Medicare Home Based Healthcare Service

Medicare Home Based Healthcare Service We give quality healthcare service with qualified and well experienced health professionals.

በሙያው በቂ ልምድና ችሎታን ባካበቱ ባለሙያዎች ምቾትዎ ሳይጓደል ሁሉንም በቤትዎ በተመጣጣኝ ዋጋ የ24 ሰዓት አገልግሎት እንሰጣለን።ይደውሉልን:       0912915008       091063...
14/08/2024

በሙያው በቂ ልምድና ችሎታን ባካበቱ ባለሙያዎች ምቾትዎ ሳይጓደል ሁሉንም በቤትዎ በተመጣጣኝ ዋጋ የ24 ሰዓት አገልግሎት እንሰጣለን።

ይደውሉልን:
0912915008
0910634174

16/02/2024

የታችኛዉ አከርካሪ ዲስክ መንሸራት | Lumbar disc herniation

የታችኛዉ አከርካሪ ዲስክ መንሸራት የተለመደ የወገብ እና በአንድ እግር የሚሰማ የነርቭ ህመም (radiculopathy) መንስኤ ነዉ። በ አከርካሪዎቻችን መካከል የሚገኙት እና ወገባችን እንዲተጣጠፍ የሚያግዙት ዲስኮች ከቦታቸዉ ለቀዉ የነርቭ መተላለፊያ ቱቦ በመግባት የነርቭ ዘንግ ሲጫኑ የሚከሰት ህመም ነዉ።

የተለመደ ባይሆንም የተንሸራተተዉ የዲስክ መጠን ከፍተኛ ሲሆን የሽንት ወይም የሰገራ መቆጣጠር እና የእግር መስነፍ ሊያስከትልም ይችላል።

ዲስክ መንሸራት በታካሚው ላይ በሚታዩ ምልክቶች እና ባለሞያዉ በሚያደርገዉ አካላዊ ምርመራ በተጨማሪም በMRI ምርመራ በሽታዉ ይታወቃል።

አብዛሀኛዉ የታችኛዉ አከርካሪ ዲስክ መንሸራት በሚዋጥ ማስታገሻ እና ፊዚዮቴራፒ ከፍ ካለም ወገብ ላይ በሚሰጥ መርፌ ይታከማል። ህመሙ ለዉጥ ካላመጣ ወይም የእግር መስነፍ፣ የሰገራ/ሽንት መቆጣጠር ችግር ካስከተለ በቀዶ ህክምና ነርቭ የተጫነዉን የተንሸራተተ ዲስክ በማዉጣት ይታከማል።

መንስኤዎቹ
◦ ተደጋጋሚ የሆነ የወገብ መታጠፍ/መጠማዘዝ
◦ በእድሜ ምክንያት የሚከሰት የ ዲስክ መበላት
◦ በወገብ ላይ የሚደርስ ጉዳት
◦ ከፍተኛ የሆነ ክብደት ያለዉ ነገር ወገብ እንደታጠፈ ማንሳት ( ስፖርተኞች፣ የኮንትራክሽን እና የቀን ሰራተኞች)
◦ የስራ ሁኔታ፥ ረዘም ላለ ጊዜ ወደጐን በመታጠፍ እና ንዝረት ባለበት ቦታ መስራት (የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች)

አይነቶቹ

◦ የዲስክ ማበጥ (disc protrusion)
◦ የዲስክ መንሸራተት(disc extrusion)
◦ የዲስክ ሙሉ በሙሉ መዉጣት(sequestered fragment)

የበሽታዉ ምልክቶች

◦ ድንገተኛ የሆነ ከባድ እቃ ከማንሳት / ስራ ከመስራት በኋላ የሚከሰት የወገብ፣ የመቀመጫ ወይም የ እግር ህመም፣ መንዘር፣ ማቃጠል ወይም መዉረር (በምንቀመጥበት ወቅት የሚባባስ)
◦ የ እግር መስነፍ
◦ ፊንጢጣ አካባቢ መደንዘዝ
◦ የ እግር ህመም በሌለበት በኩል ማዘንበል

የሚያስፈልጉ ምርመራዎች
◦ ራጅ
◦ MRI

ህክምናዎቹ ፥
90 በመቶ የሚሆኑት የዲስክ መንሸራተት ታካሚዎች ያለ ቀዶ ህክምና ይድናሉ።

◦ የመጀመሪያ ህክምና ፥ እረፍት ማድረግ፣ የፊዚዮቴራፒ ህክምና እና የቁስለት መቀነሻ / ማስታገሻ መደሀኒቶች
◦ ለዉጥ ከሌለዉ ወይም ከአቅም በላይ የሆነ ህመም ካለ፥ በጀርባ በመርፌ የሚሰጥ መደሀኒት (selective nerve root block or epidural steroid)
◦ ህመም ለ 6-8 ሳምንታት ከላይ በተጠቀሱት ህክምናዎች ካልቀነሰ ፣ የ እግር መስነፍ ከተከሰተ፣ የ ሰገራ እና የሽንት አለመቆጣጠር ከጀመረ ፥ በ ቀዶህክምና መታከም ይኖርበታል።

07/02/2024

ሰላም ዛሬ በተለምዶ ጭርት (Tinea corporis) ስለሚባለው በሽታ ይዤላቹ ቀርቢያለሁ

ጭርት ምንድን ነው?

- ጭርት (tinea corporis) የምንለው በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ፣ በሁሉም የእድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን ከሰው ወደ ሰው፣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ፣ በንክኪ የሚተላለፍ የላይኛውን የቆዳ ክፍል የሚያጠቃ በሽታ ነው።

ከየት ሊይዘን ይችላል?

-በበሽታው ከተያዙ ሰዎች፣ከተለያዩ የቤት እና የዱር እንስሳቶች፣ ከአፈር ሊሆን ይችላል። በተለይ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተጠቀመበትን እንደ ፎጣ፣ አልጋ ልብስ፣ ካልሲ፣ የፀጉር ማበጠሪያ በጋራ መጠቀም እና ንክኪ መፍጠር ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።

አጋላጭ ምክንያቶቹስ ምንድን ናቸው?

-ሞቃታማ እና እርጥበታማ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች፣ ሰውነትን የሚያጣብቁ ልብሶችን መልበስ፣ ደካማ የበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች፣ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ ከመጠን በላይ ላብ የሚያልባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምልክቶቹስ?

-አንድ ሰው ተጋላጭ ከሆነ በዃላ ከ4-14 ቀን ምልክት ሊያሳይ ይችላል። በሰውነት ላይ ክብ ክብ የሆነ ፣ ጠርዝ ጠርዙ ቀላ ያለ (erythematous)፣ የማሳከክ ስሜት ሊኖረው የሚችል እየሰፋ የሚሄድ እንደ ቅርፊት (scaly)፣ የተሰነጠቀ (cracked) የሚመሰስል ነገር ሊወጣ ይችላል።

ምርመራዎቹስ

-የህክምና ባለሙያው በቆዳ ላይ የወጣውን ነገር አይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ከቆዳ ላይ ናሙና በመውሰድ በቤተ ሙከራ በmicroscope በመታገዝ ፈንገስ መኖር አለመኖሩን ሊያረጋግጥ ይችላል።

የሚያመጣውስ መዘዝ?

-በተለይ ደካማ ዠበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች ለምሳሌ (HIV ህመምተኞች፣ የካንሰር ህክምና የሚወስዱ) በቶሎ በሽታውን ለማስወገድ ሊቸገሩ ይችላል።

-የሚያሳክክ፣ የተቆጣ እና የቆዳ መሰንጠቅ ሲኖር ለሌላ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን (secondary bacterial infection) ሊጋለጡ ይችላሉ።

አእዴት መከላከል እንችላለን?

-የግል እና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ

-ሰውነታችነንን ከታጠብን በዃላ በንፁህ ፎጣ ወይም ጨርቅ በደንብ ማድረቅ

-የግል መጠቀም ያልብንን ነገሮች በጋራ አለመጠቀም

-በተቻለ መጠን በዚህ በሽታ ከተበከሉ እንስሳት ንክኪ አለመፍጠር፣ በአካባቢያችን የታመሙም እንስሳት ካሉ የእንስሳት ሀኪም ጋር በመውሰድ ማሳከም ተገቢ ነው።

ህክምናውስ?

-እነደ ወጣበት ቦታ እና ስፋት የሚወሰን ሲሆን በቦታው ላይ የሚቀባ ፀረ ፈንገስ ወይም የሚዋጥ ፀረ ፈንገስ በሀኪም ሊታዘዝ ይችላል።

04/02/2024

'ሚስ አሜሪካ 2019' ምን ጎሎባት ራሷን አጠፋች?
==========================
የ2019 የአሜሪካ የቁንጅና ውድድር አሸናፊዋ ቼልሲ በሞያዋ ጠበቃ ነበረች። የስኬት ማማ ላይ እየወጣች ነበር። ከውበት ውበት፤ ከአእምሮም ብሩህ አእምሮ የታደለችውን ቼልሲ ህይወቷን ብዙዎች ይቀኑበት ነበር።

ከወራት በፊት ከኒው ዮርክ ሰማይጠቀስ ህንፃዎች ላይ አንድ ሴት ስትዘል የህግ አስከባሪ ሰዎች ወደ ቦታው ሲደርሱ ህይወቷ አልፏል። ፊቷን ሲያዩ ማመን አልቻሉም በቲቪ የሚያውቋት መልከመልካሟ፣ ስኬታማዋ ቼልሲ ናት። "ምን ጎሎባት ራሷን አጠፋች?" ሳይሉ አይቀርም።

ሰዎች ራሳቸውን የሚያጠፉት ከሚቋቋሙት በላይ ከፍተኛ ጭንቀትና የስነ ልቦና ስቃይ ውስጥ ሲሆኑ ነው። እነሱ ካለፉ በኋላ "ግን ለምን?" ብለን ብንጠይቅም መልስ አናገኝም።

የአእምሮ ህመምና ጭንቀት ሀብታም ደሀ፤ የተማረ ያልተማረ፤ ስኬታማ መደበኛ ብሎ አይለያይም። ሁላችንም ላይ ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ ሁላችንም ያገባናል። ከመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ ራሳቸውን ያጠፉ የማውቃቸውንና የምወዳቸውን ሰዎች ሳስብ ልቤ ያዝናል። ሌሎች ጭንቀት ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን እገዛ እንዲያገኙ እተጋለሁ።

ቼልሲን "ምን ጎሎባት ራሷን አጠፋች?" ብለን በፍረጃ ከመጠየቅ "ምን ያህል ተጨንቃ ይሆን?" ብንል የተሻለ እንረዳታለን። ሌሎችንም ለማገዝ ያስችለናል።

25/01/2024

✋መሃንነት ምንድን ነው?

👨🏽‍⚕️መካንነት የወንድ ወይም የሴት የመራቢያ ሥርዓት በሽታ ሲሆን ይህም ከ12 ወራት ወይም ከዚያ በላይ መደበኛ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከተፈጸመ በኋላ እርግዝና ባለመቻሉ የሚገለጽ በሽታ ነው።

✋ምን ያህል ሰዎች በመሃንነት እየተሰቃዩ ነው?
👨🏽‍⚕️ከ 6 ሰው አንዱ መሃን የመሆን እድል አለው።

✋የመሃንነት መንስኤ ምንድን ነው?
👨🏽‍⚕️መሃንነት ከወንድ ወይም ከሴት ሊሆን ይችላል

👉🏽የወንድ መሃንነት መንስኤዎች

1. የወንድ የዘር ፍሬ ምን ብዛት እና ጥራት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች መኖር፣

ወደ ቦታው ያልወረዱ የዘር ፍሬዎች፣ የዘረመል ጉድለቶች፣ የሆርሞን ችግሮች እና እንደ የስኳር በሽታ ያሉ የጤና ችግሮችን ሊያካትቱ ይችላሉ። እንደ ክላሚዲያ፣ ጨብጥ፣ ደዌ ወይም ኤች አይ ቪ ያሉ ኢንፌክሽኖች የወንድ የዘር ፍሬን ሊጎዱ ይችላሉ። varicocele ተብሎ የሚጠራው በ sc***um ውስጥ ያሉ ደም መላሽ ቧንቧዎች የወንድ የዘር ፍሬን ጥራት ይጎዳሉ።

2. የወንድ የዘር ፍሬ ወደ ሴት የመራቢያ ክፍል መድረስ ላይ ያሉ ችግሮች

ያለጊዜው መፍሰስ፣ እንደ ሳይስቲክ ፋይብሮሲስ ባሉ አንዳንድ የጄኔቲክ በሽታዎች፣ በወንድ ብልት ውስጥ መዘጋት ያሉ የአካል ችግሮች፣ ወይም የመራቢያ አካላት ላይ በሚደርስ ጉዳት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።

3. ለፀረ-ተባይ መድሃኒቶች, ሌሎች ኬሚካሎች ወይም ጨረሮች መጋለጥ የመራባት ሁኔታን ሊጎዳ ይችላል። አንዳንድ መድሃኒቶች እንዲሁም የዘር ፍሬዎቹ ከመጠን ላለፈ ሙቀት መጋለጥ።

4. ከካንሰር እና ከህክምናው ጋር የተያያዘ ጉዳት
እንደ ኬሞቴራፒ እና ጨረሮች ያሉ የካንሰር ህክምናዎች የወንድ የዘር ፍሬን ሊጎዱ ይችላሉ።

25/01/2024

አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሕፃናት እና ልጆች ከልክ ያለፈ ውፍረት

የሕጻናት እና የልጆች እድገት ክትትል እድሜ፣ ክብደት እና ቁመትን ያማከለ ነው፡፡ አንድ ሕፃን/ልጅ ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት/ ውፍረት አለው የሚባለው በእድገት ክትትል መመዘኛ ክብደቱ ከቁመቱ ጋር ያለው ልኬት ከዕድሜው ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለመሆኑን የሚያሳየው ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን ነው፡፡
በሕጻናት ላይ ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት መታየቱን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው በአዋቂነት ዕድሜያቸውም ይህን ችግር ይዘውት ሊቀጥሉ የሚችል ስለሆነ ነው፡፡

አጋላጭ ምክንያቶች

በዘርፉ ላይ ጥናት የሚያደርጉ ባለሙያዎች እንደሚገልፁት የዘረ-መል ተጋላጭነትና የተለያዩ አካባቢያዊ ምክንያቶች በሕጻናት ላይ ለሚከሰት ከልክ ያለፈ ውፍረት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የዘረ-መል ተጋላጭነት፡ የወላጆች ከልክ ያለፈ ክብደት ልጆች ተመሳሳይ ሁኔታ እንዲኖራቸውና በአዋቂነት ዕድሜያቸውም በተመሳሳይ ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት የመያዝ እድላቸውን በእጥፍ የሚጨምር ሁኔታ ነው፡፡ ከሁለት አንዳቸው ወላጆች ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት ሲኖራቸው የልጆች ተመሳሳይ ሁኔታ የመኖር እድላቸው የቀነሰ ቢሆንም በዚህ ሁኔታ በታዳጊነት እድሜያቸው ላይ ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት ያላቸው ልጆች በአዋቂነታቸው ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት የመያዝ እድላቸው በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡

አካባቢያዊ ምክንያቶች

የአመጋገብ ሁኔታና በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ አለመኖርም ሌሎቹ የዚህ ምክንያቶች ናቸው!
በአሁኑ ወቅት እንደሚስተዋለው ቀለል ያሉና ፈጣን ምግቦች እንዲሁም ከቤት ውጪ መመገብ፣ ብዙ እንቅስቃሴ የማይጠይቁ ተግባራት ማለትም ለረጅም ጊዜ ቴሌቭዥን መመልከት እንዲሁም የቪዲዮ እና የኮምፒውተር ጨዋታዎች አብዛኛውን የልጆችን ጊዜ ስለሚወስዱ አካላዊ እንቅስቃሴ የማድረግ፣ በትምህርት ቤትም ሆነ ከዚያ በኋላ ውጪ የመጫወት እድላቸው እንዲቀንስ ሆኗል፡፡

በቀን ውስጥ ለ1 ወይም 2 ሰዓት ቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር ወይም ሌላ ትስስር ገፅ ላይ የሚያጠፋ ልጅ በተመሳሳይ ዕድሜ ካለ በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ ካለው ልጅ ጋር ሲነፃፀር፤ ያነሰ የምግብ አወሳሰድ ቢኖረው እንኳ ከልክ ያለፈ ውፍረት እንዲሁም የደም የቅባት መጠን መዛባት ይታይበታል፡፡
ማስታወሻ፡ ሕጻናት በአብዛኛው አመጋገብን እና የምግብ ምርጫዎችን የሚማሩት ከቤተሰብ ነው፤ ስለዚህ የልጅን የአመጋገብ ዘይቤ ለብቻ ጤናማ ለማድረግ ከመሞከር ይልቅ እንደ ቤተሰብ ጤናማ አመጋገብን ማዳበር የበለጠ ውጤታማ ያደርጋል፡፡

በልጆች ላይ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ምን ያስከትላል?

በጤናማ መንገድ ያልተከተለ የሰውነት ዕድገት
የተለያዩ የጤና አክሎች (የደም ቅባቶች መጠን መዛባት፣ የደም ግፊት፣ የስኳር ሕመም፣ የመተንፈሻ አካላት ጤና መታወክ ወ.ዘ.ተ)

የስነ አዕምሮአዊ፣ የስሜታዊ እና የማህበራዊ እድገት ችግሮች (ከማህበረሰብ የመገለል እና ለመግባባት የመቸገር እንዲሁም የጭንቀት ስሜቶች ወ.ዘ.ተ)

ማስታወሻ፡ ልጆች ተጋላጭነት ካላቸው ቀድሞ ለመከላከል የሚመረጠው ዕድሜ በህፃንነታቸው ሲሆን ውጤታማ የሚሆኑት መንገዶች ደግሞ የአመጋገብ ዘይቤ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ፣ የስነልቦና ድጋፍ እና የባሕርይ ለውጥ ድምር ውጤቶች ናቸው፡፡

06/01/2024

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Medicare Home Based Healthcare Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram