OASIS Center for Quality Life

OASIS Center for Quality Life We are here to professionally help you with , , , issues and beyond.

ሰላም ውድ የኦሲስ ቤተሰቦች! በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2017 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር የተማሪዎች ስልጠና። እድሜያቸው ከ12-18 አመት ለሆኑ ተማሪዎች።ቀን: ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ...
01/03/2025

ሰላም ውድ የኦሲስ ቤተሰቦች! በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2017 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር የተማሪዎች ስልጠና። እድሜያቸው ከ12-18 አመት ለሆኑ ተማሪዎች።

ቀን: ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ሰዓት: ከቀኑ 8:00 - 11:00
ቦታ: በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን አዳረሽ (CMC)

ለመመዝገብ እና ለበለጠ መረጃ በ:- 0946444445 ይደውሉ።
ጥቂት ቦታዎች ስላሉ ፈጥነው ይመዝገቡ!

🤰🤰በእናቶች ተገረምን....🤱🤱ይህን የምታነቡ ሁሉ አንዴ ከመቀመጫችሁ ብድግ ብላችሁ ለእናቶች አጨብጭቡ እያልን በትህትና እንጠይቃቿለን።🙏🙏🙏ለምን❓❓እመኑን፤ሸጋ ነገር ስለ እነሱ ልንነግራችሁ ...
19/02/2025

🤰🤰በእናቶች ተገረምን....🤱🤱

ይህን የምታነቡ ሁሉ አንዴ ከመቀመጫችሁ ብድግ ብላችሁ ለእናቶች አጨብጭቡ እያልን በትህትና እንጠይቃቿለን።🙏🙏🙏

ለምን❓❓
እመኑን፤ሸጋ ነገር ስለ እነሱ ልንነግራችሁ ነው።🥰🥰

"ለምን ማለት መልካም"..

ቅዳሜ የካቲት 8/2017ዓ.ም "ወላጅነት በግንኙነት"(connection parenting) የተሰኘ በልጆች እና ወላጆች መሃከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር አቅጣጫን የሚጠቁም መርሃግብር ብናዘጋጅ አዳራሻችንን እናቶች ሞሉታ፤እኛም ተገረምን።🤭🤭

በእናቶች ተደሰትን፤ለልጆቻቸው ያላቸው ትኩረት እና ንቁ የሆነ ወላጅነትን መሻታቸው፣ ንቁ ተሳትፏቸው፣በመጨረሻም የነበራቸው ግብረ መልስ እና ለቀጣይ parenthon ሴሚናር ያሳዩን ጉጉት አስደሰተን። 😃😃

በአንድ ልባችን ግን አዘንን።😔

"አባቶች እናንተስ?" አልን። ተቋማችን ኦሲስ "በበረሃ ያለ ለምለም ስፍራ" ነውና የበረሃውን(የስራ፣የቤተሰብ፣የሌሎች ብዙ ጉዳዮች) ጫናን እንረዳለን፤ በዚህ ተጠምዳችሁ እዳልተገኛሁም እንገምታለን።
ቢሆንም ግን ወደ ለምለሟ ስፍራ ጠጋ ብሎ ሃይል መሰብሰቡ መልካም ነው።

የኦሲስን(Oasis) ትርጉም ልናመራምራችሁ ነው።🫣

በመርሃ ግብሩ የተገኙትን ሁለት አባቶች ሳናመሰግን ብናልፍ ግን ንፉግ ያስብለናልና ለእናቶች ቆማችሁ ባጨበጨባችሁበት በዛው ሳትቀመጡ ለእነዚህ ጀግና አባቶችም 👏👏

በአሁኑ የparenthone መርሃግብር ሜዳሊያችን ለእናቶች ሆኗል።👩‍🦳🥇

በነበረን ሸጋ የሆነ ቆይታ ተደስተናል፤ በቀጣይ parenthon ስንገናኝ አባቶች በቁጥር በዝታችሁ፤እናቶች ከቁጥር ሳትጎድሉ፣ ያልመጡ ወላጆችንን ጋብዛችሁ፣አዳራሻችንን ሞልተን፣የየልባችንን የምንወያይበት እና የምንማማርበትን ዝግጅትን ለማየት እንናፍቃለን።

ኦሲስ ሥልጠናና ማማከር ማዕከል
https://t.me/+ESVZ5qsyls9lODJk

24/01/2025

Parenthon

ወላጅነት በግንኙነት (Connection Parenting) በሚል ርዕሰ ጉዳይ በተሰናዳው የወላጅነት ሴሚናር በመሳተፍ ከልጆችዎ ጋር ጠንካራ፣ ትርጉም ያለው ግንኙነት ለመገንባት፣ ስሜታዊ እውቀትን ለማጎልበት እና ተስማሚ የቤተሰብ አካባቢ ለመፍጠር የሚረዱ ተግባራዊ ስልቶችን ያግኙ። በልጅዎ ውስጥ ቁጣን ወይም በየዕድሜ ክልሎቹ ውስጥ ያሉ ፈተናዎችን እያስተዋሉ ከሆነ፣ Parenthon እርስዎን በወላጅነት ጉዞዎ ላይ ለማበረታታት የባለሙያ ምክሮችንና እና የእርስ በእርስ ልምደ መለዋወጫ ክፍለ ጊዜዎችን ይዝዎ ይጠብቆታል።
እንገናኝ፣ እንማማር እና አብረን እንደግ!

ቅዳሜ የካቲት 8, 2017 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ከቀኑ 8:00- 11:00 ሰዓት
ለመመዝገብ 0946444445 ይደውሉ ጥቂት ቦታዎች ስላሉ ፈጥነው ይመዝገቡ።

24/01/2025
ቅድመ ጥምረት-የፍቅር ግንኙነት በመጀመር ውሳኔ ዙሪያ ግራ ተጋብተዋል?-ግንኙነታችሁን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ዝግጁ ኖት?-የፍቅር ጓደኝነት አደጋ ሰልችቶታል?ቆይ!እንግዲያውስ ስለ ቅድመ ጥምረ...
17/11/2024

ቅድመ ጥምረት
-የፍቅር ግንኙነት በመጀመር ውሳኔ ዙሪያ ግራ ተጋብተዋል?
-ግንኙነታችሁን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ዝግጁ ኖት?
-የፍቅር ጓደኝነት አደጋ ሰልችቶታል?
ቆይ!

እንግዲያውስ ስለ ቅድመ ጥምረት የስልጠና ፕሮግራም እንንገራችሁ

የቅድመ ጥምረት የስልጠና ፕሮግራም አስደሳች፣ መስተጋብራዊ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የስልጠና ፕሮግራም ነው። ስልጠናው የግንኙነት አቅምን ለማወቅ እና ለጤናማ፣ አስደሳች እና ዘላቂ አጋርነት የሚያስፈልጎትን ክህሎቶች ለመማር የሚረዳ የስልጠና ፕሮግራም ነው።

ካልተሳካ የፍቅር አዙሪት ለመላቀቅ ፣ እዉነተኛ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት እና ለዘላቂ ግንኙነት ጠንካራ መሰረት ለመገንባት አሁኑኑ ይደውሉ ...0946-444445

ቀን :-05/04/2017 ዓ.ም
ቦታ :- ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክ አሶሴሽን አዳራሽ

ኦሲስ ሥልጠናና ማማከር

አውንታዊ ወላጅነት"በ አንድ ጊዜ አንድ አውንታዊ እርምጃ ለልጆች ሁለንተናዊ እድገት!"የወላጅነት ጉዞዎን ለመለወጥ ዝግጁ ንዎት? እንዲያውስ የአዉንታዊ ወላጅነትን ኃይል በመጠቀም በልጅዎ ውስጥ...
24/10/2024

አውንታዊ ወላጅነት

"በ አንድ ጊዜ አንድ አውንታዊ እርምጃ ለልጆች ሁለንተናዊ እድገት!"

የወላጅነት ጉዞዎን ለመለወጥ ዝግጁ ንዎት? እንዲያውስ የአዉንታዊ ወላጅነትን ኃይል በመጠቀም በልጅዎ ውስጥ ያለዉን እምቅ ችሎታ ይግለጡ!

ይህን ልጆቻቸውን በፍቅር፣ በትግስት እና በአውንታዊነት ለመንከባከብ እና ለመምራት ለሚፈልጉ ወላጆች የተዘጋጀ ሥልጠናን ይቀላቀሉ።

በስልጠናው የሚዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች፣

➡️በልጆቻችን ውስጥ ስሜታዊ ብልሀትን ለማዳበር የተረጋገጡ ዘዴዎች
➡️ጠንካራ የወላጅ እና የልጅ ትስስር ለመፍጠር የሚረዱ ስልቶች
➡️የውጤታማ ግንኙነት እና ግጭት አፈታት ምክሮች
➡️የተግባራዊ ልምምድ እና የህይወት ተሞክሮዎች

ቀን: ጥቅምት 23፣ 2017 ዓ.ም
🕖 ሰዓት: ከ8:00 - 11:00
📍ቦታ: ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክስ ማህበር አዳራሽ (ሲ ኤ ም ሲ ሚካኤል)

በልጆ ህይወት ላይ ዘላቂ የሆነ አዉንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር ይህ እድል እንዳያመልጦት።
ልጆቻችን የሚበቅሉበትን እና የሚያብቡበትን ማህበራዊ አካባቢ ለመፍጠር በጋራ እንስራ።

ውስን ቦታዎች ስላሉ ፈጥነው ይመዝገቡ።
ለበለጠ መረጃ እና ለመመዝገብ
☎️0946444445 ይደውሉ።

የመጀመሪያውን እርምጃ ወደ አውንታዊ ወላጅነት አብረን እንጀምር፣

2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል Charge UP! For an effective school year!አዲሱን የትምህርት አመት ጅማሮን አስመልክቶ መልካም ጅማሮ ልዪነት ይፈጥራል በሚል ለተማሪዎች የተዘጋጀ...
10/10/2024

2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል
Charge UP! For an effective school year!

አዲሱን የትምህርት አመት ጅማሮን አስመልክቶ መልካም ጅማሮ ልዪነት ይፈጥራል በሚል ለተማሪዎች የተዘጋጀ ልዪ የስልጠና ፕሮግራም።

ስልጠናው ለተማሪዎች ስኬታማ፣ አሳታፊ፣ እና ጠቃሚ የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉትን መሳሪያዎች ለማስታጠቅ የተዘጋጀ ስልጠና ነው።

ቅዳሜ ጥቅምት 2, 2017 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሴሽን ከቀኑ 8:00- 11:00 ሰዓት

ለመመዝገብ 0946444445 ይደውሉ ጥቂት ቦታዎች ስላሉ ፈጥነው ይመዝገቡ።

ቅዳሜ ጥቅምት 2, 2017 ዓ/ም

የክረምት ብልጭታ ድግሳችን 3 ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እርሶ ተመዝግበዋል?ፈጥነው ይመዝገቡ፣የወላጅነት ማራቶን ትጥቆን ይልበሱ።☎️ 0946444445
10/07/2024

የክረምት ብልጭታ ድግሳችን 3 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
እርሶ ተመዝግበዋል?
ፈጥነው ይመዝገቡ፣የወላጅነት ማራቶን ትጥቆን ይልበሱ።
☎️ 0946444445

29/06/2024

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when OASIS Center for Quality Life posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram