Urology in Ethiopia- የኩላሊት፥ ሽንት ቧንቧ፥ የፕሮስቴትና የወንድ ስነ-ተዋልዶ በኢትዮጵያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Urology in Ethiopia- የኩላሊት፥ ሽንት ቧንቧ፥ የፕሮስቴትና የወንድ ስነ-ተዋልዶ በኢትዮጵያ

Urology in Ethiopia- የኩላሊት፥ ሽንት ቧንቧ፥ የፕሮስቴትና የወንድ ስነ-ተዋልዶ በኢትዮጵያ የኩላሊት፣ ሽንት ቧንቧ፣ ፕሮስቴትና የወንድ ስነ-ተዋልዶ የህክምናና ነፃ የምክር አገልግሎት! urology free consultancy
Addis Ababa, Ethiopia, 0975256636

30/11/2025

Celebrating my 7th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

ስለኩላሊት ካንሰር (Renal cell cancer) በጥቂቱ እነሆ:-°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°መግቢያ፦ በአሁኑ ጊዜ የኩላሊት ካንሰር(incidence) እየጨመረ ቢመ...
09/11/2025

ስለኩላሊት ካንሰር (Renal cell cancer) በጥቂቱ እነሆ:-
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
መግቢያ፦ በአሁኑ ጊዜ የኩላሊት ካንሰር(incidence) እየጨመረ ቢመጣም ገዳይነቱ ግን እየቀነሰ መምጣቱን ጥናቶች ያሳያሉ። ይህም ሊሆን የቻለው ህብረተሰቡ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ የማድረግ ልምድ ማዳበሩና በቀላል ምርመራ ማወቅ በመቻሉ በጊዜ ህክምናው ስለሚሰጥ ነው።
****

ለኩላሊት ካንሰር አጋላጭ ነገሮች(risk factors)

1) እድሜ መጨመር(ageing)
👉በተለይ 60 እና 70ዎቹ የዕድሜ ክልል ላይ የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
2) ወንድ መሆን( male gender)
👉ወንዶች ላይ የመከሰት ዕድሉ ከሴቶች የበለጠ ነው(M:F=~2:1)።
3) በዘረመል(genetic)
👉በዘር የመከሰት ዕድሉ በሁለት እጥፍ(2x) የሚደርስ ነው። በዘረመል የሚመጣው ካንሰር በወጣትነት የዕድሜ ክልልና በሁለቱም ኩላሊቶች ላይ ሊከሰት ይችላል።
4) ሲጋራ ማጨስ(smoking)
5) ውፍረት(obesity)
6) የደም ግፊት (hypertension)
7) በደም ዕጥበት የሚታከም የቆየ ኩላሊት ድክመት (chronic renal failure on dialysis)
*

የኩላሊት ካንሰር አይነቶች(histology)

ዋና ዋናዎቹ የኩላሊት ካንሰር አይነቶች:-

1) Clear cell Renal cell cancer
አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው(~75%) የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

2) Papillary Renal cell cancer
ከ10-15% የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

3) Chromophobe renal cell cancer
እስከ 5% የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

4) Cortical duct carcinoma
በአብዛኛው ታችኛው የዕድሜ ክልል ላይ የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር ሲሆን ብዙውን ጊዜ አይከሰትም(rare)።

5) Renal medullary carcinoma
👉በጣም ሊከሰት የማይችል(very rare) ነገር ግን በጣም ገዳይ የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው። በልዩነት የሲክል ሴል በሽተኞች(sickle cell disease) ላይ ይከሰታል።
እነዚህ የካንሰር አይነቶች በባሪያቸው ቅደም ተከተል ሲቀመጡ
*Papillary RCC(የተሻለው)-->Chromophobe RCC-->Clear cell RCC--> Collecting duct Ca-->Renal medullary ca(መጥፎው)
****

የኩላሊት ካንሰር ምልክቶች

👉50%ቱ ለሌላ ህክምና በሚደረግ የአልትራሳውንድ/ሲቲ ስካን ምርመራ ወቅት በአጋጣሚ የሚታወቅ/የሚገኝ(incidental) ነው። ይህም ማለት አብዛኛው የኩላሊት ካንሰር ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል።
👉 የሽንጥ ህመም(flank pain)
👉 የሽንጥ ዕብጠት(flank mass)
👉 ደም የቀላቀለ ሽንት(haematuria)
➜እነዚህ ሦስቱ ምልክቶች ከታዩ የካንሰር ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑንም ያመላክታሉ።
👉 ሌሎች ምልክቶች
➜ክብደት መቀነስ
➜የደም ግፊት(hypertension)
➜በደም ውስጥ የካልሽየም መጠን መጨመር(hypercalcemia)
➜የደም ማነስ(anemia) ወይም የደም መብዛት(polycythemia)
➜ የጉበት ችግር መከሰት(Stauffer's syndrome)
የኩላሊት ካንሰር መኖሩ በሚታወቅበት ጊዜ እስከ 20% ድረስ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ተሰራጭቶ ሊገኝ ይችላል። ይህም በደም ዝውውር ወይም በሊፍፋቲክ(hematogeneous or lymphatic) ሊሰራጭ ይችላል። በደም ዝውውር ወደ ሳንባ፣ አጥንት፣ ጉበትና አንጎል ሊሰራጭ ይችላል።
****

የምርመራ መንገዶች
1) አልትራሳውንድ(ultrasound)
👉ካንሰር መኖር አለመኖሩን በአልትራሳውንድ (በእርግጠኝነት ባይሆንም) ማወቅ ይቻላል።

2) ሲቲ ስካን(CT scan): ከአልትራሳውንድ በተሻለ የካንሰሩን መኖርና የካንሰሩን ደረጃ(stage) ለማወቅ ይጠቅማል።

3) MRI: በCT scan ማወቅ ካልቸቻለ ወይም CT scan ማንሳት የማይቻልባቸው ምክንያቾች ሲኖሩ ይታዘዛል።
****

የኩላሊት ካንሰር ደረጃዎች(staging)

👉እንደማንኛውም የካንሰር አይነት አራት ደረጃዎች(stage 1-stage 4) ሲኖሩት ደረጃው በጨመረ ቁጥር በካንሰር የመኖር(cancer specific survival)ዕድሜን ይቀንሳል::
****

የኩላሊት ካንሰር ህክምናዎች

1) ቀዶ ጥገና ህክምና(partial/radical/cytoreductive nephrectomy)፦ ለሁሉም የኩላሊት ካንሰር ደረጃዎች የሚደረግ ህክምና ነው(ወደሳንባ፣ አጥንት፣ ጉበትና አንጎል የተሰራጨን ካንሰር ጨምሮ) ።

2) የጨረር ህክምና፦ ወደ አጥንት(spine) እና አንጎል የተሰራጨውን ካንሰር ለማከም እንደ አማራጭ ህክምና ይወሰዳል።

3) Target and immunotherapy: በዋጋ ደረጃ ውድ ሲሆኑ በህይወት የመኖር ጊዜን እምብዛም አይጨምሩ

4) ኬሞ ቴራፒ(chemotherapy): የኩላሊት ካንሰር ሁሉንም ኬሞ ቴራፒዎች መቋቋም ስለሚችል እንደ አንድ የህክምና አማራጭ አይወሰድም።
****

የኩላሊት ካንሰር መጥፎ ትንቢያዎች(poor prognosis signs) ከሚያሳዩት ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።
1) የወረደ የሰውነት ወቅታዊ አቋም(poor performance status)
2) ትልቅ የዕጢ መጠን(larger tumor size)
3) ከፍተኛ የካንሰር ደረጃ(higher tumor stage)
4) የተሰራጨ ካንሰር(distant metastasis)
5) መጥፎ ካንሰር አይነት (bad histology type like collecting duct and renal medullary ca) እና ሌሎችም።
****

መውጫ
-በቀዶ ጥገና ህክምና ከኩላሊት ካንሰር ሙሉ በሙሉ ሊዳን(cured) ይችላል::
- የኩላሊት ካንሰር የኩላሊት ካንሰር ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገለት ሰው ከህክምና ክትትል መጥፋት የለበትም::

ዶ/ር ልጃለም መኮንን
የኩላሊትና ሽንት ቧንቧ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት(Urologist)
አዲስ አበባ

https://t.me/lijurologist
lijumekonnen4@gmail.com
0918028032

ስለ ፕሮስቴት   # በጥቂቱመግቢያ:- ፕሮስቴት ግላንድ (prostate gland):- የወንድ ልጅ ፊኛ መውጫን ከቦ የተቀመጠና ለስነ ተዋልዶ አስተዋፅኦ ያለው የሰውነት ክፍል ነው።   ኘሮስቴ...
02/11/2025

ስለ ፕሮስቴት # በጥቂቱ
መግቢያ:- ፕሮስቴት ግላንድ (prostate gland):- የወንድ ልጅ ፊኛ መውጫን ከቦ የተቀመጠና ለስነ ተዋልዶ አስተዋፅኦ ያለው የሰውነት ክፍል ነው።

ኘሮስቴት መጠን ከጨመረ ከ3ቱ አንዱ ሊሆን ይችላል። እነዚህም:-
1) Benign Prostatic Hyperplasia-BPH
2) prostate cancer እና
3) prostatitis ናቸው።

1) ገር የፕሮስቴት ዕድገት (Benign Prostatic Hyperplasia-BPH)

👉በአዛውንት የዕድሜ ክልል ከሚከሰቱ በሽታዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከ40 አመት ዕድሜ ጀምሮ ሊከሰት ይችላል። ዕድሜ ሲጨምር የመከሰት ዕድሉ አብሮ ይጨምራል(linear relation)። ይህም ማለት በ60አመት የዕድሜ ክልል ከ50% በላይ የመከሰት ዕድል ሲኖር 85አመት ላይ ደግሞ ከ90%በላይ ይከሰታል።

BPH መኖር/አለመኖሩን እንዴት ማወቅ ይቻላል? (ሀ ለ ሐ...)

ሀ) የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶች(LUTS) ሲከሰት
➜ገር የፕሮስቴት ዕድገት (Benign Prostatic Hyperplasia-BPH) ያለበት ሰው የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል እነዚህም(1,2,3)፦

1) ሽንት በሽንት ፊኛ የማጠራቀም ችግር( storage LUTS): እነዚህም

👉ሽንትን ቶሎ ቶሎ መሽናት (frequency): በቀን ከ6-8 በላይ መሽናት

👉ማጣደፍ (urgency): ሽንትን በተፈለገው ቦታና ሰዓት የመሽናት ችግር እስከ ሽንት ማምለጥ ሊደርስ ይችላል።

👉ሌሊት ከእንቅልፍ ተነስቶ ሽንት መሽናት (nocturia): ከሁለት ጊዜ በላይ ሌሊት ከእንቅልፍ ተነስቶ ሽንት መሽናት

2) ሽንት ከሽንት ፊኛ የማስወገድ ችግር (Voiding LUTS)

እነዚህም:-
👉ለመሽናት ማስማጥ (Straining)
👉ሽንት "ፏ" ብሎ አለመውረድ (weak urinary stream)
👉የሽንት መቆራረጥ (intermittency),
👉መዘግየት (hesitancy),
👉መንጠባጠብ (Dribbling)
👉ጨርሶ መሽናት አለመቻል (incomplete voiding)

3) ሌሎች ምልክቶች እንደ ሽንት መዝጋት (urinary retention)፥ ደም የቀላቀለ ሽንት መሽናት (hematuria)

ለ) የፕሮስቴት መጠንን በመለካት (Imaging)

👉በUltrasound: ሁልጊዜ የፕሮስቴት መጠንን ለመለካት የምንጠቀምበት ሲሆን የፕሮስቴት መጠኑ ከ30ግራም (30cc) ከሆነ የፕሮስቴት ዕደገት አለ እንላለን።

👉በMRI: በተለይ ለፕሮስቴት ካንሰር ምርመራ ተመራጭ ነው።

👉በCT scan: የፕሮስቴት ካንሰር ወደ ተለያዩ የሰውነታችን ክፍል ስርጭት መኖር አለመኖሩን ለማወቅ እንጠቀምበታለን።

ሐ) ከፕሮስቴት ናሙና (Prostate Biopsy) በመውሰድ
➜በመለስተኛ ቀዶ ጥገና የሚሰራ ነው።
➜ይህም ገር የፕሮስቴት ዕድገትን (Benign Prostatic Hyperplasia-BPH) የፕሮስቴት ካንሰር (Prostatic cancer) በእርግጠኝነት ለመለየት እንጠቀምበታለን።

ገር የፕሮስቴት ዕድገት (Benign Prostatic Hyperplasia-BPH) መቼ ነው ህክምና የሚደረገው?

👉ገር የፕሮስቴት ዕድገት መኖር በራሱ በሽታ አይደለም።

👉በሽታ የሚሆነው ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች ውስጥ በከፊል ወይም በሙሉውን ማምጣት ሲችል ብቻ መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው።

ህክምና የሚያስፈልግባቸው ሁኔታወች

1) መሃከለኛ (moderate) ወይም አደገኛ (severe) የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶች መከሰት፦ ይህም የዕለት ከዕለት ስራችንንና ጤናችንን ማወክ ሲጀምር

2) በBPH ምክንያት የኩላሊት ችግር ሲፈጠር (renal insufficiency)

3) ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽር ሲከሰት (recurrent urinary tract infection)

4) ተደጋጋሚ አጣዳፊ የሽንት መዝጋት ሲከሰት (recurrent acute urinary retention)

5) ስር የሰደደ የሽንት መዝጋት (chronic urinary retention)

6) ተደጋጋሚ ደም የቀላቀለ ሽንት መሽናት (persistent gross hematuria)

7) በፕሮስቴት ምክንያት የሽንት ፊኛ ጠጠር (bladder stone) መፈጠር እና

8) ከፍተኛ በሆነ የሽንት ማስማጥ የተከሰተ የአንጀት መውረድ (hernia) ከተከሰተ ናቸው

የገር የፕሮስቴት ዕድገት (BPH) የህክምና አይነቶች

1) ክትትል ብቻ ማድረግ (watchful waiting):-

👉ምንም አይነት ምልክት ለሌላቸው ወይም አነስተኛ (mild) ምልክት ለሚያሳዩ ሰዎች ያለምንም ቀዶ ጥገና ወይም መድኃኒት የሚደረግ ነው። በክትትል ወቅትም የመባባስ ምልክት ከተከሰተ ህክምናው እንዲጀመር ይደረጋል።

2) በመድሃኒት ህክምና (medical therapy)

👉መሃከለኛ (moderate) ወይም አደገኛ (severe) የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶች ሲኖር የሚጀመር ህክምና ሲሆን በየቀኑ ለብዙ ወራት የሚዋጥ መድኃኒት በመውሰድ የሚደረግ ህክምና ነው። እንደ አስፈላጊነቱም መድኃኒቱ ሊቆም ይችላል። በተለይ ወልደው ላልጨረሱ ወይም ቀዶ ህክምናን መቋቋም ለማይችሉ ወይም ቀዶ ጥገና ለማይፈልጉ ታካሚዎች ይሰጣል።

3) በቀዶ ጥገና ያደገውን ፕሮስቴት የማውጣት ህክምና (simple prostatectomy (ሆድ ተከፋቶ) or TURP (ሆድ ሳይከፈት) ናቸው):- ይህም የሚከተሉት ምልክቶት ሲኖሩ የሚደረግ ህክምና ነው። እነርሱም:-

1) የመድኃኒት ህክምናው ውጤት ሳያመጣ ሲቀር (failed medical therapy)

2)ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽር (recurrent urinary tract infection)

3) ተደጋጋሚ አጣዳፊ የሽንት መዝጋት ሲከሰት (recurrent acute urinary retention)

4) ስር የሰደደ የሽንት መዝጋት (chronic urinary retention)

5) የቆየ/ተደጋጋሚ ደም መሽናት (persistent gross hematuria) ሲኖር

6) በፕሮስቴት ምክንያት የሽንት ፊኛ ጠጠር (bladder stone) መፈጠርና

7) ከፍተኛ በሆነ የሽንት ማስማጥ የተከሰተ የአንጀት መውረድ (hernia) ሲከሰት ናቸው።

Ⓒሁለቱም የህክምና አይነቶች (የመድኃኒት ህክምናው ሆነ ቀዶ ጥገና ህክምናው) የየራሳቸው የሆኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሲኖሯቸው ታካሚው ከሃኪሙ በሚሰጠው ማብራሪያ መሠረት ከሁለቱ የህክምና ዓይነቶች መካከል የሚሻለውን እንዲመርጥ ይደረጋል።

መውጫ
➜የፕሮስቴት መጠንና የሚያሳያቸው ምልክቶች ቀጥተኛ ግኑኝነት የላቸውም። ይህም ትንሽ ፕሮስቴት ኖሮ አደገኛ (severe) ምልክት ሊያስከስት ይችላል በተቃራኒው ትልቅ ፕሮስቴት ኖሮ ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል ማለት ነው።

➜አብዛኛውን ጊዜ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የምልክቶቹ ደረጃ ይጨምራል

➜ለገር የፕሮስቴት ዕድገት (BPH) የሚደረግ ቀዶ ጥገና ከፕሮስቴት ካንሰር አይከላከልም ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ገሩ የፕሮስቴት ዕድገት (Benign Prostatic Hyperplasia-BPH )እና የፕሮስቴትካንሰር (Prostatic cancer) የሚነሱት ከተለያየ ፕሮስቴት ክፍል(prostatic zones) ስለሆነ ነው።

ዶ/ር ልጃለም መኮንን: የኩላሊትና ሽንት ቧንቧ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት (Consultant Urologist)

አድራሻ: አዲስ አበባ
https://t.me/lijurologist
lijumekonnen4@gmail.com
📞 0918028032

13 ኪ.ግ የሚመዝን የሆድ ውስጥ እጢ (ካንሰር) በተሳካ ሁኔታ በቀዶ ህክምና በመቅረዝ ሆስፒታል ተወገደ። A retroperitoneal Liposarcoma weighing 13.0 kg has be...
25/02/2025

13 ኪ.ግ የሚመዝን የሆድ ውስጥ እጢ (ካንሰር) በተሳካ ሁኔታ በቀዶ ህክምና በመቅረዝ ሆስፒታል ተወገደ።
A retroperitoneal Liposarcoma weighing 13.0 kg has been successfully excised for 61 years old woman by team of surgeons led by Dr. Kassaw Demilie (General Surgeon and Hepatobiliary Surgeon ) at MeQrez Hospital. The right ureter was pushed anteriorly and to the midline, resection and anastomosis of redundant ureter and JJ stent was put in place by Urosurgeon. The patient was stable and discharged after close follow up.
Surgical team
Dr. Kassaw D. (General Surgeon, Hepatobiliary surgery subspecialist)
Dr. Mekbib B. ( General Surgeon )
Dr. Lijalem M. (Urosurgeon)
Anesthesia team
Dr. Habtamu (Anesthesiologist) and Meseret
Nursing Team - Sr. Nardos, Nrs Bitew, Tesfaye and Sr. Meseret
Consent taken for use of patient information and pictures.

22/08/2024

ውፍረት በወንዶች ስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ

ከመጠን ያለፈ ውፍረት (obesity) ተጽእኖ ከተለመዱት ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ለአብነትም ስኳር ህመም፣ ኮሌስትሮል ችግር፣ የልብና ደም ስር ህመሞች ወዘተ ባሻገር የወንዶች የስነ ተዋልዶ እክሎችን ያመጣል።

ውፍረት በወንዶች ስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ምንድን ነው?

በዚህ ረእሰ ጉዳይ ዙርያ የሚሰሙ የተለመዱ የተሳሳቱ አመለካከቶች ምንድን ናቸው?

ውፍረት እና የወንዶች የስነ ተዋልዶ ጤናን ለማሻሻል መደረግ የሚገባቸው ተግባራዊ እርምጃወች ምንድር ናቸው?

የerectile dysfunction እና መሰል የወንዶች የስነ ተዋልዶ ህመሞች በመድሃኒት (Medical Treatment) ይታከማሉን?

አዎ! የወንዶች የስነ ተዋልዶ ችግሮች እንደማንኛውም ህመም ውጤታማ ህክምና አላቸው። ይታከማሉ። ሊድኑም ይችላሉ።

ይህ ትምህርታዊ ጽሁፍ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በተለይም ቦርጭ በወንዶች የስነ ተዋልዶና ጾታዊ ጤና መካከል ያለውን ውስብስብ ግንኙነት በጥልቀት ያስረዳል ፣ የተለመዱ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማስወገድ ያብራራል በተጨማሪም የተሟላ ጤናን ለማሻሻል ተግባራዊ ምክሮችን ይሰጣል።

ዝርዝር መረጃውን በዚህ link ያንብቡ
-
💚💛❤️
Melaku Taye, M.D.
Let us connect at Blog | TikTok | LinkedIn | Telegram | Rate me

26/10/2023

ዶ/ር ልጃለም መኮንን(Dr. Lijalem Mekonnen)
(የኩላሊት፣ የሽንት ቧንቧ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት)
(Senior Urologist)

👉ሙሉ የኩላሊትና የሽንት ቧንቧ ቼክ አፕ ምርመራ
👉የኩላሊት ጠጠር ህክምና
👉የኩላሊት ካንሰር ህክምና
👉የሽንት ቧንቧ ጥበት ህክምና
👉የፕሮስቴት ዕጢ ህክምና
👉የዘር ፍሬ ዕጢ ህክምና
👉የወንድ ብልት አፈጣጠር ችግር ህክምና
👉የወንድ ማሃንነት ህክምና
👉በቀለበት ግርዛትና ሌሎችም...
👉በስልክ ነፃ የማማከር አገልግሎትን ጨምሮ

#አድራሻ፦ መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
ካሳንችስ
👉 ዘወትር ጧት (ሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስና ቅዳሜ)
📳0918028032

ገር የፕሮስቴት ዕድገት(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH)****ሁለት ዋና ዋና የፕሮስቴት ዕድገት አይነቶች ያሉ ሲሆን እነዚህም ገር የፕሮስቴት ዕድገት(Benign Prost...
28/06/2023

ገር የፕሮስቴት ዕድገት
(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH)
****

ሁለት ዋና ዋና የፕሮስቴት ዕድገት አይነቶች ያሉ ሲሆን እነዚህም ገር የፕሮስቴት ዕድገት(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH) እና አደገኛ የፕሮስቴት ዕድገት(Prostatic cancer) ናቸው።
****

1) ገር የፕሮስቴት ዕድገት(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH)
****

👉በአዛውንት የዕድሜ ክልል ከሚከሰቱ በሽታዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከ40 አመት ዕድሜ ጀምሮ ሊከሰት ይችላል። ዕድሜ ሲጨምር የመከሰት ዕድሉ አብሮ ይጨምራል(linear relation)። ይህም ማለት በ60አመት የዕድሜ ክልል ከ50% በላይ የመከሰት ዕድል ሲኖር 85አመት ላይ ደግሞ ከ90%በላይ ይከሰታል።
****

BPH መኖር/አለመኖሩን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

ሀ) የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶች(LUTS) ሲከሰት

➜ገር የፕሮስቴት ዕድገት(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH) ያለበት ሰው የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል እነዚህም፦

1) ሽንት በሽንት ፊኛ የማጠራቀም ችግር( storage LUTS): ሦስት ሲሆኑ እነዚህም
👉ሽንትን ቶሎ ቶሎ መሽናት(frequency): በቀን ከ6-8 በላይ መሽናት
👉ማጣደፍ(urgency): ሽንትን በተፈለገው ቦታና ሰዓት የመሽናት ችግር እስከ ሽንት ማምለጥ ሊደርስ ይችላል።
👉ሌሊት ከእንቅልፍ ተነስቶ ሽንት መሽናት(nocturia): ከሁለት ጊዜ በላይ ሌሊት ከእንቅልፍ ተነስቶ ሽንት መሽናት

2) ሽንት ከሽንት ፊኛ የማስወገድ ችግር (Voiding LUTS)
አራት ምልክቶችን ሲያጠቃልል እነዚህም:-
👉ለመሽናት ማስማጥ(Straining)
👉ሽንት "ፏ" ብሎ አለመውረድ(weak stream)
👉የሽንት መቆራረጥ(intermittency), መዘግየት(hesitancy), መንጠባጠብ(Dribbling)
👉ጨርሶ መሽናት አለመቻል(incomplete voiding)

3) ሌሎች ምልክቶች እንደ ሽንት መዝጋት(urinary retention)፥ ደም የቀላቀለ ሽንት መሽናት(hematuria)

ለ) የፕሮስቴት መጠንን በመለካት(Imaging)

👉በUltrasound: ሁልጊዜ የፕሮስቴት መጠንን ለመለካት የምንጠቀምበት ሲሆን የፕሮስቴት መጠኑ ከ30ግራም (30cc) ከሆነ የፕሮስቴት ዕደገት(BPH) አለ እንላለን።
👉በMRI: ፕሮስቴት ካንሰር ፀባይ የሚያሳይ ከሆነ ተመራጭ ነው።
👉CT scan: የፕሮስቴት ካንሰር ወደ ተለያዩ የሰውነታችን ክፍል ስርጭት መኖር አለመኖሩን ለማወቅ እንጠቀምበታለን።

ሐ) ከፕሮስቴት ናሙና(Prostate Biopsy) በመውሰድ

➜ይህም በከፍተኛ ወይም በመለስተኛ ቀዶ ጥገና የሚሰራ ነው።
➜የፕሮስቴት ካንሰር ፀባይ በሚታይበት ጊዜ ገር የፕሮስቴት ዕድገትን(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH) ከአደገኛ የፕሮስቴት ዕድገት(Prostatic cancer) በእርግጠኝነት ለመለየት እንጠቀምበታለን።

ገር የፕሮስቴት ዕድገት(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH) መቼ ነው ህክምና የሚደረገው?
*

ገር የፕሮስቴት ዕድገት መኖር በራሱ በሽታ አይደለም። በሽታ የሚሆነው ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች ውስጥ በከፊል ወይም በሙሉውን ማምጣት ሲችል ብቻ መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው።

ህክምና የሚያስፈልግባቸው ሁኔታወች
****

1) መሃከለኛ(moderate) ወይም አደገኛ(severe) የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶች መከሰት፦ ይህም የዕለት ከዕለት ስራችንንና ጤናችንን ማወክ ሲጀምሩ
2) በBPH ምክንያት የኩላሊት ችግር ሲፈጠር(renal insufficiency)
3) ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽር ሲከሰት( recurrent urinary tract infection)
4) ተደጋጋሚ አጣዳፊ የሽንት መዝጋት ሲከሰት( recurrent acute urinary retention)
5) ስር የሰደደ የሽንት መዝጋት(chronic urinary retention)
6) የቆየ/ተደጋጋሚ ደም መሽናት(persistent gross hematuria)
7) በፕሮስቴት ምክንያት የሽንት ፊኛ ጠጠር(bladder stone) መፈጠርና
8) የአንጀት መውረድ(hernia):- ከፍተኛ በሆነ የሽንት ማስማጥ የተከሰተ ከሆነ።

የገር የፕሮስቴት ዕድገት(BPH) የህክምና አይነቶች
****

1) ክትትል ማድረግ(watchful waiting):-
👉ምንም አይነት ምልክት ለሌላቸው ወይም አነስተኛ(mild) ምልክት ለሚያሳዩ ሰዎች ያለምንም ቀዶ ጥገና ወይም መድኃኒት የሚደረግ ነው። በክትትል ወቅትም የመባባስ ምልክት ከተከሰተ ህክምናው እንዲጀመር ይደረጋል።

2) በመድሃኒት ህክምና(medical therapy)
👉መሃከለኛ(moderate) ወይም አደገኛ(severe) የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶች ሲኖር የሚጀመር ህክምና ሲሆን በየቀኑ ለብዙ ወራት የሚዋጥ መድኃኒት በመውሰድ የሚደረግ ህክምና ነው። እንደ አስፈላጊነቱም መድኃኒቱ ሊቆም ይችላል። በተለዬ መልኩ ወልደው ላልጨረሱ ወይም ቀዶ ህክምናን መቋቋም ለማይችሉ ወይም ቀዶ ጥገና ለማይፈልጉ ታካሚዎች ይሰጣል።

3) በቀዶ ጥገና ያደገውን ፕሮስቴት የማውጣት ህክምና (simple prostatectomy or TURP)
👉ይህ ህክምና የሚከተሉት ምልክቶት ሲኖሩ የሚደረግ ህክምና ነው። እነርሱም:-
👉የመድኃኒት ህክምናው ውጤት ሳያመጣ ሲቀር(failed medical therapy)
👉ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽር( recurrent urinary tract infection)
👉ተደጋጋሚ አጣዳፊ የሽንት መዝጋት ሲከሰት( recurrent acute urinary retention)
👉ስር የሰደደ የሽንት መዝጋት(chronic urinary retention)
👉የቆየ/ተደጋጋሚ ደም መሽናት(persistent gross hematuria) ሲኖር
👉በፕሮስቴት ምክንያት የሽንት ፊኛ ጠጠር(bladder stone) መፈጠርና
👉ከፍተኛ በሆነ የሽንት ማስማጥ የተከሰተ የአንጀት መውረድ(hernia) ናቸው።

መውጫ
➜የፕሮስቴት መጠንና የሚያሳያቸው ምልክቶች ግንኙነታቸው ቀጥተኛ አይደለም። ይህም ትንሽ ፕሮስቴት ኖሮ አደገኛ(severe) ምልክት ሊታይ ይችላል በተቃራኒው ትልቅ ፕሮስቴት ኖሮ ምንም አይነት ምልክት ላይኖር ይችላል ማለት ነው።
➜አብዛኛውን ጊዜ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የምልክቶቹ ደረጃ ይጨምራል
➜ለገር የፕሮስቴት ዕድገት(BPH) የሚደረግ ቀዶ ጥገና ከፕሮስቴት ካንሰር አይከላከልም ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ገሩ የፕሮስቴት ዕድገት(Benign Prostatic Hyperplasia-BPH)እና አደገኛው የፕሮስቴት ዕድገት(Prostatic cancer) የሚነሱት ከተለያየ ፕሮስቴት ክፍል(prostatic zones) ስለሆነ ነው።

ዶ/ር ልጃለም መኮንን
የኩላሊትና ሽንት ቧንቧ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት(Urologist)

#አድራሻ: መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
ካሳንችስ

https://t.me/lijurologist
lijumekonnen4@gmail.com
0918028032

26/06/2023

Address

Addis Ababa

Telephone

+251975256636

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Urology in Ethiopia- የኩላሊት፥ ሽንት ቧንቧ፥ የፕሮስቴትና የወንድ ስነ-ተዋልዶ በኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Urology in Ethiopia- የኩላሊት፥ ሽንት ቧንቧ፥ የፕሮስቴትና የወንድ ስነ-ተዋልዶ በኢትዮጵያ:

Share