
10/09/2025
እንኳን ለ2018 ዓ/ም አደረሳችሁ!
በአገሪቱ የጤና አጠባበቅ ረገድ ጉልህ ሚና ያለው የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር ከተመሰረተ ከ36 አመት በላይ ሆኖታል።
ማኅበሩ 11,000 የሚጠጉ በልዩ ልዩ ዘርፍ የተሰማሩ አንጋፋና ወጣት አባላትን አቅፎ የያዘ ሲሆን ከመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት ይሰራል።
የተሻለ የጤና አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ማኅበሩ የሙያና ስነምግባር ክህሎትን ለማሳደግ የሚረዳ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና (CPD) ይሰጣል።
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና በሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ለሚሰሩ አባላቱ በጥናትና ምርምር የላቀ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚያስችል ተቋማዊ የጥናትና ምርምር ግምገማ ኮሚቴ (IRERC) ያለው በመሆኑ ለበርካታ ድርጅቶችና ግለሰቦች አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ ሲሆን በዚህም እውቅናን አግኝቷል።
የጤና አገልግሎት ጥራት ከማኅበሩ እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ልዩ ልዩ የምርምር ማእከላትን የያዘ ባለ 7 ወለል ህንጻ በማስገንባት ማኅበሩ ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራ አስቀምጧል።
በተጨማሪም ዘመናዊ ቤተ መጽሐፍትና ማተሚያ ቤት ያለው በመሆኑ አባላቱንና አጋር ድርጅቶችን በትጋት በማገልገል ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር የዓለም የጤና ኮንግረስን ጨምሮ ታላላቅ ሳይንሳዊ ኮንፍረንሶችን በማስተባበር በአገራችን ተጠቃሽ ሚና ካላቸው ማኅበራት ተርታ ከፊት የሚሰለፍ ነው።
የኢትዮጵያ ሙያ ማኅበራት ሕብረት (EPAA) ሰብሳቢም በመሆኑ ከሌሎች ሙያ ማኅበራት ጋር በመቀናጀት በ2018 ዓ/ም ታላቅ አገር አቀፍ ኮንፍረንስ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነው።
ማኅበሩ በየአመቱ በርካታ የጥናት ውጤቶችን በአመታዊ ጉባኤው ከማቅረብ በዘለለ፤ ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን በማሳተምና በማሰራጨት ለማኅበረሰቡ ተደራሽ ያደርጋል።
የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር በአገሪቱ ማንኛውም አይነት የጤና ችግር በተከሰተ ጊዜ በፈጥኖ ደራሽነቱ የተመሰከረለት ማኅበር ነው።
በአዲሱ አመት የዚህ ማኅበር አባል እንዲሆኑ የአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።
መልካም አዲስ ዓመት!