Shalom Herbal Healing center

  • Home
  • Shalom Herbal Healing center

Shalom Herbal Healing  center Natural healing for body & soul 🌿 | 100% traditional remedies | Herbal food & medicine in harmony.

06/07/2025

Celebrating my 7th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

ምናልባት ዘመኑን በዋጀው የ TikTok  መንደር በቪድዮ መልካሙን የእፅዋት ትምህርታችን መከታተል ቢሹ ይህ ሊንክ በመጫን ዘመድ ይሁኑ::
24/06/2025

ምናልባት ዘመኑን በዋጀው የ TikTok መንደር በቪድዮ መልካሙን የእፅዋት ትምህርታችን መከታተል ቢሹ ይህ ሊንክ በመጫን ዘመድ ይሁኑ::

9356 Followers, 4 Following, 16.0k Likes - Watch awesome short videos created by Shalom Herbal Healing

ለከባድ ሳል/ ጉንፋን #ግማሽ ሌትር የላም ወተት #የተፈጨ ትንሽ ማንኪያ ነጭ ዕጣን #ሰባት ፍሬ የተፈጨ የቁርንፉድ ፍሬእነዚህን አንድ ላይ በወተቱ ላይ በማፍላት ጧት ጧት ለ 3 ቀን መጠጣት ...
15/06/2025

ለከባድ ሳል/ ጉንፋን

#ግማሽ ሌትር የላም ወተት
#የተፈጨ ትንሽ ማንኪያ ነጭ ዕጣን
#ሰባት ፍሬ የተፈጨ የቁርንፉድ ፍሬ

እነዚህን አንድ ላይ በወተቱ ላይ በማፍላት ጧት ጧት ለ 3 ቀን መጠጣት ነው::

ፍቱን ነው ይድናል::

Traditional healer | Natural remedies 🌿 | Healing body & soul with herbs 🍃
አድራሻችን~
ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በመሳለምያ ወደ ካራ በሚያስወጣው መንገድ ገጠር መናፈሻ አጠገብ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍ ብለው ቢደውሉልን አድራሻችን ያገኙታል።

መልእክት ለማስቀመጥ
https://t.me/Shalomso
#0929922070
#0911274140

"ስመ እግዚአብሔር ዘተሰብሐ ይኩን ለዘአብጽሐነ ለዛቲ ዕለት "❤❤                     የሞትን ቁራኝነት በደሙ አጠፋ           ሲኦል በብርሀን ተጥለቀለቀች            ...
20/04/2025

"ስመ እግዚአብሔር ዘተሰብሐ ይኩን ለዘአብጽሐነ ለዛቲ ዕለት "❤❤

የሞትን ቁራኝነት በደሙ አጠፋ
ሲኦል በብርሀን ተጥለቀለቀች
ነፍሳት በደስታ ከሲኦል
ተፈተለኩ ከቁራኝነት ነፃ
አውጥቷቸዋልና ዲያቢሎስን
ድል መታው ገሀነምም ፈራረሰ
ሲኦልም ተዘጋ 💛💛

እነሆ የዓለም መድኃኒት እሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል👏👏👏 እንኳን አደረሳችሁ።

ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ አሎሄ። ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅፀነ ነፍሶ ሶቤሃ። ጊዜ ተስዓቱ ...
18/04/2025

ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ አሎሄ። ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅፀነ ነፍሶ ሶቤሃ። ጊዜ ተስዓቱ ...

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሃገረ ዳዊት።"ከአባቱ ሳይወጣ መጣ፣ ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ። ከሦስትነቱ ሳይለይ መጣ፣ ከአንድነቱም ሳይለይ ወረደ። ከ...
07/01/2025

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ
ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሃገረ ዳዊት።

"ከአባቱ ሳይወጣ መጣ፣ ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ። ከሦስትነቱ ሳይለይ መጣ፣ ከአንድነቱም ሳይለይ ወረደ። ከዙፋኑ ሳይለይ በሥጋ ልጅ አደረ። ምላቱ ሳይወሰን በማኅፀን ተጸነሰ፣ በላይ ሳይጎድል በማኅፀን ተወሰነ፤ በታችም ሳይጨመርበት ተወለደ። ከኃጢአት በቀር ፈጽሞ ሰው ሆነ። እንደ እግዚአብሔር እየሠራ እንደ ባርያ ታዬ። ወንጌሉን ያስተማሩ እንደመሰከሩ። ከአባቱ ዘንድ ተመሰገነ፣ ከራሱም ከበረ። የጌትነቱም ምስጋና በሰማይና በምድር መላ። እኛም እንግዲህ በልቡናችንዘወትር አናርፍም። ቅዱስ እያልንም የጌትነቱን ምስጋና እንናገራለን።"
/ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ/

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን። በግርግም ተወልዶ የእኛን ራቁትነት ያራቀ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በትልቅ መከራ እና ችግር ውስጥ ያለችውን ሀገራችንን ከመከራ እና ከችግር አላቅቆ የምሕረት እና የይቅርታ ልብስ ያልብስልን።

ሻሎም ነኝ!

የመጽሐፍ ምርቃት መዝሙረ ዳዊት በዓለ ምልክት ሊመረቅ ነው🙏  #የንባብ መማርያ #የጸዋትወ ዜማ ማስተማርያ #ለጸሎት መገልገያይህ መዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሊገለገልበት የሚችል ...
05/12/2024

የመጽሐፍ ምርቃት
መዝሙረ ዳዊት በዓለ ምልክት ሊመረቅ ነው🙏
#የንባብ መማርያ
#የጸዋትወ ዜማ ማስተማርያ
#ለጸሎት መገልገያ

ይህ መዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሊገለገልበት የሚችል ባል ምልክት መዝሙረ ዳዊት ነው::

👉ለቅኔ ተማሪዎች
👉ለዜማ ተማሪዎች
👉ለአቋቋም ተማሪዎች
👉እንዲሁም ለቅዳሴ ተማሪዎች እጅጉን የሚረዳ ትልቅ ድንቅ መጽሐፍ ነው::

ይህ የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ እጁ ላይ ያለው ሰው ግእዝ አልተማርኩም ለማንበብ እቸገራለሁ ብሎ ነገር የለም!
ምክንያቱም አራት አይነት የአነባበብ ስልት የያዘ
#ተነሽ
#ተጣይ
#ሰያፍ
#ወዳቂ የሚያመላክት ድንቅ መጽሐፍ ነውና፣፣
የሚላላ እና የሚጠብቁትን ቃላት አበጥሮ በምልክት የሚያስረዳ በደንብ ታርሞ የተዘጋጀ መምህር ለምኔ መጽሐፍ ነው::

አዘጋጅ!
የኔታ ጽጌ ገ/ማርያም
የዱጋ ዝማሬ መዋስእት መምህር

መጽሐፉን በጅምላ እንዲሁም በፍሬ መግዛትን ቢፈልጉ መምህሩን በዚህ ቁጥር ማግኘት ይችላሉ::

ስ.ቁ0918190165

🌼እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን አዲሱ ዓመት🌼የሰላም :የፍቅር :የአንድነት :የመቻቻል :የጥበብ :የጤና :የሃብት :የመከባበር :የምሕረት እንዲሁም የጎደለውን የ...
11/09/2024

🌼እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን አዲሱ ዓመት🌼የሰላም :የፍቅር :የአንድነት :የመቻቻል :የጥበብ :የጤና :የሃብት :የመከባበር :የምሕረት እንዲሁም የጎደለውን የሚሞላበት የታመመውን የሚድንበት የታሰሩትም የሚፈቱበት የተጣሉትም የሚታረቁበት የከበረ ያበበ ዘመን ያድርግልን🙏
መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን አሜን
Happy Ethiopian new
year2017🌼🌼🌼🌼
ሻሎም ነኝ!

በባሕል ሐኪም ተጭበርብረው ያውቃሉ❓❓❓👉እውነተኛ ዶክተር እና በስም ዶክተር እንዳለ ሁሉ እውነተኛ የባሕል ሐኪም እና ሃሰተኛ የባሕል ሐኪም የለም ማለት አንችልምና እንመርምር!ውድ የሆነ እውቀ...
29/04/2024

በባሕል ሐኪም ተጭበርብረው ያውቃሉ❓❓❓

👉እውነተኛ ዶክተር እና በስም ዶክተር እንዳለ ሁሉ እውነተኛ የባሕል ሐኪም እና ሃሰተኛ የባሕል ሐኪም የለም ማለት አንችልምና እንመርምር!

ውድ የሆነ እውቀት ውድ እውቀትን በሚጠሉ ሰዎች አያሌ ሊቃውንት ጥበበኞች ለምን ይሸማቀቁ❓

🙏ሰላም ሰላም የዚህ ቻናል ውድ ቤተሰቦች እና የጥበብ ባለቤቶች!
ጠበብን እና እጽዋትን በሰፊው መልኩ በሶሻል ሚድያ የማስተዋወቅ ስራ ፈር ቀዳጅ በሚባል መልኩ ሰፋ አድርገን የጀምረነው ቢሆንም ቅሉ !

ከ 2 ዓመት ወዲህ ግን በሶሻል ሚድያ እንደጠበቅነው መራመድ አልቻልንም::
ለ 6 እና 7 ዓመታት ያህል ለተለያዩ መንፈሳዊ እና የስጋ ደዌ ህመሞች እንዲሁም ለሌሎች ህመሞች የሚረዱ መንፈሳዊ እና ጥበባዊ መፍትሔዎችን ስንማማር እንዲሁም ሕክምና ስንሰጥ ቆይተናል::

#እንዲሁም ከዚህ በፊት የተማማርናቸው ድንቅ የፈጣሪ ጥበብ በራሳቸው መጠቀም ላልቻሉ በአድራሻችን መሰረት በመምጣት ለቁጥር በሚያዳግት መልኩ እጅግ ብዙ ቤተሰቦች በፈጣሪ ኃይል ፈውስ አግኝተዋል ብዙዎቹ ምስክር ናቸውና!

#ከዚህም አልፈው በውጭም በሃገር ውስጥም እንደየችግራቸው በቤታቸው በመጠቀም ብዙ ተስፋ እና ሰላም አግኝተዋል::አሁንም የተጠቀሙ ቤተሰቦች ምስክር ናቸውና!

#እንደጠበቅነው አለመራመዳችን ደግሞ 👇

‼️ብዙዎች ለሕሊናቸው ያልተገዙ ሰዎች Coppy በማድረግ ብዙ የማጭበርበር ስራ በመስራት እዲሁም ያልተገባ ስራ ሲስሩ ሰዎችን ስያሳዝኑ በመመልከቴ :
‼️ጊዜው በፈጠረው ዘመናዊ ቴክነሎጂ በመታገዝ ሰዎችን በማሳመን ያለእውቀት እና በድፍረት ከፈውስ ይልቅ በሽታን የሚፈጥሩ አካላት በመብዛታቸው:
‼️የኛ ሎጎ እና ተመሳሳይ ስያሜ በመያዝ ጭራሽ እኛን የማይመለከቱ አጋንንታዊ ይዘት ያላቸው አስተምህሮዎች እና ክፉ ድርጊቶች ስያስተላልፉ በመረዳቴ:
ከድህረገጹ በስሱ በመራቅ በቅርበት መጥተው መፍትሔ ለሚወስዱ እንዲሁም እውቀት ለሚገበዩ በቅርበት ስናስተናግድ ቆይተናል::
ይህ ጥበባዊ ትምህርት በሌላ የተሻለ መንገድ እንመጣ ዘንድም የተቻለንን ነገር እይሞከርን እንገኛለን::

ምክር!
⁉️የትም የባሕል ሐኪም መሄድን ቢሹ!⁉️

#ትክክለኛ የመገኛ አድራሻ መኖሩን ያረጋግጡ::
#ትክክለኛ ሕጋዊ ፈቃድ መያዙን ያረጋግጡ::
#ሰው በሰው አልያም በትክክል የዳነ ሰው መኖሩን ያረጋግጡ!
#ረዥም የስራ ልምድ እና መልካም የሆነ ግንዛቤ ቢኖረው ደግ ነው::
#በስልክ ብቻ አውርተው መገኛችን ሩቅ ነው ብር አስገቡ ክሚሏችሁ ተጠንቀቁ::
#በተቻለ መጠን ልጥፋቸው Coppy አለመሆኑን ያረጋግጡ::

አድራሻችን ለምትሹ👇
ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በመሳለምያ ወደ ካራ በሚያስወጣው መንገድ ገጠር መናፈሻ አጠገብ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍ ብለው ደውለልን ቢመጡ ያገኙናል::

#ለበለጠ መረጃ
#0911274140
#0929922070

የቴሌግራም ቻናላችን ለመቀላቀል
https://t.me/+TQcAXSzUFJAiH3BQ

መልእክት ለማስቀመጥ
https://t.me/Shalomso

‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️ስለ አድራሻ ለውጥአዲሱ እና በእድሳት ምክንያት የቀየርነው አዲሱ የስራ ቦታችን--- ከመምህራን ኮሌጅ በመሳለምያ ወደ ካራ በሚያስወጣው መንገድ ገጠር መናፈሻ አጠገ...
20/04/2024

‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ስለ አድራሻ ለውጥ
አዲሱ እና በእድሳት ምክንያት የቀየርነው አዲሱ የስራ ቦታችን---

ከመምህራን ኮሌጅ በመሳለምያ ወደ ካራ በሚያስወጣው መንገድ ገጠር መናፈሻ አጠገብ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍ ብለው ቢደውሉልን አድራሻችን ያገኙታል።

ሻሎም ነኝ!

👉🏾በአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ እና በፈጣሪ ኃይል፣ ከህይወትዎ ላይ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችልና፣ እንዲሁም የብራና መጽሐፍት ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ::

አድራሻችን~
ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በመሳለምያ ወደ ካራ በሚያስወጣው መንገድ ገጠር መናፈሻ አጠገብ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍ ብለው ቢደውሉልን አድራሻችን ያገኙታል።

መልእክት ለማስቀመጥ
https://t.me/Shalomso

ለበለጠ መርጃ በስራ ሰዓት ይደውሉልን
☎️0911274140
☎️0929922070

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሃገረ ዳዊት።"ከአባቱ ሳይወጣ መጣ፣ ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ። ከሦስትነቱ ሳይለይ መጣ፣ ከአንድነቱም ሳይለይ ወረደ። ከ...
06/01/2024

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ
ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሃገረ ዳዊት።

"ከአባቱ ሳይወጣ መጣ፣ ከአነዋወሩ ሳይለይ ወረደ። ከሦስትነቱ ሳይለይ መጣ፣ ከአንድነቱም ሳይለይ ወረደ። ከዙፋኑ ሳይለይ በሥጋ ልጅ አደረ። ምላቱ ሳይወሰን በማኅፀን ተጸነሰ፣ በላይ ሳይጎድል በማኅፀን ተወሰነ፤ በታችም ሳይጨመርበት ተወለደ። ከኃጢአት በቀር ፈጽሞ ሰው ሆነ። እንደ እግዚአብሔር እየሠራ እንደ ባርያ ታዬ። ወንጌሉን ያስተማሩ እንደመሰከሩ። ከአባቱ ዘንድ ተመሰገነ፣ ከራሱም ከበረ። የጌትነቱም ምስጋና በሰማይና በምድር መላ። እኛም እንግዲህ በልቡናችንዘወትር አናርፍም። ቅዱስ እያልንም የጌትነቱን ምስጋና እንናገራለን።"
/ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ/

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን። በግርግም ተወልዶ የእኛን ራቁትነት ያራቀ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በትልቅ መከራ እና ችግር ውስጥ ያለችውን ሀገራችንን ከመከራ እና ከችግር አላቅቆ የምሕረት እና የይቅርታ ልብስ ያልብስልን።

ሻሎም ነኝ!

ይስማዕ ሰማይ ወትዜኑ ምድር ከመ ተረክበ ዮም   ለክርስቶስ ዕፅ ዘለከፎ ደሙ ክቡር ዝንቱ ውእቱ  #መስቀል ዕፅ ዘኢያፀንኖ ኃይለ ነፋሳት ዘአዳም ቆሙ ወሠናይ ራዕዩ መካን ዘደፈኑ አይሁድ   ...
27/09/2023

ይስማዕ ሰማይ ወትዜኑ ምድር ከመ ተረክበ ዮም ለክርስቶስ ዕፅ ዘለከፎ ደሙ ክቡር ዝንቱ ውእቱ #መስቀል ዕፅ ዘኢያፀንኖ ኃይለ ነፋሳት ዘአዳም ቆሙ ወሠናይ ራዕዩ መካን ዘደፈኑ አይሁድ #መስቀል ቃል ቅዱስ ወተረክበ በሐሢሥ ዕፅ ዘቀደሶ ወባረኮ ክርስቶስ ፤

" የከበረ የክርስቶስ ደሙ የቀደሰው እንደ ተገኘ ምድር ትናገር ሰማይም ታድምጥ፤ እርሱም የነፋሳትን ኃይል የማያጸነው መልኩ ያማረና ቁመቱ የተወደደ አይሁድ በመካነ ጎልጎታ የቀበሩት ክርስቶስ የቀደሰውና የባረከው ዕፅ በፍለጋ ተገኘ ።"

ቅዱስ ያሬድ ( ዝማሬ መዋስዕት ዘመስቀል)

መልካም የመስቀል በዓል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ቤተሰቦች::

#ሻሎም

Address


Opening Hours

Monday 03:00 - 10:00
Tuesday 03:00 - 10:00
Wednesday 03:00 - 10:00
Thursday 03:00 - 10:00
Friday 03:00 - 10:00
Saturday 04:00 - 17:00

Telephone

+251929922070

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shalom Herbal Healing center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Shalom Herbal Healing center:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Opening Hours
  • Alerts
  • Contact The Practice
  • Claim ownership or report listing
  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share