Gandhi Memorial Hospital ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል

Gandhi Memorial Hospital                  ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል Gandhi Memorial Hospital is a pioneer Maternal and Neonatal Health Hospital located in Addis Ababa E

ይነበብ....የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ___________የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊ...
29/04/2026

ይነበብ....
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
___________

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ባለሙያዎች በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ስለዚህም አዲስ በለማው ሲስተም መረጃችሁን ለማስገባት የብሄራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (National ID FAN 16 Digit) እና ስልክ ቁጥር አስፈላጊ በመሆኑ ተመዛኞች ከሚያዚያ 21/2018 እስከ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ይህንን https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ/Link/ በመጫን ከላይ የተገለጸውን እንዲሁም ሲስተሙ የሚጠይቃችሁን መረጃ በማሟላት ለምዝገባ ዝግጁ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የጤና ሚኒስቴር ቴሌግራም ቻናል ይመልከቱ፡ t.me/M0H_EThiopia

ሜዲካል ቱሪዝም...‎''ጤና ተቋማትን ለተገልጋይ ምቹ ማድረግ፣ የጤና አገልግሎቱን ማሻሻል እና ሀገራችን ለሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው  ይቀጥላሉ" ጠቅላይ ...
29/04/2026

ሜዲካል ቱሪዝም...

‎''ጤና ተቋማትን ለተገልጋይ ምቹ ማድረግ፣ የጤና አገልግሎቱን ማሻሻል እና ሀገራችን ለሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ።

"የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ!" በሚል መሪ ቃል በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት የለዉጥ ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች ላይ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ በጤናዉ ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን አስመልክቶ ሪፓርት ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለ30 ዓመታት የቆየውን የጤና ፖሊሲ ከአገራዊ ራዕይ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር በመጣጣም፣ እያደገ የመጣውን የሕዝባችን ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት እና ከወቅቱ ጋር በተናበበ መልኩ የጤና ፖሊሲ ክለሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች የአስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር ውጤታማ እና ወቅታዊ ትንበያ፣ መከላከል፣ ቅድመ ልየታ፣ ፈጣን ምላሽ፣ ቁጥጥር፣ መልሶ በማቋቋም የማህበረሰብ ደህንነት ላይ ጫና የሚያሳድሩትን የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ቀውስ ለመቋቋምና ለመቀነስ የሚያስችል ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር መዘርጋቱን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለአብነትም ኮቪድ 19 ን ጨምሮ በቅርቡ የተከሰቱ MPoX እና ማርበርግ ወረርሽኞችን ከፍተኛ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር መቻሉን አዉስተዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በማጠቃልያ ንግግራቸውም የማህበራዊ ዘርፍ ልማት ምንም እንኳን ዉጤቱ በአጭር ግዜ ዉስጥ የሚታይ ባይሆንም ለትዉልድና ሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በጤናዉ ዘርፍ የግሉንም በማሳተፍ እየተመዘገቡ ያሉ ዉጤቶች አበረታች መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ዐብይ አህመድ የህብተሰቡን ፍላጎት ያማከለ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ጤና ተቋማትን ለተገልጋይ ምቹ ማድረግ፣ የጤና አገልግሎቱን ማሻሻል እና ሀገራችን ለሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የከተማ አስተዳደራችንን የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ገምግመን ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀናል።በግምገማችንም ከአምስት ዓመት አንፃር የደረስንበትን እያነፃፀርን፣ የተገኙ ውጤቶች እና  ...
28/04/2026

የከተማ አስተዳደራችንን የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ገምግመን ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀናል።

በግምገማችንም ከአምስት ዓመት አንፃር የደረስንበትን እያነፃፀርን፣ የተገኙ ውጤቶች እና ተስፋ ሰጪ አፈጻጸሞች እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል ያለባቸው ተግባራትን ለይተናል።
የ9 ወር አፈፃፀምን ጨምሮ ባለፋት አምስት አመታት ከተከናወኑ በርካታ ተግባራት ዋና ዋናዎቹን ለአብነት ያህል:-

• ስር የሰደዱ ኋላ ቀር አስተሳሰቦችንና ችግሮችን ተጋፍጠን የጋራ እሴት ግንባታ ላይ በትጋት ሰርተናል። በዚህም አዲስ አበባን ከሰፈር ፖለቲካ አውጥተን፣ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷ ይበልጥ ጎልብቶና አድጎ ከተማችን ከእኔነት ወደ የሁላችን ከተማነት ከፍ አድርገናታል። በዚህም ለኢትዮዽያዊያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊያን ሁሉ ዋና ከተማችን ብለው የሚኮሩባት ከተማ አድርገናታል።
“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እናደርጋታለን” ብለን በገባነው ቃል መሰረት:-
• የከተማችንን ጎስቋላ ገጽታ ለመቀየር 74 በመቶ የሚሆነውን የጭቃ ቤት ወደ ውብ ምቹ ከተማ ለቀየር በሰራነው ሥራ በ44 በመቶ መቀነስ ችለናል።
• ለተማሪዎቻችን የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም እና ዩኒፎርም የማቅረብ የትውልድ ግንባታን አከናውነናል።
• የአዲስ አበባ ህጻናት ቦርቀው የሚጫወቱበት ከ5 ሺህ በላይ የልጆች መጫወቻ፣ እንክብካቤ የሚያገኙበት ከ1000 በላይ ዴይ ኬር ገንብተን በርካታ ወላጆችን እፎይ አስብለናል።
• በከተማችን 30 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላትን በመገንባት ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣ አቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖቻችንን ተጠቃሚ አድርገናል።
• በ “የለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል” በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ከአስከፊ ህይወት እንዲወጡና በተጨባጭ የሥራ ባለቤት እንዲሆኑ ተደርጓል።
• የአረጋዊያን መጦሪያ ፣ መስማትና ማየት ለተሳናቸው ት/ቤቶች ተገንብተው ልማታችን ማንንም ወደ ኋላ የተወ እንዳይሆን በጥንቃቄ ሰርተናል።
• የተበከሉ ወንዞች ፀድተው፣ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ እና በቆሸሹ የወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች ይኖሩ ለነበሩ ነዋሪዎች የተሻለ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ተሰጥተዋል።
• ጨለማ የነበሩ ጐዳናዎች በርተዋል ። በዚህም ለወንጀል፣ ለዝርፊያ እና ለአስገድዶ መድፈር አጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች ተቀይረዋል።
• በየሜዳው ከመፀዳዳት ለህዝባችን ምቾትን የሚጨምሩና ክብርን የሚጠብቁ እንዲሁም ጤናው እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ንጹህ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎችን በስፋት ገንብተናል።

• የመንገድ ሽፋንን ከ12 % ወደ 20 % አሳድገናል። በርካታ የመኪና ማቆሚያዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች፣ ሰፋፊ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች እና ማጣሪያ ማዕከላት ተገንብተዋል።
• የከተማችንን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከ70 % በላይ ማሳደግ ችለናል።
• የቤት አቅርቦትን 480 ሺህ አድርሰናል ።
• ወጣቶች በአካል እና በአዕምሮ የዳበሩ እንዲሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያ እና ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት መወዳደሪያ ማዕከላት በየአካባቢው ገንብተናል።
• አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሲደረጉ፣ ነባሮቹም ታደሰው ደረጃውን ለጠበቀ አገልግሎት ዝግጁ ተደርገዋል።
• የከተማዋን የመንገድ እና የአረንጓዴ ስፍራ ሽፋን ከ2.8 % ወደ 24 % አሳድገናል።
• ከአፍሪካ አስር ንጹህ ከተሞች አዲስ አበባ አንዷ ንጹህ ከተማ መሆን ችላለች።
• በዚህም የቱሪዝም ማዕከል በመሆን በ2018 ዘጠኝ ወራት ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ኮንፍራንሶችን አስተናግደናል።
• በህዝብ ተሳትፎ እና በመንግስት በጀት ከ60 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
• ከፍተኛ ተግዳሮት የሆነብንን ስር የሰደደ ቀርፋፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እና የጉበኝነት ልምምድ ለመለወጥ የመንግስት አገልግሎቶችን በ6 የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በአንድ ዲጅታል ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት መስጠት የቻልን ሲሆን፣ ቀሪ 5 ማዕከላት በቅርቡ ወደ ስራ ይገባሉ።
• ሌላኛው ተግዳሮት የሆነብንን የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ የገበያ ማዕከላትን እና የእሁድ ገበያዎችን በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች አስፋፍተናል።
አሁን ያገኘናቸውን ስኬቶች እና አፈጻጸም በቀጣይ የበለጠ በማጠናከር ከተማችንን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ መግባባት ላይ ደርሰናል።
በመሆኑም በልማት፣ በሰላም፣ በማህበራዊ ስራዎች አብሮን ሳይለየን የሰራውን መላው የከተማችን ነዋሪ በጣም እናመሰግናለን።

ከሁሉ በላይ ያሳካልን ፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይገባዋል!!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ!

የከተማ አስተዳደራችንን  የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት  ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል። በበጀት ዓመቱ በእቅድ  ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል። ለሁለት ተከታ...
26/04/2026

የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።

በበጀት ዓመቱ በእቅድ ከያዝናቸው ተግባራት 96 በመቶ መፈፀም ችለናል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም ካቀድናቸው ውስጥ በ9 ወራት በጥብቅ ክትትል የተከናወኑትን የምንገመግምበት እና በቀሪ ወራት የትኩረት ማዕከል አድርገን የምንፈፅማቸው በመልካም አስተዳደር ተለይተው ያልተመለሱትን ምላሽ በመስጠት ማጠናቀቅ፣ የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ችግሮችን በመቀነስ የዋጋ ንረትን መከላከል፣ የገበያ ማዛባት ችግሮችን መከላከል፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በመሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት የጀመርነውን ውጤታማ ስራ በቀሪ ወራት በተሟላ ሁኔታ በማጠናቀቅና ወደ ስራ ማስገባት እንዲሁም ቀሪ አገልግሎቶችን ዲጅታላይዝ አድርጎ ወደ መሶብ ማስገባት፣ ተጀምረው በዚህ ዓመት መጠናቀቅ ያለባቸውን ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የአፈፃፀም ግምገማ ማዕከላችን ይሆናሉ።

ባለፉት አምስት ዓመታት የእቅድ አፈፃፀማችን ከ90 በመቶ በላይ እያደገ መጥቶ በ2018 ደግሞ 96 በመቶ የደረሰበት ውጤታማ አፈፃፀም መኖሩን በመገምገም፣ ይህንን እያደገ የመጣ የመፈፀም ልምድ አጠናክረን መቀጠል እንድንችል በትኩረት እንገመግማለን ።

በተጨማሪም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነፃ፣ ተዓማኒና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን ሁሉም አመራራችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ ሃላፊነት መወጣት እንዲችሉ የግምገማ አቅጣጫን አስቀምጠናል።

የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል፣ ጉድለቶችን በመሙላት በቀሪዎች ወራት በላቀ መፈፀም የግምግማችን ማዕከል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የስልጠና ማዕከል ለዳይሬክተሮች እና ለቡድን መሪዎች በአመራር ክህሎት ዙሪያ የተሠናዳዉ አሳታፊ መድረክ ለሁለት ቀናት ተከናዉኗል።የህይወት ክህሎት፣የግጭት አፈታት አ...
23/04/2026

በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የስልጠና ማዕከል ለዳይሬክተሮች እና ለቡድን መሪዎች በአመራር ክህሎት ዙሪያ የተሠናዳዉ አሳታፊ መድረክ ለሁለት ቀናት ተከናዉኗል።

የህይወት ክህሎት፣የግጭት አፈታት አንዲሁም ሚዛናዊ አስተሳሰብን ለማዳበር የሚያግዙ ነጥቦች ተነስተዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለገብርኤል ኪዳኔ መድረኩን ለታደሙ የቋሙ ሃላፊዎች የሆስፒታሉን ራዕይ ለማሳካት ከፈፃሚዎች ጋር እጅና ጓንት ሆነዉ መስራት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
15/08/2018
👉 Follow us on tiktok
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZM-91G3us8dOF2

" ደም በመለገስ የሰዉ ህይወት እናድን ! " በሚል መሪ ቃል  በሆስፒታላችን ቅጥር ግቢ ሲካሄድ የነበረዉ የ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር የደም ልገሳ መርሐ-ግብር በሰኬት ተጠናቋል።14/08/20...
22/04/2026

" ደም በመለገስ የሰዉ ህይወት እናድን ! " በሚል መሪ ቃል በሆስፒታላችን ቅጥር ግቢ ሲካሄድ የነበረዉ የ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር የደም ልገሳ መርሐ-ግብር በሰኬት ተጠናቋል።
14/08/2018
👉 Follow us on tiktok
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZM-91G3us8dOF2

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!ሁልጊዜም በበዓላት ወቅት እንደምናደርገው፣ ዛሬ በትንሣኤ በዓል ዋዜማ በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የገ...
11/04/2026

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

ሁልጊዜም በበዓላት ወቅት እንደምናደርገው፣ ዛሬ በትንሣኤ በዓል ዋዜማ በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የገነባናቸውን 215 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች፤ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአገር ባለውለታዎችና ለልማት ተነሺዎች ከሙሉ የቤት ቁሳቁስና ከበዓል መዋያ ጋር በስጦታ አበርክተናል።

በከተማችን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተና ባህል እየሆነ መምጣቱ የሚያስደስት ነው። ይህንን በጎ ተግባር በተለያየ መልኩ ለደገፋችሁ ልበ ቀና በጎ ፈቃደኞች፣ ተቋማትና አመራሮች በሙሉ በተለይም ከ 80 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ላደረገው የኦሮሚያ ባንክ በተጠቃሚዎች ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የትንሣኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ በፍቅር ራሱን እስከ መስቀል የሰጠበት እና በትንሣኤ የምሥራች የተበሰረበት ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በትሳኤን ዓላማ እና ምሳሌነት መሰረት በታላቅ ፍቅር እና መተሳሰብ ሊሆን ይገባል። ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን መተሳሰብ በተግባር የምንገልጽበት፣ አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም እና የአብሮነት ምክንያት የምንሆንበት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Address

Addis Ababa
782

Telephone

+251115514981

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gandhi Memorial Hospital ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Gandhi Memorial Hospital ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል:

Share

Category