተሰቦቹን ተስፋ እየሰጠ...ሳይታወቀው ተስፋ በሌለው መንገድ ገብቶ በጨለማ የሚርመሰመስ አንድ የህይወት ብላቴናን ህይወት እንታደግ!

በዘመናት የሰው ልጅ ታሪክ ሁልጊዜም የሰው ልጅን ምልከታ: እይታ እና የታሪክ አቅጣጫ ያስቀየረ የምድራችን ገፀ በረከት የሆነ ....የሆነ ሰው ወይም የሆነ ትውልድ አለ። ምናልባት ያቺ ሰው ወይም ያ ትውልድ በህይወት ዘመኑ ወይም በስልጣኔ ከፍታው ሊገመት በማይችል የታሪክ መጨቆን :መረገጥ ወይም መገለል ደርሶበት ይሆናል። ደግሞም የዓለም ታሪክ እንዲህ ነው። የተሻለ ጊዜ እና ዘመን በተለይ ደግሞ እንደ ሃገራችን የጤና ባለሙያዎች እድሜያቸውንና ሙሉ ማንነታቸውን ለትምህርት ሰጥተው እንዲህ ነው ተብሎ በማይነገር ሁኔታ የትምህርት ጫና: የኢኮኖሚ ጥገኝነት: እንቅልፍ አልባ ዓመታት እና የስርዓተ ትምህርቱ ከተግባራዊ ልምምዱ እና አሁናዊ የዓለም ሁኔታ ጋር ያለመጠጣም ችግር አንድ ላይ ሆነው አንድ ትምህርት ብቻ የህይወት መንገዱ አድርጎ ለሚያይ የሳይንስ ዓለማዊ እና የህይወት ባህታዊ ሰው የእድሜ ልክ የህልውና ጥያቄ እና የፀፀት ምንጭ ይሆናል።

እኛ ደግሞ ገና በህክምናው መግቢያ በር ላይ እንደመሆናችን እጃችን ይዘው የአካልን የአወቃቀር ቀመር ያስጠኑን ባዕድ በሆነ ቋንቋ ከአፍ መፍቻ ቋንቋ በላይ እንድንናገር ምላሳችንን የፈቱልን ሰዎች የገባንበትን የሙያ መንገድ ጠርገው ልክ ከዚህ በፊት በነበረው ክብሩ አስቀጥለው እነሱን መስለ
ን ህዝባችንን እንድናገለግል የማድረግ የሙያ ግዴታ: የሰብዓዊነት ተጠየቅ እና የህሌና ክስ አለባቸው።

የስፔሻሊስት ሐኪሞችን ደሞዝ እና የሙሉ ጤና ባሉሙያዎችን የተደበቀ የአኗኗር ዘዴ እንዲሁም መንግስት ለጤናው ያለውን ግዴለሽነት: ለባለሙያዎች ያለውን ንቀት በተለይ ደግሞ ከልክ ያለፈ ኑሮ እየኖሩ በእኛ የዳቦ ጥያቄ እየተገረሙ የጥያቄውን አውድ ወደ ፓለቲካ ቀይረው የሚሳለቁ ጤና ባለሙያዎችንና ካድሬዎችን ሳይ መጪው ዘመን ለእኔ ጨለማ ነው። ትንሽ እንኳን የተስፋ ጭላንጭል የለኝም።

እስካሁን ድረስ ህዝባቹህን በታላቅ የሞራል ብርታት እና የሙያ ግዴታ ያገለገላቹህ ታላላቆቻችን ለመጪው ዘመናችን ቢያንስ ትንሽ ተስፋ የምናገኝበት እና ያለን የእውቀት አቅም ተጠቅመን ህዝባችንን የምናገለግለበት የሞራል ድጋፍ እንደሰጡን የኃላፊነት አደራ ልንሰጣቹህ እንወዳለን።

የተጀመረው በድል እንዲጠናቀቅ ሁሉም በእያለበት ይፅና! አንድ ሲታሰር ብዙዎቻችን የምንፈልገው ይመጣል።

" በሽታህ ብዙ ጊዜ ሳይወስድ በንቁ አዕምሮዎች ተገኝቷል። መድሃኒቱም 12 ሆኖ በግልፅ ተሰናድቷል። ሌላውን ስታድን የነበርክ ሰው ሆይ እጅህ መርፌውን ለማንሳት ስለምን ደከመ???

Now or Never!

Stay united!

Free yourself and the coming generation!

Let us keep the profession safe!

🔈 " ባለሙያው 'ርቦኛል፣ ረሃብ ጊዜ አይሰጥም ነው' ያለው። ስለዚህ አቅምም ከሌላቸው በግልጽ መናገር ነው። ድለላ ነው የደበረው ባለሙያው ” - ማኀበሩየጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በ...
14/05/2025

🔈

" ባለሙያው 'ርቦኛል፣ ረሃብ ጊዜ አይሰጥም ነው' ያለው። ስለዚህ አቅምም ከሌላቸው በግልጽ መናገር ነው። ድለላ ነው የደበረው ባለሙያው ” - ማኀበሩ

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ያደረጉት ቃለ ምልልስ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሊሆን አይችልም ብለው እንደሚያምኑ ባለሙያዎችና የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ባለሙያዎቹና ማኀበሩ ይህን ያሉት ሚኒስትሯ ከሰሞኑ ባደረጉት ገለጻ፣ ለጤና ባለሙያዎች በቀጣይ ዓመት ከፍ ያለ በጀት ለመበጀት በቂ ዝግጅት መደረጉን ጨምሮ የሰጡትን ማብራሪያ በተመለከተ ነው።

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ምን አለ ?

“ እንደዚህ አይነት ምላሾች የተለመዱ ናቸው። ነግሮች ለተሾሙበት ስልጣናቸው ስጋት ሲሆኑባቸው በመንግስታዊ ሚዲያዎች ወጥተው መናገራቸው የተለመደ ነው።

ግማሹ አንቋሾ ይመልሳል፤ ፓለታካዊም ያደርጋል። ግማሹ ደግሞ 'እውነት ነው፤ ጥያቄያቸውን ተረድተነዋል ፤ ግን ሌላ አካል እንዳይዘውራቸው' ይላሉ።

ጥያቄ እያቀረበ ያለው እስከ 20 ዓመት በትምህርት የቆየው ጤና ባለሙያ ነው። በዚህ ልክ በትምህርት ዝግጅት ያለፈን ባለሙያ ‘የማኀበራዊ ድረ ገጽ አክቲቪስቶች አእምሯቸውን ዋሽ አድርገውታል’ ብሎ መግለጽ በራሱ አሳፋሪ ነው።

ባለሙያዎች በቁጥር ጠቅሰው ጥያቄዎችን ጠይቀዋል። ግን በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚመለከታቸው አካላት በሚገባ እውቅና አልሰጡትም ‘ባለሙያው ጥያቄ ይኖረዋል፤ እውነት ነው’ ይበሉ እንጂ።

ጤና ሚኒስትሯ የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ እውቅና ቢሰጡት ኖሮ የቀረቡ 12ቱንም ጥያቄዎች ማስረዳት ነበረባቸው። ይሄ ባለሙያ የሚናቅ አይደለም። ቀጥተኛ ምላሽ ቢሰጡበት ነው ምላሻቸውን የምናምነው።

ባለሙያው 'ርቦኛል፣ ረሃብ ደግሞ ጊዜ አይሰጥም' ነው ያለው። ስለዚህ አቅምም ከሌላቸው በግልጽ መናገር ነው። ባለሙያው ድለላ ነው የደበረው። አቅም የለንም እንዳይሉ ደግሞ አለን እያሉ ነው ” ብሏል።

ጤና ባለሙያዎችስ ምን አሉ ?

“ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አይተነዋል፤ ግን ለጥያቄያችን ምንም ምላሽ አላገኘንበትም።

ስለበጀት ማንሳት ካስፈለገ፣ በጀት መበደብ መብት ሳይሆን ግዴታ ነው።

ኢትዮጵያ የፈረመችው ስምምነት አለ በዓለም ጤና ድርጅት። ሪከመንድ የሚያደርገው አገሪቱ ከምትመድበው በጀት 15% ለጤና መበጀት አለባት ይላል። ይሄ ኢትዮጵያ የፈረመችው ነውና ያን ማክበር ነው ያለባቸው።

በ2017 ዓ/ም 3.7% ነው የመደቡት፤ በጤናው ዘርፍ ግማሹን እንኳ ለመመደብ አልታደለችም። እናም ይሄ ባልሆነበት ሁኔታ በቀጣይ ይደረጋል የሚለው ከሆነ ጥሩ ነው። በመልካም ጎኑ እናየዋለን።

ግን በጀት መመደቡ በጤና ባለሙያው የሚያመጣው ኢምፓክት ነው መታየት ያለበት።

ጤና ተቋማትን ለማስገንባት፣ ማሽነሪዎችን ለማስገባት የተደረጉ ነገሮች አሉ እናደንቃለን። ግን የጤና ባለሙያውን እርካታ ሊጨምር የሚችለውን ኢምፓክት አልተነሳም፤ መነሳት ነበረበት።

በቃለ ምልልሱ ሪፎርሙን ሳይሆን ባለሙያው አንገብጋቢ 12 ጥያቄዎች አሉት ሊመሱለት የሚገባ፤ እነዛን ነበር አድሬስ ማድረግ የነበረባቸው። ስለዚህ ገለጻው ለጥያቄያችን ምላሽ ነው ብለን ለመውሰድ ያስቸግረናል ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

BBC!
14/05/2025

BBC!

Health workers in Ethiopia demand better pay, working conditions and more benefits

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 2019 GC /2011 ዓም መሰረት ሰራተኛው አንድን ሰራተኛ መብቱን በመጠየቁ ምክንያት ከስራ ማገድ እንደማይቻል ህጉ ይደነግጋል። ሌላው ሰራተኞች ከስራ ቢታገዱ ለእያን...
14/05/2025

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 2019 GC /2011 ዓም መሰረት ሰራተኛው አንድን ሰራተኛ መብቱን በመጠየቁ ምክንያት ከስራ ማገድ እንደማይቻል ህጉ ይደነግጋል። ሌላው ሰራተኞች ከስራ ቢታገዱ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ እንደ የአገልግሎት ዘመኑ የአገልግሎት ካሳ ክፍያ ሊከፈለው ይገባል። በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰራተኞች ደግሞ ካሳውን ከፍሎ ለማሰናበት የመንግስት ገንዘብ ካዘና afford ማድረግ ይችላል ብየ አልገምትም። በዚሁ አጋጣሚ የሙያ ማህበሩ ከወዲሁ የህግ ባለሙያ /ጠበቃ ሊያመቻች ይገባል። የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ጎግል ላይ ''Labor proclamation 2019'' ብላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

Simachew Zelalem

“የታሰረ ሰው አስፈታለሁ" እያሉ ነው ባሕል መድኃኒት “አዋቂው" 😀
14/05/2025

“የታሰረ ሰው አስፈታለሁ" እያሉ ነው ባሕል መድኃኒት “አዋቂው" 😀

😃አንዳንዴ ዘና እያላችሁ🤗Dr Ephrem Haile , Pediatric HematoOncologist at TASH
14/05/2025

😃
አንዳንዴ ዘና እያላችሁ🤗

Dr Ephrem Haile , Pediatric HematoOncologist at TASH

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Medical Information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Medical Information:

Share

Our Story

Feed Health Information